Don,t hear those who talk at your back

Don,t hear those who talk at your back Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Don,t hear those who talk at your back, Mining Company, Addis Ababa.

mandatory
09/07/2018

mandatory

★ የስልኮትን ፓተርን ረስተውት ስልኮ አልከፍት ብሎታል?
እንግዳውስ የተረሳውን ፓተርን አጥፍተን እንዴት ስልኩን እንደገና መክፈት እንዴምንችል እናያለን።
★ አንድ ማወቅ ያለባችሁ ነገር ቢኖር ግን Install ያደረግናቸው አፕሊኬሽኖች እንዲሁም የመዘገብናቸው ስልክ ቁጥሮች መጥፋታቸው የማይቀር ነው።
√√ እነዚህን ስድስት (6) ስቴፖች ይጠቀሙ።

1 Step One ~ ስልክዎትን Switch Off ያድርጉትና
ለጥቂት ሰከንዶች ይጠብቁት።

2 Step Two ~ ከዛም እነዚን ቁልፎች
ማለትም ድምፅ መጨመሪያውን(+) •Home Key •Power በተኑን በአንድ ላይ ይጫኗቸውና ስልኮትን ያስነሱት።

3 Step Three ~ ከዛም የተለያዩ ምርጫዎች ይመጡለዎታል።

4 Step Four ~ ከዛም Restore factory defults ወይም "Delete All User Data" የሚለውን ይምረጡ።

5 Step Five ~ ከዛም "Reboot System Now" የሚለውን ይምረጡ።

6 Step Six ~ ከዛም ስልኮት Reboot አድርጎ እስኪጨርስ ይጠብቁ።
★ ከዚያም ስልኮት እንዴ አዲስ ይከፈታል ማለት ነው፡፡

√ ለወዳጅ ዘመድዎ Share በማድረግ ያካፍሉ፡፡
√ ይሄን Page_Like በማድረግ የተለያዩ ጠቃሚ እና አስተማሪ የሆኑ ነገሮችን ይከታተሉ፡፡

07/07/2018

Good

02/07/2018

አትሌት መሰረት ደፋር በለንደን O 5000 ሜትርን ባሸነፈችበትና የያዘችውን ስእለ ማርያም ከፍ ባረገች ጊዜ /ር_አቡኑ_ማሞ የተግጠመ ልብ የሚነካ ቁጭ ብድግ የሚያደርግ ታላቅ ግጥም ..............."ለንደን ግሸን ሆነች"................
የሳት ትንታግ ፍንጣሪ
የድል ዜማ ወገን አኩሪ
የክብር ጥግ ማማ
የደስታ ውበት ቄጤማ
የመስቀሉን ሀይል ከግሸን የጠበሉን በረከት ዘግና
ይኸው አየዋት በለንደን የሳት ልጅ እሳት ሆና
የደም አዙሪት ምሬቱ
የሳት ትግል ሽረቱ
እየፈላባት ሀሞቷ እየታገላት ሲቃ
ታቦቷን ከራሷ ሳይሆን ከደረቷ ላይ ደብቃ
ተሻገረችው ያንን ጉድ አስለቀሰችን ነፍርቃ
ጀመረች አግዥኝ ብላ
ድንግልን በደረቷ አዝላ
ታሪክ ናት ይቺ ማርያም ለተማጸናት በብርቱ
ልጇን ላመነ በልቡ ፍቅሯን ላሰረ ባንገቱ
ረሳችውና ድካሟን የልፋት ውጤት ወርቋን
ከፍ አደረገች በስእሏ የድንግል ማርያምን ስሟን
ግሸን ሆነች አሉ ለንደን ተቀይራ
መሰረተ ህይወት ድንግል ተዘምራ
እምነት ከጉያ ውስጥ ድንገት ፈለቀና
ሀሌ ሀሌ ሆነ ድካም ተረሳና
የኛ ርግብ አማኝቷ
የኢትዮጲያ ልጅ መሰረቷ
ቢላላባት ያሰረችው ቢበጣጠስ መቀነቷ
ተወራርዳ አሸነፈች በጌታ እናት ባዛኝቷ ። ...............................መ/ር አቡኑ ማሞ (ካህን)

30/06/2018
30/06/2018
good, I accept it.
30/06/2018

good, I accept it.

ተሳፋሪዎች አውሮፕላኑ ይከስከስ አሉ ለምን?????
*****************************************
📮ባልና ሚስት ወደ ኢጣልያን እየበረሩ ሳለ የአውሮፕላኑ ካፒቴን በድምፅ ማጉያ አንድ ነገር ተናገረ
" ክብራንና ክብራት ይህን ስናገር ባጣም አዝናለው አንደኛው የአውሮፕላኑ ሞተር አይሰራም ሁለተኛውም ቆሞአል በጥቂት ደቂቃዎች የመከስከስ አደጋ ይደርስብናል ግዜው የመናዘዝና የይቅርታ ግዜ ነው ፀልዩ ንስሃ ግቡ ማስተካከል ያለባችውን ነገር አስተካክሉ " አላቸው።
📮አቶ ዳኒ የሚስቱን የኤልዛቤት እጅ ይዞ.. የኔ ማር ይቅር በይኝ በጣም ይከብዳል ታውቂያለሽ እህትሽ ሳምራዊት ከእኛ ጋር የምትኖረው አብሬያት እተኛ ነበር እሷ በጣም ልክ እንደ እንዝርት ናት ብዙ ግዜ አስወርዳለች ከጣልያን ስንመለስ አንቺን በመርዝ ገድላ ወደ አሜሪካ ሄደን አብረን እንድንኖር አቅዳለች። እባክሽ ይቅር በይኝ ሲላት...

📮ኤልሳቤት... ምንም ማለት አይደለም ይቅር ብያለው ግን እኔም የምናዘዘው ነገር አለኝ አለች .. እባክህ ይቅር በለኝ.. ሁሁሁ ካሉን ሦስት ልጆች መሃከል ሁለቱ ማለት ዮሐንስና አስቴር ያንተ ልጆች አይደሉም ያንተ ልጅ ቪክቶሪያ ብቻ ናት የቀሩት የውድ ጓደኛህ የኤርሚያስ ናቸው። የኔ ማር ታስታውሳለህ አንዴ ሌቦች አልዘረፉህም ?
👦አቶ ዳኒ... አዎ የኔ ማር አስታውሳለው።
👱ኤልሳቤዝ.. ....ሌቦች እንዲዘርፉ ያደረኩት እኔነኝ ምክኒያቱም ቦይ ፍሬንዴ አሌክስ የትምህርት ክፍያ አልነበረውም ያየተዘረፍከው ገንዘብ ለእሱ የትምህርት ክፍያ አውሏል።
ታውቃለህ ከጣልያን እንደተመለስን አንተን ለማስገደል ሰው ቀጥሬያለው ..ይቅር በለኝ
📮አቶ ዳኒ.. ምንም አይደል ይቅር ብዬሻለው አለ።

#ድንገት የአውሮፕላኑ ካፒቴን በድምፅ ማጉያው "እናንተ ልዩ ናችው ፈጣሪ ፀሎታችውን ሰምቶዋል ሁለቱም ሞተሮች በትክክል መስራት ጀምረዋል በሰላም እናርፋለን አለ።
#ሁሉም ተሳፋሪዎች ከመደሰት ይልቅ ፀጥ አሉ። አንድ ተሳፋሪ በድንገት ብድግ አለና አብራሪ ስማ አብራሪ ማረፍ የለብንም አውሮብላኑን #ከስክሰው ጣለው ጣለው ሲል ሁሉም ተሳፋሪዎች በአንድ ድምፅ
☎ ፈጥፍጠው ☎ከስክሰው ብለው ጮኹ!

ምን ተሰማችው?????? ሐጥያት አስቀያሚ ነው አይደል!

ጎበዝ እራሳችንን እንፈትሸው
አሁኑኑ ንስሀ/ተውበት ያስፈልገናል

ፓስቶች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሳችሁ
📮 📮
ያድርጉ✔

29/06/2018

realy!

28/06/2018

ሰኔ ወር ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች የተማረ የሰው ኃይል ለሕዝብ የሚያስረክቡበት ነው። በመሆኑም አብዛኞቹ ተቋማት ከዚህ ወር ጀምሮ የቅጥር ማስታወቂያ ያጎርፋሉ። ዘመኑ የውድድር መንፈስ የተጠናወተው ነውና ራስን ማዘጋጀት የብልህ ሰው መለያ ነው። በመሆኑም በብዛት የሚገኙ የ" #ቃለመጠይቅ [Interview] ጥያቄዎችንና መልሶቻቸውን በዚህ ገጽ ( ) በክፍል በክፍል እየተደረገ እስከ ጥቅምት ድረስ በተከታታይ ይቀርባል። እርስዎ የሚለውን ተጭነው የሚመለከትዎን መረጃ ብቻ ይከታተሉ።
/ Interview/
++++✍. [ክፍል አንድ]...........
#1ኛ. ራስዎን ያስተዋውቁን? (Please introduce yoursef to know who you are?)..
ይህ ጥያቄ ቀላል ይመስላል እንጂ ብዙዎች ገና ከጅምሩ ስህተት የሚሰሩበት እንደሆነ ይስተዋላል። ብዙዎች የህይወት ታሪካቸውን ያወራሉ። የጥያቄው አይን ግን በሥራ (በትምህርት) ህይወት ላይ ስለቆዩበት ማንነትዎ፣ የት/ት ደረጃዎ፣ የስራ ልምድ ካለዎት ስለልምድዎ፣ ስላስመዘገቡትና ስለሠሩባቸው ጥሩ ሥራዎች፣ ጀማሪ ተቀጣሪ ከሆኑ በዩኒቨርሲቲ ቆይታዎ ስለነበረዎት መልካም እንቅስቃሴዎች ወይም ስለሠሯቸው የመመረቂያ ጥናቶች (Research) ወይም ፕሮጀክቶች በመዘርዘር እራስዎን ቢያስተዋውቁ የተሻለ ነው። በንግግርዎ ወቅት ለጠያቂው የመጀመሪያ ምርጫው እንዲሆኑ ጠቃሚ ነገሮችዎ ላይ ትኩረት ያድርጉ። የዘር ሀረግ እየቆጠሩ፣ የትውልድ ቦታ እየከለሉ ጥያቄውን እንዳይወድቁ ይጠንቀቁ። (ለዚያውም በዚች ጎጠኛ ዓለም ላይ ተሳታፊ ሆኖ ጎጥ መቁጠር ተገቢ አይደለም።)..
#2ኛ. ስለዚህ የሥራ ማስታወቂያ እንዴት መረጃ አገኙ? (How did you got an information about this vacancy?)..
ይኸም በተደጋጋሚ ይጠየቃል። የዚህ ጥያቄ ዓላማው ድርጅቱን ምን ያክል እንደሚወዱትና እንደሚፈልጉት ለማወቅም ጭምር ነው። በመሆኑም መልስዎ "የድርጅቱን ድህረ ገጽ እከታተል ስለነበር ከድህረ ገጹ ላይ"፣ በጋዜጣ የወጣ ከሆነ "ከጋዜጣ ላይ"፣ "ከማስታወቂያ ቦርድ" በማለት በትክክል ያገኙበትን መልስ ይመልሱ። ለመልስ ውበት ብለው ያልተለቀቀበትን መረብ ከጠቀሱ ውሸታም እንደሚባሉ ይወቁ።..
#3ኛ. ስለመስሪያ ቤታችን ምን ያውቃሉ? (Have any knowhow about this organization?)..
ለቃለመጠይቅ ፈተና ከመቅረብዎ በፊት ስለ መስሪያቤቱ፦ የምስረታ ዘመን፣ ተልዕኮውን (Mission)፣ አላማውን እና ስፋቱን (scope and objective)፣ ራዕዩን (vision)፣ የምርት ውጤት (Final output) አስቀድመው ለማወቅ እና እርሰዎ ለአላማው መሳካት የሚያደርጉትነ አስተዋጽኦ ለማካተት ይሞክሩ። ይህንን መረጃ ከድኅረ ገጽ እና ከተለጠፉ ታፔላዎች ማግኘት ይችላሉ። ለዚህ ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ መስጠት ለሥራው የሰጡትን ትኩረት ያመለክታል።..
#4ኛ. ለምን እዚህ መቀጠር ፈለጉ? (Why did you want to be employee in this company?)..
ጥሩ ልህቀት የሆነውን ሰው ነውና ራስዎን ያዘጋጁ። በምንም ምክንያት "ሥራ ዕድል ስለፈጠረልኝ፣ ደመወዝተኛ ለመሆን፣ ሥራ ላለማጣት" የሚል ነገር እንዳይመልሱ።

✔. "መስሪያ ቤት በሚሠራባቸው ዘርፎች ላይ ብሳተፍ ትልቅ አስተዋፅኦ እንደማበረክት ስላመንኩኝ"

✔. "መስሪያ ቤቱ የላቀ እንቅስቃሴዎችን እያስመዘገበ በመሆኑ እኔም የዚህ አካል በመሆን ሀገሬንና መስሪያ ቤቱን ማሳደግ ስለምፈልግ፡፡"
✔. (መስሪያ ቤት የሚሰጠውን አገልግሎት በመጥቀስ) "እንደዚህ ያለ አገልግሎት የሚሰጡ ቦታዎች ላይ መሆን ታላቅ እርካታን ስለሚሰጠኝ።" ብለው ይመልሱ።..
#5ኛ. ለመስሪያ ቤቱ ምን አይነት አስተዋጽኦ አደርጋለሁ ብለው ያምናሉ (If you will employed, what role do you believe that you may pay for company?
በመስሪያ ቤቱ የሥራ ቤተሰብ ከሆንኩ፦ በቡድን እንቅስቃሴ ውስጥ የቡድኑን አንድነት በማጠናከር (Team work)፣ የአቅም ማጎልበቻ ሥልጠናዎችን በማመቻቸት (Skill building tranings)፣ የሥራ ልምድ ልውውጥ በማድረግ (Experience sharing)፣ አዳዲስ ጥናቶችን ከመደበኛ ሥራዬ ጎን ለጎን በመስራት (Researchs and projects)፣ ደንበኞችን በአክብሮትና በተገቢው ሆኔታ በማስተናገድ (Respect and legality for customers)... ለመስሪያቤቱ እድገት ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክቱ ይናገሩ፡፡..
#6ኛ. ጠንካራ ጎኖችዎ ምን ምን ድናቸው? (What are your strength)..
እውነተኛ ጥንካሬዎትን ይመስክሩ። (የሚፈልጉትን ምኞት ሳይሆን ያለዎት ነገር)። ከሚወዳደሩበት የሥራ መደብ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ሙያዊ ጥንካሬዎችዎን ቢያስቀድሙ የተሻለ ነው ፡፡


[ክፍል 2፣ 3፣ 4] ይጠብቁ። እስከዚያ የሚለውን ተጭነው ይጠብቁ። የሚጠቅምዎትን መረጃ ያንብቡ፣ የማይመችዎትና የማይመለከትዎት ካለ ደግሞ በፀባይ ይለፉ።
፡..... [Daniel Shewatatek]..... [Instructor @ Dire Dawa University]
#ምንጮች፦

✔. ተመራቂ ተማሪዎች የሥራ ማስታወቂያ የሚል የFacebook ገፅ
✔. Most Interview questions and thier concern
✔. ከተከታታይ እና ታሪካዊ እይታ አንፃር የእስከዛሬው የድርጅቶች ጥያቄ በጥቅል ተጨምቆ የቀረበ

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Don,t hear those who talk at your back posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category