BM Engineering Academy

የሚሸጥ አስፓልት ሬንጅ አለን 80/100 ፣ጠቅላላ 200 በርሜልዋጋ 15500 ብር በበርሜል።
16/01/2023

የሚሸጥ አስፓልት ሬንጅ አለን 80/100 ፣ጠቅላላ 200 በርሜል
ዋጋ 15500 ብር በበርሜል።

👉 የአፈርን የመሸከም አቅም (BEARING CAPACITY) እንዴት እንጨምር??...* ሶስት አይነት የአፈርን የመሸከም አቅም ማስተካከያ ቴክኒኮች አሉ - mechanical, chemical & ...
16/03/2022

👉 የአፈርን የመሸከም አቅም (BEARING CAPACITY) እንዴት እንጨምር??...
* ሶስት አይነት የአፈርን የመሸከም አቅም ማስተካከያ ቴክኒኮች አሉ - mechanical, chemical & other stabilization techniques
A) ሜካኒካል ውስጥ :-
1. Compaction - አፈሩን ስንጠቀጥቀው density/ unit
weight ይጨምራል ያ ማለት ደግሞ አፈርን የመሸከም አቅም ጨመረ ማለት ነው::
2. Excavation and Replacement – expansive soil ከሆነ ወይም ሌላ አስቸጋሪ አፈር ከሆነ ይህን መጠቀም እንችላለን
3. Mixing of Different Soils - ሳይታችን ላይ ያለው አፈር
coarse ወይም fine ብቻ ከሆነ ወይም ደግሞ አፈሩ አንድ አይነት
ብቻ ፀባይ ካለው ከተለያዩ አፈሮች ጋር በመደባለቅ የተሻለ የአፈር
ፀባይ ማግኘት እንችላለን
B) ኬሚካል :-
1. Lime stabilization - ይህንን የምንጠቀመው በአብዛኛው
ለexpansive soil ነው፡፡ አፈሩን ከ Lime ጋር በመደባለቅ
plasticity መቀነስ እንችላለን፡፡ የlime መጠኑ ከሚያስፈልገው
በላይ ከበዛ ግን B.C. ይቀንሳል፡፡
2. Cement stabilization - ሲሚንቶን ከአፈር ጋር በመደባለቅ
የተሻለ ውጤትን የምናገኝበት መንገድ ነው፡፡ concrete
pavement ስር መጠቀም እንችላለን በአብዛኛው ለአየር
መንገዶች ፤ ለአውራ ጎዳናዎች ፤ ግድቦችን ከሽርሸራ ለመከላከል
ወ.ዘ.ተ. መጠቀም እንችላለን፡፡
3. Asphalt stabilization - አስፓልትን ከአፈር ጋር በመደባለቅ
የተሻለ ውጤትን የምናገኝበት ዘዴ ነው በተለይም ለcohesive
አፈሮች፡፡ አፈሩን water proof በማድረግና ውሃማነትን በመቀነስ
B. Cን መጨመር እንችላለን፡፡ በአብዛኛው ይህንን ድብልቅ
ለመንገዶች እንደ base course መጠቀም እንችላለን፡፡
C) ሌሎች የአፈርን ባህሪ ማስተካከያ መንገዶች:-
1. Drainage - ፓይፖችን አፈር ውስጥ በመቅበር ወይም
ጉድጓዶችን በመጠቀም ground water የምንቆጣጠርበት ነው
2. Precompression - ግንባታ ከመጀመራችን በፊት አፈሩ ላይ
ሎድ በመጫን ኮምፓክት የምናደርግበት ዘዴ ነው

3. Dynamic Stabilization
ሀ) Blasting - ቦምብ ወደውስጥ በመቅበር በፍንዳታው አፈሩ ይጠቀጠቃል::
ለ) Compaction Piles - ፓይሎችን ወደውስጥ በማስገባት
አፈሩ ወደ ጎን እንዲሸሽና እንዲጠቀጠቅ ማድረግ ይቻላል፡፡
ፓይሉን ስናስወጣውም በተቦረቦረው ጉድጓድ ውስጥ የተሻለ አፈር በማስገባት የአፈርን የመሸከም አቅም ማስተካከል እንችላለን፡፡
4. Injection And Grouting - አፈሩን በሲሚንቶ ወይም
በተለያዩ chemical ውህዶች በpressure በመምታት ground
water ና settlement መቆጣጠር እንችላለን፡፡
የተሻለውን ዘዴ ለመምረጥ የአፈሩንና የአካባቢውን ሁኔታ ፤
ኢኮኖሚ ፤ ሴፍቲና የመሳሰሉትን ነገሮች ማጤን አለብን፡፡
👉For More Updated Con information

https://t.me/addisengineers

   "🏗አንድ ህንፃ የተለያዩ structural member (column , beam , slab..etc) ውቅር ነው ስዋቀርም ሁሉም የየራሳቸው አገልግሎት አላቸው የህንፃው ህልውና የመፍረስና ያ...
07/03/2022

"

🏗አንድ ህንፃ የተለያዩ structural member (column , beam , slab..etc) ውቅር ነው ስዋቀርም ሁሉም የየራሳቸው አገልግሎት አላቸው የህንፃው ህልውና የመፍረስና ያለመፍረስ ዋስትና ተገብውን አገልግሎት በተገቢው መንገድ የመስጠት ሀላፊነትና የህንፃው የአገልግሎት እድሜ የሚወሰነው well designed structural member መሆኑ እሙን ነው። በመሆኑም ለአንድ ህንፃ መፍረስ መክንያት ይሆናል ተብለው ብዙ ልህቃን የሚስማሙበት ጉዳይ፦

🏗The reasons a building collapses can be due to

🔸poor structural design,
🔸poor compliance with specifications
🔸poor quality control
🔸Faulty construction methodology foundation failure
🔸Extraordinary loads and corruption. A natural disaster is also identified as a cause of building collapse.

🏗በመሆኑም በእኛ አገር በስፋት ከሚስተዋለው ምክንያቶች መሀከል

👉poor structural design
👉faulty construction
👉poor quality control and corruption ዋነኞቹ ናቸው።

🏗አንድ ህንፃ እኛ ዲዛይን ካደረግንበት ባነሰና በጣም ትንሽዬ በሆነ ሎድ ሊፈርስ ይችላል ? እንዴት??

ህንጻው መሸከም ከሚችለው ባነሰ በትንሽዬ ሎድ ሊፈርስ የሚችለው በሁለት ምክንያቶች ነው
1, በ Fatigue ና
2, በ Creep ነው

1,Fatigue
👉ሎዶቹ ትንንሽዬ ቢሆኑም እንኳን በሎድ ድግግሞሽ የተነሳ የህንጻው ጥንካሬ ሲደክም የሚፈጠር ነው፡፡ ይህ ሁኔታ በአብዛኛው የሚከሰተው ድልድዮች ላይ ነው - የመኪና ድግግሞሽ፡፡

2,Creep
👉አንድ ሎድ አንድ ቦታ ላይ ለብዙ ጊዜ በመቀመጡ ሳቢያ Strain ሲጨምር የሚፈጠር ነው፡፡

🏗አራት መአዘን ቅርፅ ያለው ለአነስተኛ ቤተሰብ የሚውል የውሃ ታንከር እንዴት ዲዛይን እናደርጋለን❓እንደ አለማቀፋዊው የIS ኮድ አንድ ሰው በቀን ውስጥ ለተለያየ አገልግሎቶች የሚጠቀመው የውሃ...
25/02/2022

🏗አራት መአዘን ቅርፅ ያለው ለአነስተኛ ቤተሰብ የሚውል የውሃ ታንከር እንዴት ዲዛይን እናደርጋለን❓
እንደ አለማቀፋዊው የIS ኮድ አንድ ሰው በቀን ውስጥ ለተለያየ አገልግሎቶች የሚጠቀመው የውሃ መጠን 135 liter ነው።
ይህ ኮድ
*ለመጠጥ - 5 ሊትር
*ለማብሰል- 5 ሊትር
*ለመታጠብ እና ፍሳሽ ለማስወገድ - 85 ሊትረ
*ልብስ እና እቃዎችን ለማጠብ - 30 ሊትር
*ቤት ለማፅዳት - 30 ሊትር ውሃ መጠቀም እንዳለብን ይጠቁማል።
▶ይህን የIS ኮድ ይዘን 4 አባላት ላሉት አንድ ቤተሰብ እንደ Hydraulic ኢንጂንየርነታችን አራት መአዘን ቅርፅ ያለው የውሃ ታንከር ዲዛይን እናርግ።
4 አባላት (ሰዎች) ላሉት የቤተሰብ አባል ተፈላጊ የውሃ መጠን በliter
135×4 = 650 liter (ለአንድ ሰው በቀን 135 liter )
የውሃ ታንከሩን መጠን ለማወቅ ከርዝመቱ (length ) ከየጎን ስፋት (width ) እና ከቁመቱ/ጥልቀቱ( depth) አንዱን ማወቅ አለብን ።
▶ከ Volume ቀመር እንደምንረዳው
1cu.m = 1000liters
1liter = 0.001 cu.m ነው ስለዚህ
650liter = 0.65 cu.m
የታንከራችንን ቁመት 0.6m ብናደርገው የታንከራችን ስፋት (area ) እንዲ ማግኘት እንችላለን
Area= 0.65÷0.6 = 1.083 sq.m ስፋት (area) ማለት ርዝመት (length) ሲባዛ የጎን ስፋት (width) ይሆናል ። ይህም
A=L×W= 1.083 sq.m
በ IS ተጠቃሽ (recommended) የርዝመት መጠን ከሁለት እጥፍ የጎን ርዝመት መጠን ጋር እኩል ነው ።
ይህም L= 2W
L×W=1.083 sq.m
2W×W = 1.083 sq.m
B^2 = 0.054 sq.m
B= 0.74
L= 2×0.74 = 1.48 m
▶ስለዚህ 650 liter የሚይዝ ታንከር ፦
ርዝመት (L) =1.48m
የጎን ርዝመት (W) = 0.74m
ቁመት/ጥልቀት= 0.6 m ይሆናል ማለት ነው ። ልንረሳው ማይገባ ነገር ለታንከሩ free flow provide ማረግ አለብን [125mm free flow ]

ጥራት ያለው ስራ የአገርን ብልፅግና ያረጋግጣል!በአፃሩ ጥራት የሌለው ስራ ደግሞ ሀገርንም ይጎዳል ክቡር የሰው ህይወትንም ይቀጥፋል።🤨🤨
27/12/2021

ጥራት ያለው ስራ የአገርን ብልፅግና ያረጋግጣል!
በአፃሩ ጥራት የሌለው ስራ ደግሞ ሀገርንም ይጎዳል ክቡር የሰው ህይወትንም ይቀጥፋል።🤨🤨

17/12/2021
🏷የ Foundation (መሠረት) አይነቶች 🚧1)Shallow Foundation➡️እነዚህን ፋውንዴሽኖች የምንጠቀመው አፈሩ ብዙም ሳይቆፈር በቅርብ ጥልቀት ጠንካራ የአፈር ሁኔታ ካለ ነው፡፡➡️ለ...
04/12/2021

🏷የ Foundation (መሠረት) አይነቶች

🚧1)Shallow Foundation

➡️እነዚህን ፋውንዴሽኖች የምንጠቀመው አፈሩ ብዙም ሳይቆፈር በቅርብ ጥልቀት ጠንካራ የአፈር ሁኔታ ካለ ነው፡፡

➡️ለመገንባት ትልልቅ ማሺኖች አያስፈልጉም ብዙ ችሎታም አይጠይቁም::

▶️1.1) Spread/ Pad/Isolated Footing

➡️አንድ ኮለን ብቻ ነው support የሚያደርጉትእንዲሁም የሚመጣውን ፎርስ eccentricity መሰረት በማድረግ circular/ rectangular or square የሆነ ቅርፅ ሊኖራቸው ይችላል፡፡

▶️1.2)Combined Footing

➡️ሁለትና ከዛ በላይ ኮለኖችን በአንድ ፓድ support ለማድረግ ነው የምንጠቀምባቸው፡፡

➡️እነዚህን የምንጠቀመው ሁለት ተቀራራቢ Isolated Footing ካሉ ሁለቱን አንድ ላይ combine በማድረግ ኮንክሪትም ፌሮም ሴቭ ማድረግ እንችላለን፡፡

➡️በተጨማሪም isolated ለመጠቀም property limit ካለ እነዚህን መጠቀም እንችላለን::

➡️2 አይነት Combined Footing አሉፐእነርሱም

▶️1.2.1) Rectangular Combined Footing

➡️ይህንን የምንጠቀመው ሁለቱም ኮለኖች የሚሸከሙት ሎድ ተቀራራቢ ወይም እኩል ከሆከሆነይም ትራፖዞይዳል ለመጠቀም የስፋት ገደብ ካለ ነው።

▶️1.2.2. Trapezoidal Combined Footing

➡️ሁለቱ ኮለኖች የሚሸከሙት ሎድ ልዩነት የተጋነነ ከሆነ ነው።

▶️1.3) Strap/ Cantilever Footing

➡️ሁለት ፓዶችን በቢም በማያያዝ ሎድ ከአንዱ ፓድ ወደሌላው እንዲተላለፍ ማድረግ እንችላለን፡፡

➡️ቢሙ በራሱ ሎድ አይሸከምም ሎድ ያስተላልፋል እንጂ እነዚህን የምንጠቀመው ኮለኖቹ ከ7 ሜትር በላይ ከተራራቁ combined footing ብንጠቀም ኢኮኖሚካል ስለማንሆን ፓዶቹን በቢም በማያያዝ እንደ combined footing ልንጠቀምባቸው እንችላለን፡፡

▶️1.4) Mat/ Raft foundation

➡️እነዚህን የምንጠቀመው መሬቱ የመሸከም አቅሙ ትንሽ ከሆነና spread footing ስንጠቀም የህንጸውን ስፋት ከ50 ፐርሰንት በላይ ከሸፈኑት ነው።

➡️አንዳንዴ ግን spread footing ከ 50 ፐርሰንት በላይ ቢሸፍኑትም ለ spread footing negative reinforcement ስለማንጠቀም ከ Mat ይልቅ ኢኮኖሚካል ሊሆኑ ይችላሉ ምክንያቱም Mat negative & positive reinforcement ይጠቀማሉ፡፡

➡️ማን ኢኮኖሚካል እንደሆነ ቼክ ማድረግ የኢንጅነሩ ድርሻ ነው፡፡

22/09/2021

👉A turned mass damper (TMD) also known as a harmonic absorber or seismic damper is a device mounted in structures to reduce the amplitude of mechanical vibrations. Their application can prevent discomfort, damage or outright structural failure. They are frequently used in power transmission, automobiles and buildings.

👉የአርማታ ብረት በሜትር ምን ያህል ይመዝናል? ⏩ለኮንስትራክሽን ግብዐት የምንጠቀማቸው የአርማታ ብረት በቅርፃቸው በሁለት ይከፈላሉ1. ልሙጥ ብረት(Mild Steel or plain rebar)2...
06/06/2021

👉የአርማታ ብረት በሜትር ምን ያህል ይመዝናል?
⏩ለኮንስትራክሽን ግብዐት የምንጠቀማቸው የአርማታ ብረት በቅርፃቸው በሁለት ይከፈላሉ

1. ልሙጥ ብረት(Mild Steel or plain rebar)

2. ባለ ክርክር/አርማታ ብረት(Deformed steel rebar)

➡️በጥንካሬ ደረጃ ደግሞ በስፋት Grade 60 እና Grade 40
በመባል ይለያሉ ይህም ውጥረታዊ ሀይል/tensile strength/ በመቌቌም አቅማቸው ነው።
*Grade 40=275.79MPa yield strength ሲኖረው
*Grade 60=413.68MPa yield strength ይኖረዋል።

Share አድርጉልን

👉A turned mass damper (TMD) also known as a harmonic absorber or seismic damper is a device mounted in structures to reduce the amplitude of mechanical vibrations. Their application can prevent discomfort, damage or outright structural failure. They are frequently used in power transmission, automobiles and buildings .

👉የአርማታ ብረት በሜትር ምን ያህል ይመዝናል? . ⏩ለኮንስትራክሽን ግብዐት የምንጠቀማቸው የአርማታ ብረት በቅርፃቸው በሁለት ይከፈላሉ 1. ልሙጥ ብረት(Mild Steel or plain rebar) 2. ባለ ክርክር/አ.....

04/06/2021

✿በተደጋጋሚ በስራ ቃለመጠይቅ/ ኢንተርቪው ጊዜ
የሚጠየቁ ጥያቄዎች✿
ክፍል1
በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ወደ 30 የሚደርሱ ጥያቄዎችንና ልታሰጡ የሚገባቸውን ምላሾች እንዲሁም ማድረግ የሚገባችሁን ጥንቃቄ በተመለከተ ለዛሬ 10 ያህሉን ይዘናል ቀሪዎቹን በሌላ ጊዜ የምናቀርብ ይሆናል፡፡
1, እስኪ ስለራስህ ንገረን?
ይህ ጥያቄ እንዲሁ በግርድፉ ሲታይ ቀላል ይመስላል ይሁን
እንጂ ብዙዎች ገና ከጅምሩ ስህተት የሚሰሩበት ነው፡፡ ብዙ
ተጠያቂዎች ለዚህ ጥያቄ መልስ የሚመስላቸው ስለራሳቸው የህይወት ታሪክ ማውራት ነው ፡ ይሁን እንጂ እንዲያ ለማለት ሳይሆን በስራ ህይወት ላይ ስላለህ ማንነት ፡ የስራ ልምድ
ካለህ በዚያኛው የስራ ቦታ ስላስመዘገብካቸውና ስለሰራሀቸው ጥሩ ስራዎች እንዲሁም ጀማሪ ተቀጣሪ ከሆንክ በዩኒቨርሲቲ ቆይታህ ስለነበረህ መልካም እንቅስቃሴ ወይም ስለሰራኸው የመመረቂያ ፕሮጀክት ልታወራ ትችላለህ፡፡ በንግግርህም ወቅት ጠያቂው የመጀመሪያ ምርጫው እንድትሆን ጠቃሚ ነገሮቹ ላይ ትኩረት አድርግ፡፡
2,ስለዚህ የስራ መደብ እንዴት ሰማህ??
ሌላው በተደጋጋሚ የሚጠየቀው ጥያቄ ይሄ ነው ፡ በዚህ ወቅት ማድረግ የሚገባችሁ ነገር በትክክል ስለዚህ የስራ መደብ የሰማችሁበትን ቦታ በግልፅ ተናገሩ ፡ በጋዜጣ ; በማስታወቂያ ቦርድ ; በጓደኛችሁ አልያም በማህበራዊ ድህረ ገፆች ላይ አይቼ አመለከትኩኝ ማለት ትችላላችሁ፡፡
3፡ ስለመስሪያ ቤታችን ምንተውቃለህ?
ይህ ጥያቄ ለጠያቂው የሚሰጠው ትልቅ መልዕክት አለ ፡ በተቻለ መጠን ወዳመለከታችሁበት መስሪያቤት ከመሄዳችሁ በፊት ስለ መስሪያቤቱ በቂ ግንዛቤ ሊኖራችሁ ይገባል ፡ ተልዕኮውን, አላማውን, ራዕዩን በግልፅ ልትረዱ ይገባል
እናንተም በዚሁ መስሪያቤት ተልዕኮ አላማና ራዕይ ውስጥ
ልታበረክቱ ስለምትችሉት ነገር በአጭሩ ተናገሩ፡፡
ያመለከታችሁበት መስሪያ ቤት ድህረገጽ ካለው About
የሚለውን በመጫን መረጃውን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
አልያም በአንዳንዶቹ ዘንድ ገና ወደ ግቢያቸው ስትገቡ ተገቢውን
መረጃ በሆነ ቦርድ ወይም በአንዳች ነገር በግልፅ ተፅፎ ታገኙታላችሁ፡፡
ለዚህ ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ መስጠት ለስራው የሰጣችሁትን ትኩረት ያሳያል፡፡
4፡ ለምን እዚህ መቀጠር ፈለክ ?
ብዙውን ግዜ ቀጣሪዎች በቅጥር ወቅት ሊቀጥሩ የሚፈልጉት በተቻለ መጠን ልህቀቱ ጥሩ የሆነውን ሰው ነው እናም ለሚጠየቀው ጥያቄ አሳማኝ መልስ መስጠት አንዱ ማሳያ
ነው፡
★የእናንተ መስሪያ ቤት ትኩረት አድርጎ በሚሰራባቸው ዘርፎች ላይ ብሳተፍ ትልቅ አስተዋፅኦ እንደማበረክት ስላመንኩኝ፡፡
★ መስሪያ ቤቱ ትልቅ እና መልካም እንቅስቃሴዎችን እያስመዘገበ በመሆኑ እኔም የዚህ አካል መሆንን ስለምፈልግ፡፡
★ ያመለከታችሁበት መስሪያ ቤት የሚሰጠውን አገልግሎት በመለየት እንደዚያ አይነት ግልጋሎት የሚሰጡ ቦታዎች ላይ መሆን በህይወታችሁም ላይ እንዲሁም ለህሊነሠችሁ የሚሰጠውን እርካታ ተናገሩ፡፡
5, ለምን አንተን እንቀጥርሀለን?
እንዲህ የሚል ጥያቄ ከተጠየቃችሁ አልፈለጉኝም ማለት
ነው ብላችሁ እንዳትደነግጡ ይልቁን ደስ ሊላችሁ ይገባል ምክንያቱም በጠያቂው ዘንድ ጥሩ ቦታን አግኝታችኋል ማለት ነው ፡ እናም በዚህ ወቅት
★ እናንተን በመቅጠራቸው በመስሪያ ቤቱ ጉዞ ላይ የእናንተን አቅም በመጨመር ተገቢውን አገልግሎት እንደምትሰጡ፡፡
★ በቡድን እንቅስቃሴ ውስጥ የቡድኑን አንድነት በማጠናከር ለመስሪያቤቱ እድገት ጉልህ አስተዋጽኦ እንደምታበረክቱ
ተናገሩ፡፡
እንዲሁም መሰል ምላሾችን አክሉበት
6፡ በሙያህ ጠንካራ ጎኖች አሉኝ ብለህ የምታምናቸው ነገሮች ምንድን ናቸው?
★ ያሉህን እውነተኛ ጥንካሬዎች ተናገር ፡ እንዲኖርህ የምትፈልገውን ሳይሆን ያለህን ነገር፡፡
★ ከምትወዳደርበት የስራ መደብ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን
ሙያዊ ጥንካሬዎችን አስቀድም፡፡
7፡ ድክመቶችህ ምን ምን ናቸው?
ሀለሉም ሰው ድክመቶች ቢኖሩበትም ቅሉ በስራ ቃለ
መጠይቅ ወቅት እኒህ እኒህ ድክመቶች አሉብኝ ብሎ መናገር አይመከርም ይልቁን የሚታይ ድክመት አለብኝ ብዬ አላምንም ለዚህም ማስረጃ የሚሆነኝ እኔ ባለብኝ ድክመት ምክንያት ነገሮች
ተበላሽተውበኝ አለማወቃቸው አንዱ ማሳያዬ ነው ብሎ መመለስ ተገቢ ይሆናል፡፡
8፡ በሙያህ ያስመዘገብከው ስኬት ምንድነው?
አሁን ልትቀጠርበት ባለው የሙያ ዘርፍ ቀደም ብለህ ያስመዘገብከውን ውጤት ተናገር ፡ የሰራኸውን ነገር መናገር ጉራ አይደለምና ዘና ብለህ ስላበረከትከው ነገር አውራ ፡
ጀማሪ ተቀጣሪም ከሆነክ መመረቂያህ ተግባራዊ ተደርጎ ተሰርቶ ከሆነ እሱን ጥቀስ፡፡
9፡ ቀደም ብሎ በነበረህ የስራ ወቅት የገጠመህ ግጭት ወይም አለመግባባት ነበር ወይ? ከገጠመህስ እንዴት ፈታኸው?
አስተውል ጠያቂህ ይህን ጥያቄ የጠየቀህ ስለአንተ ጀብድ ወይም ሌላ ለመስማት ሳይሆን፡ ለችግሮች ምላሽ የምትሰጥበትን መንገድ ለማወቅ ነው ፡ እናም ጉዳዩ ገጥሞህ ከሆነ የፈታህበትን መንገድ ጥበብ በተሞላበት መልኩ መልስ፡፡
10: ከአምስት አመት በኃላ እደርስበታለሁ ብለህ የምታስበው ራዕይ ምንድነው? የምር ራዕያችሁ የሆነውን ነገር መናገር ተገቢ ነው ፡ ልትደርሱበት የምትፈልጉበትን ቦታ ግልፅ መሆኑን ሊለካ እና ሊደረስበት የሚችል ነገር ተናገሩ ፡ በዛው መስሪያ ቤት እስከ መጪዎቹ አምስት አመታት የመቆየት ሀሳብ ካላችሁ በዛ
መስሪያቤት የት ቦታመድረስ እንደምትፈልጉ ጭምር ተናገሩ፡
ይህም ከእነርሱ ጋር የረጅም ጊዜ እቅድን አንግባችሁ እንደመጣችሁ እንዲረዱ ያደርጋቸዋል፡ እናም ከሌሎች ተወዳዳሪዎች በተሻለ ትኩረት እንድትስቡ ያደርጋችኃል
ማለት ነው፡፡
እንግዲህ እነኚህንና የመሳሰሉትን ነገሮች ተግባራዊ ማድረግ በቃለመጠይቅ ወቅት የተሻለ ማንነት እንድትላበሱ ያደርጋችኃል ብለን እናስባለን፡፡
ክፍል ሁለት እንሆ!!
11; ለምን አሁን ያለህበትን ስራ ትለቃለህ? አስተውሉ ለዚህ ጥያቄ በምትመልሱት መልስ ለቀጣሪዎቻችሁ ከአንድ በላይ ትርጓሜን ያሰጣል በመጀመሪያ ደረጃ ቀድሞ ስትሰሩበት የነበረውን መስሪያ ቤት መጥፎነት ለመናገር አትድፈሩ ይልቁን አዲስ ነገር ለማወቅ ፍላጎት እንዳላችሁ ፣ አሁን እየተወዳደራችሁ እንዳላችሁበት አይነት የስራ ዘርፍ ላይ መስራት ህልማችሁ እንደሆነ ፣ ለምሳሌ፦ ያመለከታችሁበት መስሪያ ቤት ለህዝብ አገልገሎት መስጠት ከሆነ ፡ እናንተ በቀጥታ ከህብረተሰቡ ጋር የሚያገናኙ ስራዎች ላይ መስራት እንደምትፈልጉ ይሁን እንጂ ቀድሞ የነበራችሁበት እንዲህ አይነቱን አገለግሎት እንደማይሰጥ ፡ ከዚህም መነሾነት የቀደመውን ስራችሁን ለመተው እንደወሰናችሁ ተናገሩ፡፡
12 ፦ ምን አይነት የስራ አካባቢ ያስደስትሀል / የስራ መንፈስ / Work environment ?
በዚህ መስሪያ ቤት ከማመልከታችሁ በፊት በዛ ቦታ
ስላለው የስራ መንፈስ በቂ ጥናት እንዳደረጋችሁና እንደተማረካችሁበት በመጥቀስ አሁን እያመለከታችሁ እንዳላችሁበት አይነት የስራ መንፈስን እንደምትመርጡ መናገር ትችላላችሁ፡፡
13 ፦ ምን አይነት የአመራር ስልትን ትከተላለህ?
ምናልባት አሁን እያመለከታችሁ ያላችሁበት የስራ መደብ
የአመራርነት ላይሆን ይችላል ነገር ግን ቀጣሪዎቻችሁ ይህን
ጥያቄ የሚጠይቋችሁ ከእነርሱ ጋር በምትዘልቁበት ወቅት
ምናልባት በአመራርነት የመስራታችሁ እድል ስላለ ምን
አይነት መሪ እንደሆናቸህ ቀድመው የሚለኩበት ነው፡ ጥሩ መሪ ጠንካራ እና ከነገሮች ጋር ተጣጣፊ መሆን የሚችል ፣ በቡድን ስራ
የሚያምን እና የገዢነት ሳይሆን የመሪነት ስሜት የሚሰማው
አይነት ነው፡፡ እናንተም በእንዲህ አይነት የመሪነት ዘርፍ ውስጥ የምትመደቡ መሆኑን ግለፁ፡፡
ይቀጥላል ......

Address

Cherchil
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 08:30 - 17:00
Tuesday 08:30 - 17:00
Wednesday 08:30 - 17:00
Thursday 08:30 - 17:00
Friday 08:30 - 17:00
Saturday 08:30 - 17:00

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when BM Engineering Academy posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to BM Engineering Academy:

Share