Fancy Construction Work ፋንሲ ኮንስትራክሽን ስራ

  • Home
  • Fancy Construction Work ፋንሲ ኮንስትራክሽን ስራ

Fancy Construction Work ፋንሲ ኮንስትራክሽን ስራ Road and Building Constructions from A to Z

29/03/2024

የጨረታ ማስታወቂያ

ለእግረኛ መንገድ ታይልስ አምራች ድርጅቶች በሙሉ፤
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በተለያዩ የከተማዋ ክፍሎች ለሚገነባቸው የእግረኛ መንገዶች ንጣፍ የሚውል ደረጃውን የጠበቀ ታይልስ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም በጨረታው የሚሳተፉ የታይልስ አምራቾች፡-

1ኛ/ የሚያመርቱትን ታይልስ ዲዛይን እና የጥራት ደረጃ ማረጋገጫ፣

2ኛ/ የሚያቀርቡትን ታይልስ የካሬ ሜትር እና የነጠላ ዋጋ፣

3ኛ/ በቀን የማምረት አቅምን የሚያሳይ የተረጋገጠ ማስረጃ፣

4ኛ/ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን ሰርተፍኬት)፣

5ኛ/ በማህበር የተደራጁ ከሆነ በሚመለከተው አካል የተደራጁበትን እና ወደ ስራ እንዲገቡ የተሰጠ ማረጋገጫ

ሰነዶችን በማያያዝ ይህ ማስታወቂያ ከተነገረበት ቀን ጀምሮ እስከ መጋቢት 25 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ አዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ዋና መስሪያ ቤት ቢሮ ቁጥር 107 በስም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማቅረብ እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡


አድራሻ፡- ሳር ቤት ከአዳምስ ፓቪሊዮን ህንጻ ጎን

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን

የጨረታ ማስታወቂያ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ያለበትን የፋይናንስ እጥረት በመፍታት ተጨማሪ ወጪ ቆጣቢ ቤቶችን ገንብቶ ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ  እንዲችል ከዲዛይን ግንባታ ቢሮ ጋ...
04/02/2024

የጨረታ ማስታወቂያ

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ያለበትን የፋይናንስ እጥረት በመፍታት ተጨማሪ ወጪ ቆጣቢ ቤቶችን ገንብቶ ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ እንዲችል ከዲዛይን ግንባታ ቢሮ ጋር በመሆን በመንግስት በተመደበ ካፒታል በጀት በተለያዩ ክፍለ ከተሞች ተገንብተው የተጠናቀቁ 3,146 የመኖሪያ ቤቶችን እና 306 የንግድ ቤቶችን በድምሩ 3,452 ቤቶችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ በሽያጭ ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡

ማንኛውም ለጨረታ የቀረቡ የመኖሪያ እና የንግድ ቤቶችን ለመግዛት የሚፈልግ ሁሉ ማንነቱን የሚገልጽ መታወቂያ በመያዝ የጨረታ ሰነድ ከ27/05/2016 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 20/06/2016 ዓ.ም ድረስ ቅዳሜን እስከ 11፡00 ሰአት እና እሁድ ግማሽ ቀን ጨምሮ ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 1፡30 እስከ ማታ 1፡30 ድረስ በመቅረብ የማይመለስ ብር 1000.00(አንድ ሺህ) በመክፈል የጨረታ ሰነዱ መግዛት የሚቻል መሆኑን እየገለጽን የሰነድ መሸጫ ቦታ ከዚህ በታች ባለው ሰንጠረዥ ተመላክቷል

የማሽን ክራይ
12/08/2023

የማሽን ክራይ

የገልባጭ መኪና ክራይ
10/08/2023

የገልባጭ መኪና ክራይ

  /  /  By: Gubaie A.          ---------   ---------------   ----   📜በዚህ ጽሁፍ ተቋራጭን ከግንባታ ስፍራ/ሳይት የማባረር መብት ለማን የተሰጠ ነው?በ...
01/07/2023

/ /

By: Gubaie A.
--------- --------------- ----
📜በዚህ ጽሁፍ ተቋራጭን ከግንባታ ስፍራ/ሳይት የማባረር መብት ለማን የተሰጠ ነው?በየትኛው ህግ?በምን ሁኔታ?በየትኛው የውል አይነት?በዚህ ጊዜ ማን ምን መስራት አለበት?የሚሉትን በአጭሩ ለመጠቆም እንሞክራለን፡፡

*ይህ መብት ያለው የትኛው አካል ነው? የሚለውን በተመለከተ ተቋራጭን ከግንባታ ሳይት/ከግንባታ ስፍራ ለማባረር መብት ያለው አሰሪው ነው ስለዚህ መብቱ የግንባታው ባለቤት ወይም የአሰሪው ነው፡፡

⏺ስለዚህ ይህን መብት ተቋራጮች ሆኑ አሰሪ ያልሆነ ሌላ አካል ተግባራዊ ሊያደርገው አይችልም ማለት ነው፡፡
*በየትኛው ህግ? ለሚለው ምላሹ በፍትሀብሄር ህጉ እና በጀኔራል ኮንዲሽነን ኦፍ ኮንትራክት ነው፡፡በዝርዝር ሲታይ፡-

▶️በግንባታ ውሎች በተለይ ጀኔራል ኮንዲሽነን ኦፍ ኮንትራክት መጠቀም የተለመደ ነው፡፡እነዚህ ጀኔራል ኮንዲሽኖች በራሳቸው ህግ አይደሉም፡፡እዚህ ላይ አንዳንድ የህግ ባለሙያዎች እንደ መመሪያ እና ህግ ስለሚቆጥሩት ይህ የግንዛቤ ክፍተት መታረም ይኖርበታል፡፡የግንባታ ውል ተዋዋዮች በስምምነታቸው እነዚህን ጀኔራል ኮንዲሽኖች የውሉ አካል ሲያደርጓቸው በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 1731 መሰረት በተዋዋዮች መካከል እንደ ህግ ሆነው ይቆጠራሉ፡፡እዚህ ላይ ሌላው ጉዳይ ስፔሻል ኮንዲሽን ኦፍ ኮንትራክት ተብለው የሚቀመጡት ከጀኔራል ኮንዲሽኑ ድንጋጌዎች የተፈጻሚነት ቅድሚያ ይኖራቸዋል፡፡ለምሳሌ ከነዚህ ጀኔራል ኮንዲሽኖች ውስጥ የሲቪል ግንባታ ስራዎች ቋሚ የውል መተዳደሪያ/Standard condition of contract for the construction of civil work projects/ አንዱ ነው፡፡ይህ ጀኔራል ኮንዲሽን በከተማ ልማት ሚኒስቴር በኩል የተዘጋጀ ሲሆን ይዘቱ በዋናነት ከFIDIC 1987 version የተወሰደ ነው፡፡

በአብዛኛው MoWUD 1994 ተብሎ ይጠራል፡፡ሆኖም ዋናው ነጥብ ተዋዋዮች ጥቅም ላይ ያዋሉትና የውላቸው አካል ያደረጉት የትኛውን ጀኔራል ኮንዲሽን እንደሆነ መለየትና ማወቅ የግድ ይላል፡፡

⏺ከዚህ አንጻር MoWUD 1994 ክሎዝ 63 ተቋራጭን ከግንባታ ስፍራ/ሳይት የማባረር መብትን አስመልክቶ በዝርዝር አስቀምጦታል፡፡በዚህ ድንጋጌ መሰረት በዋናነት አማካሪ መሀንዲሱ ለአሰሪው የተቋራጩን እንደውሉ ያለመፈጸም ሲያሳውቅ በተለይም ተቋራጩ ስራውን እንደተወው አማካሪው ሲያስታውቅ፣ተቋራጩ በአማካሪ መሀንዲሱ ማስጠንቀቂያ እየተሰጠው ለ28ቀናት ስራውን ሳይጀምር ሲቀር፣በመሀንዲሱ ተቀባይነት የላቸውም የተባሉ የግንባታ ቁሳቁሶችን በ28 ቀናት ውስጥ ከሳይት ያላስወጣ እንደሆነ፣በተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ እየተሰጠው ስራውን በውሉ አግባብ ለመፈጸም ፈቃደኛ ያልሆነ እንደሆነ፣አማካሪ መሀንዲሱ እየከለከለው የስራውን ክፍል ለሌላ ተቋራጭ አሳልፎ የሰጠ እንደሆነ ወይም ተቋራጩ የከሰረ እንደሆነ አሰሪው የ14 ቀን ማስጠንቀቂያ በመስጠት ተቋራጭን ከግንባታ ስፍራ/ሳይት ማባረር የሚችል ይሆናል፡፡በዚህ ጊዜ ውሉ ይቋረጣል ማለት ነው፡፡/Termination of contract/
በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3288 አና ተከታዮቹ ላይ የተደነገገውም ተቋራጩ የውል ግዴታውን ባልፈጸመ ጊዜ የግንባታ ባለቤት ለሆነው ለአስተዳደር መስሪያ ቤት የግንባታ ስራውን ከተቋራጩ ለመንጠቅ እና ውሉ ሳይቋረጥ ስራው በስራ መሪ ስር ሆኖ እንዲቆይ ለማድረግ መብት ይሰጠዋል፡፡እንዲሁም ውሉ ሊሰረዝ የሚችልበት ፈቃጅ የውል ቃል በግንባታ ውሉ ላይ ያለ እንደሆነ አሰሪው ቀሪውን ስራ ለሌላ ተቋራጭ በጨረታ ወይም በስምምነት በማሰራት እንዲጠናቀቅ ማድረግ ይችላል፡፡/የፍ/ህ/ቁ 3291(1) በዚህም ምክንያት አሰሪው ለተጨማሪ ወጭ/Additional cost/ የተዳረገ እንደሆነ ከተቋራጩ ላይ ለመጠየቅ እንደሚችል የፍ/ህ/ቁ 3291(2) በግልጽ መብት ይሰጠዋል፡፡ሆኖም በውል ህግ ላይ አሰሪው የተቋራጩን ግዴታ በሚያከብድ ሁኔታ ቀሪውን ስራ ማከናወን እንደሌለበት የሚያስገነዝበውን ግዴታውንም ማክበር አለበት፡፡

በየትኛው የውል አይነት? ለሚለው በዋናነት የአስተዳደር መስሪያ ቤት የግንባታ ውሎችን በሚመለከት ሊተገበር የሚችል ነው፡፡ በግል የግንባታ ውሎች/private construction contract/ በተለይ ከፍ/ህ/ቁ 2610 እና ተከታዮቹ እንዲሁም ከፍ/ህ/ቁ 3019 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች ውስጥ ተቋራጭን ስለማባበር አስመልክቶ ግልጽ ድንጋጌ አለመኖሩ ይህ መብት ለግለሰቦች ለመተግበር አስቸጋሪ የመሆኑን ሁኔታ ታሳቢ ተደርጐ በህግ አውጭው በማወቅ/ፐርፐዝሊ/ የተተወ ይመስላል፡፡ተዋዋዮች የግንባታ ውል ሲዋዋሉ ጀኔራል ኮንዲሽን ቢጠቀሙና በዚህም ስለተቋራጭ የማባረር መብት ድንጋጌ ቢኖረውስ የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል?ይሄን እንዴት ይተገብረዋል የሚለው ጉዳይ እንዳለ ሆኖ ውሉ ግን ለተዋዋዮች ህግ ስለሚሆን በተቻለ መጠን ሊተገበር ይገባዋል የሚል እሳቤ አለኝ፡፡

በዚህ ጊዜ ማን ምን መስራት አለበት? ለሚለው በዋናነት በ MoWUD 1994 ክሎዝ 63(2) ላይ እንደተቀመጠው በግንባታ ሳይት ላይ የተገኘ ቁሳቁስ በሙሉ በዝርዝር መመዝገብና ዋጋ ወጥቶለት መጠኑ ሊታወቅ ይገባል፡፡በተቋራጩ የተሰራው ስራ መጠን/level of work done/ በትክክል መታወቅና በዝርዝር መመዝገብ አለበት፡፡ተቋራጩ ያለበት እዳ/ከወሰደው የቅድሚያ ክፍያ ውስጥ ያልመለሰው ማለት ነው/ መታወቅ አለበት ለተቋራጩ የተከፈለው የስራ ክፍያ ሊታወቅ ይገባል፡፡

እነዚህን የሂሳብ ሁኔታዎች አመዛዝኖ እና ዋጋ አስቀምጦ ተቋራጩ የሚከፈለው ገንዘብ ካለ እንዲከፈለው ለአሰሪው የሚመልሰው ገንዘብ ካለም እንዲመልስ ሂሳብ የማስተሳሰብና ሪፖርት የማቅረብ ሀላፊነቱ የአማካሪ መሀንዲሱ ነው፡፡

በዚህ ረገድ አማካሪ መሀንዲሶች ብዙ ጊዜ እንደዚህ አይነት ሪፖርት ስለማያቀርቡ የግንባታ ክርክሮች ያልተሸከፉ ይሆኑና ለፍርድ ቤቶች ለትክክለኛ ፍትህ አሰጣጥ አስቸገሪ ሁኔታ ይፈጥራሉ፡፡

አሰሪው ይህን መብቱን ለመጠቀም ሀይል መጠቀም የሚችልበት ግልጽ ፈቃጅ ህግ ግን የለም፡፡

በመጨረሻም አሰሪና ተቋራጮች ለግንባታ ጥራት በመስራትና ለትክክለኛ እና እውነተኛ ነገር በመተባበር የኮንስትራክሽኑ ዘርፍ እድገት እንዲያሳይ ማገዝና አለመግባባቶችን በስምምነት መፍታት ቢችሉ ጠቀሜታው ለሀገርም ለራሳቸውም ነው፡፡

በአሰሪና ተቋራጭ ክርክር ብዙ ትምህርት ቤት እና የጤና ተቋም እንዲሁም ሌሎች መሰረተ ልማቶች ግንባታቸው ተቋርጦ ማህበረሰቡን ከተጠቃሚነት የሚያዘገይበት ሁኔታ ወደፊት ተቀርፎና ተቃልሎ ማየት የዘወትር ምኞታችን ነው፡፡

ማስታወቂያ ለነባር እና ለአዳዲስ ስራ ተቋራጮች እና ማህበራት በሙሉ ፡-የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ከቤት ልማቱ ጎን ለጎን ለበርካታ ዜጎች የስራ ዕድ...
23/06/2023

ማስታወቂያ ለነባር እና ለአዳዲስ ስራ ተቋራጮች እና ማህበራት በሙሉ ፡-

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ከቤት ልማቱ ጎን ለጎን ለበርካታ ዜጎች የስራ ዕድል በመፍጠር በኢኮኖሚው ተጠቃሚ ሲያደርግ የቆየና እያደረገም ይገኛል፡፡

በዚህም መሠረት ኮርፖሬሽኑ በቀጣይ በሚኖረው የግንባታ ፕሮጀክቶች በዘርፉ የተሠማሩ ስራ ተቋራጮችንና ማህበራትን አሳታፊ አድርጎ ለመስራት ያሰበና ለዚህም ይረዳው ዘንድ በከተማችን ያሉትን የስራ ተቋራጮችንና ማህበራትን በመመዝገብ መረጃዎችን አደራጅቶ መያዝ እና መመልመል አስፈላጊ ሆኖ ማግኘቱን በቅርቡ በተቋሙ ማህበራዊ ድረ-ገጽ አሳውቋል፡፡

በዚህም መሰረት ለነባር እና አዳዲስ ተመዝጋቢዎች ከቀን 13/10/2015 - 27/10/2015 ዓ.ም ድረስ ለለተከታታይ አስራ አምስት ቀናት online ምዝገባ ማካሄድ እንደሚጀመር እየገለጽን ከዚህ በታች የተቀመጠውን ማስፈንጠሪያ (Link) https://www.aahdc.gov.et
በመጫን እና የሚጠይቀውን መረጃ በአግባቡ በማስገባት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡-

በነባር፡-

በተቋማችንና በተለያዩ ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶቻችን ስር ከ2006 ዓ.ም ጀምሮ የስራ ትስስር ተደርጎላችሁ ስትሠሩ የነበራችሁ ስራ ተቋራጮችና ማህበራት ነባር በሚለው ስር ምዝገባችሁን ማድረግ ያለባችሁ ሲሆን፤

በአዲስ፡-

ከዚህ በፊት በተቋማችንም ሆነ በቅርንጫፍ ፅ/ቤቶቻችን ስር ምንም ዓይነት የስራ ትስስር ያልተደረገላችሁ አዲስ በሚለው ስር ምዝገባችሁን ማካሄድ ትችላላችሁ፡፡

ለምዝገባ አስፈላጊ ማስረጃዎችን በድጋሚ ለማስታወስ ያህል፡-

- የታደሰ ንግድ ፍቃድ
- የግበር መክፈያ መለያ ቁጥር( Tax
Identification Number- TIN.)
- የስም ስያሜ ምዝገባ ሰርተፊኬት
- የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት
- የስራ ልምድ ከ1-2 ገፅ በማይበልጥ
በዝርዝር ይጠቀስ
- የስራ ልምድ ክብደት በገንዘብ ሲቀየር
የሚያሳዩ መረጃዎች
- እና ሌሎች ስራ ተቋራጩን እና
ማህበራቱን የሚገልጹ ሰነዶችን ናቸው

ማሳሰቢያ፡-

ከስራ ዕድል ፈጠራ ጋር በተያያዘ ከሚመለከተው አካል በሚላከው መረጃ መሠረትና በተቋማችን ባለው መረጃ መሠረት ወደ ስራ ሲገባ በነባር መመዝገብ እያለባችሁ በአዲስ ተመዝግባችሁ የተገኛችሁት ላይ እንዲሁም በሁለቱም (በነባርም፣በአዲስም) ተመዝግቦ የሚገኝ ስራ ተቋራጭም ሆነ ማህበራት ላይ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን ከወዲሁ ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን

ለነባር እና ለአዲስ ስራተቋራጮች እና ማህበራት በመሉየአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በቀጣይ በጀት አመትም በያዘው መደበኛ እቅድ  በመንግስት እና በግ...
18/06/2023

ለነባር እና ለአዲስ ስራተቋራጮች እና ማህበራት በመሉ

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በቀጣይ በጀት አመትም በያዘው መደበኛ እቅድ በመንግስት እና በግል አጋርነት የቤት ልማት ፕሮግራሞች አዲስ ለሚያስገነባቸው 120ሺ የጋራ መኖሪያ ቤቶች በተለያዩ ዘርፎች በግንባታ ፣ በአገልግሎት እና በአምራች ዘርፍ በቀጣይ 5 ወራት ከ4500 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች አዲስ የስራ እድል ለመፍጠር በዝግጅት ላይ ሲሆን በዘርፉ የተሠማሩ ስራ ተቋራጮችንና ማህበራትን አሳታፊ አድርጎ ለመስራት አስቧል።

በመሆኑም ተቋሙ በቤት ልማት መሳተፍ የሚፈልጉ አዳዳስ እና ነባር ከ2006 ዓ.ም ወዲህ በተቋሙ የስራ ዕድል ተፈጥሮላቸው በተቋማችን ሲሰሩ የነበሩትን ባለድርሻ አካላት በአዲስ መልክ ለመጀመሪያ ዙር ለመመልመል እንዲሁም አሰራሩን ለማዘመን እንዲያስችለው በተደራጀ እና በዘመናዊ በሆነ መልኩ አዲስ እና ዘመናዊ የዌብ ሳይት ፕላትፎርም አዘጋጅቶ መረጃዎችን በማደራጀትና በማጥራት ወደ ስራ ለመግባት ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡

ስለሆነም በቅርቡ በተቋሙ ድረ-ገጽ በሚለቀቀው አዲስ ፕላት ፎርም ለአግልግሎቱ ፈላጊ በሙሉ ምዝገባ ስለሚጀምር ከወዲሁ ዝግጅት እንድታደርጉ ኮርፖሬሽኑ እያሳሰበ ተመዝጋቢዎች ከታች ያሉትን መረጃዎች አደራጅታችሁ እንድትጠብቁ ያሳውቃል ፡-

👉 የታደሰ ንግድ ፍቃድ
👉 TIN NO
👉 የስም ስያሜ ምዝገባ ሰርተፊኬት
👉 የብቃት ማረጋገጫ
👉 የስራ ልምድ በአንድ በተጠቃለለ ገጽ
👉 የስራ ክብደት በገንዘብ ሲቀየር
የሚያሳዩ መረጃዎች ከገፅ1 - 2
👉 እና ሌሎች ስራ ተቋራጩን እና
ማህበራቱን የሚገልጽ ሰነዶችን ……
ናቸው።

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን

የውሃ ታንከር ስራ
18/12/2022

የውሃ ታንከር ስራ

Construction vacancy
17/05/2022

Construction vacancy

ጠጠር 00 (ፊኖ) ለመግዛት የወጣ ጨረታ
15/10/2021

ጠጠር 00 (ፊኖ) ለመግዛት የወጣ ጨረታ

እንኳን አደረሳችሁ!!🌼  🌼  🌼  🌼  🌼  🌼   🌼  🌼   🌼   🌼   🌼                          መልካም አዲስ አመት
10/09/2021

እንኳን አደረሳችሁ!!
🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼
መልካም አዲስ አመት

ለመላው የእስልምና ሀይማኖት ተከታዮች እንኳን ለ1442ኛው የዒድ አል-አድሐ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!Hordoftoota amantaa Islaamaa mara baga ayyaana IID AL A...
20/07/2021

ለመላው የእስልምና ሀይማኖት ተከታዮች እንኳን ለ1442ኛው የዒድ አል-አድሐ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!

Hordoftoota amantaa Islaamaa mara baga ayyaana IID AL ADAHAA waggaa 1442ffaatiin isin ga' e!

Happy 1442nd Eid-ul-Adha to all followers of Islam !!

EID MUBAREK!

Address

Bole

Telephone

+251911863248

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Fancy Construction Work ፋንሲ ኮንስትራክሽን ስራ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

  • Want your business to be the top-listed Engineering Company?

Share