Esdros Construction Trade and Industry S.C.

Esdros Construction Trade and Industry S.C. ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አክሲዮን ማኅ?

25/01/2026
የቀጠለ......በዕለቱ 500 እና ከዛ በላይ ላመጡ 41 ተማሪዎች የሜዳሊያ እና የምስክር ወረቀት ሽልማት የተሰጠ ሲሆን፣ ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ ከ1ኛ እስከ 3ኛ ለወጡ ተማሪዎች፡-1ኛ. ...
14/10/2025

የቀጠለ......

በዕለቱ 500 እና ከዛ በላይ ላመጡ 41 ተማሪዎች የሜዳሊያ እና የምስክር ወረቀት ሽልማት የተሰጠ ሲሆን፣ ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ ከ1ኛ እስከ 3ኛ ለወጡ ተማሪዎች፡-
1ኛ. ተማሪ መንግስቱ ዘላለም 580/600
2ኛ. ተማሪ አቤል ዳዊት 576/600
3ኛ. ተማሪ አፎምያ ፍቅረማሪያም 569/600
ከፍተኛ ውጤት በማምጣታቸው ለእያንዳንዳቸው መጠናቸው የተለያዩ ታብሌቶችን እና የምስክር ወረቀት ተሸልመዋል፡፡

በማስከተልም፣ ተማሪዎቻቸውን ለከፍተኛ ውጤት በማብቃት ከ1ኛ እስከ 3ኛ ለወጡ መምህራን፡-
1ኛ. የፊዚክስ መምህር ለሆኑት መምህር ሀብቴ ከበደ የገንዘብ እና የምስክር ወረቀት
2ኛ. የኬሚስትሪ መምህር ለሆኑት መምህር መረሳ ተበጀ የገንዘብ እና የምስክር ወረቀት
3ኛ. የባዮሎጂ መምህር ለሆኑት መምህር ገበያነው ነጋሽ የገንዘብ እና ምስክር ወረቀት ተሸላሚ ሆኗል፡፡

ተማሪዎቻቸውን ለከፍተኛ ውጤት ያበቁ ር/መምህርና እና ም/ር/መምህራን በዕለቱ እውቅና የተሰጣቸው ሲሆን በዚህ መሰረት፡-
1ኛ. የአዋሬ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ም/ር/መምህር አቶ ግደይ ገ/መስቀል የገንዘብ እና
የምስክር ወረቀት፣
2ኛ. የለቡ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ም/ር/መምህር አቶ ካላዩ ሃየሎም የገንዘብ እና የምስክር
ወረቀት ተሸልመዋል፡፡

በተመሳሳይ በር/መምህራን ዘርፍም ሽልማት የተሰጠ ሲሆን፡-
1ኛ. የአዋሬ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ር/መምህር አቶ ሳሙኤል ይልማ የገንዘብ እና የምስክር
ወረቀት፣
2ኛ. የለቡ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ር/መምህር አቶ ፍሬዘር ገድሉ የገንዘብ እና የምስክር
ወረቀት
3ኛ. የመሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ር/መምህር አቶ ጣሳቸው ጫኔ የገንዘብ እና የምስክር
ወረቀት ተሸላሚ ሆኗል፡፡

ቀጥሎም በ2017 ዓ.ም ሃገር አቀፍ 12ኛ ክፍል ፈተና ከፍተኛ ውጤት እንዲመዘገብ በማድረግ ከ1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃ ለወጡ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች፡-
1ኛ. የአዋሬ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የወርቅ ዋንጫ እና የምስክር ወረቀት
2ኛ. የለቡ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የብር ዋንጫ እና የምስክር ወረቀት
3ኛ. የመሪ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የነሐስ ዋንጫ እና የምስክር ወረቀት
ሽልማት ተሸላሚ ሆኗል፡፡

በማስከተልም የ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ር/መምህራን በራሳቸው ተነሳሽነት ያዘጋጁትን ስጦታ ይህ ከፍተኛ ውጤት እንዲመዘገብ ከፍተኛ ሚና ለነበራቸው የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አክሲዮን ማህበር የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል እና የትምህርት እና አይሲቲ ዘርፍ ክትትልና ድጋፍ ንዑስ ኮሚቴ አባላት ለሆኑት ለአቶ ተስፋዬ ይሁኔ እና ለአቶ የሰውዘር በላይነህ ላበረከቱት አይተኬ ድጋፋቸው የክብር እና የምስጋና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

በመጨረሻም የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አክሲዮን ማህበር የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር መሐሪ መኮንን የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት ካስተላለፉ በኋላ የዕለቱ መርሃ ግብር ተጠናቋል፡፡

ለበለጠ መረጃ፡-
በስልክ ቁጥር 0111575954/ 0973-60-00-10 በመደወል
ወይም የአክሲዮን ማኅበራችንን ድረ ገጽ https://esdros.com
በመከታተል ወቅታዊ መረጃዎችን ያግኙ::

በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችየእውቅና እና ሽልማት መርሐ-ግብር ተካሄደ*************      **************      ****...
14/10/2025

በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች
የእውቅና እና ሽልማት መርሐ-ግብር ተካሄደ
************* ************** ************

የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች በ2017 ዓ.ም ካስፈተናቸው የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች 92% በቀጥታ ወደ ከፍተኛ ትምህርት ማሳለፉን ተከትሎ ለትምህርት ቤቶች፣ ለመምህራን እና ለተማሪዎች የእውቅና እና ሽልማት መርሐ-ግብር በታላቅ ድምቀት ተካሄደ፡፡
ጥቅምት 1/2018 ዓ.ም በለቡ 2ኛ ደረጃ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤት በተካሄደው የእውቅና እና ሽልማት መርሐ-ግብር ላይ የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ ከፍተኛ ባለአክሲዮኖች፣ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት፣ የማኔጅመንት አባላት፣ የኩባንያው ሠራተኞች፣ የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች መምህራን እና ርዕሰነ መምህራን፣ ከ500 በላይ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች፣ የተማሪ ወላጆች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችም በዝግጅቱ ላይ ተገኝተዋል፡፡

በዕለቱ መርሐ-ግብር ላይ የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ ትምህርት ዘርፍ፣ አቶ ዓለሙ ወልዴ ”በ2017 ዓ.ም በ6ኛ ክፍል 98.57% እና በ8ኛ ክፍል 100% ተማሪዎችን ወደ ቀጣይ የትምህርት ክፍል የተዘዋወሩ ሲሆን በ12ኛ ክፍል የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች 92% ማሳለፍ መቻላችን ትልቅ ድል ነው፡፡” በማለት አጠቃላይ ሪፓርት ያቀረቡ ሲሆን የመክፈቻ ንግግር እንዲያቀርቡ የኩባንያውን ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አንተነህ ፈለቀን ወደ መድረክ ጋብዘዋል፡፡

የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አንተነህ ፈለቀ በበኩላቸው “ለዚህ ውጤት መመዝገብ በየደረጃው ያላችሁ የኩባንያችን ከፍተኛ የአክሲዮን፣ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት፣ በተለይም የትምህርት እና አይሲቲ ዘርፍ ክትትልና ድጋፍ የቦርድ ንዑስ ኮሚቴ አባላት፣ የማኔጅመንት አባላት፣ የመማር ማስተማሩን ስራ በታላቅ ትጋት የምትወጡ መምህራን፣ ርዕሳነ መምህራን እና የትምህርት ቤቶቻችን ማኅበረሰብ ድምር ውጤት በመሆኑ እንኳን ደስ አለን ደስ አላችሁ ማለት እፈልጋለሁ፡፡ በቀጣይም እንደዚህ ጠንክረን ከሠራን 100% ማሳለፍ እንደምንችል የ2017 ዓ.ም ትምህርት ዘመን ውጤት ማሳያ እና ትምህርት የወሰድንበት ዓመት ነው፡፡” በማለት የዝግጅቱን መጀመር በይፋ አብሥረዋል፡፡

የኩባንያው የዳሬክተሮች ቦርድ አባል እና የትምህርት እና አይሲቲ ዘርፍ ክትትልና ድጋፍ ንዑስ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ተስፋዬ ይሁኔ ባደረጉት ንግግር ”ለዚህ ዝግጅት መዘጋጀት ምክንያት የሆናችሁ ባለድል ተማሪዎቻችን እንኳን ደስ አላችሁ፡፡ እናንተ ዛሬ አንዱን ምዕራፍ ጨርሳችኋል፣ በቀጣይ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ያለው ነባራዊ ሁኔታ ላይ በመረዳትና በመገንዘብ ከትምህርት ባሻገር ሊገጥሟችሁ የሚችሉ በርካታ ጉዳዮች እንድትወጡ ምክሬ ነው፡፡” በማለት ሰፋ ያለ ሙያዊ የሆነ ተሞክሯቸውን እና በቀጣይ የዩኒቨርሲቲ ህይወታቸው የሚገጥማቸውን ተግዳሮቶች፣ ፈተናዎችን የሚያልፉበትን ጥበብ አስመልክቶ ለተማሪዎች ጠቃሚ የሆነ ምክር የለገሱ ሲሆን ሌሎች የትምህርት ባለድርሻ አካላትም የበኩላቸውን ወሳኝ ሚና እንዲወጡ በማስገንዘብ የእንኳን ደስ አላችሁና የመልካም ምኞት መግለጫ አስተላልፈዋል፡፡

ይቀጥላል.....

21/09/2025

Check out Abune Gorgorios Schools’s post.

እንኳን ደስ አላችሁ !እንኳን ደስ ያለን
17/09/2025

እንኳን ደስ አላችሁ !እንኳን ደስ ያለን

በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች የ2017 ትምህርት ዘመን ያስፈተናቸው የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ከፍተኛ ውጤት አስመዘግበዋል!!!የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች በ...
16/09/2025

በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች የ2017 ትምህርት ዘመን ያስፈተናቸው የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ከፍተኛ ውጤት አስመዘግበዋል!!!

የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች በ2017 ትምህርት ዘመን በክልል እና በአዲስ አበባ ካስፈተናቸው የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች 86% በቀጥታ በማሳለፍ በሀገሪቱ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበ ሲሆን በአዲስ አበባ ከተማ ካስፈተናቸው ተማሪዎች 90% ያህሉን በቀጥታ ያሳለፈ መሆኑን በኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ/ማ ከትምህርት ዘርፍ ለማወቅ ተችሏል፡፡
ተማሪ መንግስቱ ዘላለም በተፈጥሮ ሳይንስ ከመሪ ቅርንጫፍ 578/600፣ ተማሪ አቤል ዳዊት በተፈጥሮ ሳይንስ ከመሪ ቅርንጫፍ 574/600፣ ተማሪ አፎሚያ ፍቅረማርያም 567/600 በተፈጥሮ ሳይንስ ከለቡ ቅርንጫፍ፣ እንዲሁም ተማሪ ቢታንያ መንግስቱ በተፈጥሮ ሳይንስ ከመሪ ቅርንጫፍ 558/600 እጅግ በጣም ከፍተኛ ውጤት ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

የተማሪ አአሮን አብረሃም 554 /600፣ የተማሪ አቤል ታደለ 550/600፣ የተማሪ ነብዩ ተስፋ 546/600፣ የተማሪ ናሆም እያሱ 545/600፣ የተማሪ አቤሜሌክ ሙሉጌታ 537/600 የተማሪ ብሩክ ሰውክንዱ 526/600 እንዲሁም የተማሪ ፊናሃንስ አምደጽዮን 526/600 በጣም ከፍተኛ ውጤት ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

በአጠቃላይ የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች በቀጥታ ካሳለፋቸው 331 ተማሪዎች ውስጥ 500 እና ከ500 በላይ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ብዛት 37 መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ለዚህ ውጤት መሳካት ከፍተኛ አስተዋጽዖ ያበረከታችሁ የአቡነ ጎርጎርዮስ ርዕሳነ መምህራን፣ መምህራን፣ ወላጆች፣ የኤስድሮስ የማኔጅመንት እና የቦርድ አባላት እንኳን ደስ አላችሁ፡፡

የ2018 ዓ.ም ትምህርት መስከረም 5 በይፋ ይጀመራል*************      **************      ************በሁሉም የአቡነ ጎርጎርዮስ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች የ20...
14/09/2025

የ2018 ዓ.ም ትምህርት መስከረም 5 በይፋ ይጀመራል
************* ************** ************
በሁሉም የአቡነ ጎርጎርዮስ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች የ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ትምህርት መስከረም 05/ 2018 ዓ.ም በታላቅ ድምቀት ይጀመራል፡፡

ሰኞ መሰከረም 05/ 2018 ዓ.ም በመላው ሀገሪቱ በሚገኙት 29 ቅርንጫፍ የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ የማኔጅመንት ዓባላት፣ ወላጆች፣ ተማሪዎች፣ መምህራን፣ የአስተዳደር ሰራተኞች፣ የትምህርት ባለሙያዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በደማቅ የመክፈቻ መርሐ-ግብር እንደሚከፈት ይጠበቃል፡፡

የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ የትምህርት ዘርፍ እንዳስታወቀው በ2018 የትምህርት ዘመን ከ25 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ለማስተማር ሙሉ ዝግጅቱን ማጠናቀቁ ታውቋል፡፡
ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0111575954/0973-60-00-10 በመደወል ወይም/እና የአክሲዮን ማኅበራችንን ድረ ገጽ https://esdros.com በመከታተል ወቅታዊ መረጃዎችን ያግኙ::

የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች የምዝገባ ጊዜ ይፋ ሆነ *************      **************      ************የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች የ2018 ዓ.ም ...
16/07/2025

የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች የምዝገባ ጊዜ ይፋ ሆነ
************* ************** ************
የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች የ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ምዝገባ የሚካሄድበትን የጊዜ ሰሌዳ ይፋ አደረገ፡፡
የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ የትምህርት ዘርፍ ባወጣው የምዝገባ ሰሌዳ መሠረት የነባር ተማሪዎች (ከቅርንጫፍ ቅርንጫፍ የተዘዋወሩ ተማሪዎችን ጨምሮ)፣ የነባር ተማሪዎች ጀማሪ እህት ወንድም እና የሠራተኛ ልጆች ምዝገባ ከሐምሌ 9-15 ቀን 2017 ዓ.ም በየቅርንጫፍ ት/ቤቶች ምዝገባ የሚካሄድ ሲሆን፤ አዲስ ተማሪዎች ከጀማሪ እስከ 12ኛ ክፍል ለሚያመለክቱ የማመልከቻ ጊዜ ከሐምሌ 10-19 ቀን 2017 ዓ.ም በዋናው መ/ቤት የሚካሄድ መሆኑን አስታውቋል፡፡
ምዝገባም ወይም የማመልከቻ በቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶችና በዋና መስሪያ ቤት የማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ባስቀመጠው ዝርዝር መረጃ መሠረት ከሰኞ እስከ ዓርብ ጠዋት ከ2፡30 – 6፡30 ሰዓት፣ ከሰዓት ከ7፡30 – 11፡00 ሰዓት እና ቅዳሜ ጠዋት 2፡30 – 6፡30 የሚካሄድ በመሆኑ በተጠቀሰው የስራ ሰዓት እንዲያስመዘግቡ አስታውቋል፡፡
ለበለጠ መረጃ፡-በስልክ ቁጥር 0111575954/0973-60-00-10 በመደወል ወይም/እና የአክሲዮን ማኅበራችንን ድረ ገጽ https://esdros.com በመከታተል ወቅታዊ መረጃዎችን ያገኛሉ::

Address

+251930363779
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 02:30 - 05:30
Tuesday 02:30 - 11:30
Wednesday 02:30 - 11:30
Thursday 02:30 - 11:30
Friday 02:30 - 11:30
Saturday 02:30 - 06:30

Telephone

+251930363779

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Esdros Construction Trade and Industry S.C. posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Esdros Construction Trade and Industry S.C.:

Share