Dawitworknehpr

Dawitworknehpr Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Dawitworknehpr, Construction Company, 6kilo shromada steeat, Addis Ababa.

እኛንም ይቅር ይበለን ዘነድ ጸልዩ
27/02/2024

እኛንም ይቅር ይበለን ዘነድ ጸልዩ

የነነዌ ሰዎችና እኛ

ከነነዌ ሰዎች በላይ ማን ክፉ ነበር? ከእነርሱ በላይ አላዋቂስ ማን ነበር? (“ቀኛቸውንና ግራቸውን የማይለዩ” ተብለው ተጠርተዋልና፡፡) ነገር ግን እነዚህ አሕዛብ፣ እነዚህ አላዋቂ፣ እነዚህ አንድ ሰውስ እንኳን የጥበብን ነገር አስተምሮአቸው የማያውቁ፣ እነዚህ ከማንም ይኹን ከማን እንደዚህ ዓይነት ትእዛዝን ያልተቀበሉ ሰዎች ነቢዩ፡- “በሦስት ቀን ውስጥ ነነዌ ትገለበጣለች” ሲል በሰሙት ጊዜ ክፉ ልማዳቸውን ኹሉ በሦስት ቀናት ውስጥ አስወግደዋል (ዮና.3፥4)፡፡

ዘማዊው ንጹህ፣ ደፋሩ ትሑት፣ ስስታሙና ጨቋኙ ራሱን የሚገዛና ደገኛ፣ ሐኬተኛውም ትጉህ ኾነ፡፡ እነዚህ ሰዎች በርግጥ ያሻሻሉት ክፋታቸውን ኹሉ እንጂ አንዱን ወይም ኹለቱን ወይም ሦስቱን ወይም አራቱን አይደለም፡፡ “እንዲህ የሚልስ የት አለ?” ብሎ የሚጠይቅ ሰው ሊኖር ይችላል፡፡ እኔም እንዲህ ብዬ እመልስለታለሁ፡- እነርሱን ሲወቅሳቸው የነበረውና፣ “የክፋታቸውም ጩኸት እስከ አርያም ድረስ ወጥቷል” ብሎ የተናገረው ነቢይ መልሶ ደግሞ የዚሁ ፍጹም ተቃራኒ የኾነን ምስክርነት አስቀምጧልና፤ እንዲህ ሲል፡- “እግዚአብሔርም ከክፉ መንገዳቸው እንደ ተመለሱ ሥራቸውን አየ” (ዮና.1፡5፣ 3፡10)፡፡ ተመልከት! ከዝሙት ወይም ከአመንዝራነት ወይም ከሌብነት ራቁ አላለም፤ “ከክፉ መንገዳቸው” እንጂ፡፡ እንዴትስ ከዚያ ሊርቁ ቻሉ? ይህን እግዚአብሔር ያውቋል እንጂ ሰው ሊመረምረው አይችልም፡፡

እንግዲህ አሕዛብ በሦስት ቀናት ውስጥ ብቻ ክፋታቸውን ኹሉ ማስወገድ ከቻሉ፥ ለአያሌ ቀናት የተመከርንና የተዘከርን እኛ ግን አንዲት ክፉ ልማድን [ለምሳሌ መሐላን] ሳናስወግድ ስንቀር ልናፍር አይገባንምን? ከዚህም በላይ እነዚህ ሰዎች ቀድሞ ክፋታቸው ጣሪያ ደርሶ ነበር፤ “የክፋታቸውም ጩኸት እስከ አርያም ድረስ ወጥቷል” የሚለውን ስትሰማ ከክፋታቸው ብዛት በቀር ሌላ ምንም ልትገነዘብ አትችልምና፡፡ ነገር ግን በሦስት ቀናት ውስጥ ወደ መልካም ምግባር ፍጽምና መድረስ ተችሏቸዋል፡፡ ፈሪሐ እግዚአብሔር ባለበት ቀናት ወይም የጊዜ ብዛት አያስፈልግምና፡፡ በተቃራኒው ይህ ፍርሐት በሌለበት ደግሞ የጊዜ ብዛት ምንም ጥቅም የለውም፡፡

የዛጉ ብረቶችን በውኃ ብቻ የሚያጥባቸው ሰው ምንም ያህል ጊዜ እነርሱን በማጠብ ቢያሳልፍም እነዚያን ዝገቶች ኹሉ ማስለቀቅ አይቻለውም፡፡ ወደ እሳት ጨምሮ የሚያወጣቸው ሰው ግን አዲስ ከተሠሩ ብረቶችም ጭምር ሳይቀር እጅግ ጽሩያን ያደርጋቸዋል፡፡ በኃጢአት የዛገ ልብም እንዲሁ በትንሽ በትንሹና በግድየለሽነት ኾኖ ዕለት ዕለት ንስሐ ቢገባም ምንም ጥቅም አያገኝም፡፡ ራሱን ወደ እቶን – ይኸውም ወደ ፈሪሐ እግዚአብሔር የሚጥል ከኾነ ግን በአጭር ጊዜ ውስጥ ኹሉንም ማስወገድ ይቻለዋል፡፡

(በእንተ ምክንያተ ሐውልታት፥ ፳:፳፩ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳስተማረው)

27/02/2024

Today best photo
#ቅዱስገብርኤልአባቴ♥






25/04/2023
25/04/2023

ሠላም የተዋህዶ ልጆች እንደምን አላችሁ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
አሐዱ አምላክ አሜን።

"በዉኑ ይህ ቤት ፈርሶ ሳለ እናንተ ራሳችሁ በተሸለሙ ቤቶቻችሁ ለመኖር ጊዜው ነዉን ?" ትንቢተ ሐጌ 1:4
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ውድ የእግዚአብሔር ልጆች ይቺ ከታች የምትመለከቷት ለአይን የምታሳሳ ቤተክርስቲያን የምትገኘው በከምባታ ጠምባሮና ሀለባ ሀገረስብከት በጠምባሮ ቤተክህነት ስር ጊደንሦንጋ እየሱስ ቤተክርስቲያን ነው የተመሰረተችውም 1974 ዓ/ም ቢሆንም ምዕመናን ብዛታቸው ከ200 በላይ ሲሆኑ ሙሉ በሙሉ አ/አደሮች በመሆናቸው ቤተክርስቲያንቱን ለመስረት በተደጋጋሚ ጥራት ቢያደርጉም የሰበሰቡት እንጨት ከሦስት ዙር በላይ ሌሎች ቤት መስርያ ግብዓቶች በማጣታቸው በስብሷል ። በተጨማሪ በአሁኑ ሰዓት በእጃቸው 200(ሁለት መቶ) ቆርቆሮ አላቸው በተጨማሪ በአካውንታቸው ብር 6,000 (ስድስት ሺህ ብር ) ብቻ አላቸው ፣ ይዞታ 1.5 ሄ/ር ወይም 15000 ካሬ ሜትር ስፋት መሬት ከግለሰቦች በግዥ ቢይዙም የእግዚአብሔርን ቤት እንዳይሰሩ የኢኮኖሚ አቅማቸው ስላልቻለ ውድ የተዋህዶ ልጆች በሀገር ውስጥም በውጭም ያላቹ ወገኖቻችን እባካችሁ ይህችን ቤተክርስቲያን እየሰራን የበሩከቱ ተካፋይ እንድንሆን በልዑል እግዛብሄር ስም እንጠይቃለን።

በተለያየ አማራጭ ቤተክርስቲያኗኗን መርዳት የምትፈልጉ
በ094 336 4432
እትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000504933532

25/04/2023
ሰው አረ ሰው ፈልጉ
25/04/2023

ሰው አረ ሰው ፈልጉ

25/04/2023

ሚያዚያ 23 በመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን (አራዳ ጊዮርጊስ) የሰማዕቱን ዓመታዊ በዓል በጋራ እናክብር ።ሼር በማድረግ ላልሰሙት እናሰማ።

25/04/2023

☞እንኳን ለዳግም ትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፡፡ይህ ማለት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞቶ ተቀብሮ ዳግም የተነሣ ሳይሆን ከሙታን ተለይቶ ለሐዋርያት በተገለጠላቸው ሣምንት በድጋሚ
ቅዱስ ቶማስ ባለበት ልክ እንደመጀመሪያ ሆኖ ሰለተገለጣለቸው ነው፡፡
☞ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመጀመሪያ ለዓሥሩ ሐዋርያት
ሲገለጥላቸው ሐዋርያው ቶማስ አልነበረም፡፡
☞መጥቶ በተገኛቸው ጊዜ እርሱም ስለ ጌታችን መነሳት እንዳዩትም ሲነግሩት
ቶማስ እንዲህ አለ ሌሎቹ ሐዋርያት ሞትን ድል አድርጎ ተነሣ አየነው እያሉ
ሲያስተምሩ እኔ ግን ሰማሁ ብዬ ላስተምር ነው ብሎ ያስብ ነበር፡፡
☞በዚህም ጊዜ ቶማስ እንዲህ አለ"እጅና እግሩ ካለየሁ አላምንም አለ፡፡(ዮሐ
፳፥፳፭)
☞ቶማሰ ይህንን ሊል የቻለበት ምክንያት ትንሣኤ ሙታን የለም ከሚሉ
ከሰዱቃውያን ወገን ጌታችንም የቶማሰን ጥርጣሬ ያስወግድ ዘንድ በተነሣ
በሣምንቱ በሥምንተኛው ቀን ቅዱስ ቶማስ ከሌሎች ሐዋርያት ጋር እንዳለ
በተዘጋ ቤት"ሰላም ለእናንተ ይሁን"ብሎ ካረጋጋቸው በኃላ ሐዋርያው ቶማስን
☞"ቶማስ ና በችንኳር የተቸነከሩ እጆቼን በጦር የተወጋ ጎኔን እጅህን አምጥተህ
ዳሰሰኝ ያመንክ እንጂ የተጠራጠርክ አትሁን ባለው ጊዜ ቶማስ በጦር የተወጋ
ጎኑን በዳሰሰ ጊዜ ከእሳት እንደገባ ጅማት ኩምትርትር ሲል ጌታዬ አምላኬ ብሎ
ጮኸ አምላክነቱም መሰከረ፡፡ አንተ አይተህ አምነሃል ነገር ግን ሳያዩ የሚያምኑ
ብፁዓን ናቸው፡፡(ዮሐ ፳፥፳፱)

☞እንኳን ለዳግም ትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፡፡

ቸሩ መድኃኔዓለም በቸርነቱ ለዓመቱ በሰላም ያድርሰነ አሜን።🙏❤
☞መልካም በዓል ይሁንላችሁ፡፡

20/04/2023
20/04/2023

አሜን አሜን አሜን

20/04/2023

ጌታችን ኢየሱስ በምሳሌ ሲያስተምር ባለ ጠጋ መንግስተ ሰማይ ከሚገባ ይልቅ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢያልፍ ይቀላል ብሎ ተናግሯል የዚህ ዘመን ምሳሌ ማይገባቸው ሰዎች ያኔ ጌታ በምሳሌ ሲያስተምር ቢያዩት ግመልንና የመርፌ ቀዳዳን አስተያይተው ምን ሊሉት ይችላሉ ብዬ አስቤያለሁ።
ለነገሩ ይለፍልፉ ምን ቸገረን!
ሊቀ ማእምራን ፕሮፌሰር ዘበነ ለማ የአገልግሎት ዘመንዎን ይባርከው።
አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

Address

6kilo Shromada Steeat
Addis Ababa

Telephone

+251923023990

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dawitworknehpr posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share