Domain Engineering P.L.C

Domain Engineering P.L.C Engineering Ltd

17/12/2025

👉 ቅደመ ክፍያ
➡ ADVANCE PAYMENT

በልዩ ሁኔታ ለፕሮጀክቱ የተዘጋጀው የኮንትራት ውል ቅድሚያ ክፍያ/advance payment/ የሚፈቅድ ከሆነ ስራ ተቌራጩ ስራ ማስኬጃ ማሽነሪና የግንባታ ግብአት ለማስገባት በሚጠየቅ ግዜ የሚከፈል ክፍያ ሲሆን ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ቅድመ ሁኔታዎች መሟላት ይኖርባቸዋል።

1. ክፍያው ስራ ተቋራጩን የስራ ውሉን ተፈፃሚ የሚያደርግበት የጠቅላላ ግምት ነው።

2) በልዩ ሁኔታ የተዘጋጀ የኮንትራት ውል (Special contract) የቅድመክፍያውን መጠን መግለፅ ሲኖርበት ነገር ግን ከጠቅላላ ፕሮጀክት ወጪ 30% መብለጥ የለበትም።

3) ውል ተፈፅሞ ሳይት ርክክብ ሳይደረግ ቅድመክፍያ አይኖርም

4) ስራ ተቋራጩ ለሚወስደው ክፍያ ዋስትና ቦንድ ያቀርባል።

➡ Advance Security and Performance Security.

1. Advance security

ስራ ተቋራጩ ለሚወስደው የቅድም ክፍያ ገንዘብ በሚከፈለው የገንዘብ መጠን ልክ የሚያሲዘው የባንክ ዋስትና ቦንድ ነው።
እውነተኛነቱ በተረጋገጠ ቼክ፣ ያልተገደበ የባንክ ዋስትና ወይም ከህጋዊ ጥቃቅን ማይክሮ ፋይናንስ የተፃፈ የዋስትና ደብዳቤ ማስያዝ ይኖርበታል።

ስራ ተቋራጩ የወሰደውን ቅድመ ክፍያ ከፍሎ እስኪጨርስ ያስያዘው ዋስትና ግዜው ማለቅ(Expire) አይችልም።
ከአንድ ወር ቀደም ብሎ የዋስትና ቀነ ገደቡ ከማለፉ በፊት ከአማካሪ በሚፃፍለት ደብዳቤ መሰረት ሊታደስ ይገባል።
ነገር ግን ስራ ተቋራጩ ያስያዘውን ዋስትና ቀነ ገደቡ አልፎ ሳያሳድስ ቢቀር ቀሪ ያልተከፈለ ቅድመ ክፍያ ሙሉ ለሙሉ
ከሚቀጥለው ክፍያ ቅፅ ላይ ተቀናሽ ይደረጋል።

ስራ ተቋራጩ ያስያዘውን ዋስትና ቅድመ ክፍያ ገንዘብ ከፍሎ እንደጨረሰ ተመላሽ ይደረግለታል።
የተለየ የቅድመ ክፍያ እና የዋስትና አከፋፈል አካሔድ ለፕሮጀክቱ የተዘጋጀው ውል/special contract/ ይችላል።

2. Performance Security

ስራ ተቋራጩ ውል ተቀብሎ ተፈፃሚ ማድረግ የሚችልበትን ለብቃት ማረጋገጫ የሚያስዘው ዋስትና ነው።
ውል በተፈራረመ በአስራ አምስት ቀናት ውስጥ (15) ውሉ የሚያዘውን መጠን ዋስትና ያቀርባል ።
ዋስትናው ስራ ተቋራጩ በተገቢው መንገድ ውሉን ተፈፃሚ ሳያደርግ ቢቀር ለውል ሰጪ (ባለቤት) እንደ ካሳ ክፍያ ይሆናል።
እውነተኛነቱ በተረጋገጠ ቼክ፣ የባንክ ዋስትና ወይም ከህጋዊ ጥቃቅን ማይክሮ ፋይናንስ የተፃፈ የዋስትና ደብዳቤ ውሉ ላይ በተቀመጠው ፎርማት መሰረት ማስያዝ ይኖርበታል። ይህ ዋስትና ሳይቀርብ ምንም ክፍያ ተፈፃሚ ሊደረግ አይገባም
ስራው ተጠናቆ እስኪያልቅ ድረስ።

⚡መያዥያ ገንዘብ (Retention money)

ይህ ስራ ተቋራጩ የተሰጠውን ስራ ጨርሶ የስህተት ማስተካከያ ግዜ ድረስ ሀላፊነት ለመወጣቱ ማረጋገጫ እንዲሆን ከያንዳንዱ የክፍያ ቅፅ የሚያዝ ገንዘብ ነው። ከክፍያ ቅፅ ምን ያህል ገንዘብ ሊቆረጥበት እንደሚገባ ለፕሮጀክቱ በልዪ ሁኔታ የተዘጋጀው ውል በግልፅ ሊያስቀምጥ ይገባል። ሆኖም ግን ከ 10% መብለጥ አይችልም። በሀገራችን ብዙ ግዜ 5% ብቻ የተለመደ ነው።

ስራው እንደተጠናቀቀ ግማሹ ከመጨረሻ ክፍያ ጋር፡ ቀሪው ደግሞ ከርክክብ በኋላ ስህተት ቢገኝ የማስተካከያ ቀነ ገደብ ተሰጥቶ በ45 ቀናት ውስጥ ይለቀቅለታል።

🚩ለጓደኞቻችሁና ወዳጆቻችሁ እንዲዳረስ
ፖስቶቹን SHARE ማድረግ አይዘንጉ።
👆👆👆

Huge \Big\ Stage Principle
06/12/2020

Huge \Big\ Stage Principle

Address

Mickey Leland Street, Bole Atlas
Addis Ababa
P.O.BOX14680CODE1000

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00
Saturday 09:00 - 17:00

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Domain Engineering P.L.C posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share