Hossana Intra-Town Concrete Asphalt Road Project

Hossana Intra-Town Concrete Asphalt Road Project በሀዲያ ዞን በሆሳዕና ከተማ የውስጥ ለውስጥ የ14.134ኪ.ሜ ኮንክሪት አስፋልት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ።

24/06/2024

Best picture

18/05/2024
እንደምታወቀው በሀዲያ ዞን በሆሳዕና ከተማ የውስጥ ለውስጥ ኮንክሪት አስፋልት ፕሮጀክቶች ግንባታ በኅብረተሰብ ተሳትፎና በከተማ አስተዳደሩና በማዘ/ቤታዊ እንዲሁም በዞኑ መንግሥት በጀት ድጋፍ ...
18/05/2024

እንደምታወቀው በሀዲያ ዞን በሆሳዕና ከተማ የውስጥ ለውስጥ ኮንክሪት አስፋልት ፕሮጀክቶች ግንባታ በኅብረተሰብ ተሳትፎና በከተማ አስተዳደሩና በማዘ/ቤታዊ እንዲሁም በዞኑ መንግሥት በጀት ድጋፍ እየተገነባ እንደሆነ ይታወቃል ።
የፕሮጀክቶቹ አጠቃላይ እንቅስቃሴ በዞናችን ዋና አስተዳዳሪ፣በሆሳ/ከተማ አስ/ከንቲባ እና ሌሎች የመንግሥት ኃላፊዎችና ባለድርሻ አካላት በጋራ በዛሬ ቀን ጎብኝተዋሉ። የእስከ አሁኑ አጠቃላይ የፕሮጀክት አፈፃፀሙም አበረታች እንደሆነም ዋና አስተዳዳሪ ገልፀዋል።

17/11/2023
በቀን 29/09/2015 ዓ.ም የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም መጫ በተገኙበት የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንትና የሆ/ከተማ የዉ/ለዉስ/አስፋ/መን/ማስፋፊያ ፕሮጀክት  የስራ አመራር  ...
06/06/2023

በቀን 29/09/2015 ዓ.ም የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም መጫ በተገኙበት የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንትና የሆ/ከተማ የዉ/ለዉስ/አስፋ/መን/ማስፋፊያ ፕሮጀክት የስራ አመራር ቦርድ አባል የሆኑ ዶ/ር ሀብታሙ አበበ ከዩኒቨርስቲዉ ከፍተኛ የማኔጅሜንት አባለት/አመራር ጋር በመሆን በሀዲያ ዞን በሆሳዕና ከተማ ውስጥ በዞኑ፣በከተማ አስተዳደሩና በሆ/ከተማ ማ/ቤታዊ በጀት ድጋፍ እንዲሁም በዋናነት በኅብረተሰብ ተሳትፎ እየተገነባ ያለውን የ14.134ኪ.ሜ ኮንክሪት አስፋልት መንገዶች ግንባታ ፕሮጀክትን ጎበኙ።

ፕሮጀክት ሳይቶችን ተዘዋውረው ጎበኝተዉ ባዩት ነገር ላይ ተደንቀው በተለይም የፕሮጀክቱ እንቅስቃሴ ደርሰው ያለበት ደረጃ በተለይም ደረጃውን የጠበቀ ኮንክሪት አስፋልት ግንባታ በራስ አቅም መገንባት መቻል እጅግ አበረታችና የሚያስደስት እንደሆነም ገልጸዋል ።

ዶ/ር ሀብታሙ አያይዘውም ከዚህ ፕሮጀክት የምንማረው እንዴት ይቻላል የተባለው የሚቻል ሆኖ መገኘቱ እንዳስደነቃቸውም ገልጸዋል።

ፕሮጀክቱ ውጤታማ እንዲሆንም ፕሮጀክቱን በመምራት"፣ በማስተዳደር ፣ በመከታተልና በመቆጣጠር ሚና የተጫወቱ ባለድርሻ አካላትንና የአተም ጠ/ስራ ተቋራጭን አድንቀው፦
በመጨረሻም ለዚህ ወሳኝ ልማት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ በግልም በጋራ እንዲሁም መላውን እስከ 5000 የሚሆኑ የዩኒቨርስቲ ማህበረሰቡን በማነሳሳት
ለልማቱ ገንዘብ ለማዋጣት ቃል ገብተዋል።

ይህ የዋንዛ ቦቢቾ አስፋ/መንገድ  ፕሮ/ግንባታ ሳይት ሲሆን አስፋልት መጀመሩ ማህበረሰቡን የሚያነቃቃ ሆኖ ማግኛታችን ደስ ያሰኛል።
25/05/2023

ይህ የዋንዛ ቦቢቾ አስፋ/መንገድ ፕሮ/ግንባታ ሳይት ሲሆን አስፋልት መጀመሩ ማህበረሰቡን የሚያነቃቃ ሆኖ ማግኛታችን ደስ ያሰኛል።

ይህ በምስሉ የሚታየው የአብዮ ኤርሳሞ ስታዲየም ሄጦ ሳይት የኮንክሪት አስፋልት ግንባታ አሁናዊ ሁኔታን የሚያሳይ ሲሆን እስከ 700 ሜ ያህሉ ደረጃውን በጠበቀ ሁኔታ  ማለቁ ደስ የሚያሰኝ ነው...
25/05/2023

ይህ በምስሉ የሚታየው የአብዮ ኤርሳሞ ስታዲየም ሄጦ ሳይት የኮንክሪት አስፋልት ግንባታ አሁናዊ ሁኔታን የሚያሳይ ሲሆን እስከ 700 ሜ ያህሉ ደረጃውን በጠበቀ ሁኔታ ማለቁ ደስ የሚያሰኝ ነው። እንኳን ደስ አለን።

Address

Hossana

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Hossana Intra-Town Concrete Asphalt Road Project posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share