Ethiopian Chamber of Commerce & Sectoral Associations

Ethiopian Chamber of Commerce & Sectoral Associations It is an apex body of the chamber system in Ethiopia. ECCSA has been reorganized in line with the proclamation No. 341/2003.

The Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations (ECCSA) is an autonomous, non-for-profit, private sector institution and membership based organization. Accordingly, it has eighteen members including nine Regional Chambers of Commerce and Sectoral Associations, Two City Chambers of Commerce and Sectoral Associations, one National Chamber of Sectoral Associations and six Sectoral Associations organized at national level

The Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations (ECCSA), in collaboration with IGAD and ECA, is planning to ...
28/08/2026

The Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations (ECCSA), in collaboration with IGAD and ECA, is planning to facilitate a capacity-building training on AfCFTA trade rules, with priority given to businesses already exporting under AfCFTA or interested in exporting under AfCFTA.

To help us prepare the training effectively, please complete the survey using the link below.
Note: Businesses that complete the survey will be given priority for the training support.
For more information, please contact

+251 911 810 741.

https://docs.google.com/forms/u/1/d/e/1FAIpQLSflrR5Xh66EgY8iSYLWfBwalphjB3U9Tn4ep_uwz4yuoS_QsA/viewform

❇️❇️❇️❇️
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት
ስልክ፡ +251115514005
ፋክስ፡ + 251115517699
P. O. Box 517,
ኢ.ሜይል: [email protected]
ድረ ገጽ: www.ethiopianchamber.com
ቴሌግራም t.me/ethiopiachamber
X- https://x.com/EthiopiaChamber
ፌስ ቡክ፡ https://www.facebook.com/EthiopianChamber
Youtube:https://www.youtube.com/
Linkedin(ሊንክዲን):https://www.linkedin.com/company/ethiopianchamber/in

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት (ECCSA) ከምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ-መንግሥታት ባለሥልጣን (IGAD) ልዑካን ከተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን (ECA) ...
27/08/2026

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት (ECCSA) ከምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ-መንግሥታት ባለሥልጣን (IGAD) ልዑካን ከተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን (ECA) ቡድን እንዲሁም ከኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኃላፊዎች ጋር በአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነት (AfCFTA) ውጤታማነት ዙሪያ ተወያዩ።

የስምምነቱን አፈጻጸም ውጤታማ ለማድረግ ሊወሰዱ በሚገቡ ተግባራዊ እርምጃዎች እንዲሁም በAfCFTA ማዕቀፍ ሥር ንግድ ለሚያካሂዱ ድርጅቶች የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን ማቃለል በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ተወያይተዋል።

የAfCFTA Enterprise Champions ወይም በስምምነቱ ማዕቀፍ ውስጥ አርአያ የሚሆኑ የንግድ ድርጅቶችን አቅም በመጠቀምና በማጎልበት የስምምነቱን ተጠቃሚነት ማሳደግ፣ አቅም ማጠናከር እንዲሁም በIGAD ቀጣና ውስጥ ድርጅቶች የሚያጋጥሟቸውን የሎጂስቲክስ፣ የክፍያ ስርዐት እና መሠል ችግሮችን በመቅረፍ ተጠቃሚነትን ማሳደግ እንደሚገባ ተነስቷል።

በAfCFTA ማዕቀፍ ሥር የንግድ ሥራቸውን ለማካሄድና ለማስፋፋት ለተመረጡ የንግድ ድርጅቶች የቴክኒክ ድጋፍ ስለሚደረግበት ሁኔታ እንዲሁም ይህ የቴክኒክ ድጋፍ ድርጅቶች በስምምነቱ የተፈጠሩ የገበያ እድሎችን በተሻለ ሁኔታ እንዲጠቀሙ የሚያስችላቸው መሆኑ ተገልጿል።

የAfCFTA ስምምነት ውጤታማ እንዲሆን የቀጣናው ሀገራት ተቋማት፣ የመንግሥት አካላት፣ የልማት አጋሮችና የግሉ ዘርፍ በቅንጅት መሥራታቸው ወሳኝ መሆኑ ተጠቁሟል።

እንደ ሱዳን ያሉ ሥምምነቱን ያልፈረሙ ሀገራት ባሉበት የምሥራቅ አፍሪካ የኢትዮጵያንና የቀጣናውን የንግድ ተሳትፎ ለማጠናከር የተቀናጀ ትብብር አስፈላጊ ስለመሆኑ ነው በውይይቱ የተነሳው።
❇️❇️❇️❇️❇️
The Chamber of Commerce and Sectoral Associations (ECCSA) held discussion with an Inter Governmental Authority on Development (IGAD) delegation and a team from the United Nations Economic Commission for Africa (ECA) on ways to ensure the effective and efficient implementation of the African Continental Free Trade Area (AfCFTA) Agreement.

The discussion focused on practical measures to strengthen the implementation of the Agreement and address the challenges faced by businesses trading under the AfCFTA framework.

Participants exchanged views on improving the business environment and creating better opportunities for the private sector to benefit from Africa's expanding continental market.

Particular attention was given to leveraging AfCFTA Enterprise Champions and strengthening customs capacity to address firm-level constraints and awareness barriers that continue to affect the uptake of AfCFTA opportunities across the IGAD region.

The officials also discussed the importance of providing targeted technical assistance to champion companies to enhance their capacity to undertake and expand trade operations under the AfCFTA framework.

Such support is expected to help businesses better understand and utilize the opportunities created by the Agreement.

The meeting further emphasized the importance of continued collaboration among regional institutions, government bodies, development partners, and the private sector to overcome implementation challenges and ensure that businesses can effectively participate in intra-African trade.

Officials from Ethiopia's Ministry of Foreign Affairs also participated in the discussion, highlighting the importance of coordinated efforts in advancing Ethiopia's and the wider region's engagement in the African Continental Free Trade Area.

❇️❇️❇️❇️
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት
ስልክ፡ +251115514005
ፋክስ፡ + 251115517699
P. O. Box 517,
ኢ.ሜይል: [email protected]
ድረ ገጽ: www.ethiopianchamber.com
ቴሌግራም t.me/ethiopiachamber
X- https://x.com/EthiopiaChamber
ፌስ ቡክ፡ https://www.facebook.com/EthiopianChamber
Youtube:https://www.youtube.com/
Linkedin(ሊንክዲን):https://www.linkedin.com/company/ethiopianchamber/in

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት በህገ ወጥ ንግድ መከላከል (Anti-Illicit Trade) ዙሪያ ከግሉ ዘርፍ ተወካዮች ጋር የምክክር መድረክ (Consultative Meetin...
27/08/2026

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት በህገ ወጥ ንግድ መከላከል (Anti-Illicit Trade) ዙሪያ ከግሉ ዘርፍ ተወካዮች ጋር የምክክር መድረክ (Consultative Meeting) አካሂዷል።

በውይይቱ የቁም እንስሳት፣ የቡና ላኪዎችን ጨምሮ የተለያዩ የዘርፍ ማኀበራትና የንግድ ተቋማት ተወካዮች ተገኝተዋል።

የምክር ቤቱ ዋና ጸሐፊ ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት ህገ ወጥ ንግድ ለሀገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት ከዋነኞቹ ማነቆዎች አንዱ በመሆኑ፣ ችግሩን ለመከላከል የግሉ ዘርፍና መንግሥት በቅንጅት መሥራት ይገባቸዋል።

ዶ/ር ቀነኒሳ አክለውም ህገ ወጥ ንግድን በተሳካ ሁኔታ ለመዋጋት የግሉ ዘርፍ ተሳትፎ የማይተካ መሆኑን ጠቁመው፣ ተቋማት፣ የዘርፍ ማኀበራትና ህጋዊ ነጋዴዎች በጋራ በመሥራት የችግሩን ምንጮች ለመለየትና ዘላቂ መፍትሔ ለማምጣት ሚናቸውን ማጠናከር እንዳለባቸው ገልጸዋል።

በምክክሩ ህገ ወጥ ንግድ በማህበረሰብ ጤና፣ በህጋዊ ንግድ ሥርዓት፣ ከምርቶች ጥራት ጋር በተያያዘ እና በሌሎች ዘርፎች ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተጽዕኖ እንደሚያሳድርም ተጠቁሟል።

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት በጉዳዩ ዙሪ የመንግሥትና የግሉን ዘርፍ አካላት ያሳተፉ የጸረ-ህገ ወጥ ንግድ ጉባኤዎች (Anti-Illicit Trade Summits) ለአራት ተከታታይ ዓመታት አካሂዷል።

እነዚህ ጉባኤዎች በችግሩ ላይ ግንዛቤ በመፍጠርና የጋራ መፍትሔዎችን ለማፈላለግ ጠቃሚ ውጤት ማስገኘታቸውም ተገልጿል።

በቀጣይም 5ኛውን የጸረ-ህገ ወጥ ንግድ ጉባኤ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል።

ምክር ቤቱ ከግሉ ዘርፍ ተወካዮች ጋር ብቻ ሳይሆን፣ ከሚመለከታቸው የመንግሥት ተቋማት ጋርም ተከታታይ ምክክሮችን በማካሄድ ህገ ወጥ ንግድን ለመከላከል የተቀናጀ አሠራር ለመፍጠር እየሠራ መሆኑ ተገልጿል።

በመድኃኒትና ፋርማሲዩቲካል፣ በማዕድን፣ በቡና፣ በአልባሳትና ጨርቃጨርቅ፣ በቁም እንስሳት፣ በትምባሆ እንዲሁም በሌሎች ዘርፎች የሚካሄዱ ህገ ወጥ የንግድ እንቅስቃሴዎች የሀገሪቱን ገቢ የሚያሳጡ፣ ህጋዊ ነጋዴዎችን ለኪሳራ የሚዳርጉና የገበያ ፍትሃዊነትን የሚያውኩ በመሆናቸው፣ ሁሉም የሚመለከታቸው አካላት በትብብር መሥራታቸው ወሳኝ መሆኑ በውይይቱ ተነስቷል።
❇️❇️❇️❇️
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት
ስልክ፡ +251115514005
ፋክስ፡ + 251115517699
P. O. Box 517,
ኢ.ሜይል: [email protected]
ድረ ገጽ: www.ethiopianchamber.com
ቴሌግራም t.me/ethiopiachamber
X- https://x.com/EthiopiaChamber
ፌስ ቡክ፡ https://www.facebook.com/EthiopianChamber
Youtube:https://www.youtube.com/
Linkedin(ሊንክዲን):https://www.linkedin.com/company/ethiopianchamber/in

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ለተለያዩ የቢዝነስ ተቋማት በአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ስምምነት ዙሪያ ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቋል።በስልጠናው ከተለያዩ ተቋማት የተውጣጡ ባ...
26/08/2026

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ለተለያዩ የቢዝነስ ተቋማት በአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ስምምነት ዙሪያ ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቋል።በስልጠናው ከተለያዩ ተቋማት የተውጣጡ ባለሙያዎች፣ አስመጪዎችና ላኪዎች ተሳትፈዋል።

በማጠቃለያው ላይ የምክር ቤቱ ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ዓይናለም አባይነህ፣ የንግዱ ማኅበረሰብ ከAfCFTA ባሻገር ኢትዮጵያ የዓለም የንግድ ድርጅት (WTO) አባል ለመሆን በሂደት ላይ መሆኗን በመገንዘብ፣ በአፍሪካና በዓለም ገበያ ተወዳዳሪና ተጠቃሚ ለመሆን ከወዲሁ መዘጋጀትና አቅሙን ማሳደግ እንዳለበት አስገንዝበዋል።

የምክር ቤቱ ምክትል ዋና ጸሐፊ ወይዘሮ ሔለን ረታ በበኩላቸው፣ የኢትዮጵያ ነጋዴዎችና አምራቾች በአፍሪካ ገበያ ያላቸውን ተጠቃሚነት ለማሳደግ የAfCFTA አሠራርን በአግባቡ መረዳታቸው ወሳኝ መሆኑን፣ ሥልጠናውም ይህንን አቅም ለመፍጠር ጉልህ ሚና እንዳለው ጠቁመዋል።

❇️❇️❇️❇️
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት
ስልክ፡ +251115514005
ፋክስ፡ + 251115517699
P. O. Box 517,
ኢ.ሜይል: [email protected]
ድረ ገጽ: www.ethiopianchamber.com
ቴሌግራም t.me/ethiopiachamber
X- https://x.com/EthiopiaChamber
ፌስ ቡክ፡ https://www.facebook.com/EthiopianChamber
Youtube:https://www.youtube.com/
Linkedin(ሊንክዲን):https://www.linkedin.com/company/ethiopianchamber/in

እንኳን ለ1501ኛው የነቢዩ መሐመድ (ሰዐወ) የመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የአንድነትና የመቻቻል እሴቶቻችንን በበለጠ የምናድስበት እንዲሁም መልካም ተግባሮቻችን...
24/08/2026

እንኳን ለ1501ኛው የነቢዩ መሐመድ (ሰዐወ) የመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የአንድነትና የመቻቻል እሴቶቻችንን በበለጠ የምናድስበት እንዲሁም መልካም ተግባሮቻችንን የምናጠናክርበት ነው።

በመሆኑም ለመላው ሙስሊም የንግዱ ማኅበረሰብ እና ሕዝብ በዓሉ የሰላም፣ የጤና፣ የደስታና የበረከት እንዲሆን ከልብ እመኛለሁ።

ሰላም፦ የልማትና የእድገት መሠረት ነው። ስለሆነም የመውሊድ በዓል የሚያስተምረንን መቻቻል፣ መረዳዳትና አብሮነት በተግባር በማጠናከር፣ ለሰላማዊ እና ለለማች ኢትዮጵያ የየራሳችንን አስተዋጽኦ እንድናበረክት በዚሁ አጋጣሚ ጥሪዬን አቀርባለሁ።

መልካም የመውሊድ በዓል!

ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት

❇️❇️❇️❇️
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት
ስልክ፡ +251115514005
ፋክስ፡ + 251115517699
P. O. Box 517,
ኢ.ሜይል: [email protected]
ድረ ገጽ: www.ethiopianchamber.com
ቴሌግራም t.me/ethiopiachamber
X- https://x.com/EthiopiaChamber
ፌስ ቡክ፡ https://www.facebook.com/EthiopianChamber
Youtube:https://www.youtube.com/
Linkedin(ሊንክዲን):https://www.linkedin.com/company/ethiopianchamber/in

ኢትዮጵያ አሸንፋለች! ከታሰበው በላይ  ተሳክተዋል ! ሀገራዊ  ምክክር ኮሚሽኑ ከ4 ዓመታት በላይ የለፋበት፣ ከ4000 ዜጎች በላይ ከዕለት ስራቸው እና ቤተሰቦቻቸው ርቀው ለ37 ቀናት የተሳተ...
22/08/2026

ኢትዮጵያ አሸንፋለች! ከታሰበው በላይ ተሳክተዋል !

ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ከ4 ዓመታት በላይ የለፋበት፣ ከ4000 ዜጎች በላይ ከዕለት ስራቸው እና ቤተሰቦቻቸው ርቀው ለ37 ቀናት የተሳተፍንበት የሀገራዊ ምክክር በኢትዮጵያ አሸናፊነት ትናንት ማታ ከምሽቱ 3 ገደማ ተጠናቋል።

ዛሬ ጠዋት ደግሞ ይፋዊ የመዝጊያ መርሃግብር ተካሂዶ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል ።

የግሉን ሴክተር በመወከል፤ የግሉን ሴክተር ችግሮች በአጃንዳ ከማስያዝ እስከ ማፀደቅ ያደረሳችሁት በየደረጃው ያላችሁ የምክር በታችን የቦርድ አመራሮች እና የንግዱ ማህበረሰብ ላደረጋችሁት የነቃ ተሳትፎ ኢትዮጵያ ሁሌም እያመሰገነቻችሁ ትኖራለች::

ከመላ ኢትዮጵያ የተሳተፋችሁ ወንድና ሴት፥ ምሁራን፥ አባቶች ፥ የሀገር ሽማግሌዎች፥ አባገዳዎች፥ ኡጋሶች፥ ወጣቶች፥ ሀደስንቄዎች፥ የሀገር ሽማግሌዎችና ሌሎች እንደ አንድ አካል ሆናችሁ በንቃት የተሳተፋችሁ ታሪክ ያስመዘገባችሁ በመሆኑ እንኳን ደስ ያላችሁ።

እያንዳንዱን ምክረ ሀሳቦችን በፍጥነት ተተግብሮ የኢትዮጵያ የብልፅግና ጉዞ ፥አካታች ኢኮኖሚ ፥ ሰላም፥ በግሉ ሴክተር የሚመራ አገራዊ ኢኮኖሚ ተረጋግጦ የምንኖርበትን ቀን ለማየት ያብቃን።

በመጨረሻም ፍትህ፣ እውነተኛ አካታችነት፣ እኩልነት ፥ሌላውን መረዳትና የሌላውን አጀንዳ እንደራስ አጀንዳ መቀበል፥ እና መደማመጥ አሸነፉ።

ኢትዮጵያ አሸነፈች!

አመሰግናለሁ

❇️❇️❇️❇️❇️❇️
Itoophiyaan injifatteetti! Kan eegame ol milkaa'eera!

Komishiniin Marii Biyyaalessaa waggoota afur oliif kan turee fi lammiileen kuma 4 ol guyyoota 37f hirmaatan, hojii guyyaa guyyaa fi maatii isaanii irraa fagaachuun, halkan edaa naannoo sa’aatii 3:00 PM irratti injifannoo Itoophiyaan xumuramera. Sirni cufiinsa har'a ganama ni gaggeeffama jedhamee eegama.

Itiyoophiyaan yeroo hunda isin, hoggantoota manneen maree, boordii fi miseensonni hawaasa daldalaa sadarkaa sadarkaan jiran, damee dhuunfaa bakka bu’uun, ajandaa kaa’uu irraa kaasee hanga rakkoo damee dhuunfaa raggaasisuutti dammaqinaan hirmaachuu keessaniif galata guddaa qabdi.

Obboleeyyan, hayyoota, abbootiin, jaarsolii, Abagedas, Ugaas, dargaggoota, Hadhesenke fi kanneen biroo guutuu Ethiopia irraa hirmaattanii dammaqinaan hirmaachuu fi seenaa hojjachuu keessaniif baga gammaddan!

Tokkoon tokkoon yaada dhihaate saffisaan hojii irra haa oolu, guyyaa imalli Itiyoophiyaa gara badhaadhina, diinagdee hunda hammate, nagaa fi dinagdee biyyaalessaa damee dhuunfaatiin hoogganamu itti mirkanaa’u haa arginu.

Dhumarratti haqni, hunda hammatee dhugaan, walqixxummaan, nama hubachuun, ajandaa nama biraa akka kan keenyaatti fudhachuun, dhaggeeffachuun ni mo’ata.

Itoophiyaan injifatte!

Galatoomaa

ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚደንት

❇️❇️❇️❇️
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት
ስልክ፡ +251115514005
ፋክስ፡ + 251115517699
P. O. Box 517,
ኢ.ሜይል: [email protected]
ድረ ገጽ: www.ethiopianchamber.com
ቴሌግራም t.me/ethiopiachamber
X- https://x.com/EthiopiaChamber
ፌስ ቡክ፡ https://www.facebook.com/EthiopianChamber
Youtube:https://www.youtube.com/
Linkedin(ሊንክዲን):https://www.linkedin.com/company/ethiopianchamber/in

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ዋና ፀሐፊ ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ የድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ፓርክንና ነፃ የንግድ ቀጣናን ጎበኙ።በአሁኑ ወቅት በኢንዱስትሪ ፓርኩ ዉስጥ በሶስት ዘርፎች  ማ...
22/08/2026

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ዋና ፀሐፊ ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ የድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ፓርክንና ነፃ የንግድ ቀጣናን ጎበኙ።
በአሁኑ ወቅት በኢንዱስትሪ ፓርኩ ዉስጥ በሶስት ዘርፎች ማለትም በፓኬጂንግ ( ቀደም ሲል ከዉጭ ሲገባ የነበረዉን የሲሚንቶ ከረጢቶችንበማምረት)፣በተሽከርካሪና ጀነሬተሮችን በመገጣጠም ላይ የተሰማሩ አምራቾች በስራ ላይ መሆናቸዉን አይተዋል። በተመሳሳይ በኢንዱስትሪ ፓርኩ ዉስጥ በተቋቋመዉ ነፃ የንግድ ቀጠና አስር የዉጭ አገራት ድርጅቶችና ሃያ ገደማ የሚሆኑ የአገር ዉስጥ የንግድ ድርጅቶች ቦታ መረከባቸዉንና አብዛኞቹ ወደ ስራ መግባታቸዉን በጉብኝቱ ወቅት ለማወቅ ተችሏል። በነፃ የንግድ ቀጣናዉ ዉስጥ ግብይቱ የሚከናወነዉ በዉጭ ምንዛሪ በመሆኑ ለመንግስት የዉጭ ምንዛሪ ማግኛ ሲሆን አስመጪዎችና አከፋፋዮችም ዕቃ ለማምጣት ወደ ዉጭ ለመሄድ ሳይገደዱ በአገር ዉስጥ ካለዉ ነፃ የንግድ ቀጣና መግዛት እንደሚችሉና LC ለመክፈትም በቀጣናዉ ዉስጥ አራት ባንኮች በመኖራቸዉና ሌሎች ባንኮችም እየገቡ በመሆናቸዉ እንዲሁም የጉሙሩክ ጉዳዮችን እዚያዉ መጨረስ እንዲቻል ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን አስጎብኝዎቹ አስረድተዋል።
በተመሳሳይ ዋና ፀሐፊዉ የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክ የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ደረቅ ወደብ እና ተርሚናልንም ጎብኝተዋል። የደረቅ ወደቡን ያስጎበኙ የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ኦፕሬሽን ማናጀር በተርሚናሉ የጉሙሩክ አገልግሎት እየተሰጠ ቢሆንም የገቢ ምርቶች ጥራትና ደህንነት ማረጋገጫ ላብራቶሪ በማዕከሉ አገልግሎት ባለመጀመሩና ናሙናዎች እየተወሰዱ ከተማ ተወስደዉ ስለሚሰሩ የተቀላጠፈ አገልግሎት እየተሰጠ አለመሆኑንና ይህም የንግዱን ማህበረሰብ ለእንግልት፣ ለምርቶች ያለአግባብ በወደቡ መቆየት ምክንያት መሆኑን ጠቁመዉ የሚመለከተዉ አካል አፋጣኝ የማሻሻያ እርምጃ እንዲወስድም ጠይቀዋል።
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ዋና ፀሐፊ ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ ሁለቱም ተቋማት ለንግዱ ማህበረሰብ ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠራቸዉንና ለአገር የኢኮኖሚ ዕድገት እያበረከቱ ያሉት አስተዋፅኦ ጉልህ መሆኑን ተናግረዋል።
በድሬዳዋ ደረቅ ወደብና ተርሚናል የምርት ጥራትና ደህንነት ማረጋገጫ ላብራቶሪ አለመቋቋሙ የጉሙሩክ ጉዳይን ጨርሰዉ ዕቃዎችን ወደ መሃል አገር ገበያ ለማድረስ መዘግየትን እንደሚፈጥሩና ዕቃዎችን ለመጫን የሚላኩ ተሽከርካሪዎችም ለረጅም ጊዜ ስለሚቆሙ ለአላስፈላጊ
ወጪ እየተዳረጉ መሆናቸዉን የንግዱ ማህበረሰብ በተደጋጋሚ የሚያነሳዉ ቅሬታ ስለሆነ መንግስ አፋጣኝ የማስተካከያ እርምጃ ሊወስድ ይገባልም ብለዋል።
❇️❇️❇️❇️
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት
ስልክ፡ +251115514005
ፋክስ፡ + 251115517699
P. O. Box 517,
ኢ.ሜይል: [email protected]
ድረ ገጽ: www.ethiopianchamber.com
ቴሌግራም t.me/ethiopiachamber
X- https://x.com/EthiopiaChamber
ፌስ ቡክ፡ https://www.facebook.com/EthiopianChamber
Youtube:https://www.youtube.com/
Linkedin(ሊንክዲን):https://www.linkedin.com/company/ethiopianchamber/in

21/08/2026
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት  ከGIZ/AU እና ከድሬዳዋ ከተማ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ጋር በመተባበር በአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ስምምነት (AfCFTA) ትግ...
21/08/2026

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ከGIZ/AU እና ከድሬዳዋ ከተማ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ጋር በመተባበር በአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ስምምነት (AfCFTA) ትግበራ ዙሪያ በድሬዳዋ ከተማ ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቋል።
የስልጠናው ዋና ዓላማም የግሉ ዘርፍ ተዋናዮች የAfCFTA ስምምነት ፕሮቶኮሎችን፣ የንግድ ሂደቶችንና የአተገባበር መስፈርቶችን በተሻለ ሁኔታ እንዲረዱ በማድረግ፣ በአፍሪካ ገበያ ተወዳዳሪና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማብቃት መሆኑን የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ዋና ፀሐፊ ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ በAfCFTA ስምምነት በመጠቀም ምርቶችን ወደ ተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት በመላክ አወንታዊ ውጤቶችን እያስመዘገበች ሲሆን፣ የአፍሪካን ሰፊ ገበያ በበለጠ ለመጠቀም የግሉን ዘርፍ አቅም ማሳደግ እንደሚገባም ዶ/ር ቀነኒሳ ጠቁመዋል።
በስልጠናዉ ላይ የተሳተፉ በድሬዳዋ ከተማ የሚገኙ ላኪዎች፣ አስመጪዎች፣ አምራቾች እና በኢንዱስትሪው ዘርፍ የተሰማሩ የግሉ ዘርፍ ተዋናዮች ስልጠናዉ ስለ አፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነቶች መሠረታዊ ሂደቶችና ሊሟሉ ስለሚገባቸው መስፈርቶች የተሻለ ግንዛቤ እንዳገኙና በቀጣይም በየሚሰማሩባቸው የንግድ ዘርፎች ላይ በትኩረት በመስራት በአፍሪካ ገበያ ያላቸውን ድርሻ ለማሳደግ እንደሚረዳቸዉ አስታዉቀዋል።
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የኢትዮጵያን የግሉ ዘርፍ በአፍሪካ ገበያ ተወዳዳሪና ተጠቃሚ ለማድረግ ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር ተከታታይ የግንዛቤ ማሳደጊያና የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን እየሠጠ ይገኛል፤ ይህም ከአበይት ተልዕኮዎቹ አንዱ ነዉ።
❇️❇️❇️❇️
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት
ስልክ፡ +251115514005
ፋክስ፡ + 251115517699
P. O. Box 517,
ኢ.ሜይል: [email protected]
ድረ ገጽ: www.ethiopianchamber.com
ቴሌግራም t.me/ethiopiachamber
X- https://x.com/EthiopiaChamber
ፌስ ቡክ፡ https://www.facebook.com/EthiopianChamber
Youtube:https://www.youtube.com/
Linkedin(ሊንክዲን):https://www.linkedin.com/company/ethiopianchamber/in

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ዋና ፀሐፊ ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች  ጋር በዩኒቨርሲቲ እና በንግድ ምክር ቤቶች መካከል ሊኖር በሚገባ ትስስር ላይ ተወ...
21/08/2026

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ዋና ፀሐፊ ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች ጋር በዩኒቨርሲቲ እና በንግድ ምክር ቤቶች መካከል ሊኖር በሚገባ ትስስር ላይ ተወያዩ።
የዩኒቨርሲቲና የንግድ ም/ቤቶች ጠንካራ ግንኙነት በግሉ ዘርፍ የሚስተዋለዉን የዕዉቀትና ክህሎት ክፍተት ለመሙላት፣ አሁን ያለዉና ወደፊት የሚኖረዉ ኢንዱስትሪ የሚፈልገዉን የሰዉ ኃይል ለማፍራት የሚያስችል ስርዐተ ትምህርት ከግሉ ዘርፍ ጋር ተነጋግሮ ለመቅረፅና ለማሻሻል፣ በተማሪዎች ዘንድ የስራ ፈጣሪነት ስሜትን ለመፍጠርና፣ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን በምርምርና በቴክኖሎጂ ሽግግር ለማገዝ፣ የግሉን ዘርፍ ችግር የሚፈቱና በተግባር ሊተረጎሙ የሚችሉ ምርምሮችን ለመስራት ምቹ መደላድልን እንደሚፈጥር ዶ/ር ቀነኒሳ አብራርተዋል።
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና የቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ተማም አወል በበኩላቸዉ ዩኒቨርሲቲዉ ከከተማ አስተዳደሩ የንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ጋር ብዙ ነገሮችን በጋራ እየሰራ ቢሆንም ትኩረቱ በኢንዱስትሪ ላይ ብቻ የተወሰነ መሆኑን ጠቅሰዉ ከዚህ በኋላ ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር ለመስራት የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት በፈጠረዉ መነቃቃት ነፃ የቢዝነስ ማማከር አገልግሎት ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ለመስጠት ቁርጠኛ መሆኑን አስረድተዋል።
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስና ቢዚነስ ኮሌጅ ዲን ረዳት ፕሮፌሰር ኢዩኤል ኢዶሳ፣ የኢንዱስትሪ ትስስር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር እሸቱ መኮንን፣ እና ሌሎች የዩኒቨርሲቲዉ አመራሮች በዉይይቱ ላይ ተሳትፈዋል።
በዉይይቱ ላይ የተገኙት በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የንግድ፣ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ የንግድ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አሚኖ ጠሃ እና በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ም/ቤት የበጀት ኢኮኖሚ፣ንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ አይናለም ተዘራ በበኩላቸዉ ዩኒቨርሲቲዉ እስካሁን ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በርካታ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን ገልፀዉ የከተማችን የግል ዘርፎች በተለይም የንግዱ ማህበረሰብ በአህጉራዊና አለም አቀፍ ገበያዎች ተወዳዳሪና ተጠቃሚ የሚሆኑበትን አቅም ከመፍጠር አንፃር ብዙ ድጋፎች ይጠበቁበታል ብለዋል።
ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ ከወይይቱ በኋላም
የዩኒቨርሲቲዉን የቴክኖሎጂ ማበልፀጊያ ማዕከል ጎብኝተዋል።
❇️❇️❇️❇️
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት
ስልክ፡ +251115514005
ፋክስ፡ + 251115517699
P. O. Box 517,
ኢ.ሜይል: [email protected]
ድረ ገጽ: www.ethiopianchamber.com
ቴሌግራም t.me/ethiopiachamber
X- https://x.com/EthiopiaChamber
ፌስ ቡክ፡ https://www.facebook.com/EthiopianChamber
Youtube:https://www.youtube.com/
Linkedin(ሊንክዲን):https://www.linkedin.com/company/ethiopianchamber/in

Address

Mexico Square
Addis Ababa
P.O.BOX517

Opening Hours

Monday 08:30 - 17:30
Tuesday 08:30 - 17:30
Wednesday 08:30 - 17:30
Thursday 08:30 - 17:30
Friday 08:30 - 17:30

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Chamber of Commerce & Sectoral Associations posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Ethiopian Chamber of Commerce & Sectoral Associations:

Shortcuts

Share