The Truth

The Truth መልካሙን እናበረታታለን፣ጥፋትን እንተቻለን፣የትም አለን።

This sidama engineers group basically focus on development of sidama with structure and design of construction with in new region of Ethiopia future

28/05/2026

፦ የ12 ዓመቷ ታዳጊ አዜብ በላይነህ የደረሰችበት አልታወቀም

በሲዳማ ክልል ምስራቃዊ ዞን፣ በንሳ ወረዳ ዳዬ ከተማ ባለፉት ቀናት በማኅበራዊ ሚዲያና በአካባቢው ማኅበረሰብ ዘንድ ከፍተኛ ስጋትና ቁጭትን የፈጠረው የታዳጊዋ መታፈን ጉዳይ፣ እስካሁን ድረስ ምንም ዓይነት ፍንጭ ሳይገኝለት 11 ቀናትን አስቆጥሯል።

ገና የ12 ዓመት ዕድሜ ያልሞላትና የአንደኛ ደረጃ ተማሪ የሆነችው ታዳጊ አዜብ በላይነህ በዕለቱ ግንቦት 9 ቀን 2018 ዓ.ም (ከቀኑ 8:00 አካባቢ) ወደ እምነት ተቋም ለመሄድ ከቤቷ ትወጣለች።

ሆኖም ግን ማንነታቸው ባልታወቁ ግለሰቦች አማካኝነት፣ በአንድ ባለሦስት እግር ተሽከርካሪ (ባጃጅ) ውስጥ በኃይል ተገዳና እየጮኸች መታፈኗን የአይን እማኞች ጠቁመዋል።

የአካባቢው ነዋሪዎችና ቤተሰቦቿ ድምፅ ሰምተው ለማስጣል ጥረት ቢያደርጉም፣ ተሽከርካሪው በከፍተኛ ፍጥነት ከአካባቢው በመሰወሩ ሳይሳካ ቀርቷል።

ታዳጊዋ ተጠልፋ ከተወሰደችበት ዕለት ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ሙሉ በሙሉ አድራሻዋ የጠፋ ሲሆን፣ ወላጆቿና የቅርብ ዘመዶቿ በከፍተኛ የሥነ-ልቦና ስቃይና በዕንባ ውስጥ ይገኛሉ።

ቤተሰቦቿ እንደሚገልጹት፣ ጉዳዩን ለሚመለከተው አካል ቢያመለክቱም እስካሁን ድረስ የሚጠበቀውን ያህል ፈጣንና ተገቢውን ክትትል እያገኙ እንዳልሆነ በምሬት ይናገራሉ።

"ሕግ የቆመበት ዓላማ የዜጎችን ደኅንነት ለመጠበቅ ካልሆነ ታዲያ ለምንድነው?" የሚለው ጥያቄ በአሁኑ ወቅት የብዙዎችን ልብ የነካና ምላሽ የሚሻ ሆኗል።

ይህች ተጫውታ ያልጠገበችና የቤተሰቧ ተስፋ የሆነች ጨቅላ ሕፃን ወደ ወላጆቿ እቅፍ በሰላም እንድትመለስ እና ፍትህ እንድታገኝ የሁላችንም ሰብዓዊ ግዴታ ነው።

መረጃው ሰፊ ተደራሽነት አግኝቶ ለሚመለከታቸው ከፍተኛ የጸጥታ አካላትና ለሕዝብ እንዲደርስ ፍትህ ለአዜብ በላይነህ" በማለት ጽሑፉን በስፋት Share እና Comment በማድረግ አጋርነታችሁን እንድታሳዩ በትሕትና እንጠይቃለን።

ማንኛውንም ፍንጭ ወይም መረጃ ካላችሁ በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች በአስቸኳይ እንድታሳውቁ ተማጽነናል፦

* 0916031825
* 0960927729
* 0937210547

የሕፃን ልጅ ዕንባና የቤተሰብ እሮሮ ዝም ሊባል አይገባም፤ መረጃውን ለሌሎች በማጋራት የበኩላችንን እንወጣ!

24/05/2026

Alert❗
ትኩረት ይደረግ!

አሁን ከምሽቱ 1:30 ጀምሮ በምስራቃዊ ስዳማ ዞን እና በኦሮሚያ ክልል አርስ ዞን ወሰን አከባቢ የሰላም መደፍረስ እንዳለ መረጃዎች እየወጡ ነው ስለዚህ የሚመለከተው የመንግስት አካል ትኩረት እንድያደርግ እንጠይቃለን።

Ethiopian Federal Police
Office of the Prime Minister-Ethiopia
Ethiopian Human Rights Commission
@

12/04/2026

የፓኪስታን መርከቦች ተመለሱ‼️
ሁለት የፓኪስታን ባንዲራ የያዙ ባዶ የነዳጅ ታንከሮች ከኩዬት እና የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ነዳጅ ለመጫን በሆርሙዝ የባህር ሰርጥ ለማለፍ ተቃርበው የነበረ ቢሆንም መመለሳቸውን ፋርስ ኒውስ ዘግቧል።
እነዚህ ነዳጅ የጫኑ መርከቦች የተመለሱት በኢራን ትዕዛዝ ሳይሆን ትራምፕ የአሜሪካ የባህር ኃይል በሆርሙዝ ሰርጥ ለማለፍ የሚሞክሩትን ማንኛውንም እና ሁሉንም መርከቦችን የማገድ ሂደት መጀመሩን መናገራቸውን ተከትሎ መሆኑን ዘገባው ጠቅሷል። ፓኪስታን ድርድሩ ባይሳካም የአሜሪካ እና የኢራንን ድርድር አመቻች ሀገር እንደነበረች ይታወቃል።

Truth

Address

Hawassa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when The Truth posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share