Defense Construction Enterprise

Defense Construction Enterprise Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Defense Construction Enterprise, Construction Company, Addis Ababa.

Defense Construction Enterprise was established in 2010 by Ethiopian ministry of council regulation NO 185/2010 as public enterprise and national defense as supervising authority of the enterprise.

28/05/2026
27/05/2026

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች
በሙሉ እንኳን ለ1447ኛው ታላቁ የኢድ አል አድሃ
(አረፋ) በዓል በሰላምና በጤና አደረሳችሁ!
ዒድ ሙባረክ!

#የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ

ኢንተርፕራይዙ በድሬዳዋ ከተማ የገነባው የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ፕሮጀክት ተመረቀ። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ግንቦት 16 ቀን 2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የምስራቅ ፈጥኖ ደራሽ ...
24/05/2026

ኢንተርፕራይዙ በድሬዳዋ ከተማ የገነባው የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ፕሮጀክት ተመረቀ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ግንቦት 16 ቀን 2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የምስራቅ ፈጥኖ ደራሽ ማዕከል ግንባታን ከተሰጠው የውል ጊዜ ቀድሞ ያጠናቀቀው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ምስጋና ተችሮታል።

በድሬዳዋ ከተማ የተገነባው የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የምስራቅ ፈጥኖ ደራሽ ማዕከል በዛሬው እለት በተመረቀበት ወቅት፣ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አዛዥ ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገብረሚካኤል የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝን በልዩ ሁኔታ አመስግነዋል።

ኢንተርፕራይዙ ለፕሮጀክቱ ከተሰጠው የውል ማጠናቀቂያ ጊዜ አስቀድሞ ግንባታውን ሙሉ በሙሉ በጥራት አጠናቆ ማስረከቡን በከፍተኛ አድናቆት የገለፁት ኮሚሽነር ጄኔራሉ የማዕከሉ ግንባታ ሳይጓተት የተጠናቀቀው፣ ያጋጠሙ የተለያዩ ማነቆዎችን በተግባር በመቅረፍ መሆኑን አብራርተዋል።

በተጨማሪም በአሁኑ ወቅት ለግንባታው የወጣው ወጪ ካለው አጠቃላይ የገበያና የኮንስትራክሽን ሁኔታ አንጻር እጅግ ወጪ ቆጣቢ መሆኑን ጠቅሰው፤ የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ማዕከሉን ልክ እንደ ራሱ ተቋም በመቁጠር በጥራትና በከፍተኛ ቁርጠኝነት የገነባ መሆኑን ገልጸዋል።

ኢንተርፕራይዙ በተመሳሳይ መልኩ በሐረር ከተማ የሚገኘውንና በቀጠናው ዘመናዊ የሆነውን የፖሊስ ሆስፒታል ግንባታ ወደ ማጠናቀቂያው ማድረሱንም ጠቁመዋል።

ማዕከሉ ድሬዳዋ ላይ መመስረቱ ለአካባቢውና ለአጎራባች የሐረሪና የሶማሌ ክልሎች ሰላምና ደህንነት አስተማማኝ ዋስትና የሚሰጥ መሆኑን የገለጹት የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር በበኩላቸው፣ ግንባታው በጥራትና በተያዘለት ጊዜ መጠናቀቁ ለቀጠናው ትልቅ ኩራት መሆኑን ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን አማካሪነት ግንባታው የተከናወነውና ዛሬ በይፋ የተመረቀው ይህ ግዙፍ ማዕከል የአስተዳደር ቢሮ ህንጻ፣ ደረጃቸውን የጠበቁ የሴቶችና የወንዶች ዶርሚተሪዎች፣ ክሊኒክ፣ የእንግዳ ማረፊያ እንዲሁም ብዙ አገልግሎት የሚሰጡ ክፍሎችን ያካተተ ነው።

ዘጋቢ ማርታ ተፈሪ
ፎቶግራፍ መሳይ ያደታ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official

22/05/2026

ህግን አለማወቅ ከተጠያቂነት አያድንም!

ሙስናን ለመከላከል እና አጥፊዎችን ለህግ ለማቅረብ የሚደረጉ ጥረቶች ሁሉ በአስተማማኝ ሕጋዊ መሰረት ላይ የተመረኮዙ እንዲሆኑ የህግ ማዕቀፎች ወሳኝ መሳሪያዎች ናቸው።

👉 ስለ ፀረ-ሙስና ህጎች ምን ያህል ያውቃሉ?

የሀገራችንን የፀረ-ሙስና ትግል የሚመሩ ዋና ዋና ዓለም አቀፍ፣ አህጉራዊና ሀገራዊ የህግ ማዕቀፎች የሚከተሉት ናቸው፦

🌐 ዓለም አቀፍ ስምምነቶች፡

• የተባበሩት መንግስታት የፀረ-ሙስና ኮንቬሽን (አዋጅ ቁጥር 544/1999 ዓ.ም)፦ በሙስና የተገኘን ሀብት ማስመለስና ዓለም አቀፍ ትብብር ላይ ያተኩራል።

• የአፍሪካ ህብረት የሙስና መዋጊያና መታገያ ኮንቬሽን (አዋጅ ቁጥር 545/1999 ዓ.ም)፦ በአፍሪካ አህጉር (በተለይም በመንግስት ባለስልጣናት) የሚፈጸሙ ሙስናዎችን ለመዋጋት የወጣ ስምምነት ነው።

🇪🇹 ዋና ዋና የሀገር ውስጥ ህጎች፡

• የሙስና ወንጀሎች አዋጅ ቁጥር 881/2007 ዓ.ም፦ የተለያዩ የሙስና ወንጀሎችንና ቅጣቶችን በ25 አንቀጾች (ከአንቀጽ 9 እስከ 33) ደንግጎ የያዘ ተቀዳሚ ህግ ነው።

• የሀብት ማሳወቂያና ማስመዝገቢያ አዋጅ ቁጥር 668/2002 ዓ.ም፦ ተመራጮች፣ ተሿሚዎችና የመንግስት ሰራተኞች ሀብታቸውን እንዲያስመዘግቡ በማስገደድ የመንግስት ሀብት እንዳይመዘበር ይከላከላል።

• የተሻሻለው የሥነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1236/2013 ዓ.ም፦ በትውልድ ሥነ-ምግባር ግንባታ እና በአስቸኳይ ሙስና መከላከል ላይ ይሰራል፡

የፌደራል አስተዳደር ሥነ-ሥርዓት አዋጅ (1183/2012)

የምስክሮችና ጠቋሚዎች ጥበቃ አዋጅ (699/2003)፣ የመንግስት ግዥ አዋጅ (1333/2016) እና የንብረት ማስመለስ አዋጅ (1364/2017) ይጠቀሳሉ።

"ትውልድን በሥነምግባር፤ ተቋምን በአሰራር እንገንባ!"

የዘመኑን የቴክኖሎጂ ሽግግር መጠቀም አስፈላጊ መሆኑ ተገለፀ። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ግንቦት 05 ቀን 2018 ዓ.ም የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ አሰራሩን ዘመናዊና ውጤታማ ለማ...
13/05/2026

የዘመኑን የቴክኖሎጂ ሽግግር መጠቀም አስፈላጊ መሆኑ ተገለፀ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ግንቦት 05 ቀን 2018 ዓ.ም

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ አሰራሩን ዘመናዊና ውጤታማ ለማድረግ የጀመረው የዲጂታላይዜሽን ጉዞ አካል የሆነው የተግባር ስልጠና ዛሬ ተሰጥቷል። በስልጠናው መክፈቻ ላይ የተገኙት የኢንተርፕራይዙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ብርጋዲየር ጄኔራል ኢንጂነር ሰጠኝ ሊኪሳ፤ ተቋሙ ካለበት ሰፊ ኃላፊነት አንጻር አሰራሮችን ማዘመን ወሳኝ መሆኑን ገልፀዋል።

ዋና ሥራ አስፈፃሚው አሰራራችንን ከወረቀት ንክኪ ወደ ዲጂታል ማሸጋገር አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው በማለት፣ አመራሩ በቴክኖሎጂ የታገዘ የክትትልና ቁጥጥር ሥርዓት እንዲከተል ስልጠናው ትልቅ ፋይዳ እንዳለው በአፅንኦት ሰጥተዋል።

በአመራር ደረጃ የተጀመረው ስልጠና በተዋረድ እስከ ታችኛው የሥራ ክፍል ድረስ እንደሚቀጥልና ተቋሙ ሙሉ በሙሉ ወደ ዲጂታል የሥራ አካባቢ ለመቀየር የያዘውን ግብ ለማሳካት በትኩረት እንደሚሰራም አረጋግጠዋል።

በኢንተርፕራይዙ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አገልግሎት መምሪያ የተሰጠው ይህ ስልጠና፤ የሥራ መሪዎች የኢሜል ልውውጥንና የሥራ መርሃ-ግብር ምደባን በአውትሉክ (Outlook) መተግበሪያ፣ እንዲሁም የሥራ ሪፖርት አቀራረብን በሰርኩኒ (Serkuni) መተግበሪያ በኩል በዘመናዊ መንገድ እንዲመሩ ለማስቻል የታለመ ነው። የመምሪያው ኃላፊ አቶ ሚሳኤል የማነ እንደገለጹት፤ ስልጠናው አመራሩ መረጃዎችን በፍጥነት እንዲለዋወጥና ሥራዎችን በቅልጥፍና እንዲያከናውን ትልቅ እገዛ ያደርጋል።

ዘጋቢ ማርታ ተፈሪ
ፎቶግራፍ ጥላሁን ደስታ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official

የመከላከያ ዋር ኮሌጅ ግንባታ 85 በመቶ አፈጻጸም ላይ እንደሚገኝ የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ ገለጹሚያዝያ 28 ቀን 2018ዓ.ምየመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ በአዲስ አበባ መካኒሳ ቆሬ...
06/05/2026

የመከላከያ ዋር ኮሌጅ ግንባታ 85 በመቶ አፈጻጸም ላይ እንደሚገኝ የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ ገለጹ

ሚያዝያ 28 ቀን 2018ዓ.ም

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ በአዲስ አበባ መካኒሳ ቆሬ አደባባይ አካባቢ እየገነባ ያለው የመከላከያ ዋር ኮሌጅ ግንባታ 85 በመቶ መጠናቀቁን የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ዮሃንስ ኃይሉ ገለጹ ።

የመከላከያ መሃንዲስ ዋና መመሪያ ባለቤት የሆነውና በመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት አማካሪነት የሚከናወነው ይህ ፕሮጀክት፤ በስትራቴጂካዊ የደህንነት ጉዳዮች ላይ ብቃት ያላቸው ከፍተኛ አመራሮችን የሚያፈራ የልህቀት ማዕከል ለማድረግ ታስቦ በ በከፍተኛ የጥራት ሁኔታ እየተገነባ ይገኛል ።

የተከናወኑ ዋና ዋና የግንባታዎች መካከል:-
• የተማሪዎች ማደሪያ ህንፃዎች 99 በመቶ ተጠናቀዋል ።
• የመመገቢያ ህንፃ 95 በመቶ የግንባታ ደረጃ ላይ ይገኛል ።
• የቢሮ አስተዳደር ህንፃ 87 በመቶ ደርሷል ።
• የመማሪያ ህንፃ 59 በመቶ አፈጻጸም ላይ ይገኛል ።

ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቁ ስራዎች፡- የመሰረት ቁፋሮ፣ የመዋቅር ስራ፣ የግንብ ስራ፣ የጣራ እና የብረት ሥራዎች 100 በመቶ ተጠናቀዋል ።
በተለይም ይህ ፕሮጀክት በኢንተርፕራይዙ ታሪክ አዲስ ተሞክሮ የታየበት መሆኑን ኢንጂነር ዮሃንስ ጠቁመዋል ።

ይኸውም የህንፃዎቹ የመዋቅር ፎርም ዎርክ ሥራ በጥራት በመከናወኑ ምክንያት የኮንክሬት ስላብ ሶፊት (ሶሌታ) ልስን ሥራን ማስቀረት ተችሏል ። በዚህም 5,685,138.37 ብር የሚሆን ወጪ ማዳን ተችሏል ።

ግንባታው በሂደት ላይ እያለ እንደ ዲዛይን ለውጥ፣ የቦታው ረግረጋማነት፣ የዋጋ ንረት እና ከፍተኛ የሆነያልታሰበ የድንጋይ ቁፋሮ ያሉ ፈታኝ ሁኔታዎች ቢያጋጥሙትም፤ ኢንተርፕራይዙ ያለውን ተግዳሮቶችን የመቋቋም ልምድ በመጠቀም ወደ ማጠናቀቂያው ምዕራፍ እያደረሰው ይገኛል ። በአሁኑ ወቅት ቀሪ የሆኑ 15 በመቶ ሥራዎችን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ የአመራሮች ክትትልና የሠራተኞች ትጋት በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል ።

መከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ሆስፒታልን ቀሪ ግንባታዎች ለማጠናቀቅ ከ 1.7 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የግንባታ ውል ተፈራረመሚያዝያ 21 ቀን 201...
29/04/2026

መከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ሆስፒታልን ቀሪ ግንባታዎች ለማጠናቀቅ ከ 1.7 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የግንባታ ውል ተፈራረመ

ሚያዝያ 21 ቀን 2018 ዓ.ም

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን በአዲስ አበባ ከተማ የሚያስገነባውን የሪፈራል ሆስፒታል ቀሪ ሥራዎች ለማጠናቀቅ የሚያስችለውን ከ 1.7 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የውል ስምምነት ሚያዝያ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ተፈራርሟል። በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የኢንተርፕራይዙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ብ/ጄኔራል ኢንጂነር ሰጠኝ ሊኪሳ እና የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል የኑስ ሙሉ ውሉን በጋራ ፈርመዋል።

የውል ስምምነቱ ቀሪ የሲቪል ሥራዎችን፣ የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታን፣ የቆሻሻ ውኃ ማጣሪያንና የሳይት ወርክ ሥራዎችን ሙሉ በሙሉ አጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ ማድረግን ያካትታል።

በሥነ-ሥርዓቱ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ጄኔራል የኑስ ሙሉ፤ የሆስፒታሉ ግንባታ ሂደት ከ14 ዓመታት በላይ የዘገየ መሆኑን አስታውሰው፣ አሁን ከመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ጋር በተደረገው ስምምነት ግንባታው በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ለታራሚዎችና ለአካባቢው ማኅበረሰብ የጤና አገልግሎት መስጠት እንዲችል በትኩረት እንደሚሠራ ገልጸዋል። ይህ ስምምነት በቀጣይም ኮሚሽኑ በሚያስገነባቸው ሌሎች ፕሮጀክቶች ላይ ከኢንተርፕራይዙ ጋር በጋራ ለመሥራት ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥርም አመላክተዋል።

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ዋና ሥራ አስፈጻሚ
ብ/ጄኔራል ኢንጂነር ሰጠኝ ሊኪሳ በበኩላቸው፤ ኢንተርፕራይዙ ፕሮጀክቶችን በጥራት በመገንባት በሀገሪቱ የሚስተዋሉ የግንባታ ክፍተቶችን መሙላት መሆኑን አብራርተዋል። ኢንተርፕራይዙ በሆስፒታልና በተለያዩ ግዙፍ መሠረተ ልማቶች ላይ ያለውን ሰፊ ልምድ በመጠቀም፣ ይህን ሆስፒታል በተቀመጠለት የጊዜ ገደብና በላቀ ጥራት አጠናቆ ለማስረከብ ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጠዋል።

ሆስፒታሉ180 የታካሚ አልጋዎችን፣ 16 የጽኑ ሕሙማን አልጋዎችን እና 4 የኦፕሬሽን ክፍሎችን ጨምሮ የአይን፣ የጥርስ፣ የአንገት በላይና የራዲዮሎጂ ሕክምና ክፍሎችን ያካተተ ነው። ግንባታው ሲጠናቀቅም ከማረሚያ ተቋሙ ባሻገር ለአካባቢው ማኅበረሰብ ተደራሽ በመሆን የሀገሪቱን የጤና ተደራሽነት ጥረት በእጅጉ የሚያግዝ ይሆናል።

በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ማጠቃለያ ላይ የሁለቱ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች እና አማካሪ ድርጅቶች የሆስፒታሉን የግንባታ ደረጃ በመስክ ምልከታ ጎብኝተዋል።

ዜና እረፍትበመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የጋፋት አርማመንት ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግንባታ ፕሮጀክት ሰራተኛ የነበሩት አቶ ዳርፈታ ሸዋ ባጋጠማቸው ድንገተኛ ህመም ከዚህ ዓለም ድካም...
28/04/2026

ዜና እረፍት

በመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የጋፋት አርማመንት ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግንባታ ፕሮጀክት ሰራተኛ የነበሩት አቶ ዳርፈታ ሸዋ ባጋጠማቸው ድንገተኛ ህመም ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ማኔጅመንት አባላትና ሰራተኞችም በአቶ ዳርፈታ ህልፈት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለፅን፤ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸውና ለስራ ባልደረቦቻቸው ፈጣሪ መፅናናትን እንዲሰጥ እንመኛለን፡፡

ፈጣሪ ነፍሳቸውን በገነት ያኑርልን!

ታሪካዊው የራስ ኃይሉ ዓለም-አቀፍ መዋኛ ገንዳ በዛሬው ዕለት ለህዝብ አገልግሎት እንዲሰጥ ተደረገሚያዝያ 17/2018ዓ.ምመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የሚገ...
25/04/2026

ታሪካዊው የራስ ኃይሉ ዓለም-አቀፍ መዋኛ ገንዳ በዛሬው ዕለት ለህዝብ አገልግሎት እንዲሰጥ ተደረገ

ሚያዝያ 17/2018ዓ.ም

መከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የሚገኘውን የታሪካዊው የራስ ኃይሉ ዘመናዊ መዋኛ ግንባታ ፕሮጀክት በስኬት አጠናቆ ለአገልግሎት እንዲውል አድርጓል። ኢንተርፕራይዙ የግንባታ ሥራውን ቀደም ብሎ አጠናቆ የርክክብ ሂደቱ የዘገየ ቢሆንም፣ በዛሬው ዕለት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ማዕከሉን በይፋ መርቀው ለሕዝብ አገልግሎት እንዲሰጥ አድርገዋል።

የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ደረጄ ኃ/ገብርኤል እንደገለጹት፤ ግንባታው በዋናነት 4,100 ሜትር ኪዩብ ውሃ መያዝ የሚችልና 50 በ 25 ሜትር ስፋት ያለው ዓለም-አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ መዋኛ ገንዳን ነው። ከዚህም በተጨማሪ የሕፃናት መዋኛ ገንዳ፣ የመዝናኛ ክበብ፣ የልብስ መቀየሪያ ክፍሎች፣ ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ ሱቆች እና የፓምፕ ቤት በውስጡ የያዘ ዘመናዊ ማዕከል ነው።

ይህ ግዙፍ መዋኛ ገንዳ እጅግ ዘመናዊ የሙቀት መቆጣጠሪያ (Heating System) ቴክኖሎጂ የተገጠመለት ሲሆን፤ ይህም የውሃውን ሙቀት እንደ አስፈላጊነቱ በማስተካከል ለውድድሮችና ለልምምዶች ምቹ እንዲሆን ያደርገዋል። በተጨማሪም ውሃው በፊዚካላዊ፣ ኬሚካላዊ እና ባዮሎጂካዊ መንገዶች ታክሞና ተጣርቶ መልሶ ጥቅም ላይ እንዲውል የሚያስችል ዘመናዊ የአሠራር ሥርዓት ተዘርግቶለታል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዛሬው ዕለት ማዕከሉ ወደ አገልግሎት እንዲገባ ያደረጉ ሲሆን፤ ይህም ለከተማዋ ስፖርታዊ እንቅስቃሴና ለመዝናኛ ዘርፍ ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር ይታመናል።

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Defense Construction Enterprise posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share