The Truth

The Truth መልካሙን እናበረታታለን፣ጥፋትን እንተቻለን፣የትም አለን።

This sidama engineers group basically focus on development of sidama with structure and design of construction with in new region of Ethiopia future

12/04/2026

የፓኪስታን መርከቦች ተመለሱ‼️
ሁለት የፓኪስታን ባንዲራ የያዙ ባዶ የነዳጅ ታንከሮች ከኩዬት እና የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ነዳጅ ለመጫን በሆርሙዝ የባህር ሰርጥ ለማለፍ ተቃርበው የነበረ ቢሆንም መመለሳቸውን ፋርስ ኒውስ ዘግቧል።
እነዚህ ነዳጅ የጫኑ መርከቦች የተመለሱት በኢራን ትዕዛዝ ሳይሆን ትራምፕ የአሜሪካ የባህር ኃይል በሆርሙዝ ሰርጥ ለማለፍ የሚሞክሩትን ማንኛውንም እና ሁሉንም መርከቦችን የማገድ ሂደት መጀመሩን መናገራቸውን ተከትሎ መሆኑን ዘገባው ጠቅሷል። ፓኪስታን ድርድሩ ባይሳካም የአሜሪካ እና የኢራንን ድርድር አመቻች ሀገር እንደነበረች ይታወቃል።

Truth

ካሜሩን በህዝባዊ አመጽ እየተናጠች ነው። መከላከያው እና የጸጥታ ሀይሉ ከህዝቡ ጋር በመሆን አመጹን ተቀላቅሏል። የካሜሩን መንግስት በዚህ ሁኔታ ብዙም ሚቆይ አይመስልም።ይህን ያዩ ኢትዮጵያንም...
07/11/2025

ካሜሩን በህዝባዊ አመጽ እየተናጠች ነው። መከላከያው እና የጸጥታ ሀይሉ ከህዝቡ ጋር በመሆን አመጹን ተቀላቅሏል። የካሜሩን መንግስት በዚህ ሁኔታ ብዙም ሚቆይ አይመስልም።

ይህን ያዩ ኢትዮጵያንም ለካሜሩን የደረሰው በረከት ለኛም ይድረሰን እያሉ ነው።

07/11/2025

በማህበራዊ ሚድያ ላይ ከ5ሺ በላይ ተከታይ ያለው ሰው የማህበራዊ ሚድያ ተፅኖ ፈጣሪዎች ማህበርን መቀላቀል ይችላል የምል ዜና ሰማን ይህ ማህበር ውስጤ ደንቡና ከተጠያቂነት አንፃር ያለው ነገር እንዴት ነው፣ እንዴትስ ይተገበራል?

07/11/2025

በዚህ ዘመን አንድ የተረዳሁት ነገር አብዛኛው በምባል ደረጃ የገዥው ፓርቲ ተሿም ጊዜውን የሚያጠፋው በማህበራዊ ሚድያ ላይ ነው።ይህ አካሄድ ጥቅምም ጉዳትም እንዳለው ይሰማኛል።
ከጥቅም አንፃሪ ስናዬው መረጃዎችን ለመከታተልና ለመከወን ያስችላል ብዬ አምናለው።
ጉዳቱ ደግሞ ለህዝብና ለገዛ ቤተሰቡ የምሰጠውን ጊዜ የሚያሳንስ ይመስለኛል።
አንድ የመንግስት ተሿም እራሱን በብዙ ነገር ማብቃት መቻል አለበት በትንሹ የተሻለ የመግባባት ብቃት ልኖረው ይገባል፣ትልቁ የመረዳት ጥበብ እንዳለ ሆኖ ማለት ነው።

ስለዚህ በማህበራዊ ሚድያ ላይ የምናጠፋቸውን ደቂቃዎች አድስ ልምድ በመቅሰምና መፅሐፍ በማንበብ ብናሳልፍ ለራሳችንም ለህዝቡም ልንጠቅም እንችላለንና ጊዜያችንን እራሳችንን የበለጠ በማብቃት ላይ እናተኩር!

26/10/2025

ዛሬም እንትናችን ሥራ ላይ ናቸው፣የእናንተ እንትን የኛም እንትን አይደለም እንደ ቆይ?

እንትና ነኝ ከሁርሶ😉

20/10/2025

በዚህ ዘመን ማህበራዊ ሚድያ እንዴ መሳሪያ ነው የሚያገለግለው ጠያቅውም ጥያቀውንና ትችቱን ያቀርብበታል፣ተሿምውም በዛው ልክ ወደ ሚድያ ለወጡ ጉዳዮች ቅድሚያ ይሰጣል ይህ በጣም የምበረታታ ጉዳይ ነው።

የምገርመው ግን አብዛኛው የመንግስት ተሻምም ሆነ የሚድያ ሠራዊቱ ትኩረቱ በሙሉ ከመንግስት በተቃራንው በቆሙት ወይም ትችት በሚያቀርቡ ሚድያዎች ላይ መሆኑ ግሪታን ፈጥሯል።

እንደውም ከአንዳንድ ቦታ ከምመጡት መረጃዎች መሠረት ተሿምው ከቢሮ ይልቅ ማህበራዊ ሚድያ ላይ በስፋት እንደምታዩ የታዘቡት ባለጉዳዮች ቢሮ ስሄዱ በአካል ለማግኘት እንደከበዳቸውና በተቻላቸው መጠን በውስጥ መስመር ለማውራት ጥረት እንደምያደርጉም ጨምረው ገልፀዋል።

ስለዚህ እባካችሁ በሰዓታችሁ በመገኘት ባለጉዳይ ማስተናገድ እንዳለባችሁ እያሳሰብን፣ይህንንም እንድትተገብሩት በትህትና እንጠይቃለን

.

19/10/2025

"የሚድያ ላይ ጋጋታና ስብሰባ ስበዛ ጠርጥር ያልተሰራ ሥራ አለ ማለት ነው ወዳጄ"😂

ትዝብት #1.

18/10/2025

◉◉◉◉◉መርነት ጥበብ ነው፣መር ስትሆን፣ትደነቃለህ፣ትተቻለህ፣ትጠየቃለህ።◉◉◉

▶የሚሰነዘሩ ሀሳቦች በሙሉ መርውን ልሰሩት፣ልያሰሩት እንጅ ልያሳስቱት በፍፁም አይገባም፤ መር በመርህ ነው የሚመራው የምመራው።

▶መር ከፊት ሆኖ መምራት ወይም ከኋላ ሆኖ የማብቃት ሀላፍነት አለበት፣እኔ ብቻዬን እበቃለው ወይም እወጠዋለው ማለት ዘበት ነው።

▶ትልቅ መር ወይም ሀላፊ ማለት ሌላውን ማብቃት የቻለ ለብዙዎች መስመር የጠቆመ ነው፤መር ትዕግስተኛ፣ታጋሽ፣በሁሉም ነገር የበቃ ነው።

◉በመጨረሻም አንተ/ች በተሰጠሽ ህዝባዊ ሀላፊነት ተተክ እያፈራሽ/ህ ነው ወይ?

ሰላም፣ፍቅር ለሀገራችን🇪🇹

የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ዘርፍ ከየት ወደየት!?በተለይ በመንግስትና በአንዳንድ የውጭ ድርጅቶች ፌንድ የምሰሩ የመሠረተ ልማት ሥራዎች ትልቅ ፈተናና ማነቆዎች እየገጠሙት እንዴሆነ እያዬን ነው...
15/10/2025

የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ዘርፍ ከየት ወደየት!?

በተለይ በመንግስትና በአንዳንድ የውጭ ድርጅቶች ፌንድ የምሰሩ የመሠረተ ልማት ሥራዎች ትልቅ ፈተናና ማነቆዎች እየገጠሙት እንዴሆነ እያዬን ነው፣ዋናው መንስኤ ግን የበጀት እጥረትና የግብዓት ዋጋ ማሻቀብ ብቻ ሳይሆን ስር የሰደዴ የሙስና ቅለት እንዴሆነ ይነገሪለታል።

በዋናነት በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የምሰሩ የመንገድ መሠረተ ልማቶች ጥብቅ ቁጥጥርና ኦድት በየጊዜው ካልተደረገ የባሰ ፈተና ልገጥመን ስለምችል የሚመለከተው የመንግስት ተቋም ክትትልና ቁጥጥር ልያደርግበት ይገባል።

በየቦታው የህዝብ ጥያቄ የሆነው የመንገድ መሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች መጓተት ከሥሩ ችግሩ ተቀርፎ መፍትሄ ልበጅለት የሚገባ አንገብጋብ ጉዳይ ነው።

የኢትዮጵያ የመንገዶች አስተዳደርም እራሱን እስኬ ታችኛው እርከን ልፈትሽ እንደምገባ ከወዲሁ ልናሳስብ እንወዳለን።

"ጥራቱንና ደረጃውን የጠበቀ መሠረተ ልማት ለህዝባችን!።"

ያለፈቃድ ደመወዝ መቁረጥ‼️የመንግስት ሰራተኞች ከፈቃዳቸው ውጪ፣ ከደመወዛቸው ገንዘብ እየተቆረጠባቸው ነው ተባለ። ይህም ህገ ወጥም አሳሳቢም ነው ተብሏል። ይህንን ያለው የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ...
15/10/2025

ያለፈቃድ ደመወዝ መቁረጥ‼️
የመንግስት ሰራተኞች ከፈቃዳቸው ውጪ፣ ከደመወዛቸው ገንዘብ እየተቆረጠባቸው ነው ተባለ።

ይህም ህገ ወጥም አሳሳቢም ነው ተብሏል።
ይህንን ያለው የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ነው።
ተቋሙ ከህግ ውጪ የመንግስት ሰራተኞች ከደመወዛቸው የሚቆረጥባቸው ገንዘብ ነገር አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል ብሏል።

የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋሙ በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ተደጋጋሚ ቅሬታ እየቀረበልኝ ነው ብሏል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሲዳማ ክልል በተለያዩ ወረዳዎች ያሉ መምህራን፣ የጤና ባለሙያዎችና ሌሎች ሰራተኞች ፈቃዳቸውን ሳይሰጡ ከደመወዛቸው ላይ ገንዘብ እየተቆረጠባቸው መሆኑን ነግረውኛል ብሏል።

በተመሳሳይ በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ክልል ዳውሮ ዞንም በተለያዩ ወረዳዎች የሚሰሩ መምህራን ተመሳሳይ ጥያቄ ማቅረባቸውም ተነግሯል።

ይህም የችግሩን አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረስ ያሳያል ብሏል የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋሙ መግለጫ።

ማንኛውም የመንግስት ሰራተኛ ስምምነቱን በፅሁፍ ሲገልፅ፣በፍርድ ቤት ትእዛዝ ወይንም በህግ በተደነገገው መሰረት ካልሆነ ደሞዙን መቁረጥም ሆነ መያዝ እንደማይቻል ሊታወቅ ይገባል ብሏል።

ችግሩ አለ ተብሎ ቅሬታ በቀረበባቸው አካባቢዎችም አስቸኳይ እርምት ሊደረግ ይገባል ሲል የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም አሳስቧል።

29/09/2025

የዳዬ ከተማ ነዋሪዎች መብራት እና ኔትወርክ መሠረተ-ልማት መቆራረጥ ምክንያት መቸገራቸውን በምሬት ገለጹ፤

የዳዬ ከተማ አስተዳደር እነዚህ መሠረተ ልማት ተደራሽነት የተሟላ ብሆንም፤ የተሟላ አገልግሎት ማግኘት አለመቻላቸዉን እና መብራት ከመቆራረጥ አልፎ ከነአካቴው መጥፋት የክትትል እና አመራር የመስጠት ክፍተት በሰፊው መኖሩን ተገልጿል።

ነዋሪዎች ለሉዋ ሚዲያ በላኩት መረጃ እንደገለጹት፤ በከተማይቱ መብራት አንደ ከጠፋ ለወራት አንደማይመለስ ገልጸዉ፤ ይህንን ቅሬታ አቤት የምባል አመራር አለመኖሩን ጉዳዩ ከባድ አድርጎብናል ይላሉ። ከተማዋ የምስራቃዊ ሲዳማ ዞን መቀመጫ ከተማ ብትሆንም፤ ትኩረት የተነፈግነው በምን ምክነያት እንደሆነ አልገባንም ያሉት ነዋሪዎች፤ ከመብራት ጋር በተገኘ ስራ የሚተዳደሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የእለት ጉርስ ለመሸፈን መቸገራቸውን አክሏል።

አክሎም ዳዬ ከተማ የዞኑ መቀመጫ ብትሆንም ከሌሎች ዞን ከተማዎች በተለየ መልኩ ነዋሪዎቿ ላይ መሠረተልማታዊ አድሎ እና የአገልግሎት መቆራረጥ በደል በሰፊው ይሰተዋላል ተብሏል። አመራሮቹ ከሀዋሳ እየተመላለሱ የሚያመሩ ናቸዉ ያሉት ነዋሪዎቹ፤ አንድን ጉዳይ አቤት ለማለት ወደ ቢሮ ብሄዱም በተደጋጋሚ ሃላፊዎችን ለማግኘት አለመቻላቸውን ገልጸዉ፤ ለታርክ አጋጣሚ አንድ ግዜ ተገኝተዉ ችግሩን ብናስረዳም፤ የእነሱ ጉዳይ የዞኑን ሀብት ለግል ጥቅም ለማዋል ከመሯሯጥ ባለፈ የህዝብ ችግር ላይ ግን ግድ የማይሰጣቸው ሆነዋል ብሏል ነዋሪዎቹ።

ከዚህ ቀደም የነበሩት የዞኑ አስተዳዳሪ እነዚህን ችግሮች በአንጻሩም ብሆን ለመፍታት ይጥሩ እንደነበር ያስታወሱት ነዋሪዎቹ፤ የአሁኖቹ ግን ሃላፍነታቸዉ ምን እንደሆነ እንኳ የሚያውቁት አይመስሉም ይሉና፤ ቀድሞ አስተዳዳሪ በሙስናና ብልሹ አሰራር ይታገላል የአሁኖቹ ግን ሙስናን በካብኔ አስወስኖ ለመዝረፍ ሙከራ እስከማድረግ መድረሳቸውን በላኩት መረጃ አስታወሷል።

©Luwa media

16/09/2025

እኔ ያልኩት ብቻ ትክክል ነው ማለት አላዋቂነት ነው።

Address

Hawassa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when The Truth posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share