02/02/2026
በደቡብ ትግራይ የሚንቀሳቀሰው አርሚ 24 የህወሓት ታጣቂ ተቃዉሞ ማሰማት ጀምሯል!
📍ሁኔታው ታጣቂውን ለሚመራው ኮ/ል ካህሳይ መኮንን ለተባለ የቡድኑ አመራርም ራስ ምታት ሆኗል!
ፅንፈኛው የህወሓት ቡድን ደቡብ ግንባር በማለት የሚጠራው ታጣቂ የቡድኑን ትዕዛዝ መቀበል እያቆመ እንደመጣ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ እንግዲህ ሃራ መሬት ካለው ሃይል አብዛኛው ከዚህኛው አደረጃጀት የሄደ እንደሆነም ይታወቃል፡፡ ቀሪው ታጣቂም ሰሞኑን ህወሓት በለኮሰው ጦርነት አልሳተፍም በማለት ከቡድኑ አፈንግጦ እየወጣ የሚገኝ ሲሆን በዋናነትም ከአርሚ 44 በርካታ ታጣቂዎች ከነትጥቃቸው ከቡድኑ አፈንግጠው ወጥተዋል፡፡ እንዳይወጡ ቡድኑ ያደረገውን እንቅስቃሴ ተከትሎ ከአርሚ 44 የወጡት ቡድኑ በሰንዓለ ድባቅ እንደመቱት በአይናችን ተመልክተናል፡፡
አሁንም ቢሶበር በሚባል አካባቢ የሰፈረው አርሚ 24 ታጣቂ የሚሰጠውን ትዕዛዝ መቀበል እንዳቆመ የሚደርሱን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ታጣቂ ሃይሉ ወደፊት ውጊያውን እንዲገፋ ከአርሚ አዛዦች የሚወርድለትን አቅጣጫ ከመቀበል ይልቅ ወደኋላ እያፈገፈገ እንደሆነም ከሚደርሱን መረጃዎች ለማወቅ ተችሏል፡፡ ሁኔታው እንዲስተካከል የአርሚ አዛዡ ኮ/ል ካህሳይ መኮንን ከስሩ ለሚገኙት የቡድኑ አመራሮች ትዕዛዝ እያወረደ ቢሆንም የሚሰማውን አጥቷል፡፡
እንዲሁም አጋምሸት የነበረው ሁለት የቡድኑ ሬጅመንት ወደሃራ መሬት መግባቱን የደረሰን መረጃ አመላክቷል፡፡ ከዚህም ውጭ በአርሚ 43 ውስጥም ተመሳሳይ ተቃዉሞ በታጣቂው ዘንድ እየተስተዋለ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል፡፡