Astucompeng/04

Astucompeng/04 adama science and technology university computer engineering

What does to mean by dis?
22/09/2017

What does to mean by dis?

12/09/2017
Graduated students will only understand this pic
11/09/2017

Graduated students will only understand this pic

Like it if u understand
21/08/2017

Like it if u understand

ሁል ግዜ ከሱ በማትለይ በትንሽዋ ዲጂታል ካሜራ ግቢውን እየተዘዋወረ ጥሩውንም የተበላሸውንም ፎቶ ያነሳል፡፡ ከተማሪው ቀድሞ ችግሮችን ስለሚያይ ችግሮች ሳይታወቁይፈቱ ነበር፡፡ ዶክተር ዶክተር ...
21/08/2017

ሁል ግዜ ከሱ በማትለይ በትንሽዋ ዲጂታል ካሜራ ግቢውን እየተዘዋወረ ጥሩውንም የተበላሸውንም ፎቶ ያነሳል፡፡ ከተማሪው ቀድሞ ችግሮችን ስለሚያይ ችግሮች ሳይታወቁይፈቱ ነበር፡፡ ዶክተር ዶክተር ፕሮፌሰር አልበርት ኢቸሌ የአዳማ ዩኒቨርስቲ ጀርመናዊው ፕሬዝዳንት በተማሪው እጅግ የሚወደድ ሲሆን ጀርመን ሀገር የግሉ ዩኒቨርስቲ አለው፡፡ ከኢትዮጵያ መንግስት የሚያገኘውን ሙሉ የወር ደሞዙን ለዩንቨርስቲው ማስፋፊያ ነበር የሚያውለው ከዚህ በተጨማሪም ከሌሎች ዩኒቨርስቲዎች በተለየ ኮስት ሼሪንግ ላይ የማይደመር በቀን 4 ብር ተጨማሪ የምግብ ድጎማ ይደረግ ነበር ይህ ብርም የፕሮፌሰር ኢቸሌ የወር ደሞዝ ከነበረው ብር ላይ የተወሰደ ነበር፡፡እንዲሁም ፕሮፌሰር ኢቸሌ ኢትዮጵያ ውስጥ በመስራቱ ብቻ ከጀርመን እና ከሌሎች ሀገራት ያሉ የቴክኖሎጂ ተቋማት አይናቸው አዳማ ዩኒቨርስቲ ላይ ሆነ፡፡ ገና ዩኒቨርስቲ ከተባለ 5 አመት ያልሞላው አዳማ ዩኒቨርስተ የምስራቅ አፍሪካው ሞዴል ዩንቨርስቲ የሚል ስም ተሰጠው 2002 እንደ ኢትዮጵያውያን አቆጣጠር፡፡ዶክተር ዶክተር ፕሮፌሰር አልበርት ኢቸሌ የግቢው ትልቁ ጀነሬተር ሲበላሽ ቱታውን አድርጎ የተበላሸው ጀነሬተር ስር ተኝቶ ብቻውን ሲሰራ አይቶ ያልተገረመ የግዜው የአዳማ ዩኒቨርስቲ ተማሪ የለም፡፡ የሆነ ግዜ ተማሪዎች እና የግቢው አስተዳደር ስብሰባ እያደረጉ ፕሮፌሰር ኢቸሌ 3 ደቂቃ ያህል አርፍዶ ስብሰባው ላይ ደረሰ ቆሞ ተማሪውን ይቅርታ ጠይቆ ተማሪው በክብር አጨብጭቦለት ተቀመጠ ከ30 ደቂቃ በዋላ በግዜው ምክትል ፕሬዝዳንት የሆነው ሰው 30 ደቂቃ አርፍዶ ደረቱን እንደነፋ ገብቶ ተቀመጠ ነገሩን ያስተዋለው ጨዋው ተማሪ በከፍተኛ ድምጽ እየጮኸ ኢቸሌ እያለ በድጋሜ ለፕሮፌሰሩ አጨበጨበለት፡፡አዳማ ዩንቨርስቲ አዳዲስ ካሪኩለሞች እና አዳዲስ ዲፓርትመንቶች መከፈት ጀመሩ፡፡ ትልልቅ እስኮላሮች ወደ ጀርመን ሀገር እና ወደ ሌሎች የአውሮፓ ሀገራት በ6 ዓመት እቅድ ተዘጋጁ፡፡ ከአፍሪካ የመጀመሪያ የሚያስብለውን የኤሮ ስፔስ ኢንጂነሪንግን አዳማ ዩንቨርስቲ ለመጀመር ቃል ተገባ፡፡ ከዚህ በፊት ሜካኒካል፣ ኤሌትሪካል እንዲሁም ኬሚካል ኢንጂነሪንግን ለመማር የሚያመነታው ተማሪ በሚገርም ሁኔታ እነዚህን ዲፓርትመንቶች መቀላቀል ጀመረ፡፡ ለተማሪው ፈጣን ኢንተርኔት መጠቀሚያ የሚሆኑ በኮንፒተር የተሞሉ ሰፋፊ ክፍሎች ስራ ጀመሩ ኢቸሌ የሚል ዋይፋይ የግቢው አየር ላይ ተለቀቀ በጣም ፈጣን ኮኔክሽን በነገራችን ላይ በኢንተርኔት ብዛትም ስፋትም አዳማ ዩኒቨርስቲ የመጀመሪያው ዩንቨርስቲ ነው፡፡የአዳማ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች እና መምህራን ለዚህ ሰው ከፍተኛ ፍቅር አላቸው፡፡ አስተዳደሩ ላይ ግን አብሶ ከሱ በታች ያሉ ሰወች ላይ ግን የሙስና እና የጥራትን ነገርእየገፋባቸው ስለሆነ ደስ አላላቸውም፡፡ እንደ ውጫሌ ውል ሁለት አይነት ሪፖርት መቅረብ ጀመረ አንዱ በእንግሊዘኛ ለፕሮፌሰሩ አንደኛው ደግሞ በአማርኛ ትክክለኛው ሪፖርት ሲተረጎም በጣም የማይመሳሰል የሚገርመው ቁጥር እንኳን ለማመሳሰል አልሞከሩም ይባላል፡፡2003 እንደ ኢትዮጵያውያን አቆጣጠር መብራት ሲጠፋ ጀነሬተሩ አይሰራም ተብሎ ግቢው በጭለማ ተውጦ ላይብረሪዎች ተዘግተው ያድሩ ጀመር፡፡ የካፌው ምግብ በጥራትም በአይነትም ቀነሰ፡፡ አስተማሪዎች በብዛት ይባረሩ ነበር ግቢው በአዳዲስ እና ፍሬሽ ህንድ አስተማሪዎች ተሞላ፡፡ ኢንተርኔት አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩት ክፍሎች ተዘጉ፡፡ ኢቸሌ የምትለውም ዋይፋይ ጠፋች፡፡ እንደ በፊቱ ፕሮፌሰር ኢቸሌ መንገድ ላይ አይታይም፡፡ በዚህ መሃል ነበር ከግቢው በአንዱ ካፌ የምግብ መመረዝ የተከሰተው በእለቱ ብዙ ተማሪዎች ታመሙ በንጋታው ተማሪው የምግብ አድማ አደረገ፡፡ ቁርሱን ሳይበላ ሰልፍ ወጣ በዚህ ግዜ ነበር የአዲስ አበባ እና የአዳማ ዩኒቨርስቲ የቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት ጂነዲን ሳዶ ወደ አዳማ ዩኒቨርስቲ የመጡት ከተማሪው ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ ተወያዩ፡፡ ተማሪው ምንም የምግብ መመረዙ ቢያሰባስበውም ከዛ የባሰ ብሶት ነበረበት፡፡ ተማሪው በተራ እጁን እያወጣ ብዙ ጥያቄ ጠየቃቸው፡፡አንዲት ልጅ እጅዋን አውጥታ ሙሉ ተማሪውን ግራ እያጋባ የነበረውን ጥያቄ አፈረጠችው ዶክተር ዶክተር ፕሮፌሰር አልበርት ኢቸሌ የት ሄዱ? ሙሉ ተማሪው በጩኸት ጥያቄዋን አስተጋባ፡፡ አቶ ጁነዲን ሳዶ አላቅማሙም ፕሮፌሰሩ ወደ ኢትዮጵያ እንደማይመለሱ እና የቀረጹትን ካሪኩረም ለጠቅላይ ሚኒስተር መለስ ዜናዊ ሰተዋቸው በጣም እንዳዘኑ ኢትዮጵያ ውስጥ መስራት እንደማይቻል ነግረዋቸው ሄደዋል፡፡ እሳቸው ከሄዱ ጀምሮ አዳማ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት እንደሌለው ለተማሪው ገለጹለት፡፡ ሙሉ የአዳማ ዩኒቨርስቲ ተማሪ ቅስሙ ተሰበረ፡፡ዶክተር ዶክተር ፕሮፌሰር አልበርት ኢቸሌ እኖድሀለን ረጅም እድሜ ከጤና ጋር ባለህበት እንመኝልሃለን —
©Yonan!

15/08/2017

Do you still remember those awkward days in schools during Exams?
1. When a bright student tells the invigilator that question 4 has a problem, but you have already answered it...
2. When a fellow student asks for a graph paper, but you are finished and did not see anywhere where it was required...
3. When the invigilator says jump question 6 we will rectify it later, but it was the question you enjoyed most when answering...
4. When you see people busy using rulers and you are wondering what is going on...
5. When you hear your friends arguing after the exam whether the answer to question 5 was 35.5% or 36% and your answer was -45000

Good bye
18/07/2017

Good bye

Astu civil graduated student have did this amazing road. Please xpress your support this guy
04/07/2017

Astu civil graduated student have did this amazing road. Please xpress your support this guy

04/07/2017
Bezih library ber lay setalfu chikoch lemayet metnteraru hula yet nachu
04/07/2017

Bezih library ber lay setalfu chikoch lemayet metnteraru hula yet nachu

04/07/2017

የኮሌጅ ትዝታዎች

አንድ ጓደኛችን በአንድ ወቅት ይታመማል። እንደ አብዛኛው ተማሪ እዛው የምንኖርበት ግቢ ውስጥ ወዳለው የኮሌጁ ክሊኒክ ያመራል። ብዙውን ግዜ የህመምተኛው ኬዝ ቀለል ያለ ከሆነ እዛው ክሊኒክ ውስጥ እንዲታከም ይደረጋል ፤ ከክሊኒኩ አቅም በላይ ከሆነ ግን ወደ adama hospital ሪፈር ይደረጋል።

ታዲያ ጓደኛችን ተራው ደርሶ ነርሱ ጋር ገባ። በነገራችን ላይ በክሊኒኩ ውስጥ ዶክተር የሚባል ነገር የለም። መቼም ለራሱ ቅንጣት ያክል ክብር ያለው ዶክተር እዚህ ቀልድ ቦታ መጥቶ ግዜውን አያባክንም። ጓደኛችን ለነርሱ የህመሙን ስሜቶች ሲነግረው የሰገራ ምርመራ አዘዘለት። ለነገሩ ምልክቱ ምንም ይሁን ምን ነርሱ ለሁሉም በነፍስ ወከፍ የሰገራ ምርመራ ነው የሚያዘው።

ጓደኛችን እስቲ ጉዳቸውን ልይ ብሎ፣ ካፌ እስከሚከፈት ጠበቀና ለምሳችን ከተዘጋጀው የሽሮ ወጥ ላይ ቀንሶ ለሰገራ ሳምፕል መስጫ ከተሰጠው እቃ ለይ ገልብጦ ለክሊኒኩ ላቦራቶሪ አስረከበ።

ከአንድ ፣ ከሁለት ሰአት በኋላ የምርመራው ውጤት ደረሰና ዳግም ነርሱ ጋር ቀረበ።

" ዌል እንግዲህ ፣ የምርመራህ ውጤት እንደሚያሳየው የአሜባ ፕሮቶዟ ተገኝቶብሃል!"

ይሄኔ ካፌውንም ፣ ክሊኒኩንም መሸሽ ነው!
እስከ ዛሬ ስንበላ የነበረው አሜባ ነበር ማለት ነው ወይንም እስከ ዛሬ ስንታከም የነበረው ሃሰት ነበር ማለት ነው! 😬😁

እስኪ የእናንተም የኮሌጅ ገጠመኞቻችሁን አካፍሉን።

Address

510
Adama
251

Telephone

0910261177

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Astucompeng/04 posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share