Amhara pipe factory plc

Amhara pipe factory plc Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Amhara pipe factory plc, Industrial Company, Bahir Dar.

Amhara pipe quality objective and quality policy
31/01/2024

Amhara pipe quality objective and quality policy

አማራ ፓይፕ ፋብሪካ የገና በዓልን አስመልክቶ ድጋፍ አደረገ፡፡አማራ ፓይፕ ፋብሪካ ኃላ/የተ/የግል ማህበር የጌታችን የመድሀኒታችን የእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓልን አስመልክቶ በባህር ዳር ከ...
09/01/2024

አማራ ፓይፕ ፋብሪካ የገና በዓልን አስመልክቶ ድጋፍ አደረገ፡፡

አማራ ፓይፕ ፋብሪካ ኃላ/የተ/የግል ማህበር የጌታችን የመድሀኒታችን የእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓልን አስመልክቶ በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር በተለያዩ ክፍለ ከተማዎች ለሚገኙ ለ70 ዝቅተኛ ገቢ ላለቸው የሕብረተሰብ ክፍሎች ለእያንዳንዳቸው ዶሮ፣ ዘይት 5 ሊትር እንዲሁም የፊኖ ዱቄት 25 ኪሎ ግራም እንኳን አደረሳችሁ በማለት አበርክቷል፡፡
ለመላ የክርስትና እምነት ተከታዮች በዓሉ የሠላም፣ የጤና እና የመተሳሰብ እንዲሆንልን ፋብሪካችን መልካም ምኞቱን ይገልፃል፡፡

መልካም የገና በዓል

የአማራ ፓይፕ ፋብሪካ ለሰራተኞቹ ልጆች በ3,321,596.60  ብር ያስገነባዉ የህፃናት ማቆያ ዛሬ ሰኔ 1/2015ዓ.ም የፋብካዉ ዋና ስራ አስኪጅ የሆኑት አቶ ወርቁ ባዮ ፣የሰዉ ሃይል አሰ/...
10/06/2023

የአማራ ፓይፕ ፋብሪካ ለሰራተኞቹ ልጆች በ3,321,596.60 ብር ያስገነባዉ የህፃናት ማቆያ ዛሬ ሰኔ 1/2015ዓ.ም የፋብካዉ ዋና ስራ አስኪጅ የሆኑት አቶ ወርቁ ባዮ ፣የሰዉ ሃይል አሰ/ጠቅ/አገ ስራ አስኪያጅ አቶ አንተነህ ደባሱ እና የሰራተኛ ማህበር ሊቀመንበር አቶ ተገኜ አይናለም የመክፈቻ ንግግር፣ ዳቦ በመቁረስ እና ሪባን በመቁረጥ የማናጅመንት አባላት እና ሰራተኛዉ በተገኙበት በይፋ ስራ አስጀምረዉታል፡፡ የፋብሪካዉ ሰራተኞች እና በተለይ ሴት ወላጆች እንኳን ደስ አላችሁ፡፡

3ኛው የአማራ ክልል ከተሞች የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎቶች ማህበር ጠቅላላ ጉባዔ በጐንደር ከተማ ተካሄደ፡፡በጉባዔው ላይ የክልሉ ውሃና ኢነርጂ ቢሮ፣ የኢትዮጵያ ከተሞች መጠጥ ውሃና ፍሳሽ ...
06/06/2023

3ኛው የአማራ ክልል ከተሞች የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎቶች ማህበር ጠቅላላ ጉባዔ በጐንደር ከተማ ተካሄደ፡፡

በጉባዔው ላይ የክልሉ ውሃና ኢነርጂ ቢሮ፣ የኢትዮጵያ ከተሞች መጠጥ ውሃና ፍሳሽ ፌዴሬሽን፣ የክልሉ ውሃ ልማት ፈንድ ጽ/ቤት፣ የዞን ውሃና ኢነርጂ መምሪያዎች፣ በክልሉ የሚገኙ ከደረጃ 1 እስከ 6 የሆኑ 220 የከተሞች ውሃና ፍሳሽ አገልግሎቶች እንዲሁም አጋር አካላት ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

ጉባዔው ከግንቦት 26 - 27 ቀን 2015 ዓ.ም በጐንደር ከተማ የተካሄደ ሲሆን በዚህም የፋብሪካችንን ምርቶች ማስተዋወቅ ተችሏል፡፡

ፋብሪካችን ስፖንሰር በመሆን ላደረገው ድጋፍ የጉባዔው አዘጋጅ በሆነው በጐንደር ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት በኩል የምስክር ወረቀት ተሰጥቶታል፡፡

31/05/2023
በኢትዬጵያ ካይዘን ልህቀት ማእከል በስካይ ላይት ሆቴል በቀን 23/08/2015 አ.ም በተዘጋጀው 8ተኛው አመታዊ አዋርድ ኮንፍረንስ ላይ ፋብሪካችን በተቋም ደረጃ ከአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ  ...
02/05/2023

በኢትዬጵያ ካይዘን ልህቀት ማእከል በስካይ ላይት ሆቴል በቀን 23/08/2015 አ.ም በተዘጋጀው 8ተኛው አመታዊ አዋርድ ኮንፍረንስ ላይ ፋብሪካችን በተቋም ደረጃ ከአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ 3 ተኛ እና በጥምር ቡድን በምርት ግድፈት ቅነሳ በድጋሚ 3ተኛ በመውጣት የፋብሪካችን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ወርቁ ባዬ 2ለት ሰርተፍኬት :2ለት ዋንጫ እና 2ለት የግድግዳ ሰአት ከተከበሩ የኢትዮጵያ እንዱስትሪ ሚኒስተር አቶ መላኩ አለበል እና ከጃፓን አምባሳደር እጅ እውቅና እና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል ። እንኳን ደስ ያለን።

የአማራ ክልል ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት እና ኮርድ ኤድ ኢትዮጵያ በመተባበር የአምራች ዘርፉ ምርቶችን እንዲያስተዋውቅ በተዘጋጀው ኢግዚቢሽን ላይ በመሳተፍ በባህር ዳር ከተማ በአለ በጅምላ ግ...
27/02/2023

የአማራ ክልል ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት እና ኮርድ ኤድ ኢትዮጵያ በመተባበር የአምራች ዘርፉ ምርቶችን እንዲያስተዋውቅ በተዘጋጀው ኢግዚቢሽን ላይ በመሳተፍ በባህር ዳር ከተማ በአለ በጅምላ ግቢ ውስጥ ከየካቲት 10 - 12/2015 ዓ.ም ፋብሪካችን ምርቶችን አስተዋውቆል፡፡

የአማራ ፓይፕ ፋብሪካ በ4ኛው አለም አቀፍ የንግድ ትርኢት ላይ ተሳትፏል፡፡የአማራ ፓይፕ ፋብሪካ “BuildExpo Africa” በሚል በተዘጋጀው 4ኛው አለም አቀፍ የንግድ ትርኢት ከጥር 15-...
25/01/2023

የአማራ ፓይፕ ፋብሪካ በ4ኛው አለም አቀፍ የንግድ ትርኢት ላይ ተሳትፏል፡፡

የአማራ ፓይፕ ፋብሪካ “BuildExpo Africa” በሚል በተዘጋጀው 4ኛው አለም አቀፍ የንግድ ትርኢት ከጥር 15-17/2015 ዓ.ም (January 23-25, 2023 G.C) በአዲስ አበባ ሚሊየም አዳራሽ ምርቶችን በማስተዋወቅ ላይ ይገኛል፡፡
በንግድ ትርኢቱ ላይ ከተለያዩ የአህጉሪቱ ክፍሎች በመምጣት ድርጅቶች የተሳተፉ በመሆኑ ፋብሪካው ምርቶችን ለማስተዋወቅ እና ብሎም የንግድ ግንኙነት በመፍጠር የገበያ መዳረሻ ምህዳሩን እንዲያሰፋ ያደርገዋል፡፡

Amhara Pipe Factory Quality Policy
25/01/2023

Amhara Pipe Factory Quality Policy

Amhara Pipe Factory Quality Objectives Obejectives
25/01/2023

Amhara Pipe Factory Quality Objectives Obejectives

ለፈተናዎች ያልተንበረከከው ፋብሪካ            **************        ሕዳር 01/2015 ዓ.ም ባሕር ዳር፤በምስራቅ አፍሪካ ደረጃ ተወዳዳሪና ተመራጭ የፕላስቲክ ፋብሪካ ሆኖ ...
12/11/2022

ለፈተናዎች ያልተንበረከከው ፋብሪካ
**************
ሕዳር 01/2015 ዓ.ም ባሕር ዳር፤
በምስራቅ አፍሪካ ደረጃ ተወዳዳሪና ተመራጭ የፕላስቲክ ፋብሪካ ሆኖ የመገኘት ዓላማን ሰንቆ በመንቀሳቀስ በርካታ አመርቂ ውጤቶችን ያስመዘገበው የአማራ ፓይፕ ፋብሪካ በበርካታ ፈተናዎች ታጅቦ ባለፈው የ2014 በጀት ዓመት 189,376,423.00 ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታውቋል፡፡
ለዚህ ውጤት መገኘትም ሰራተኞች፣ የማኔጅመንት አባላትና የቦርድ አመራሮች ተቀናጅተውና ተናበው ከመስራት ባለፈ የፋብሪካውን ምርቶች ከክልሉ ውጭ በአፋር፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ ደቡብ፣ አዲስ አበባ፣ ኦሮሚያ፣ ኢትዮ ሶማሊያና ሌሎች ክልሎች ድረስ ገብቶ በመሸጥ ተደራሽነትን ለማስፋት የተደረገው እንቅስቃሴ ተጨባጭ ውጤት እንዳስገኘ ተመላክቷል፡፡
ፋብሪካው በክልላችን ውስጥ ካሉት የመንግስት የልማት ድርጅቶች በተለየ ሁኔታ ተከታታይነት ያለው የትርፍ እድገት በማስመዝገቡ ከልማት ድርጅቶች አስተዳደር የዋንጫና የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቶለታል፡፡
በተመሳሳይም በበጀት ዓመቱ 88,082,574.68 ብር ግብር በመክፈል በፌደራል ደረጃ የዓመቱ ምርጥ ግብር ከፋይ በመሆን በክብርት ፕሬዘዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ የዋንጫ ሽልማትን ተቀብሏል፡፡
ምን ይሄ ብቻ!!
በ2014 በጀት ዓመት በተለያዩ ማህበራዊ ጉዳይ ዘርፎች ላይ ፈጥኖ ደረሽ በመሆን በገንዘብ ብቻ 25,543,653.06 ብር በላይ በመለገስ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ተወጥቷል፤ አጋርነቱንም አሳይቷል፡፡
በተያዘው የ2015 በጀት ዓመትም 10 ሺህ ሜትሪክ ቶን ምርት በማምረትና 1 ነጥብ 59 ቢሊዬን ብር ሽያጭ በማከናወን ከ265 ሚሊዮን ብር በላይ የተጣራ ትርፍ ለማግኘት ታቅዶ በመትጋት ላይ የሚገኝ መሆኑን የፋብሪካው ዋና ሥራ አሥኪያጅ አቶ ወርቁ ባዬ አስረድተዋል፡፡
በም/ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የአስተዳደር ጉዳዮች ክላስተር አስተባባሪና የፋብሪካው የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት ሰማ ጥሩነህ (ዶ.ር) በበኩላቸው ፋብሪካው ወደፊትም የበለጠ ትርፋማ እንደሚሆን ሙሉ እምነት ያላቸው መሆኑን በመግለጽ የቦርድ አባላትም ስትራቴጂክ የሆኑ የትኩረት ነጥቦችን ለይተው ወደ ተግባር የገቡ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ በተለይም ደግሞ ማሽኖች ዘመኑን የሚዋጁና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪና ተመራጭ እንዲሆኑ ለማስቻል የዕድሳትና የማስፋፊያ ስራዎች እንደሚተገበሩ ጠቁመዋል፡፡
የዶላር ችግርን ለመቅረፍም ምርቱን ከኢትዮጵያ ውጭ ወደሌሎች የአፍሪካ አገራት በመላክ ሙሉ በሙሉም ባይሆን በከፊል የምንዛሬ ዕጥረቱን ለመቅረፍ እየተንቀሳቀሱ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
በመድረኩ ማጠቃለያም የተሻለ አፈጻጸም ለነበራቸው የካይዘን ልማት ቡድኖች፣ በስራቸውና በመልካም ስነ-ምግባራቸው አርዓያ መሆን ለሚችሉ ሰራተኞችና ፋብሪካው እዚህ ደረጃ እንዲደርስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ለነበራቸው የማኔጅመንት አባላትና የቀድሞ የቦርድ አባላት የገንዘብ፣ የአይነትና የዕውቅና ሰርትፊኬት ተበርክቶላቸዋል፡፡
ተሸላሚ የሆኑት ሠራተኞችም የማበረታቻ ሽልማቱ ተነሳሽነታቸውን እንደጨመረላቸውና ለበለጠ ውጤት የማትጋት ሚናው የጎላ መሆኑን ገልጸዋል።
መልካም የስራ ጊዜ እንዲሆንላችሁ ምኞታችን ከልብ ነው!!

25/03/2022
ለ2014 ክርምት(summer) ኢንተርንሽፕ ለምትወጡ ተማሪዎች
14/03/2022

ለ2014 ክርምት(summer) ኢንተርንሽፕ ለምትወጡ ተማሪዎች

የአማራ ፖይፕ ፋብሪካ አመራሮች እና ሰራተኞች ከሌሎች ልማት ድርጅቶች ጋር በጋራ በመሆን የዘማች ቤተሰብ ሰብል ሰበሰቡ። በሰላም ጊዜ አርሶ አደር በጦርነት ጊዜ ወታደር ሆኖ እያገለገለ ላለው ...
11/12/2021

የአማራ ፖይፕ ፋብሪካ አመራሮች እና ሰራተኞች ከሌሎች ልማት ድርጅቶች ጋር በጋራ በመሆን የዘማች ቤተሰብ ሰብል ሰበሰቡ። በሰላም ጊዜ አርሶ አደር በጦርነት ጊዜ ወታደር ሆኖ እያገለገለ ላለው ዘማች አርሶ አደሮቻችን የበቆሎ ሰብል መሰብሰብ ተችሏል። የዘማች ቤተሸቦችም በተደረገው ድጋፍ ከፍተኛ ደስታ የተሰማቸው መሆኑን በመግለፅ ዘማቾቹ በድል እንዲመለሱ መልእክቱን አስተላልፈዋል።
ህዳር 2014 ዓ.ም.

Address

Bahir Dar

Telephone

+251918029650

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amhara pipe factory plc posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Amhara pipe factory plc:

Share