Kotebe Educational university

Kotebe Educational university የተሻለ የኮንስትራክሽን አቅርቦት ለሁሉም

26/06/2021
23/10/2020

ዶርም የቀረ እቃ| ለኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ #ሴት ተማሪዎች❗️

በኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የሆናችሁ እና እቃችሁ ዶርም ውስጥ ተቀምጦ የነበረ #ሴት ተማሪዎች ዛሬ እና ነገ ወደ ጊቢው የ ID ኮፒ በመያዝ መቅረብ እና የቀረ እቃችሁን መረከብ እንደምትችሉ አረጋግጠናል።

በመሆኑም የዩኒቨርሲቲው ሴት ተማሪዎች ዛሬ እና ነገ የመታወቂያችሁን ( ID) ኮፒ በመያዝ መቅረብ እና እቃችሁን መውሰድ ትችላላችሁ።

በዚህ ጉዳይ በቂ መረጃ ለመጠየቅ ደግሞ ይህንን ስልክ መጠቀም ትችላላችሁ 0913124570

ለሌሎቻችሁም እንዲህ እያጣራን የምናሳውቅ ይሆናል።

መረጃውን በመስጠት ለተባበሩን የኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር ሰራተኞች ላቅ ያለ ምስጋና እናቀርባለን።

ላልሰሙት በማድረግ

01/11/2019

Officials Visit Kotebe Metropolitan University's Football Team- Play at the World Universities' Football Cup
************************************
01 November 2019

Kotebe Metropolitan University's football team is to battle the World Universities' Football Game which is to be held from 18 November to 02 December 2019 in Xiamen, China. Ethiopia, represented solely by Kotebe Metropolitan University scheduled in group B of first quarter with three world universities namely from: Mexico, Thailand and China. It is noted that the team is the champion of all African Universities' football game.

During the field visit with the Commissioner of Ethiopian Sport Commission and President of Ethiopian Olympic Committee, the University President Dr. Berhanemeskel Tena gave a brief on how the University struggled with all limited resources and finally won the African Universities' Football Cup competition. He also noted that nothing shall be impossible if we are determined and united to make history in the course of all walks. He added "... it is a historic moment to Kotebe Metropolitan University to show up on the world sports stage, holding our great nation's flag. The chief coach, Dr. Wogene Waltenigus, who is a staff of KMU Sport Science Academy said, we are going to recall an amazing moment once again or face a learning environment from this first ever experience of the ultima res- in all the case we are going to play good."

Finally, Mr. Abay Belayhun, Ethiopian Universities' Sport Association president and African Universities' Sport Federation Treasurer, who is also a staff of KMU underscored that whoever is our opponent we will go through - and KMU will play it.

By Corporate Communications Directorate

17/10/2019

Announcement for Grade 9 High School Education Opportunity
****************************************************
Kotebe Metropolitan University would like to announce education opportunity for grade 9 talented students who achieved highest score in their grade 8 results. The opportunity is open on the basis of competition and qualified students will be admitted in the University's Science Shared Campus, located at 4 kilo- Minililik l. Registration is on going from Oct. 17- 20/2019 or Oct. 06-09/2012 E.C .
For more information visit the Science Shared Campus.
KMU

24/09/2019
18/09/2019

የኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርስቲ ተጠሪነቱ ለሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር እንዲሆን ተወሰነ።
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር ሲመራ የነበረው የኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርስቲ ተጠሪነቱ ለፌዴራል የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር እንዲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ጳጉሜን 2 ቀን 2011 ዓ.ም ባካሄደው 29ኛ መደበኛ ስብሰባ በሙሉ ድምፅ አጽድቋል።
በተለያዩ የትምህርት መስኮች የሚያስተምሩ መምህራንና የስፖርትና የሰውነት ማጎልመሻ ባለሙያዎችን በብቸኝነት በማፍራት ይታወቅ የነበረው የዛሬው ኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ ስራውን የጀመረው በ1951 ዓ ም በቀድሞው የቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ ዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ ነው፡፡
በኋላም የአዲስ አበባ መምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጅ በሚል ስያሜ ሜክሲኮ አካባቢ ባሁኑ ተግባረ ዕድ ግቢ በርካታ መምህራንን በማሰልጠን ለመላው ሀገሪቱ ትምህርት ቤቶቸ አበርክቷል ። በ1967 ዓ.ም አሁን ወደሚገኝበት ኮተቤ ተዛውሮ ሲሰራ ከቆየ በኋላ በ1990 ዓ.ም ተጠሪነቱ ከትምህርት ሚኒስቴር ወደ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሆኖ ለከተማው ትምህርት ቤቶች መምህራንን ሲያሰጥን ቆይቷል፡፡ ከዘጠኝ ዓመታት ቆይታ በኋላ የኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ የሚል ስያሜ ተሰጥቶት ባሁኑ ወቅት በመምህራን ስልጠናና ሌሎችም መስኮች ከ14 ሺህ በላይ ተማሪዎችን በማስተማር ላይ ይገኛል። ተቋሙ ስር ሶስት ኮሌጆች እና አራት ፋኩልቲዎች እንዲሁም 26 የትምህርት ክፍሎች አሉት።

27/06/2018
07/10/2017

የኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ በ2010 ዓ/ም የትምህርት ዘመን በተከታታይና ርቀት ትምህርት መርሃ ግብር በተለያዩ የስልጠና መስኮች ማለትም ፤ በመጀመሪያ ዲግሪ በማታ (ከሰኞ እስከ እሁድ) ወይም በሳምንት መጨረሻ (ቅዳሜና እሁድ ብቻ)፣ በዲፕሎማና በሰርቲፊኬት ማታ (ከሰኞ እስከ እሁድ) አዲስ አመልካቾችን ተቀብሎ ማሰልጠን ይፈልጋል፡፡በመሆኑም መስፈርቱን የምታሟሉ ትምህርት ፈላጊዎች ከመስከረም 19 እስከ መስከረም 28/2010 ዓ/ም ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት (ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ) ኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራርና አሉሙናይ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት በመቅረብ ማመልክት የምትችሉ መሆኑንና ዝርዝር የመግቢያ መስፈርት፣ የስልጠና መስኮችንና መረጃዎችን በውስጥ ማስታወቂያ ወይም በድህረ ገጻችን ላይ ማግኘት የሚቻል መሆኑን ያስታውቃል፡፡

የተሻለ የኮንስትራክሽን አቅርቦት ለሁሉም

23/08/2017

የምታውቁት ነገር አለ
የኮተቤ መምህራን ኮሌጅ ለአዲስ ተቀጣሪዎች ብሔርን እንደ አንድ መመዘኛ አቀረበ
BBN news August 22, 2017
የኮተቤ መምህራን ኮሌጅ አዲስ ለሚቀጥራቸው መምህራን ብሔር ወይም ዘርን እንደ አንድ መመዘኛ ማቅረቡ ታወቀ፡፡ በቀድሞ አጠራሩ ኮተቤ መምህራን ኮሌጅ አሁን ደግሞ ኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ በመባል የሚታወቀው ይኸው ተቋም፣ ካለፉት ሳምንታት ጀምሮ አንድ የቅጥር ማስታወቂያ አውጥቷል፡፡ ተቀጣሪዎች የስራ ልምዳቸውን፣ የትምህርት ደረጃቸውን እና መሰል መረጃዎቻቸውን በሚሞሉበት ፎርም ላይ፣ ዘር ወይም ብሔር የሚል ጥያቄ መቅረቡ አነጋጋሪ ሆኗል፡፡
አንድ በዩኒቨርሲቲ ደረጃ ተቋቁሚያለሁ የሚል ተቋም መምህራንን ሊቀጥር የሚችለው በአካዳሚያዊ ብቃታቸው መሆን እንዳለበት ቢታመንም፣ ዘርን እንደ መስፈርት ከጥያቄዎች አንዱ ማድረጉ ግን አስተዛዛቢ ሆኗል፡፡ ምንም እንኳን ተቋሙ ብሔርን እንደ መስፈርት ያስቀመጠው፣ የትኛውን ብሔር ለመጉዳት አልያም ለመጥቀም እንደሆነ ለጊዜው ባይታወቅም፣ ድርጊቱ ግን ፍጹም አስነዋሪ መሆኑን አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ፡፡ በቀበሌ መታወቂያ ላይ የተጀመረው የብሔር ገለጻ ጉዳይ፣ አሁን ደግሞ ራሳቸውን ዩኒቨርሲቲ እያሉ በሚጠሩ የስርዓቱ ተቋማት ውስጥም ዘልቆ መግባቱ፣ የሀገሪቱን ዕጣ ፈንታ ይበልጥ አሳሳቢ ሊያደርገው ይችላል የሚል ስጋታ ያላቸው ሰዎች አሉ፡፡
‹‹ትውልድ እቀርጻለሁ›› የሚል መርህ አለኝ ከሚል፣ ያውም በዩኒቨርሲቲ ደረጃ ከሚንቀሳቀስ ተቋም እንዲህ ያለ የወረደ ተግባር እንደማይጠበቅ ታዛቢዎች ይናገራሉ፡፡ ስራ ለመቀጠር ወደ ተቋሙ ያመሩ ሰዎችም ባጋጠማቸው ነገር በእጅጉ ማፈራቸውን አልሸሸጉም፡፡ የብሔር ጥያቄው ፎርሙ ላይ የገባበት ምክንያት ግልጽ እንዳልሆነ የሚናገሩት ታዛቢዎች፣ ህወሓት ሀገሪቱን ወዴት እየወሰዳት እንዳለ አንድ ማመልከቻ መሆኑን ግን ሳይናገሩ አላለፉም፡፡ በብሔር ላይ የተመሰረተው የህወሓት ፌደራሊዝም ፖሊሲ፣ ባለፉት 26 ዓመታት ውስጥ በርካታ ነገሮችን አመሰቃቅሏል የሚሉት ታዛቢዎቹ፣ አሁን ግን ነገሩ አፍጥጦ መምጣቱንም አክለው ገልጸዋል፡

24/12/2016

KCT ++++ KUC++++KMPU

Address

Addis Ababa

Telephone

+251912909293

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kotebe Educational university posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Kotebe Educational university:

Share