Abeshge woreda science & information technology office

Abeshge woreda science & information technology office Technology service

የአበሽጌ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት በኢትዮ ኮደር ስልጠና የተሻለ ውጤት በማስመዝገቡ የእውቅና ሠርተፍኬት ተበረከተለት።መስከረም 10/2018 ዓ.ም (ወልቂጤ)የጉራጌ ዞን ሳ...
20/09/2025

የአበሽጌ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት በኢትዮ ኮደር ስልጠና የተሻለ ውጤት በማስመዝገቡ የእውቅና ሠርተፍኬት ተበረከተለት።

መስከረም 10/2018 ዓ.ም (ወልቂጤ)

የጉራጌ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ የ2017 በጀት አመት እቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2018 በጀት እቅድ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በወልቂጤ ከተማ የምክክር መድረክ በዛሬው እለት አካሂደዋል።

በዚህም የአበሽጌ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት ፣ የ2017 በጀት አመት እቅድ አፈጻጸም የተሻለ በማስመዝመዝገብ ማጠናቀቅ መቻሉ ተገልጿል።

በተጨማሪም በሀገር አቀፍ ደረጃ በንቅናቄ እንዲመራ የተደረገዉ የ5 ሚሊየን ኮደሮች ኢንሼቲቭ የተሻለ በማስመዝገብ ፣ስርቲፋይ በማድረግ ከዞኑ ካሉ መዋቅሮች 100% እና ከዛም በላይ በማምጣት የእውቅና ሰርተፊኬት ተሸላሚ ሆኖአል።

ወጣቶች በሳይንስና ፈጠራ ዘርፍ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ በማድረግና በማበረታታት ውጤታማ እንዲሆኑ ማገዝ እንደሚገባ ተገለጸጥቅምት 12/2017 ዓ/ም    አበሽጌ ወረዳ (ሳኢቴ) ጽ/ቤትበጉራጌ...
22/10/2024

ወጣቶች በሳይንስና ፈጠራ ዘርፍ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ በማድረግና በማበረታታት ውጤታማ እንዲሆኑ ማገዝ እንደሚገባ ተገለጸ

ጥቅምት 12/2017 ዓ/ም አበሽጌ ወረዳ (ሳኢቴ) ጽ/ቤት

በጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ (ሳኢቴ) ጽ/ቤት ከሚያከናውናቸው ተግባራት መካከል በሳይንስና ፈጠራ ስራዎች የተሰማሩ ግለሰቦችም ሆኑ ተቋማት መደገፍና ውጤታማ እንዲሆኑ ማገዝ እንዲሁም የፈጠራ ስራዎችን እውቅና እንዲያገኙ ማድረግ ነው።

በሳይንስና ፈጠራ ዘርፍ ላይ ወጣቶች በራሳቸው ተነሳሽነት የፈጠራ ስራ እየሰሩ ይገኛል። እነዚህ በትምህርት ቤትም ሆነ በግላቸው የፈጠራ ስራ እየሰሩ ያሉ ወጣቶችን መደገፍና የፈጠራ ስራቸው የማህበረሰቡ ችግር በሚቀርፍ መልኩ ሽግግር እንዲያደርጉ ማገዝ የሁላችንም ተግባር መሆን ይገባዋል።

በአበሽጌ ወረዳ በላይኛው ገራባ የ8ኛ ክፍል ተማሪ የሆነው ሙኒር ሙባረክ በራሱ ተነሳሽነት የሰራቸውን የራሱ የፈጠራ ስራዎችን ተመልክተናል 1ኛ የመበየጃ ማሽን 2ኛ የልብስ መጭመቂያ ማሽን 3ኛ የቤት በር ቁልፍ መቆጣጠሪያ 5ኛ በቻርጅ የሚሰራ ሞንታርቦ እነዚህን የፈጠራ ስራዎች በራሱ ቁሳቁሶች በመጠቀም መስራት መቻሉን ጠቅሶልናል።

እነዚህን የፈጠራ ስራዎች በራሱ ተነሳሽነት መስራቱን የጠቀሰው ተማሪ ሙኒር እገዛ ቢያገኝ የተለያዩ የፈጠራ ስራ ሀሳቦች እንዳሉት ገልጾልናል።

የወረዳው ሳኢቴ ጽ/ቤት በተቻለው አቅም ሁሉ ከተማሪው ጎን እንደሚቆም ገልጾ እንዲህ አይነት የፈጠራ ስራ ያላቸው በወረዳው በተለያዩ ቀበሌዎች የሚገኙ ተማሪዎችና ወጣቶች ተዘዋውሮ በማየት እገዛ እንደሚያደርግ የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ የሱፍ አብድል ሰመድ ገልጸዋል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ ከ ሰር ቶኒ ብሌየር ጋር ተወያዩ። =============ውይይቱ የቶኒ ብሌየር ኢንስትቲዩት (TBI) ለኢትዮጵያ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን አጀንዳ...
12/10/2024

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ ከ ሰር ቶኒ ብሌየር ጋር ተወያዩ።
=============
ውይይቱ የቶኒ ብሌየር ኢንስትቲዩት (TBI) ለኢትዮጵያ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን አጀንዳ ትግበራና ስኬት የሚያደርገው አስተዋጽኦ ላይ ያተኮረ ነበር።

በውይይቱ የዲጅታል ትራንስፎርሜሽን ካውንስል አባል የሆኑት የኢትዮጵያ አርተፊሻል ኢንተሊጀንስ ተቋም ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ወርቁ ጋቸና እና የዲጂታል መታወቂያ ፕሮጀከት ጽ/ቤት ሃላፊ ኢ/ር ዮዳሄ አርአያ ስላሴ ተገኝተዋል።

ሃላፊዎች የቶኒ ብሌየር ኢንስትቲዩት በዘርፉ በኢትዮጵያ እያደረገ ላለው ድጋፍ ምስጋና በማቅረብ በቀጣይም አብሮ ለመስራት ያላቸውን ፍላጎት ገልጸዋል ።

ሰር ቶኒ ብሌየር በበኩላቸው በኢትዮጵያ እየተተገበረ ያለውን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን አጀንዳ መሻሻል ያሳየ መሆኑን ገልጸዋል።

እያይዘውም ተቋማቸው የዲጅታል ትራንስፎርሜሽን ካውንስሉን እንቅስቃሴ በመደገፍ እንዲሁም በአርተፊሻል ኢንተሊጀንስ ልማት ፣ በዳታ አስተዳደር ፣ በድጅታል መታወቂያ እና በመሠረተ ልማት ግንባታ ዘርፎች ከየተቋማቱና ከካውንስሉም ጋር ተባብሮ እንደሚሠራና እንደሚያግዝ አስታውቀዋል።

ዋይፋይ /Wi-Fi/ እንዴት ይሰራልበአይናችን አንያቸው እንጂ የተለያዩ መረጃዎችን የተሸከሙ የራዲዮ ሞገዶች ሁሌም በዙሪያችን ይገኛሉ፡፡ ከእነዚህ የሬዲዮ ሞገዶች ጥቂቶቹ የWi-Fi ሲግናሎች ...
06/07/2022

ዋይፋይ /Wi-Fi/ እንዴት ይሰራል

በአይናችን አንያቸው እንጂ የተለያዩ መረጃዎችን የተሸከሙ የራዲዮ ሞገዶች ሁሌም በዙሪያችን ይገኛሉ፡፡ ከእነዚህ የሬዲዮ ሞገዶች ጥቂቶቹ የWi-Fi ሲግናሎች ናቸው፡፡ Wi-Fi በሚለው ስም ውስጥ የሚገኙ ሆሄያት እንደ አህጽሮተ ቃል የትኛውንም ነገር የማይወክሉ ሲሆን በመነሻነት አንድ ከፍተኛ መጠን ያለውን መረጃ በአጭር ርቀት ውስጥ የራዲዮ ሞገዶችን በመጠቀም ማስተላለፍ የሚችልን ቁስ በቀላሉ ማስታዎስ እንዲቻል ተብሎ የተሰጠ ስያሜ ነው፡፡

እንደ ብሮድካስት ራዲዮና ተንቀሳቃሽ ስልክ ሲግናሎች ሁሉ የWi-Fi ሲግናልም በ19ኛው ክፍለ ዘመን ማክተሚያ አካባቢ የተገኘ ፈጠራ ነው፡፡ ኤሌክትሮኖች በሽቦ ውስጥ በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ በየተወሰኑ ጊዜያት አቅጣጫዎችን ይቀይራሉ፡፡ በሌላ ሽቦ ላይ የሚገኙ ኤሌክትሮኖች ከእነዚህ አቅጣጫ ከሚቀያይሩ ኤልክትሮኖች ጋር ቴሌፋቲክ በሆነ መንገድ የተያያዙ ስለሆኑ መንቀሳቀስ ይጀምራሉ፡፡ ይህ ግኝት መጀመሪያ የታወቀው እ.አ.አ በ1887 በሄንሪክ ሄርትዝ ነው፡፡

የሚታይ ብርሃንን የያዙ ኤሌክትሮመግነጢሳዊ ህብሮች ከራዲዮ ሞገዶች የተሻለ ከፍተኛ ፍሪኩየንሲን ያመነጫሉ፡፡ የተለመዱት የኤ ኤም ወይም ኤፍ ኤም ራዲዮ እና የቴሌቪዥን ስርጭቶች መረጃን በተከታታይ ሲግናሎች ወይም በአናሎግ ያደርሳሉ፡፡ Wi-Fi መረጃን የሚያሰራጨው እንደ ያልተያያዙ ዋጋዎች የባይነሪ መረጃ ዜሮዎችና አንዶች በዲጂታል መንገድ ነው፡፡ ይህም የሞባይል ቁሶች ከፍተኛ መጠን ያላቸውን እንደ ቪዲዮ፣ ምስል፣ ድምጽ እና የጽሁፍ መልዕክቶችን በቀላሉ እንዲልኩ ያስችላቸዋል፡፡

አንድን መረጃ በዋይ ፋይ ኦንላይን ላይ ስንፈልግ የዋይ ፋይ ቁሳችን የሬዲዮ ሞገዶችን አልፎ ከዋይ ፋዩ መገኛ ነጥብ ጋር ይናበባል፡፡ ይህም በኢንተርኔት ራውተራችን አንቴና አማካኝነት ነው፡፡ ከዚያም በአካባቢው ባሉ የኢንተርኔት ገመዶች አማካኝነት ጥያቄያችን ወደምንፈልገው የመረጃ ቋት ይተላለፋል፡፡ ሂደቱ ሲያልቅም በመጣበት መንገድ ተመልሶ ይመጣል፡፡

በተለያዩ ኩባንዎች የተሰሩ የዋይ ፋይ ቁሶች 802.11 የተሰኘ ተመሳሳይ ስታንዳርድን ስለሚከተሉ እርስ በርሳቸው መናበብ ይችላሉ፡፡ ይህ ስታንዳርድ ዜሮዎችና አንዶች ራዲዮ ሞገድን በመጠቀም እንዴት እንደተወከሉና ቁሶቹ ራሳቸውን እንዴት እንደሚለዩ የሚወስን ነው፡፡ እንዲሁም ደግሞ ኬሪየር ሴንስ መልቲፕል አክሰስ (CSMA) የተሰኘ እንዴትና መቼ መግባባት እንዳለባቸው የሚወስን አሊጎሪዝም ይከተላሉ፡፡ ይህ አሊጎሪዝም የዋይ ፋይ ቁሶችን ስማርት ያደርጋቸዋል፡፡

አንዳንድ ጊዜ ከዋይ ፋይ ጋር በተያያዘ ችግሮች ይገጥሙናል፡፡ ወይም ከዋይ ፋዩ መገኛ ነጥብ ጋር ለመገናኘት እንቸገራለን ይህም የሚሆነው የራዲዮ ሲግናሎች በርቀት ምክንያ ሲደክሙ ነው፡፡ ለምሳሌ ወፍራም ግድግዳ፣ የብረት መከለያዎች አንዲሁም አኳሪየም የራዲዮ ሞገዶችን ሊያደክማቸው ይችላል፡፡

የአበሽጌ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ  ጽ/ቤት  ከትምህርት  ጽ/ቤት በጋራ በመሆን ወረዳ አቀፍ የሳይንስና የፈጠራ ስራዎች ውድድር አካሄዷል።በወረዳ ደረጃ  ሲካሄድ የነበረው ሳይንስ...
29/04/2022

የአበሽጌ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት ከትምህርት ጽ/ቤት በጋራ በመሆን ወረዳ አቀፍ የሳይንስና የፈጠራ ስራዎች ውድድር አካሄዷል።

በወረዳ ደረጃ ሲካሄድ የነበረው ሳይንስና የፈጠራ ስራዎች ውድድር ተጠናቀቀ

በአበሽጌ ወረዳ በዳርጌ 2ኛና መሰናዶ ት/ቤት በተካሄደው ሳይንስና የፈጠራ ስራዎች ውድድር በት/ቤት ፣በተማሪዎች እና በመምህራን የተሻለ የፈጠራ ስራ የቀረቡትን የገንዘብና የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል።

የአበሽጌ ወረዳ ትምሀርት ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ያብሩ ታደሰ በፕሮግራሙ ተገኝተው ባሰሙት ንግግር በት/ቤት ደረጃ ችግር ፈቺ የሆኑ የፈጠራ ስራዎች እንዲሰሩ ት/ቤቶች ባላቸው የገቢ መጠን ለሳይንስና ቴክኖሎጂ መስሪያ የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች በማቅረብ ተማሪዎች እና መምህራንን ማበረታታት አለባቸው ያሉ ሲሆን በወረዳ ደረጃ የተቋቋመው የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት በፈጠራ ስራ የተካኑ ተማሪዎችን እገዛና ማበረታቻ በማድረግ ከትምህርት ጽ/ቤት በጋራ ይሰራል ብለዋል።

የአበሽጌ ወረዳ የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት ሃላፊ በበኩላቸው ወ/ሮ ማዘጊያሽ ቢቂላ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በትኩረት ተቀናጅተው መስራት ከተቻለ እና እነዚህን የፈጠራ ባለቤት የሆኑ ተማሪዎችን ማገዝ ከቻልን ሀገርን መለወጥ የሚችሉ ብዙ የፈጠራ ውጤቶች ያስመለክቱናል ያሉ ሲሆን በቀጣይ በት/ቤት ደረጃ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ክበብ በማቋቋም ተሰጥኦ ያላቸው ተማሪዎች ይበልጥ እንዲረዳዱና የተሻለ የፈጠራ ስራ ለመስራት ያስችላል ብለዋል።

በተካሄደው የፈጠራ ስራ ውድድር በ1ኛ ደረጃ ት/ቤቶች 1ኛ ተማሪ ይድነቃቸው ደሲዬ፣2ኛ ተማሪ ጌታው ተፈራ ፣3ኛ ተማሪ ኤልዳና ሸዋረጋ።በ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ደግሞ 1ኛ ተማሪ አማኑኤል መስፍን ፣2ኛ ተማሪ ሱራፌል ቅጣው 3ኛ ተማሪ ሱራፌል ተስፋዬ ሲሆኑ በመምህራን በኩል ደግሞ 1ኛ መምህር ወርቅነህ ተስፋዬ ፣2ኛ መምህርት ሀናን ዲጋ እና 3ኛ መምህር አበበ ሚኪያስ ናቸው

የዳርጌ 2ኛ እና መሰናዶ ት/ቤት በአጠቃላይ በመማር ማስተማር ያሉ ሂደቶችን ያስጎበኘ ሲሆን በቤተ መፅሐፍት ፣በቤተ ሙከራ ፣በቅርንጫፍ ማእከል ና በሌሎችም ተግባራት ጥሩ የተደራጀ ስራ ያስጎበኘ ሲሆን ተሳታፊዎች ጥሩ ልምድ እንዳገኙ ገልፀዋል በመድረኩ ር/መ/ራን፣ሱፐርቫይዘሮች፣መ/ራንና ተማሪዎች ፣የወረዳ የሁለቱም ጽ/ቤት ባለሞያዎች እና የዞን የሁለቱም መምሪያ ባለሞያዎች የተገኙ ሲሆን በመጨረሻም
ለአሸናፊ ተማሪዎች የገንዘብና የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል ሲል የዘገበው የአበሽጌ ወረዳ መንግስት ኮ/ጉ/ጽ/ቤት ነው።

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በቀራንዮ መስቀል ላይ ራሱን አሳልፎ በመስጠት ለእኛ ብርሀን ለሆነን ለጌታችን ለመድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዐል አደረሳችሁ አደረሰን !የአበሽ...
23/04/2022

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በቀራንዮ መስቀል ላይ ራሱን አሳልፎ በመስጠት ለእኛ ብርሀን ለሆነን ለጌታችን ለመድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዐል አደረሳችሁ አደረሰን !
የአበሽጌ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት

 #ኢትዮቴሌኮም የዘመናችን የመጨረሻውን የኢንተርኔት ፕሮቶኮል 𝐈𝐏v𝟔ን ተግባራዊ አድርጏል!𝐈𝐏v𝟔 የኢንተርኔት ፕሮቶኮል እጅግ አስተማማኝ፣ የላቀ ፍጥነት ያለው፣ የኢንተርኔት ኦፍ ቲንግንስ (...
13/04/2022

#ኢትዮቴሌኮም የዘመናችን የመጨረሻውን የኢንተርኔት ፕሮቶኮል 𝐈𝐏v𝟔ን ተግባራዊ አድርጏል!

𝐈𝐏v𝟔 የኢንተርኔት ፕሮቶኮል እጅግ አስተማማኝ፣ የላቀ ፍጥነት ያለው፣ የኢንተርኔት ኦፍ ቲንግንስ (IOT) ግንኙነት አቅም በማሳደግ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ የኢንተርኔት አገልግሎትን በቀላል የኢንተርኔት ራውቲንግ ጥራቱን ጠብቆ መስጠት የሚያስችለን ሲሆን የአይ.ፒ አድራሻ አሰጣጥ አቅምን በከፍተኛ ደረጃ በማሳደግ ቀጣይ የሃገራችንን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ግብ እንድናሳካ ያስችለናል፡፡
ደንበኞች አገልግሎቱን ለማግኘት የኢትዮቴሌኮም የአገልግሎት መስጫ ማዕከላትን ይጎብኙ

#ዲጂታልኢትዮጵያ

announced that it has upgraded its Internet protocol to the next generation protocol which the most recent Internet Protocol, 𝐈𝐏v𝟔.

𝐈𝐏v𝟔 internet protocol enables Ethio telecom to provide more secured, efficient, reliable, simplified internet service with more efficient routing, more connectivity on IOT, true quality (QoS) and expanded range of IP address, in order to achieve the digital transformation of our country. Ethio Telecom invites its customers to visit the service centers to get the service

በአበሽጌ ወረዳ የሳይንስና ቴክኖሎጂ የፈጠራ ስራ ውድድር በየ ክላስተሩ በተማሪዎችና በመምህራን እየተካሄደ ይገኛል።በወረዳው ባሉ 1ኛና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እየተካሄደ ያለው ወረዳ አቀፍ...
13/04/2022

በአበሽጌ ወረዳ የሳይንስና ቴክኖሎጂ የፈጠራ ስራ ውድድር በየ ክላስተሩ በተማሪዎችና በመምህራን እየተካሄደ ይገኛል።

በወረዳው ባሉ 1ኛና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እየተካሄደ ያለው ወረዳ አቀፍ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ስራዎች ውድድር በክላስተር ቀጥሎ እየተካሄደ ሲሆን በከታ ክላስተር ቦረር ት/ቤት በተደረገው የሳይንስና ፈጠራ ስራዎች ውድድር በተማሪዎች በ1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ቦረር ት/ቤት ሆኖ ሲያሸንፋ በ3ኛ ደረጃ ሁ-1 ት/ቤት በመሆን አጠናቋል።

በመምህራን በተደረገው የሳይንስና ፈጠራ ስራዎች ውድድር ተሳትፎ መ/ርት ሀናን ዲጋ ከቦረር ት/ቤት ቀዳሚ ስትሆን መ/ር የሽዋስ ከሁ-1 ት/ቤት 2ኛ በመሆን ውድድሩን አጠናቀዋል።

በትምህርት ቤቶች ውድድር ደግሞ ቦረርና ሁዳድ 1 ት/ቤቶች አሸናፊ ሆነዋል
ለተሳታፊዎችም የመፅሐፍትና የምስክር ወረቀት በመስጠት ተጠናቋል።

05/04/2022
በአበሽጌ ወረዳ የሚገኙ ትምህርት  ቤቶች በክላስተር  ደረጃ  የፈጠራ  ስራ ውድድር እየተካሄደ ይገኛል::በወረዳው ካሉ ክላስተሮች አንዱ የሆነው የጠ/ፊቴ ክላስተር  በጠደሌ ፊቴ ት/ቤት በቀን...
05/04/2022

በአበሽጌ ወረዳ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች በክላስተር ደረጃ የፈጠራ ስራ ውድድር እየተካሄደ ይገኛል::

በወረዳው ካሉ ክላስተሮች አንዱ የሆነው የጠ/ፊቴ ክላስተር በጠደሌ ፊቴ ት/ቤት በቀን 26/7/2014 ዓ/ም የፈጠራ ስራ ውድድር በተማሪዎች እና በመምህራን ውድድር አካሂዷል፡፡ በዚህም የፈጠራ ስራ ውድድር ተማሪዎችና መምህራን የፈጠራ ስራዎቻቸውን ያቀረቡ ሲሆን በዚህም የተለያዩ የማህበረሰቡን ችግር ፈቺ የሆኑ ስራዎች ለውድድር ቀርበው አሸናፊዎችን መለየት ተችሏል፡፡
በተማሪዎች በተደረገው ውድድር ከ1ኛ - 3ኛ ጠደሌ ፊቴ ት/ቤት ተማሪዎች አሸናፊዎች ሲሆኑ በሌላ በኩል ደግሞ በመ/ራን በተደረገው ውድድር በአንደኝነት ደረጃ የጠ/ፊቴ ት/ቤት ሲወጣ በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ጭሳ ት/ቤት በመሆን ፕሮግራሙ ተጠናቋል፡፡ በቀጣይም በሌሎች ክላስተሮች ውድድሮች እንደሚቀጥሉ ይጠበቃል፡፡

ሳይበር" ምንድን ነውሳይበር የሰው ልጅ የእርስ በርስ ግንኙነቱ ማደግ የፈጠረው ረቂቅ የቴክኖሎጂ ውጤት እና መሰረተ-ልማት፣ የመረጃ እንዲሁም የሰዎች መስተጋበር የሚገለጽበት ፈጠራ ነው፡፡የሳይ...
06/03/2022

ሳይበር" ምንድን ነው

ሳይበር የሰው ልጅ የእርስ በርስ ግንኙነቱ ማደግ የፈጠረው ረቂቅ የቴክኖሎጂ ውጤት እና መሰረተ-ልማት፣ የመረጃ እንዲሁም የሰዎች መስተጋበር የሚገለጽበት ፈጠራ ነው፡፡

የሳይበር ምህዳር የምንለው የተለያዩ የኢንፎርሜሽን መሰረተ-ልማቶች ማለትም ኮምፒውተሮች ፣ራውተሮች፣የኮምፒውተር ኔትዎርኮች፣ወ.ዘ.ተ. ተሳስረው የፈጠሩት ምናባዊ ዓለም ሲሆን በዚህ ምህዳር ውስጥ ኢንፎርሜሽን ይቀመጣል፣ ይሰራጫል፣ እንዲሁም ይተነተናል፡፡

የሳይበር ምህዳሩን አንዳንዶች በቴክኖሎጂ አማካኝነት የሰው ልጅ የተቆጣጠረው አምስተኛው ግዛት በማለት ይጠሩታል፡፡ ይህም ከየብስ ፣ ውሃ ፣ የአየር እንዲሁም የውጫዊው የህዋ ግዛት መካከከል በመመደብ፡፡

የሳይበር ምህዳር፡ የብዙዎቻችን የእለት ተእለት እንቅስቃሴ አካል ከሆነም ውሎ አድሯል፡፡ ይህ ሲባል ለስራ ፣ለትምህርት ፣ ለመዝናኛ ከመጥቀምም አልፎ ለተለያዩ የእርስ በርስ ግንኙነቶች ማሳለጫ አድርገን የምንጠቀምበት ዋነኛ መሳሪያ በመሆን ላይ ይገኛል፡፡ ከዚህ አልፎ የምህዳሩ እውን መሆን የኢንፎርሜሽን ዋጋ ከምንጊዜውም በላይ እንዲጨምር ምክንያት እየሆነ ይገኛል፡፡



የሳይበር ምህዳር አካላት

የሳይበር ምህዳር የምንለው ኮምፒውተሮች ብቻ የሚፈጥሩት ሳይሆን የተለያዩ አካላት ተሳስረው እውን ያደረጉት ምህዳር ነው፡፡ እነዚህ የሳይበር ምህዳር አካላት ከላይኛው የምህዳሩ ክፍል እስከ ታችኛው ድረስ በ4 ዋና ዋና ክፍለች ከፋፍሎ ማየት ይቻላል፡፡

የውስጠኛው የምህዳሩ ክፍል፡ የሳይበር ምህዳር እውን እንዲሆን መሰረት የጣለው አካላዊ ወይም ፊዚካል ደረጃ የምንለው ነው፡፡ ይህም የተለያዩ ማሽኖች፣ኮምፒውተሮች፣ኬብሎችና የመሳሰሉ አካላት ጥምረት ነው፡፡

ሁለተኛው የሳይበር ምህዳር ውስጥ የሚቀመጠው፣ የሚተነተነው እና የሚሰራጨው ኢንፎርሜሽን ነው፡፡

ሶስተኛው የሳይበር ምህዳር ክፍል ለኢንፎርሜሽን መፈጠር፣ መተንተንና መሰራጨት መሰረት የሆኑ የተለያዩ አገልግሎቶች ናቸው፡፡ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የሚሆነው የኢንተርኔት አገልግሎት ፕላትፎርሞች ናቸው፡፡

እንዲሁም የመጨረሻው እና ውጫዊ ክፍሉ፡ የሳይበር ምህዳሩን የሚጠቀመው፣ ኢንፎርሜሽን እና ቴክኖሎጂውን የሚያንቀሳቅሰው የሰው ልጅ የሳይበር ምህዳር ውጨኛው ክፍል ነው፡፡

⚜የሳይበር ምህዳሩ ልዩ ባህሪያት

🔻ያልተማከለ ወይም ልዩ የተማከለ አስተዳደር የሌለው ሲሆን ይህም ለቁጥጥር አዳጋች እንዲሆን ያደርገዋል፡፡

🔻ለግለሰቦች እና ለቡድኖች ከፍተኛ ሃይል የሚሰጥ ሲሆን የግለሰቦች እና ቡድኖች አስተሳሰብ፣እምነት እና እሴቶችን ማንጸባረቅ የሚያስችላቸው ነው፡፡

🔻የጎንዮሽ እና ትስስራዊ ሃይል የሚያበረታታ ነው፡፡

🔻ዓለም አቀፋዊ እና ድንበር የለሽ ነው፡፡

🔻እውቀት መረጃና ምናባዊነት ላይ ያተኩራል

🔻ለደካሞች ልዩ ተጠቃሚነትን የሚሰጥ ነው

🔻ሁሉም ጋር የደራሽነት አቅም ያለው፡፡

🔻በከፍተኛ ሁኔታ ተለዋዋጭ የሆነ ፍልስፍናዊ ባህሪ ያለው ነው፡፡

በእነዚህ ልዩ ባህሪያት ምክንያት ምህዳሩ ለተጠቃሚዎች መልካም እድሎችን ይዞ መጥቷል፡፡ በዚህም ምክንያት ዓለማችን ከጊዜ ወደ ጊዜ የተለየ መልክ እየያዘች ከመምጣቷ ባሻገር የእውቀት እና የኢንፎርሜሽን ማህበረሰብ እየተፈጠረ ይገኛል፡፡ ሆኖም ግን እነዚህ መልካም እድሎች ካመጧቸው ቱሩፋቶች ጎን ለጎን ምህዳሩ የተለያዩ የደህንነት ስጋቶችን ይዞ መጥቷል፡፡ እነዚህን ስጋቶች ለመቋቋምና ምህዳሩ ያለውን መልካም ጎኖች አሟጦ ለመጠቀም ሃገራት የደህንነት ስትራቴጂዎች ከቴክኖሎጂ፣ ከሰው ልጆች እንዲሁም ከኢንፈርሜሽን ደህንነት አስተዳደር እና አሰራር ስርዓቶች አንጻር ቀርጸው በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛሉ፡፡ ከስትራቴጂዎች መካከልም የኢንፎርሜሽን ደህንነት ገዥ ሰነዶች በዋናነት ይጠቀሳሉ፡፡

Address

Wolkite

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Abeshge woreda science & information technology office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Abeshge woreda science & information technology office:

Share