23/08/2023
👉 ብዙዎች ስለስራ ቅጥር እና ቫካንሲ በዚህ ቻናል በ Messege ይጠይቁናል
እስቲ ምክር ቢጤ ጣል እናርግላቹ
የዛሬ አምስት አመት ወይም አስር አመት የት መድረስ ነው ፍላጎትህ / ሽ?
የራስህን የኮንስትራክሽን ተቋም ማቋቋም? ወይስ አንድ ካምፓኒ ውስጥ ተቀጣሪ መሆን?
አንድ ሰው ሃብታም ነው የሚባለው የጊዜው እና የገንዘቡ «አለቃ» መሆን ሲችል እንጂ ብዙ ብር ስለተከፈለው አይደለም።
አንድ ትልቅ ተቋራጭ ውስጥ ተቀጠርክ / ሽ እንበል ...15 ሺ / 20 ሺ ይከፈልሃል ...ብር አለህ ነገር ግን የገንዘብህ እና የጊዜህ አለቃ አይደለህም።
በየወሩ ይከፈልሃል ስለዚህ የገንዘብህ አለቃ አይደለህም በሚወሰንልህ ጊዜ ፍቃድ ይሰጥሃል ስለዚህ የጊዜህ አለቃ አንተ ሳትሆን ሌላ ነው።
ምን መሰለህ አንተ ኢንጅኒየር ነህ ሌሎች ሞያዎች ላይ ተደግፎ ሳይሆን በግልህ ሊያንቀሳቅስህ የሚችል የሞያ ባለቤት ነህ ።
የዚህ ሞያ ባለቤት ከሆንክ ተቀጥሮ ለሌሎች መስራትን ትተህ ለምን የራስህን ድርጅት አታቋቅምም? እውቀት አለህ፤ የመስራት አቅም እና ተነሳሽነት አለህ የቸገረህ ገንዘብ ነው?
Well እስኪ አካባቢህን አስተውል የተመቻቹልህን አማራጮች ገምግም ... አንድ አማራጭ ልጠቁምህ መንግስት ለወጣቶች ያመቻቸው የስራ እድል ፈጠራ ... የCobel እና ሌሎች
የኮንስትራክሽን ስራዎች።
ከነዚህ እድሎች አላማህ የአሁን ድሎትህን ሳይሆን የማይነቃነቅ የነገ ምቾትህን ከሆነ ምትፈልገው ፤ ራእይህ ትልቅ ከሆነ ... ይህን ራዕይ ሊያሳካ የሚችል ገንዘብ የተወሰነ ቢሆንም ታገኛለህ እንዳንተ አላማ ካላቸው ጋር ሽርክና ብትፈጥር በአጭር ጊዜ
ውስጥ የራስህን ድርጅት ታስተዳድራለህ። ስራን አታጥላላ ስራን አትናቅ አላማህን በውስጥህ ይዘህ ዝም ብለህ ስራ የነገ ስኬትህ በአደባባይ ይጮኽልሃል።
እስኪ የ ኣንድ ድርጅት አጀማመር እንንገራቹ እንይ ስሙ ሰንሻይን ኮንስትራክሽን ይባላል የተጀመረው በስለት ገንዘብ ካፒታሉም 20ሺህ ብር ነው አሁን አሉ ከሚባሉ የኮንስትራክሽን ድርጅቶች አንደኛው ነው ።
ተክለ ብርሃን አምባዬ ትልቅ ቦታ እንደሚደርስ አምኖ በትንሽ ገንዘብ ይህን ድርጅት ጀመረ ። አሁን የደረሰበት ደረጃ ሳንወድ በግድ ስለሱ እንድናወራ ያስገድደናል።
እስኪ እነዚህን ስራዎች እንደ መነሻ ልንጠቁምህ በሃይድራውሊክስ ~
የሳኒታሪ ኢንስታሌሽን ስራን በትንሹ ብትሰራ
- የሃገራችን ፎቆችን ታዝበኃቸዋል ? አብዛኞቹ ትልቁ ስህተታቸው የሳኒቴሪ ኢንስታሌሽን ስራ ማለትም ከ ዳምፕነስ እናሌሎች ተያያዥ ችግሮች ጋ በተያያዘ ብዙ ሰው ሲያማርር ይስተዋላል ፕሮፌሽናል በሆነ ሰው ስለማይሰሩ ከዚጋ ተያይዞ በሚመጡ ችግሮች ይጎዳሉ። አንተ ደሞ ዲያዝይን እና ኢንስታል የማረግ እውቀት አለክ እና ለምን ይህን ቢዝነስ የሚጠይቀው ትንሽ ካፒታል ስለሆነ ለመጀመር አታስብበትም ??..
የባኞ ቤት እቃዎች ገጠማ እና ዲዛይን ። በዚህ ስራ ራሱን ችሎ የተሰማራ ድርጅት በጣም ትንሽ ነው አስብበት ።
እና ሌሎች ኣዋጭ የ ኮንስትራክሽን ሃሳቦች ኣሉ ብቻ ኣንተ ኣስብ ... ቁጭ ብለህ ኣታማርር...
አሁንም እንድትረዳ ምፈልገው ነገር ቢኖር በመንግስት መስሪያ ቤቶች እና በግል ድርጅቶች ተቀጥረው የሚሰሩ ሰዎችን አይተህ ተማር ለነገ ሚሆናቸው ምንም ነገር የላቸውም የ«አበራሽን ጠባሳ
ያየ በእሳት አይጫወትም » እንዲሉ ይህን ለማረጋገጥ ተቀጣሪ መሆን አይጠበቅብህም።
በራስህ እምነት ይኑርህ ፤ ደፍረህ ወደ ስራ ግባ ስኬት አጠገብህ ናት!
📌ለሁሉም እንዲዳረስ ፖስቶቹን SHARE አድርጉልን።
በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ከዲዛይን ,ቅየሳ ጀምሮ እስከ ፊኒሺንግ ሁሉንም 👷♂እናማክራለን 🏢ዲዛይን እናደርጋለን 📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን 🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነ.....