Tekleab Shibeshi General Contractor

Tekleab Shibeshi General Contractor Let's Build Together!

21/12/2023
ጀሞ ቁጥር ሁለት አካባቢ ባለ አራት የኮንክሪት ወለል (G+3) ለመኖሪያ የተሠራ ህንጻ ወድቋል።ከአወዳደቁ መረዳት እንደሚቻለው ከፊት ለፊት ያሉት ዐምዶች (columns) የመሸከም አቅማቸውን ...
28/05/2020

ጀሞ ቁጥር ሁለት አካባቢ ባለ አራት የኮንክሪት ወለል (G+3) ለመኖሪያ የተሠራ ህንጻ ወድቋል።

ከአወዳደቁ መረዳት እንደሚቻለው ከፊት ለፊት ያሉት ዐምዶች (columns) የመሸከም አቅማቸውን (buckling poin5) ያለፈ ሸክም ተጭኗቸዋል። በሕንጻ ዲዛይን ሳይንስ የዐምድ (Columns) መፍረስ አልፎ አልፎ (Rarely) የሚከሰት እንጂ የዘወትር ክስተት አይደለም። በተለምዶ በመሐንዲሶች ዘንድ "ዐምድ ወድቆ አይወድቅም" ይባላል።

ሕንጻ በተለያዩ ምክንያቶች ሊወድቅ ይችላል። ለምሳሌ ከመዋቅር ዲዛይን ችግር፣ የአሸዋ መቆሸሽ፣ የሲሚንቶ ማነስ፣ በቂ ውኃ ያለማጠጣት ወዘተ ሊሆንም ይችላል።

ለባለሙያ የዲዛይን ጥናት የፕሮጀክቱን 1% የማይሞላ ገንዘብ ላለመክፈል ግንባታውንም በባለሙያ ለማሠራት መስቆንቆን እንዲህ 100% ዋጋ ያስከፍላል።

ወይ ሀበሻ ቢራ ማስታወቂያ መስራት ሲችሉ
04/05/2019

ወይ ሀበሻ ቢራ ማስታወቂያ መስራት ሲችሉ

ስንቶቻችን ነን በአካባቢያችን ላይ ያሉትን ውብ ነገሮች አይተን የምናስተውለው?

30/04/2019
27/04/2019

መልካም በዓል።

15/04/2019

በአገራችን ስላለዉ የህንፃ ህግ ምን ያህል ያዉቃሉ!
**************************
ሰላም እንዴትናቹ የፌስ ቡክ ፔጅ ተከታታዮች ዛሬ በኢትየጵያ ስላለዉ የህንፃ ህግ አንድ ፅሁፍ ወደናንተ ልናደርስ ወደድን መልካም ንባብ!
በአገራችን የተለያዩ ስፍራዎች በተለይ በከተሞች አካባቢ እዚህም እዚያም ብቅ ብቅ ያሉ ህንፃዎችን መመልከት እየተለመደ መጥቷል፡፡ይህም በአገራችን እየተካሄደ ያለውን ልማት ለመግለፅ እንደማሳያ ከሚጠቀሱ ተግባራት የህንፃዎች በብዛትና በአይነት መገንባት አንዱ ነው፡፡የህንፃዎች ግንባታ መስፋፋት በራሱ አዎንታዊ እና አሉታዊ ጎኖች የያዘ ነው፡፡እነዚህ አዎንታዊና አሉታዊ ጎኖችን ለማስተዳድ ደግሞ ከእድገቱ ጋር የሚራመድ ህግ መኖር የግድ ይላል፡፡

ህግ በባህሪው የተፈጥሮ ሚዛን ማስጠበቅና ከዚህም ጋር የተስማማ የሰዎችን አኗኗር የሚያስተዳድር ሲሆን የህንፃ ህግም በዚሁ መርህ የሚመራ መሆን አለበት፡፡ስለሆነም የሚገነቡ ህንፃዎች የተፈጥሮ ወይም የአካባቢ ደህንነትን ፣ የሰዎችን አኗኗር ምቾትን ያገናዘቡ እንዲሆኑ ማድረግ መሰረታዊ ጉዳይ ነው፡፡

በእለት ተለት ውሎአችን ከምንሰማቸው ጉዳዮች መካከል በህንፃ ግንባታ አካባቢ ስለሚደርሱ አደጋዎች፣ለህንፃ ግንባታ የተቆፈሩ ቦታዎች ላይ በማሀበረሰቡ ላይ ስለሚደርሱ የአካል ጉዳቶች እንዲሁም የህይወት መጥፋት፣ህንፃ የሚገነባበት አካባቢ የሚኖሩ እንዲሁም የሚንቀሳቀሱ ሰዎች ላይ የሚፈጠሩ አለመመቸቶች ለምሳሌ በግንባታ እቃዎች መተላለፊያዎች መዘጋት ወይም መጣበብ እንዲሁም ግንባታው በሚካሄድበት አካባቢ ሲንቀሳቀሱ አሁን ካሁን አደጋ ይደርስብኝ ይሆን የሚሉ እና የመሳሰሉ ስጋቶች የተለመዱ ናቸው፡፡

ያሁንና ከላይ የተጠቀሱትን አደጋዎችና ስጋቶች ለመከላከል እንዲሁም ከህንፃ ግንባታ ጋር የተያያዙ ሌሎች ዝርዝር ጉዳዮችን የያዘ የህንፃ ህግ በሀገራችን ይገኛል፡፡ይሀውም በዋናነት የኢትዮጵያ የህንፃ አዋጅ ቁጥር 624/2001 ሲሆን ይህንን አዋጅ ለማስፈፀም በሚኒስትሮች ምክር ቤት የወጣው ደንብ ቁጥር 243/2003 ተጠቃሽ ናቸው፡፡እነዚህና ሌሎች ከህንፃ ጋር የተያየዙ ህጎችን በስራ ላይ ለማዋል የተለያዩ ባለድረሻ አካላት ጉልህ ሚና እና ሀላፊነት አለባቸው፡፡

በዚህ አጭር ፅሁፍ የህንፃ ትርጉም በአጠቃላይና በአዋጁ ምን እንደሆነ፣በአዋጁ የተቀመጡ የህንፃ ምድቦች ምን ምን እንደሆኑ፣ በህንፃ ግንባታ የሚሳተፉ አካላት ሀላፊነቶችና ሀላፊነታቸውን ባለመወጣታቸው የሚከተሉ ቅጣቶች፣ በህንፃ ግንባታ ወቅት ሊኖሩ ስለሚገባቸው የመሬት አጠቃቀም እና በግንባታ ወቅት ሊደረጉ ስለሚገባቸው የጥንቃቄ እርምጃዎች በዋናነት አዋጅ ቁጥር 624/2001 መሰረት በማድረግ እንመለከታለን፡፡

የህንፃ ትርጉም፡- የኢትዮጵያ የህንጻ አዋጅ ቁጥር 624/2001 በአንቀፅ 2/2 ስር የሚከተለውን ትርጉም ሰጥቶታል "ህንፃ" ማለት ለመኖሪያ፣ለቢሮ፣ለፋብሪካ ወይም ለማንኛውም ሌላ አገልግሎት የሚውል ቋሚ ወይም ጊዜያው ግንባታ ነው ይላል፡
ሕንፃ ሲሰራ ጥራትን፣ ውበትን ሁለንተናዊ ተስማሚነትን አገናዝቦ እንዲሰራ ሕጉ መለኪያዎችን እና ደረጃዎችን ያስቀምጣል፡፡እነዚህ መለኪያዎች እንደሚገነቡት ህንፃ ምድቦች የተለያዩ ናቸው፡፡በአጠቃላይ በአዋጁ ሶስት የህንፃ ምድቦች ተቀምጠዋል፡፡
እነዚህም፡-
ምድብ ‘ሀ’ ሕንፃ ፡- የሆነ የግል መኖሪያ ቤት የሚያገለግል፣
ምድብ ‘ለ’ ሕንፃ ፡-እንደ ሪልስቴት ያለ የቤቶች ልማት፣
ምድብ ‘ሐ’ ሕንፃ ፡- ማለት የህዝብ መገልገያ ወይም ተቋም ነክ ሕንፃ፣ የፋብሪካ ወይም የወርክሾፕ ሕንፃ ወይም ከመሬት እስከ መጨረሻው ወለል ከፍታው ከ12 ሜትር በላይ የሆነ ማናቸውም ሕንፃ ነው፡፡
 ህንፃ ለመገንባት መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች
• የግንባታ ፍቃድ ማግኘት (በአዋጁ አንቀጽ 4)
• የፕላን ስምምነት ማግኘት ፡-ለህንፃ ግንባታ እንዲቀርብ ለሚዘጋጅ ፕላን ከከተማው ጋር የተጣጣመ እንዲሆን የሚያስችል መሆኑን በማረጋገጥ የሚሰጥ በአንድ ቦታ ሊገነቡ የሚችሉ ወይም ለቦታው ያልተፈቀዱ የአገልግሎት አይነቶች፣ለቦታው የተፈቀደ ከፍታ፣በቦታው አካባቢ የሚያልፉ የመሰረተ ልማት አውታሮች፣ነባራዊ እና የታቀዱ መጠኖችን ወይም ስፋቶችን የሚያሳይ የፕላን መረጃ ነው፡፡

የፀደቀ ፕላን ጸንቶ የሚቆበትን ጊዜ ስድስት ወራት ነው
• የህንፃ ባለቤት ሀላፊነት
አንድ ህንፃ የሚያስገነባ ባለሀብት ገንዘቡን ኢንቨስት በማድረግ ከራሱ ጥቅም በተጨማሪ ለሌሎች የስራ እድል በመፍጠር ረገድ ጉልህ አስተዋጾ ያደርጋል፡፡ይህም በአገር እድገት ላይ የማይተካ ሚና አለው፡፡ህንፃ የሚያስገነባ ሰው ህንፃ ለማስገንባት በህጉ ወይም በአዋጅ የተቀመጡ መስፈርቶችን ከማሟላት በተጓዳኝ በእለት ተእለት የህንፃ ግንባታ ሂደት ውስጥ ሊወጣቸው የሚገቡ የተለያዩ ሀላፊነቶች አሉ፡፡ከነዚህም ውሰጥ የሰራተኞችን ደህንነት እና ጤና ለመጠበቅ የሚረዱ መሳሪያዎችን ማቅረብ፣በግንባታ አካባቢ የሚኖሩ ወይም የሚንቀሳቀሱ ሰዎችና ንብረቶች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ጥንቃቄ እንዲደረግ ክትትል ማድረግ፣በግንባታ ስፍራ በጥቅም ላይ የሚውሉ ቁሳቁሶች የህንፃው ደረጃ በሚፈልገው መልኩ መሆናቸውን መከታተል እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡
በመሆኑም በአዋጁ እንቀፅ 53/2 ስር በዝርዝር እንደተቀመጠው ማንኛውም የግንባታ ባለቤት ፡-
 ለሚያከናውነው ግንባታ የሚያስፈልግን የዲዛይን ስራ፣ ወይም የተሰራውን ዲዛይን መሰረት የሚከናወነውን ግንባታ የሙያ ደረጃው በማፈቅድለት ባለሞያ ያሰራ እንደሆነ፣ ወይም
 ለሚያከናውነው ግንባታ ደረጃ ከሚጠይቀው የግንባታ ቁሳቁስ ያነሰ የጥራት ደረጃ ያላቸው ቁሳቁሶች በጥቅም ላይ እንዲውሉ ያደረገ እንደሆነ፣ ወይም
 ግንባታውን አግባብ ካለው አካል የመጠቀሚያ ፍቃድ ሳያገኝ ወይም ከተፈቀደው ውጪ ለሌላ አገልግሎት አውሎ የተገኘ እንደሆነ፣ ወይም
 በማንኛውም ሌሎች ሁኔታዎች ግንባታው የሕዝብን ደህንነት አደጋ ላይ በሚጥል ሁኔታ ያከናወነ እንደሆነ፣
ከአምስት ዓመት እስከ አስር ዓመት በሚደርስ እስራት እና ከብር ሃያ ሺህ እስከ ብር ሃምሳ ሺህ በሚደርስ መቀጮ ይቀጣል፡፡
 የስራ ተቋራጮችና የተመዘገቡ ባለሙያዎች ኃላፊነት
ማንኛውም የተመዘገበ ባለሞያ ወይም የስራ ተቋራጭ፣ በዋና ወይም በንዑስ ስራ ተቋራጭነት ወይም ከፊል ውለታ በመውሰድ ያከናወነው ህንፃ ዲዛይን ወይም የግንባታ ስራ ለሚያስከትለው ጉዳት በወንጀል ተጠያቂ የሚሆንባቸው ሁኔታዎች እንደተጠበቁ ሆነው አሰሪው ለሆነው ሰው አግባብነት ባላቸው የፍትሐብሄር ህግ ድንጋጌዎች መሰረት ተጠያቂ ይሆናል፡፡በተጨማሪ የስራ ተቋራጩ ሆን ብሎም ይሁን በቸልተኝነት በሚገነባው ህንፃ ወይም የህንፃ አካል ላይ ለሚደርሰው የስራ ጥራት ጉድለት ተጠያቂነቱ ሳይቀር ጉድለቱን የማስተካከል ግዴታ አለበት፡፡
ማንኛውም በግንባታ ስራ እንዲሰማራ ፈቃድ የተሰጠው የህንፃ ስራ ተቋራጭ በዋናነት ወይም በንዑስ ተቋራጭነት ሲሰራ፣
 የግንባታ ዲዛይን የሚጠይቀውን የግንባታ ዕቃ ወይም ደረጃውን ባለመጠበቅ የጥራት ወይም የጥንካሬ ደረጃውን ባላሟላ የግንባታ ዕቃ ወይም በሙያው ዘርፍ ተቀባይነት ያለውን አሰራር ሳይከተል የሰራ እንደሆነ፣ ወይም
 በዲዛይን ወይም በሌሎች የውለታ ሰነዶች በግልፅ የተመለከቱ የስራ ሁኔታዎችን በባለሞያ ሊለዩ የሚችሉና ተገቢውን ሙያዊ ጥንቃቄ አድርጎ ቢሆን ኖሮ ሊታረሙ ይችሉ የነበሩ ስህተቶችን ሳያርም ወይም እንዲታረሙ ሳያደርግ ያከናወነው ግንባታ አደጋ ያስከተለ እንደሆነ፣
ከአምስት አመት እስከ አስር ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት እና ከብር ሃምሳ ሺህ እስከ ብር መቶ ሺህ ድረስ ይቀጣል፡፡
በአዋጁ ላይ በሕንፃ ስራ ስለሚሳተፉ የተለያዩ አካላት ሀላፊነቶችና ሀላፊነታቸውን ባለመወጣታቸው ስለሚከተሉ ቅጣቶች ከተቀመጡት በተጨማሪ በወንጀል ህግ አንቀጽ 501 የሚከተለው ይገኛል፡፡
ማንኛውም ሰው ማንኛውንም ዓይነት የሕንፃ ስራ ወይም የሕንፃ መፍረስ ሥራ ሲቆጣጠር፣ ሲመራ፣ ወይም ሲፈፅም በሕግ የተደነገገውን ወይም በሕንፃ ሥራ ሙያ ወይም ልማድ የሚመራባቸውን የጥንቃቄ ደንቦች አስቦ በመጣስ የሕዝብን ደህንነት ወይም የሰዎችን ሕይወት፣ ጤንነት ወይም አካል፣ወይም የሌላውን ሰው ንብረት አደጋ ላይ የጣለ እንደሆነ ከሶስት ወር በማያንስ ቀላል እስራትና በመቀጮ ይቀጣል፡፡ ወንጀሉ የተፈፀመው በቸልተንነት እንደሆነ ቅጣቱ ከአንድ ዓመት የማይበልጥ ቀላል እስራት ወይም መቀጮ ይሆናል፡፡

በአጠቃላይ ከእድገት ጋር ተያይዞ የሚከናወኑ የህንፃ ግንባታዎች ደረጃቸዉን የጠበቁ፣ የህብረተሰቡን ደህንነት አደጋ ላይ በማይጥሉና የሰራተኞችን ደህንነት ባረጋገጠ መልኩ መሰራትና ለአገልግሎት መብቃት ያለባቸዉ ሲሆን ይህ ሳይሆን ቢቀር ግን የህግ ተጠያቂነትን እንደሚያስከትል ለማሳወቅ ያዘጋጀነዉን የግንዛቤ ማስጨበጫ ፅሁፍ በዚሁ አበቃን ቸር እንሰንብት!

Address

Nazareth

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Tekleab Shibeshi General Contractor posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share