ዶክተር ደዋ - Medication

ዶክተር ደዋ - Medication አላማችን በህክምናው ዘርፍ ኡማውን ማገልገል ነው።

26/05/2022

#የፍቅረኛዎን የመጀመርያ ፊደል ይፃፉና የሚሆነውን ይመልከቱ‼️

03/10/2021
31/08/2021

የደሴ ከተማ አስተዳደር
የሕልውናው ዘመቻ እስኪጠናቀቅ ድረስ ደሴ ላይ ጫት መቃም ከልክሏል።የህልውናው ዘመቻው እስኪጠናቀቅ በደሴ ከተማ የትኛውም ጫት ቤት ተብሏል። ማንም የከተማዋ ወጣት ጫት መቃም እንዳይችል የከተማ አስተዳደሩ ዛሬ ውሳኔ አሳልፏል።ሲቅም በተገኘ ላይ የማያዳግም እርምጃ ለመውሰድ የከተማ አስተዳደሩ ቁርጠኛ አቋሙን ገልጿል:: ይሄም ውሳኔ በሁሉም የአማራ ክልል ከተሞች መስፋፋት ይኖርበታል።
Seid Aragaw

04/06/2021

ትኩረት የማጣት እና የመረጋጋት ችግር (ኤዲኤችዲ)
(Attention Deficit hyperactivity Disorder)-ADHD

ኤዲኤችዲ ልጆች ላይ ሊከሰት የሚችል የእድገት እክል ነው።

አንዳንድ ወላጆች ልጆቻቸውን ከሌሎች በተለየ ትዕግስት የለሽ፣ ቀዥቃዣና አስቸጋሪ ሆነውባቸው መፍትሔ ሲፈልጉ ይታያሉ፡፡ እነዚህ ህፃናት የሚይዙት የሚጨብጡት የሚጠፋባቸው፣ አንድ ነገር ጀምረው አፍታም ሳይቆዩ ሌላ የሚያምራቸው፣ ለመናገርና ለመጠበቅ ትዕግስት የማይኖራቸውና ችኩል ናቸው፡፡
ይህ አይነት የስነባህሪና የስነአእምሮ ችግር ያለባቸው ህፃናት ትኩረት ያጡ፣ ትዕግስት የለሽ ቀዥቃዣነት (ADHD) ህመም ተጠቂዎች ናቸው፡፡

የእነዚህ ህፃናት መሰረታዊ መገለጫዎች
 አንድ ነገር ጀምረው በቀላሉ ወደ ሌላ የሚሳቡና አንድን ነገር ጀምሮ
ለመጨረስ ትኩረት የሌላቸው
 በትምህርት ቤት ግዴለሽነት የሚታይባቸውና ቀላል ስህተቶችን በፈተና
ላይ በተደጋጋሚ የሚሰሩ
 የማያዳምጡና የተባሉትን የማያደርጉ
 የክፍልና የቤት ስራን ጀምሮ ለመጨረስ እንኳን ትዕግስት የሌላቸው
 በተሰጣቸው ስራ ላይ ሀሳባቸውን መሰብሰብ የማይችሉ
 ዝንጉነት በእጅጉ የሚታይባቸው
 በየአቅጣጫው የሚሮጡና እረፍት የሌላቸው፣ ዛፍም ሆነ ደረጃ ላይ
ላይ ለመውጣት የሚታገሉ
 እጅና እግራቸው የሚቅበጠበጥና አደብ የሌላቸው
 ከጓደኞቻቸው ጋር እየተጫወቱ ተራቸው አስኪደርስ መጠበቅ ሞት
የሚመስላቸው
 በቀላሉ የሚበሳጩና የሚናደዱ ናቸው፡፡

ስለዚህም ይህ ትኩረት የለሽነታቸውና ትዕግስት አልባነታቸው የትምህርት አቀባበልና አረዳዳቸውን በእጅጉ ይጎዳዋል ።

ለዚህ ህመም እንዲህ ነው የሚባል ምክንያት ባይኖርም በእርግዝና ጊዜ አልኮልና ሲጋራ መጠቀም እንደ አጋላጭነት ይጠቀሳሉ፡፡ ዓለም አቀፍ ጥናት እንደሚያሳየው ከሆነ ለትምህርት ከደረሱ ህፃናት መካከል ከ5-10 በመቶ የሚሆኑት ህፃናት ይህ ችግር ሊታይባቸው ይችላል፡፡

አብዛኛው ትኩረት የለሽ ህፃናት በስነ ልቦና ህክምና፣ በአማራጭ ትምህርት(Special Education) እና በመድሀኒቶች በመታገዝ የሚስተካከሉና መሻሻል ሊያሳዩ ይችላሉ፡፡ ሆኖም አንዳንዶች የጎላ ችግር ያለባቸው ካደጉ በኋላም ራስን ዝቅ ማድረግና ከማህበራዊ ግንኙነቶች ማፈግፈግ ሊታይባቸው ይችላል፡፡
ወላጆች እንዲህ አይነት ባህሪ ያላቸውን ህፃናት በአግባቡ በማሳከምና በቤት ውስጥ ድጋፍና አንክብካቤ በማድረግ ችግራቸውንና የትምህርት አቀባበላቸውን ቀስ በቀስ ማስተካከል ይችላሉ፡፡
መልእክቱ ለሁሉም እንዲደርስ ያድርጉት።

በዶ/ር ሄኖክ ዘውዱ
(የህፃናት ህክምና ስፔሻሊስትና የልጅ በእድሉ አይደግ መፅሀፍ ደራሲ)

03/06/2021

የፎቶውን መልእክት ከገባህ ብቻ በማድረግ ላልደረሰው አድርስ።

29/05/2021

አብዝቶ የመጠራጠር የስብእና ህመም
========================
እንደዚህ አይነት ስብእና ያላቸው ሰዎች በብዛት 'ሲሪየስ' እና ለራሳቸው የተጋነነ ግምት የሚሰጡ ሲሆኑ ከሁሉም ሰው ጋር ያላቸውን ግንኙነት በንቃት ነው የሚከታተሉት። በሌሎች ሰዎች ንግግር እና ድርጊት የተደበቀ እነሱን ሊጎዳ የሚችል ነገር ሊኖረው እንደሚችል ስለሚያስቡ ሰውን ማመን ይከብዳቸዋል። ስነ ልቦናዊ መሰረቱ አሉታዊ ሀሳቦቻቸውንና ስሜቶቻቸውን መቀበል አለመቻል ነው። በራሳቸው የማይቀበሏቸውን ስሜትና ሀሳቦች በሌሎች ላይ ስለሚስሉ ሌሎች ሰዎችን ይፈራሉ።

ሀዘን ወይም ሀፍረት እንደሚሰማው ሰው አይናቸውን አይሰብሩም። ወይም እንደፈራ ሰው ወደ ጎንም አያዩም። በብዛት የሚያዩት 'በቆሪጥ' ነው። ሀዘን ብዙ ጊዜ አይስተዋልባቸውም። ምክኒያቱ ደግሞ ሀዘን ቢያንስ በሁለት መንገድ ሊፈጠር ይችላል። አንደኛው በራስ በመናደድ ነው። የበዛ ተጠራጣሪ ስብእና ያላቸው ሰዎች አሉታዊ ነገሮችን በራሳቸው ላይ ስለማይቀበሉ በራሳቸው ሊናደዱ አይችሉም። ሁለተኛው ሀዘን የሚፈጥረው የሚፈልጉትን ነገር ማጣት ነው። አነሱ ያላቸው "ምናልባት ባጣውስ?" የሚል ጥርጣሬ ነው እንጂ ቁርጡ የለየለት ጉዳይ አይደለም። ስለዚህ ከሀዘን ይልቅ በብዛት የሚሰማቸው ስሜት ጭንቀት፣ ፍርሀትና ምቀኝነት ነው። ምቀኝነትን እንደሌሎቹ አሉታዊ ስሜቶች በራሳቸው መቀበል ስለማይችሉ "ሰዎች ይመቀኙኛል!" ብለው ይገልፁታል።

እንደዚህ አይነት ስእብና ያላቸው ከሌሎቹ የስብእና ህመሞች አንፃር በብዛት አልተጠኑም። ምክኒያቱ ግልፅ ነው። አንደኛ ህመሙን ስለማይቀበሉት ሲሆን ሁለተኛው ቢቀበሉት እንኳ "ለምንድነው የምታጠኑት?" ወይም "እኔን ለምን መረጣችሁን?" የሚል ጥርጣሪ ስለሚፈጠርባቸው ነው። የበዛ ተጠራጣሪ የሆኑ ሰዎች በሁለት ስነ ልቦናዊ ምክኒያቶች ስልጣን ላይ ይወጣሉ። አንደኛው ስልጣን ላይ ሲሆኑ በግልፅ የሚቃረኗቸው ሰዎች ይኖራሉ። ይሄ "ምናልባት?" እያሉ በምናብ ከመጨናነቅ ይቀላል። ሁለተኛው ስልጣን ላይ ከሆኑ 'ሊጎዷቸው' የሚችሉት ሰዎች ላይ እርምጃ ለመውሰድ ይችላሉ።

የበዛ ተጠራጣሪነት ያላቸው ሰዎች ወደ ህክምና አይመጡም። ከነሱ ጋር ግንኙነት ያላቸው ሰዎች ላይ የሚሳድሩት ጫና ግን ቀላል አይደለም። ምን አይነት አስዳደግ ወደ የበዛ ተጠራጣሪ ስብእና እንደሚመራ በሌላ ጊዜ አቀርባለሁ።

አብዛኞቹ ሀሳቦች ከ Psychoanalytic diagnosis: understanding personality structure in the clinical process. Nancy McWilliams የተወሰዱ ናቸው።

መልካም ጊዜ!
ዶ/ር ዮናስ ላቀው

29/05/2021
ቦርጭን እንዴት እናጥፋ??ሰላም የዶክተር ደዋ (Dr. Dawaa) ቤተሰቦች!!ዛሬ የብዙዎች ችግር ስለሆነው ቦርጭ የማጥፊያ መንገዶች በአጭሩ እናያለን፡፡ ቦርጭ ምንድነው??ቦርጭ እጅግ በጤና ረ...
28/05/2021

ቦርጭን እንዴት እናጥፋ??
ሰላም የዶክተር ደዋ (Dr. Dawaa) ቤተሰቦች!!
ዛሬ የብዙዎች ችግር ስለሆነው ቦርጭ የማጥፊያ መንገዶች በአጭሩ እናያለን፡፡ ቦርጭ ምንድነው??
ቦርጭ እጅግ በጤና ረገድ አሳሳቢ ጉዳይ ነው፡፡ ይህ አይነት ስብ የውስጥ አካት ስብ ነው፡፡ ቦርጭ ለስካር በሽታ፣ ለልብ በሽታ እንዲሁም ለሌሎች በሽታዎች አጋላጭ ያደርጋል፡፡
ቦርጭን እንዴት ማጥፋት ይቻላል??
1. በፋይበር የበለጸጉ ምግቦችን ማዘውተር
2. መጥፎ ስብ አለመብላት
3. ብዙ አልኮል አለመጠጣት
4. በፕሮቲን የበለጸጉ ምግቦችን መውሰድ
5. ጭንቀት እና ውጥረትን መቀነስ
6. የሚወስዱትን የስካር መጠን መቀነስ
7. እንቅስቃሴ ማዘውተር
8. ካርቦሃይድሬት ያላቸውን ምግቦች አለመውሰድ
9. የኮኮናት ወይም የወይራ ዘይት መጠቀም
10. ክብደት ማንሳት
11. ጣፋጭ የበዛበት መጠጥ አለመውሰድ
12. በቂ እንቅልፍ መጠጣት
13. አመጋገቦን እና እንቅስቃሴዎትን መመዝገብ
14. አሳ በየሳምንቱ መብላት
15. የፍራፍሬ ጁስ አለማብዛት
16. ምግቦት ላይ ፖም ያለበት ኮምጣጤ መጨመር
17. ፕሮባዮቲክ ያለበትን ምግብ ማዘውተር
18. ለረጅም ሰዓታት መፆም
19. አረንÕዴ ሻይ መጠጣት
20. የኑሮ ዘይቤዎን ይቀይሩ
ይህንን መረጃ ሼር በማድረግ ለሌሎች ያጋሩ!!

25/05/2021

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ዶክተር ደዋ - Medication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share