EEU Woldia District Customer Service Center

  • Home
  • EEU Woldia District Customer Service Center

EEU Woldia District Customer Service Center Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from EEU Woldia District Customer Service Center, Energy Company, .

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎቱ የአዲስ ኃይል ማስቀጠያ የዱቤ ክፍያ ወለድ ሙሉ ለመሉ አነሳ።የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አዲስ ኃይል ማስቀጠያ ክፍያን በዱቤ ለሚከፍሉ ደንበኞች የሚጣለው...
10/08/2026

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎቱ የአዲስ ኃይል ማስቀጠያ የዱቤ ክፍያ ወለድ ሙሉ ለመሉ አነሳ።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አዲስ ኃይል ማስቀጠያ ክፍያን በዱቤ ለሚከፍሉ ደንበኞች የሚጣለውን የወለድ ክፍያ ሙሉ በሙሉ ማንሳቱን የአገልግሎቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጅነር ጌቱ ገረመው አስታወቁ።

ኢንጅነር ጌቱ ገረመው እንደገለጹት፣ የወለድ ክፍያው መነሳቱ የአዲስ ኤሌክትሪክ ኃይል ማስገባት ፍላጎት ያላቸው ሆነው የማስቀጠያ ክፍያውን በአንድ ጊዜ መክፈል ለማይችሉ ዜጎች አገልግሎቱን ይበልጥ ተደራሽ የሚያደርግ ነው።

በቅርቡ ሥራ ላይ በዋለው የአዲስ ቆጣሪ የዱቤ አሰራር ከሰኔ 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ባሉት ሁለት ሳምንታት ብቻ 19 ሺህ 231 አዳዲስ ደንበኞች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ሆነዋል።

አሰራሩ በተለይ የአዲስ ኃይል ማስቀጠያ ክፍያውን በአንድ ጊዜ መክፈል ለማይችሉ ደንበኞች ክፍያውን በተወሰነ ጊዜ ተከፋፍለው እንዲከፍሉ ዕድል የሚሰጥ ነው።

እንደ ዋና ሥራ አስፈጻሚው ገለጻ፣ ቀደም ሲል የክፍያ ጊዜው እስከ 24 ወራት የሚደርስ ሲሆን፣ ከ6 ወራት በላይ ለሚቆይ ክፍያ ከ3 እስከ 9 በመቶ የሚደርስ ወለድ ይታሰብ ነበር። አሁን ይህ የወለድ ክፍያ ሙሉ በሙሉ ተነስቷል።

የወለድ ክፍያው መነሳቱ በተለይ የአዲስ ኃይል ማስቀጠያ ክፍያን በአንድ ጊዜ መፈጸም ለማይችሉ ደንበኞች ትልቅ የምስራች መሆኑን ኢንጅነር ጌቱ ገረመው ገልጸዋል።

በዚህ ውሳኔ ደንበኞች ያለባቸውን የአንድ ጊዜ የክፍያ ጫና በማቃለል፣ በዱቤ ክፍያ ሥርዓት አማካኝነት አዲስ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስገባት ይችላሉ።

ይህም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ኃይልን ለበለጠ የህብረተሰብ ክፍል ተደራሽ ለማድረግ፣ ዜጎች ከኤሌክትሪክ ኃይል የሚገኘውን ጥቅም እንዲያገኙ ለማስቻልና የደንበኛ ተኮር አገልግሎቱን ለማጠናከር ያለውን ቁርጠኝነት ያሳያል ብለዋል።

ይህ አሰራር የዜጎችን የአንድ ጊዜ የክፍያ ጫና በማቃለል የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን ለማስፋፋትና የአዲስ ደንበኞችን ቁጥር ለማሳደግ የሚያግዝ መሆኑንም ዋና ሥራ አስፈጻሚው ገልጸዋል።

Via የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
=====================

በእቅድ የሚቋረጥ ኤሌክትሪክ   (በወልድያ ሪጅን በተወሰኑ አካባቢዎች)     በወልድያ እና በዙሪያዎ የሚገኙ ገጠር ቀበሌዎች ነገ ነሀሴ 01/2018ዓ.ም ከዶሮ ግብር ሰብስቴሽን የሚያገኙ  መ...
06/08/2026

በእቅድ የሚቋረጥ ኤሌክትሪክ

(በወልድያ ሪጅን በተወሰኑ አካባቢዎች)

በወልድያ እና በዙሪያዎ የሚገኙ ገጠር ቀበሌዎች ነገ ነሀሴ 01/2018ዓ.ም ከዶሮ ግብር ሰብስቴሽን የሚያገኙ መርሳ ከተማ እና በከፊል ሀብሩ ወረዳ ስሪቃ ፣ መርጦ መጋቢ መስመሮች ላይ የመካከለኛ መስመር የቅድመ ጥገና እንዲሁም በኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመር ውስጥ የገቡ ዞፎችን ለማፃዳት ሲባል ከጥዋቱ 2:00ሰዓት እስከ ቀኑ 6:30 ሰዓት የኤሌክትሪክ ኃይል ይቋረጣል ።

በመሆኑም ይህን የቅድመ ጥገና ሥራ ለመስራት ሲባል አርብ ነሀሴ 01/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 6፡30 ሰአት በመርሳ ከተማ እና ከፊል የሀብሩ ገጠር ቀበሌዎች የኤሌክትሪክ ሀይል አገልግሎት ይቋረጣል ።

ስለሆነም በተጠቀሱት ከተሞች እና ቀበሌዎች የምትገኙ ክቡሯን ደንበኞቻችን በዕለቱ ኤሌክትሪክ የሚቋረጠው የኃይል መቆራረጥን ለመቀነስ የሚያስችል የዛፍ ማፅዳት እና የቅድመ ጥገና ስራ ለመስራት መሆኑን እናሳውቃለን ።

ውድ እና ክቡሯን ደንበኞቻችን በዚህ ቀን የኤሌክትሪክ አገልግሎት በተጠቀሱት ቦታዎች ስለሚቆረጥ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ በአክብሮት እናሳውቃለን ።

# የኢትዮጵያ ኤሌትሪክ አገልግሎት ወልዲያ ሪጅን

ነሀሴ 01/2018 ዓ.ም

በእቅድ የሚቋረጥ ኤሌክትሪክ                              (በወልድያ ሪጅን በተወሰኑ አካባቢዎች)     በወልድያ እና በዙሪያዎ የሚገኙ ገጠር ቀበሌዎች ነገ ሀምሌ 27/2018...
02/08/2026

በእቅድ የሚቋረጥ ኤሌክትሪክ
(በወልድያ ሪጅን በተወሰኑ አካባቢዎች)
በወልድያ እና በዙሪያዎ የሚገኙ ገጠር ቀበሌዎች ነገ ሀምሌ 27/2018ዓ.ም ከዶሮ ግብር ሰብስቴሽን የሚያገኙ አዳጎ ፣መቻሬ እና ውርጌሳ 33 መጋቢ መስመሮች ላይ የመካከለኛ መስመር የቅድመ ጥገና እንዲሁም በኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመር ውስጥ የገቡ ዞፎችን ለማፃዳት ሲባል ከጥዋቱ 2:00ሰዓት እስከ ቀኑ 6:00 ሰዓት የኤሌክትሪክ ኃይል ይቋረጣል ።

በመሆኑም ይህን የቅድመ ጥገና ሥራ ለመስራት ሲባል ሰኞ ሀምሌ 27/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 6፡00 ሰአት ወልዲያ ከተማ እና ከፊል የሀብሩ እንዲሁም የጉባላፍቶ ገጠር ቀበሌዎች የኤሌክትሪክ ሀይል አገልግሎት ይቋረጣል ።

ስለሆነም በተጠቀሱት ክፍለ ከተሞች እና ቀበሌዎች የምትገኙ ክቡሯን ደንበኞቻችን በዕለቱ ኤሌክትሪክ የሚቋረጠው የኃይል መቆራረጥን ለመቀነስ የሚያስችል የዛፍ ማፅዳት እና የቅድመ ጥገና ስራ ለመስራት መሆኑን እናሳውቃለን ።

ውድ እና ክቡሯን ደንበኞቻችን በዚህ ቀን የኤሌክትሪክ አገልግሎት በተጠቀሱት ቦታዎች ስለሚቆረጥ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ በአክብሮት እናሳውቃለን ።

# የኢትዮጵያ ኤሌትሪክ አገልግሎት ወልዲያ ሪጅን

ሀምሌ 26/2018 ዓ.ም

በእቅድ የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦት     የጥገና ሥራ ለማከናወን የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦት          ✅ከጠዋቱ 2፡00 – ቀኑ 7:00 ስዓት   ቅዳሜ  ሰኔ 13 ቀን 2018 ዓ.ም የጥገ...
18/06/2026

በእቅድ የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦት
የጥገና ሥራ ለማከናወን የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦት

✅ከጠዋቱ 2፡00 – ቀኑ 7:00 ስዓት

ቅዳሜ ሰኔ 13 ቀን 2018 ዓ.ም የጥገና ሥራ ለማከናወን ኃይል የሚቋረጥባቸው ፊደሮች እና አካባቢዎች

👉 ጎንደር በር ፊደር
👉 መቻሬ ፊደር
👉 መርሳ ፊደር
በወልድያ እና በዙሪያዎ የሚገኙ ገጠር ቀበሌዎች ነገ ማለትም ቅዳሜ ሰኔ 13/2018ዓ.ም ከዶሮ ግብር ሰብስቴሽን የሚያገኙ ፊደሮች ጎንደር በር ፣ መርሳ እና መቻሬ 15/33 ሽህ መጋቢ መስመሮች ላይ ለመካከለኛ መስመር ቅድመ ጥገና ሥራ ሲባል የኤሌክትሪክ ኃይል ይቋረጣል ።

በመሆኑም ይህን የመካከለኛ መስመር ቅድመ ጥገና ቅዳሜ ከጠዋቱ 2:00 እስከ ቀኑ 7:00 ሰአት ወልዲያ ከተማ በከፊል ፣ የሀብሩ እና የጉባላፍቶ ገጠር ቀበሌዎች የኤሌክትሪክ ሀይል አገልግሎት ይቋረጣል ።

ስለሆነም በተጠቀሱት አካባቢዎች የምትገኙ የተከበራችሁ ደንበኞቻችን የጥገና ሥራው ተጠናቆ የኃይል አቅርቦቱ እስኪመለስ ድረስ በትዕግስት እንድትጠብቁን እንጠይቃለን ::

# የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ወልዲያ ሪጅን
ሰኔ 11/2018 ዓ.ም

በእቅድ  የሚቋረጥ ኤሌክትሪክ                                (በወልድያ ሪጅን በተወሰኑ አካባቢዎች)     በወልድያ ከተማ እና በዙሪያዎ የሚገኙ ገጠር ቀበሌዎች ማለትም የፒ...
05/06/2026

በእቅድ የሚቋረጥ ኤሌክትሪክ
(በወልድያ ሪጅን በተወሰኑ አካባቢዎች)
በወልድያ ከተማ እና በዙሪያዎ የሚገኙ ገጠር ቀበሌዎች ማለትም የፒያሳ እና አዳጎ እንዲሁም መቻሬ ፊደር መጋቢ መስመር ላይ ከፍተኛ የሆነ ዛፍ በኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመር ውስጥ በመግባቱ የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ እያስከተለ ይገኛል ፡፡

በመሆኑም ይህን መቆራረጥ ለመቀነስ ነገ ቅዳሜ ግንቦት 29/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 6፡30 በፒያሳ ፣ ጎንደር በር እና መቻሬ 15/33 ኬቪ መጋቢ መስመር ላይ በወልዲያ ከተማ ባሉ ክፍለ ከተሞች እና በስሩ በሚገኙ ቀበሌዎች በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ውስጥ የተተከሉ ዛፎች ለመቁረጥ ያመች ዘንድ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ይቋረጣል ።

ስለሆነም በተጠቀሱት ክፍለ ከተሞች እና ቀበሌዎች የምትገኙ ክቡሯን ደንበኞቻችን በዕለቱ ኤሌክትሪክ የሚቋረጠው የኃይል መቆራረጥን ለመቀነስ የሚያስችል የዛፍ ማፅዳት ስራ ለመስራት መሆኑን እያሳወቅን ።

በኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ውስጥ የገቡ ዛፎችን በመቁረጥ ሁሉም ማህበረሰብ ከጎናችን እንዲቆም ጥሪ እያስተላለፍን የዛፍ ቆረጣ በማከናወን የሀይል መቆራረጥ ለመቀነስ የምንሰራ በመሆኑ በዚህ አካባቢ የምትገኙ ማህበረሰብ የችግሩ አሳሳቢነትን ተረድታችሁ በመስመር ውስጥ የገቡ ዛፎችን በጋራ በመቁረጥ እንድትተባበሩን እንጠይቃለን ።

ውድ እና ክቡራን ደንበኞቻችን በዚህ ቀን የኤሌክትሪክ አገልግሎት በተጠቀሱት ቦታዎች ስለሚቆረጥ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ በአክብሮት እናሳውቃለን ።

# የኢትዮጵያ ኤሌትሪክ አገልግሎት ወልዲያ ሪጅን

ግንቦት 28/2018ዓ.ም

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when EEU Woldia District Customer Service Center posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Want your business to be the top-listed engineering company?

Share