GMTC Ethiopia

GMTC Ethiopia Speak the truth, live for the glory of God, and serve those around you.

 ።🛫 ለመድረስ ወደ አቀድኩ ደረጃ፣ ✍️ ለማከናወን ለነደፍኩት ራዕይ፣ 👁️ በአይነ ህልና ላየሁት ህልም የእያንዳንዱ ቀን ውሎዬ እንቅስቃሴ በድጋፍ ፣ በተቃርኖ ወይም በድምፅ ተሃቅቦ እጅ እየ...
26/08/2026


🛫 ለመድረስ ወደ አቀድኩ ደረጃ፣
✍️ ለማከናወን ለነደፍኩት ራዕይ፣
👁️ በአይነ ህልና ላየሁት ህልም
የእያንዳንዱ ቀን ውሎዬ እንቅስቃሴ በድጋፍ ፣ በተቃርኖ ወይም በድምፅ ተሃቅቦ እጅ እየሰጠ እንደሆነ አስባለሁ። ለውድቀቴ ማንም ተወቃሽ ወይም ተጠያቂ የለም። ባይሆን ለስኬቴ የሚመሰገኑ ሰዎች ይኖራሉ።
ማቴዎስ ሀደሮ
ቀን፡ 20/12/2018

🇪🇹

 (አርባ)_ቀን_ቆይታበመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ 40 ቀን ጾምና ፀሎትን በተመለከተ ኢየሱስ ክርስቶስ እና ሙሴ ይጠቀሳሉ።1. ሙሴ የፀሎቱ ዓላማው፦ ከእግዚአብሔር ጋር ለመገናኘትና ሕጉን ለመቀበል ስ...
22/08/2026

(አርባ)_ቀን_ቆይታ
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ 40 ቀን ጾምና ፀሎትን በተመለከተ ኢየሱስ ክርስቶስ እና ሙሴ ይጠቀሳሉ።

1. ሙሴ
የፀሎቱ ዓላማው፦ ከእግዚአብሔር ጋር ለመገናኘትና ሕጉን ለመቀበል ስሆን
የተገኘው ውጤት፦ የቃል ኪዳኑን ጽላት ተቀበለ፤ ፊቱም በክብር አበራ።
(ዘፀአት 34:28 - 30)

2. ኢየሱስ ክርስቶስ
የፀልቱ ዓላማው፦ ለአገልግሎት መዘጋጀትና የዲያብሎስን ፈተና መቋቋም ስሆን
የተገኘው ውጤት፦ የሰይጣንን ሶስቱን ፈተናዎች አሸነፈ፤ መልአክት አገለገሉት፤ ወንጌልን መስበክ ጀመረ።
(ማቴዎስ 4:2 - 11)

ወይይትም አርባ ቀናትን በመጨረስ እንደተጠናቀቀ እናውቃለን። ሙሴ የቃልኪዳኑን ጽላት እንደተቀበለ ፊቱም እንዲበራ፤ ኢየሱስም የሰይጣንን ፈተና እንዳሸነፈ መልአክት እንዳገለገሉት ወደ አገልግሎት እንደገባ፤ ሰላምን ዕድገትን የሚንቀበልበት፣ በአለም አቀፍ ጀረጃ የሚንበራበት፣ የጠላቶችን ፈተና አሸንፈን መንግስታት አገልግሎን የዕድገትና የብልፅግና ሥራችንን የሚንቀጥልበት እንድሆን እመኛለሁ።
ማቴዎስ ሀደሮ
ከGMTC_Ethiopia
🇪🇹
15/12/2018 ዓ.ም.
ከሌልት 6:36
ታርጫ

 የዘርፉ ተመርማሪ ባልሆንም ብዙ ጊዜ የትውልድን ሁኔታ ከከተማ እስከ ገጠር አያለሁ። አንድ ያስተዋልኩት ነገር ብኖር ለሰው ልጅ መጥፎ በሽታ ስራ አለመስራት ነው። ሥራ ለመስራት የተመቻቸ ሁኔ...
18/08/2026


የዘርፉ ተመርማሪ ባልሆንም ብዙ ጊዜ የትውልድን ሁኔታ ከከተማ እስከ ገጠር አያለሁ። አንድ ያስተዋልኩት ነገር ብኖር
ለሰው ልጅ መጥፎ በሽታ ስራ አለመስራት ነው።
ሥራ ለመስራት የተመቻቸ ሁኔታ፣ ቦታ አለመኖር ላለመስራቱ ምክንያት ነው። የሰው ልጅ ተባብሮ፣ ተግባብቶ በመኖር ከሌሎች ፍጡራን የመጀመሪያው ይሆናል። ስለዚህ ሥራ ለማይሰሩ ሰዎች በተለይም ለወጣቶች የተመቻቸ ባይሆንም የሚያሰራ ሁኔታ እና ቦታ በማመቻቸት እንተባበር።

12/12/2018 E.C.

16/08/2026

"
እርሳስን የሚመራዉ እጅ አለ
~ አምላክ
እርሳስ መቅረጫ አለው
~ እንግልትን ማለፍ
እርሳስ ላጵስ አለው
~ ስህተት ማጥፊያ
እርሳስ ተፈላግ ክፍሉ ውስጥ ነው
~ ትኩረትን በውስጥ እውነታ ላይ ማድረግ
እርሳስ አሻራ ያስቀመጣል
~ በመንገድ ላይ ማስታወሻ ማኖር "
ከተነበበው

የዕድገት ምሥጢርምድር በፈጠራ ብልጭታዎች ስትቀየር የሳይንስ ሊቃውንት ህዋን በመርገጥ፣ ኮከቦችን በመቃኘት እና ረቂቅ ሰው ሰራሽ አስተውሎትን በማበርከት የዕውቀትን ድንበር ሰብረውታል። ከእነዚ...
12/08/2026

የዕድገት ምሥጢር

ምድር በፈጠራ ብልጭታዎች ስትቀየር የሳይንስ ሊቃውንት ህዋን በመርገጥ፣ ኮከቦችን በመቃኘት እና ረቂቅ ሰው ሰራሽ አስተውሎትን በማበርከት የዕውቀትን ድንበር ሰብረውታል። ከእነዚህ አስደናቂ የምርምር ድንቆች ሁሉ በላይ ግን የትኛውንም ማህበረሰብ ዕጣ ፈንታ እንደ ሰም የሚቀርጸው በጎ አድራጊውም ሆነ አውዳሚው ኃይል "አመራር" የተባለው የበላይ ጥበብ ነው። አገሮች በኢኮኖሚ ቁመናቸው ሲለኩ አንዳንዶች ምንም ዓይነት የተፈጥሮ ጸጋ ሳይኖራቸው የዓለም ግዙፍ ማዕከል ሲሆኑ ሌሎች ደግሞ ማዕድን እና ለም መሬት ተቀምጦላቸው ሳለ ለሕዝባቸው የዕለት እንጀራ ማግኘት ተስኗቸዋል። ቁሳቁስ ራሱን ችሎ ሀብት ሊሆን ስለማይችል እውነተኛው ምሥጢር ያለው ያ ቁሳቁስ በብቁ አዕምሮ እና በሩቅ አሳቢ አስተዳደር ሲገራ ብቻ ነው።

ደካማ እና ስግብግብ አስተዳደር በሰፈነበት ሥርዓት የተፈጥሮ ሃብት ለሕዝብ ዕድገት መሠረት ሳይሆን ለጥቂቶች መክበሪያ እና ለግጭት መንስኤ ይሆናል። ብቁ፣ ሐቀኛ እና ራዕይ ያለው መሪ በስልጣን መንበር ላይ ሲወጣ ግን ድንጋያማ መሬት ራሱ የለመለመ ገነት፣ አስቸጋሪ ፈተናም የፈጠራ አጋጣሚ ሆኖ ይለወጣል። ቴክኖሎጂ እንደ መሣሪያ እና እሳት እንደ ጉልበት ሲያገለግሉ አስተዳደር ግን የሕዝብን ሕልም እና ዕጣ ፈንታ አቀናጅቶ የሚይዝ ኃይል ነው። ድህነት የአየር ንብረት ወይም የጂኦግራፊ ቅጣት ሳይሆን የቀጥታ የአመራር ድህነት መገለጫ ነው።

ድህነት የጂኦግራፊ ቅጣት ሳይሆን የአመራር ድህነት መገለጫ ነው የሚለውን ሃሳብ በተመለከተ የእርስዎ ምልከታ ምንድን ነው?

ዛዲግ አብርሀ
የአፍሌክስ ፕሬዝደንት
Source:AFLEX FB page

          ለጥቅም መሮጥ ማለት ራስን ከሌሎች ጋር ማወዳደር፣ ጊዜያዊ ስኬትን ማሳደድ እና የግለሰብ ጥቅም ውጤትን ብቻ ማየት ሲሆን፣ ለጥሪ መኖር ግን ራስን መረዳት፣ ሌሎችን ማገልገል እ...
11/08/2026


ለጥቅም መሮጥ ማለት ራስን ከሌሎች ጋር ማወዳደር፣ ጊዜያዊ ስኬትን ማሳደድ እና የግለሰብ ጥቅም ውጤትን ብቻ ማየት ሲሆን፣ ለጥሪ መኖር ግን ራስን መረዳት፣ ሌሎችን ማገልገል እና ለዓላማ መቆምን ያመለክታል። ብዙዎች ህይወታቸውን የሚያሳልፉት ሌሎች/ጥቅመኞች ባወደሱላቸው ነገር እየሮጡ ነው፤ ነገር ግን እውነተኛ እርካታ የሚገኘው የራስን ጥሪ ስንከተል ብቻ ነው። ለጥሪ መኖር ፍቅርን፣ ታማኝነትን እና አይበገርነትን ያስቀድማል።
ውድድሩ የሚያልቀው መቼም ቢሆን ጥሪ ግን ዘላለማዊ ነውና ከመሮጥ ይልቅ ለመኖር መምረጥ የህይወትን ጥልቅ ደስታ ያስገኛል።ምክንያቱም ለራስህ እውነት ነህ።


= ? የሚል ጥያቄ (የጥቅም ውጤት ተኮር)
= ? የሚል ጥያቄ (ተግባር ተኮር) ነው።
አመሰግናለሁ
ነሐሴ 5, 2018 ዓ.ም
ወልደሃኔ

  (fundamental tension in politics) ሁለት ናቸው።መሪ ለየተኛውም ችግር ዘላቅ   ወይስ በተለያየ መንገድ ምክንያት እየፈጠረ ነገሩን  #ማቆየት (ማስታመም)1. ብዙ ጊዜ ማ...
07/08/2026


(fundamental tension in politics)
ሁለት ናቸው።
መሪ ለየተኛውም ችግር ዘላቅ ወይስ በተለያየ መንገድ ምክንያት እየፈጠረ ነገሩን #ማቆየት (ማስታመም)

1. ብዙ ጊዜ ማስታመም የተለመደ ሆኗል— ምክንያቱም መሪዎች የአጭር ጊዜ ተቀባይነትን (popularity) ይፈልጋሉ። ዘላቅ መፍትሄ ፣ መራራ መድሃኒት ነው።
2. የአንድ ሰው ፖለቲካ ውክልና ጊዚያዊ ነው መሪዎች ከስልጣን ሲወርዱ ያልተፈቱ ችግሮችን ለሚቀጥለው ያስተላልፋሉ። ይህ የፖለቲካ "ኳስ ማስተላለፍ" (political buck-passing) ይባላል።
ውሳኔ አለመስጠት መሪን መሪ አያስብልም። ይህ ቁልፍ ነጥብ ነው!


1· ፖፑሊስት(populist) መሪ ህዝቡን ያስደስታል፣ ግን ችግር አይፈታም (ይረሳል)
2· ቢሮክራቲክ(bureaucratic) መሪ ሂደቱን ይከታተላል፣ ውሳኔ አያደርግም (ይቆያል)
3· ታሪካዊ መሪ አስቸጋሪ ውሳኔ ይወስናል፣ ተቃውሞ ይቀበላል፣ ግን ችግሩን ይፈታል (ይታወሳል)።
#ስለዚህ
እውነተኛ መሪ የሚታወቀው አስቸጋሪ ውሳኔ በመውሰዱ ነው፣ ምቾት በማስገኘቱ አይደለም። "ማስታመም" ለጊዜው ከትችት ያሳርፋል ፣ ግን ታሪክ የሚፈርደው ዘላቅ መፍትሄ በሰጡ ላይ ነው። መሪ ለመሆን ከፈለጉ፣ ውሳኔ ያለመስጠት ራሱ ውሳኔ መሆኑን አስታውሱ — እና አብዛኛውን ጊዜ ያ ውሳኔ(ማቆየት) ሽንፈትን ይጋብዛል።
አመሰግናለሁ

 #ባህል ማለት የአንድ ሕዝብ አጠቃላይ የሕይወት መንገድ፣ እምነት፣ እሴት፣ ሥነ-ሥርዓት፣ ቋንቋ፣ ጥበብና ታሪክ ድምር ነው። ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚተላለፍ ሲሆን ማኅበረሰቡን የሚለይ መሠረ...
31/07/2026

#ባህል ማለት የአንድ ሕዝብ አጠቃላይ የሕይወት መንገድ፣ እምነት፣ እሴት፣ ሥነ-ሥርዓት፣ ቋንቋ፣ ጥበብና ታሪክ ድምር ነው። ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚተላለፍ ሲሆን ማኅበረሰቡን የሚለይ መሠረታዊ ምንነት ነው።
#እኔ ግን የሚጠይቀው #ክርስቲያን በክርስቶስ አምኖ #የዳነ ሰው ሁሉ የጋራ ባህል የለውም ? ካለስ ምንድነው ? #ፃፉልኝ ቅዱሳን ።
photo credit: Donatello

23/07/2026

#የመጽሐፍ ቅዱስ 66 መጻሕፍት – አጭር ማብራሪያ
#ብሉይ ኪዳን (39)
#ዘፍጥረት – የፍጥረት፣ የሰው ውድቀት እና የአባቶች ታሪክ።
#ዘጸአት – እግዚአብሔር እስራኤልን ከግብፅ ነፃ አወጣ፤ ሕጉንም ሰጠ።
#ዘሌዋውያን – የአምልኮ፣ የቅድስና እና የመሥዋዕት ሕጎች።
#ዘኍልቍ – በምድረ በዳ የእስራኤል ጉዞና ቆጠራ።
#ዘዳግም – ሙሴ ሕጉን እንደገና ለሕዝቡ ያስተምራል።
#ኢያሱ – የተስፋይቱን ምድር መውረስ።
#መሳፍንት – የእስራኤል ፈራጆች ታሪክ።
#ሩት – የታማኝነትና የቤዛነት ታሪክ።
#1 ሳሙኤል – ሳሙኤል፣ ሳኦል እና ዳዊት።
#2 ሳሙኤል – የንጉሥ ዳዊት አገዛዝ።
#1 ነገሥት – ሰሎሞንና የመንግሥቱ መከፈል።
#2 ነገሥት – የእስራኤልና የይሁዳ ውድቀት።
#1 ዜና መዋዕል – የዳዊት ዘመን ታሪክ።
#2 ዜና መዋዕል – የይሁዳ ነገሥታት ታሪክ።
#ዕዝራ – ከምርኮ መመለስና ቤተ መቅደስ መልሶ መገንባት።
#ነህምያ – የኢየሩሳሌምን ቅጥር መልሶ መገንባት።
#አስቴር – እግዚአብሔር ሕዝቡን ያድናል።
#ኢዮብ – በመከራ ውስጥ ያለ እምነት።
#መዝሙር – የምስጋና፣ የጸሎት እና የአምልኮ መዝሙሮች።
#ምሳሌ – የጥበብ ትምህርቶች።
#መክብብ – ያለ እግዚአብሔር ሕይወት ከንቱ ነው።
#መኃልየ መኃልይ – የፍቅር መዝሙር።
#ኢሳይያስ – ስለ መሲሑ የተሰጡ ትንቢቶች።
#ኤርምያስ – ወደ ንስሐ ጥሪ።
#ሰቆቃወ ኤርምያስ – በኢየሩሳሌም ውድቀት ላይ ልቅሶ።
#ሕዝቅኤል – የፍርድና የተስፋ ራእዮች።
#ዳንኤል – በምርኮ ውስጥ ያለ ታማኝነትና ትንቢት።
#ሆሴዕ – የእግዚአብሔር ታማኝ ፍቅር።
#ኢዮኤል – ወደ ንስሐ ጥሪ፤ የመንፈስ ቅዱስ ተስፋ።
#አሞጽ – ፍትሕን እና ጽድቅን ይጠራል።
#አብድዩ – በኤዶም ላይ ፍርድ።
#ዮናስ – የንስሐና የምሕረት ታሪክ።
#ሚክያስ – መሲሑ በቤተልሔም እንደሚወለድ ትንቢት።
#ናሆም – በነነዌ ላይ ፍርድ።
#ዕንባቆም – በእግዚአብሔር መታመን።
#ሶፎንያስ – የጌታ ቀንና ተስፋ።
#ሐጌ – ቤተ መቅደስን እንደገና መገንባት።
#ዘካርያስ – ስለ መሲሑ ብዙ ትንቢቶች።
#ሚልክያስ – ለጌታ ታማኝ መሆንን ያስተምራል።
#አዲስ ኪዳን (27)
#ማቴዎስ – ኢየሱስ የተስፋው መሲሕ ነው።
#ማርቆስ – ኢየሱስ ኃይለኛ አገልጋይ ነው።
#ሉቃስ – ኢየሱስ የዓለም አዳኝ ነው።
#ዮሐንስ – ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው።
#የሐዋርያት ሥራ – የመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ።
#ሮሜ – በእምነት መጽደቅ።
#1 ቆሮንቶስ – የቤተ ክርስቲያን ሥርዓትና አንድነት።
#2 ቆሮንቶስ – በድካም ውስጥ የክርስቶስ ኃይል።
#ገላትያ – ድነት በጸጋ እንጂ በሕግ አይደለም።
#ኤፌሶን – በክርስቶስ ያለው አዲስ ሕይወት።
#ፊልጵስዩስ – በጌታ ደስታ።
#ቆላስይስ – የክርስቶስ በላይነት።
#1 ተሰሎንቄ – ለጌታ መምጣት መዘጋጀት።
#2 ተሰሎንቄ – ስለ ጌታ ዳግም ምጽአት።
#1 ጢሞቴዎስ – ለቤተ ክርስቲያን መሪዎች መመሪያ።
#2 ጢሞቴዎስ – በእምነት ጸንቶ መቆም።
#ቲቶ – ጥሩ አመራርና መልካም ሥራ።
#ፊልሞና – ይቅርታና እርቅ።
#ዕብራውያን – ክርስቶስ ከሁሉ ይበልጣል።
#ያዕቆብ – እምነት በሥራ ይገለጣል።
#1 ጴጥሮስ – በመከራ ውስጥ ተስፋ።
#2 ጴጥሮስ – ከሐሰተኛ አስተማሪዎች ተጠንቀቁ።
#1 ዮሐንስ – በፍቅርና በእውነት መኖር።
#2 ዮሐንስ – በእውነት መጽናት።
#3 ዮሐንስ – እንግዳ መቀበልና ታማኝነት።
#ይሁዳ – ለእምነት መታገል።
#ራእይ – የክርስቶስ ድል፣ የመጨረሻ ፍርድ እና አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር።
Credit : Moges Mekonnen

የኢትዮጵያ ገንዘብ "ብር" ለምን ተባለ ?  1. ቀጥተኛ ትርጉም ከብረቱ ጋር"ብር" የሚለው ቃል መጀመሪያ ላይ የብር ብረትን (silver metal) ያመለክታል። በጥንት ዘመን ሳንቲሞች ከዚህ...
21/07/2026

የኢትዮጵያ ገንዘብ "ብር" ለምን ተባለ ?

1. ቀጥተኛ ትርጉም ከብረቱ ጋር
"ብር" የሚለው ቃል መጀመሪያ ላይ የብር ብረትን (silver metal) ያመለክታል። በጥንት ዘመን ሳንቲሞች ከዚህ ብረት ይሠሩ ስለነበር፣ ቃሉ ከብረቱ ስም ጋር ተያይዟል።

2. ታሪካዊ ዳራ (የሳንቲም ባህል)
በኢትዮጵያ ውስጥ ሳንቲሞች ከ100 ዓመታት በላይ ሲታወቁ ቆይተዋል። በተለይ በዘመነ ምኒልክ (19ኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ) የተፈጠሩት ሳንቲሞች ከብር ብረት የተሠሩ ነበሩ። ሕዝቡ እነዚህን ሳንቲሞች በብረቱ ስም "ብር" ብሎ መጥራት ጀመረ።

3. የመገበያያ ገንዘብ ምትክ
ከዚያ በፊት ጨው፣ ወርቅ፣ ወይም የባር ጨርቅ እንደ ገንዘብ ያገለግሉ ነበር። የብር ሳንቲሞች ሲመጡ፣ ዘላቂ፣ ሊቆጠር የሚችል እና ከፍተኛ እሴት ስለነበራቸው በፍጥነት ተቀባይነት አገኙ። ስለዚህ "ብር" የሚለው ቃል "ገንዘብ" ከሚለው ትርጉም ጋር ተያያዘ።

4. ዘመናዊ ምንዛሪ
በ1945 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ኃይለ ሥላሴ የአሁኑን ብር እንደ ኦፊሴላዊ ምንዛሪ አስተዋወቁ። ምንም እንኳን ሳንቲሞቹ ከብር ባይሠሩም (አሁን ከብረት ወይም ከወረቀት የተሠሩ ቢሆኑም)፣ ታሪካዊው ስም ተጠብቆ ቆይቷል።

5. ተመሳሳይ ምሳሌዎች
እንግሊዝኛ "pound" (ስተርሊንግ ሲልቨር ማለት ነበር)
ፈረንሳይኛ "argent" (ማለትም ብር)
ግሪክኛ "drachma" (ማለትም እፍኝ የብር)

እናመሰግናለን

ትንሽ ብሆን አሁን እንደተረዱት እንገምታለን
Follow, share, comment, like

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when GMTC Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share