Yohamaf Construction Engineering-YCE

Yohamaf Construction Engineering-YCE Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Yohamaf Construction Engineering-YCE, Construction Company, Addis Ababa.

24/02/2021

Ready for Concrete Service Reservoir

DCI DN 300mm Pipe laying work
21/02/2021

DCI DN 300mm Pipe laying work

Construction of 1000m3 Service Reservoir
21/02/2021

Construction of 1000m3 Service Reservoir

02/03/2020

አንድ ቀን በጨረቃ ላይ እራመዳለሁ!!!(Dr. Eyob)
በሕይወታችን የሚቻለውንና የማይቻለውን የሚወስነው ማን ነው? ገደባችንስ ምንድን ነው? ካለንበት ተነስተን መድረስ ወደምንፈልግበት ቦታ ለመድረስ የሚያስፈልገን ዋነኛ እውነታ ምንድን ነው? እይታ! የአንድ ሰው አይነህሊና ሲበራ የማይቻለው ወደመቻል ይመጣል - በድንገትም ሆነ በሂደት!
ከዚህ በፊት ያልተቻለው ነገር ያልተሞከረው ነገር ነው፤ ያልተሞከረው ነገር ደግሞ በአይነ-ህሊናና በይቻላል መንፈስ ለማየት ያልደፈርነው ነገር ነው፡፡ በማየት፣ በማመን፣ በመንቀሳቀስና ሲወድቁ ተነስቶ በመቀጠል የማይቻል ይቻላል፡
ጄምስ አርዊን (James B. Irwin) እንደማንኛውም ልጅ በአማካኝ ቤት ውስጥ ያደገ ሰው ነው፡፡ በውስጡ ግን ያልተለመደ እይታ የነበረው ልጅ ነበር፡፡ በአንድ ምሽት ጄምስ ራቱን ከበላ በኋላ ሲጫወት ሳለ እናቱ፣ ሰዓቷን ካየች በኋላ፣ “መሽቷልና ወደ መኝታህ መሄድ አለብህ፣ እኔ ስራዬን ስጨርስ እመጣለሁ” ብላ ወደ ክፍሉ ላከችው፡፡ በዚያ ጨረቃዋ ደምቃ በምትታይበት ብሩህ ምሽት ጄምስ ወደክፍሉ የሚወስደውን ደረጃ ከወጣ በኋላ ክፍሉ ውስጥ ተቀመጠ፡፡
እናቱ ከአንድ ሰዓት በኋላ ልታየው ስትሄድ ጄምስ በመስኮቱ አጠገብ ተቀምጦ ብሩኋን ጨረቃ ትኩር ብሎ ሲያይ አገኘችው፡፡ በመገረም፣ “ምን እያደረግህ ነው” በማለት ጠየቀችው፡፡ “ጨረቃዋን እያየሁ ነው” አላት፡፡ “የመኝታህ ሰዓት አልፏል፣ መተኛት ነበረብህ እኮ” አለችው፡፡ በማንገራገር ወደ መኝታው እየሄደ እንዲህ አላት፣ “አንድ ቀን በጨረቃ ላይ እራመዳለሁ”፡፡
አድጎ በበረራ ስልጠና የተመረቀው ጄምስ፣ በአንድ ወቅት በልምምድ አይሮፕላኑ ላይ ከደረሰው የመከስከስ አደጋ ተርፏል፡፡ ከዚያም በተጨማሪ በተለያዩ የሕይወት ውጣ ውረዶች እንዳለፈ ይነገራል፡፡ ጄምስ አርዊን ያንን ራእይ የተሞላበትን ሃሳብ ለእናቱ ከተናገረ ከ32 ዓመታት በኋላ ጨረቃ ላይ እግራቸው ከረገጡት ሰዎች መካከል ራሱን አገኘው፡፡ የራእይ ጉልበት!!!
(“25 የስኬት ቁልፎች” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ መጽሐፍ ውስጥ የተወሰደ)፡፡

28/02/2020

የመላ-ምት ኑሮ(Dr. Eyob M.)
የምንኖርበት ዘመን ለፍርድ የሚቸኩል ትውልድ እንደጉድ የፈላበት ዘመን ነው፡፡ ሃሳብ ሰጪው ብዙ ነው፡፡ በመረጃ ብቻ ድምዳሜ ላይ የሚደርሰው ሰው ብዙ ነው፡፡
አንድ ዳኛ የአንድን ክስ መሰረታዊ መነሻ፣ እንዲሁም ግራና ቀኙን አይቶ እውነታ ጋር በመድረስ ለፍርድ ሊዘጋጅ ሲገባው ገና በሰማውና ባየው ብቻ ፍርድን ካስተላለፈ በኋላ ክስንና የግራ-ቀኝ ክርክር ልስማ ቢል እንደ እብድ ይቆጠራል፡፡ በመላ-ምት የሚኖር ሰውም እንዲሁ ነው፡፡
ጭፍንነት የተሞላበት መላ-ምት ከምክንያታዊነት ይልቅ ስሜታዊነትን፣ በአእምሮ ከመመራት ይልቅ በደመ-ነፍስ መነዳትን የሚያስቀድም ሰው አንዱ ምልክት ነው፡፡ የአንድን ሰው ተግባር ወይም የአንድን ሁኔታ ጅማሬ ገና ከማየታቸውና ከመስማታቸው ወዲያው ድምዳሜ ላይ ለመድረስ የሚቸኩሉ ሰዎች የመላ-ምት ሰዎች ናቸው፡፡ እውነታውን እስከሚያረጋግጡ ድረስ ለመቆየት ትእግስት የሌላቸው እንደዚህ አይነት ሰዎች ከአንድ ነገር መሰረት ሳይሆን ከሰሙት ታሪክ ወይም ከደረሳቸው ማስረጃ-ቢስ መረጃ በመነሳት ደምድመው የሚነሱ ሰዎች ናቸው፡፡
እውነታውን እስከሚያረጋግጡ ድረስ ለመቆየት ትእግስት የሌላቸው እንደዚህ አይነት ሰዎች ከነገር መጀመሪያው ሳይሆን ከድምዳሜው የሚነሱ ሰዎች ናቸው፡፡
የመላ-ምት ሰው ራሱ በቀውስ ውስጥ ኖሮ በዙሪያው ያሉትንም ሰዎች ቀውስ ውስጥ የሚጨምር ሰው ነው፡፡
የመላ ምት ሰው ነህ? ራስህን መዝነው
1. የሰዎችን ተግባር አይተህ ያንን ያደረጉበትን የመነሻ ሃሳብ በመገመት የመናገር ልማድ አለብህ?
2. ከሰዎቹ ሳትሰማ ስለሰዎቹ በሰማኸው ነገር ብቻ በመነዳት ስለ እነሱ አመለካከትን ትቀርጻለህ?
3. አመለካከትህና ውሳኔህ ብዙ ጊዜ በሰዎች ወሬ ተጽአኖ ስር ሲወድቅ ታገኘዋለህ?
4. ስለ አመለካከትህና ስለተገባሮችህ ሁኔታ ነገሮችን ግልጽ ከማድረግ ይልቅ ሰዎቹ ገምተው ይደርሱበታል የሚል እምነት አለህ?
5. ሰዎች ባልጠበከው ስለ አንተ ሁኔታ ሲገምቱ ስለሁኔታህ ምንም ማብራሪያ ሳታደርግ እንዲሁ፣ “እንዴት አይገነዘቡኝም” የሚል አመለካከት አለህ?
6. የነገሮችን መደጋገም አይተህ የሚቀጥለው ሁኔታ ከድግግሞሹ ውጪ የተለየ ሊሆን እንደማይችል ታስባለህ?
7. በቋንቋና በባህል ከአንተ ከሚለይ ሰው ጋር በሚገባ ካልተግባባህ ትበሳጫለህ?
8 የሰዎችን ሁኔታ ካየህ በኋላ እንዲሁ የማመን ወይም የመጠራጠር ዝንባሌ አለህ?
9. ሰዎች እንዲሁ እንዲያምኑህ ትጠባበቃለህ?
10. ሰዎች እንዲሁ ካላመኑህ ትበሳጫለህ?
ከላይ ለተጠየቁት አስር ጥያቄዎች ከግማሽ በላይ ለሆኑት “አዎ” የሚል መልስ ከሰጠህ በዚህ ምእራፍ ለተጠቀሱት ነጥቦች አስፈላጊ ትኩረት በመስጠት ለውጥን ለማስተናገድ ጥረት አድርግ፡፡

27/02/2020

የራስህ ግብ ጉዳይ!(Dr. Eyob M.)
የራስን ግብ ከሌላው ሰው ግብ ጋር ማስተያየት እንዴት ኋላ ቀርነት ነው! የዚያ ሰው እይታ፣ ፍላጎት፣ የውስጥ ግለትና ሌሎች ወሳኝ ነገሮች ከአንተ እጅግ ያነሱ ሆነው ከተገኙ በዚያ ሰው ገደብ አንተም ተገደብክ ማለት ነው፡፡
የራስን ጤንነት ከሌላው ሰው ጤንነት አንጻር መመዘን እንዴት አደገኛ ነገር ነው! አልጋው ላይ ተኝቶ ሞቱን የሚጠብቀውን ሰው አይተህ ቆመህ መሄድህን እንደ ሙሉ ጤንነት ከቆጠርከው አደገኛ አንጻራዊነት ውስጥ ነው ያለኸው (ስለዚያ ሰው የማዘንህና አንተም ስላለህበት የተሻለ ሁኔታ ያለህ ፈጣሪን አመስጋኝነት እንደተጠበቀ ሆኖ)፡፡
የራስን ደረጃ ሌላው ሰው ከደረሰበት ደረጃ አንጻር ብቻ መመዘን እንዴት ያለ ውድቀት ነው! ስኬታማና መስመር ውስጥ የገባ ሕይወት የመመዘኛችን ሁኔታ አንጻራዊ ሲሆን እጅግ አደገኛ የሆነ ጉዳይ ነው፡፡ የራሴን ደረጃ ከገባኝ ነገርና ካወጣሁት ግብ አንጻር ሳይሆን ሌላው ሰው ካለበት ሁኔታ ጋር ብቻ ካነጻጸርኩት ያለሁበትንና የምሄድበትን የማላውቅ ግራ የተጋባሁ ሰው ነኝ፡፡
ትኩረቴን የሳበው እኔ ወዳየሁትና “መድረስ አለብኝ” ወዳልኩት ከፍታ የመገስገሴ ጉዳይ መሆኑ ቀርቶ ማን ምን ደረጃ ደረሰ የሚለው ጉዳይ ከሆነ ከወዲሁ የተሸነፍኩ ሰው ነኝ፡፡
የሌላውን ሰው ልህቀት ለአንተ መነሳሳሻ እንጂ የወደፊ እምቅ ብቃትህን መመዘኛ አታድርገው፡፡
የሌላውን ሰው ኋላ ቀርነት ለአንተ መማሪያ እንጂ ባለህበት ደረጃ የመርኪያ ምክንያት አታድርገው፡፡
አቻዬ ነው ብለህ በምታስበው ሰው ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ያለህ አመለካከት ስለማንነትህ ብዙ እንደሚያወራ አትርሳ፡፡
የራስህን ራእይ፣ ዓላማ፣ ግብና ደረጃ አውጣና በዚያ ልክ ሩጥ!!!

15/01/2020

የምትገባበትና የምትወጣት በር(Dr. Eyob)
አልፎ አልፎ በትውውቅና በገጠመኝ አንዳንድ እድል በሮች የመከፈታቸው እውነታ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ በሕይወትህ የታላላቅ ስፍራዎችን በር የሚያስከፍትልህ አንድ ቀንደኛና ወሳኝ ነገር አለ፣ እርሱም በእጅህ ላይ ያለው ችሎታ፣ ተሰጥኦ ወይም የአእምሮ እውቀትህ ነው፡፡ ይህንን ሁኔታ እውቀትም በለው ችሎታ፣ ክህሎትም በለው ተሰጥኦ በሄድክበት ሁሉ የእድል በሮችን የሚያስከፍትልህ ወሳኝ ጉዳይ ነው፡፡
ሁኔታው ግን እዚያ ላይ አያቆምም፣ ችሎታህ ባስገባህ ስፍራ የመቆየትህንና ከዚያም አልፈህ የመዝለቅህን ጉዳይ የሚወስን ደግሞ አንድ ሌላ ነገር አለ፡፡ ይህ ነገር ባህሪህ ነው፡፡ ስለዚህም ችሎታህ የወሰደህና ያስገባህ ስፍራ የሚፈልገውን የማንነት ወይም የባህሪይ ጥራት በሚገባ ተገንዝበህ ለዚያ የሚመጥንን ባህሪይ ካልገነባህ በዚያ ከፍታ የሚኖርህ ቆይታ አያስተማምንም፡፡
በኖርክባት የእድሜ ዘመንህ ወደ አንድ ደረጃ በእውቀት ወይም በሌላ መንገድ ምክንያት እድሉን አግኝተው በማሕበረሰቡ መካከል ወደላይ የወጡ ሰዎችን በደንብ አጢናቸው፡፡ አንዳንዶቹ ለዚያ የሚመጥን ባህሪይ ይዘው አሁንም እያደጉ ሲኖሩ፣ ሌሎቹ ደግሞ ለደረሱበት ክብር የማይመጥንን የሕይወት ዘይቤና ባህሪይ አልለቅ በማለት ይህ የማይለወጥ ሕግ ከወጡበት ከፍታ እንዳወረዳቸው ታስተውላለህ፡፡
መሪ ሆነህና ብዙ ሰዎች እየተከተሉህ ማንም ሰው የማይከተለው ሰው የሚገልጠውን አይነት ባህሪይ መግለጥ አትችልም፡፡ ባለስልጣን ከሆንክ በኋላ አንድ “ተራ ዜጋ” እንደሚኖረው መኖር አትችልም፡፡ ባለ ትዳር ከሆንክ በኋላ ልክ ብቻውን እንዳ ሰው መኖር፣ መናገርና መውጣት መግባት አትችልም፡፡ በአጭሩ፣ ያለህበት ደረጃ የሚጠይቅብህ የባህሪይና የማንነት ከፍታ አለ፡፡
ይህንን እውነታ ለመለማመድ ምናልባት የሚከተሉትን ጥያቄዎች ራስህን መጠየቅ ትችላለህ፡፡ ላለሁበት ደረጃና ለወደፊት ዓላማዬ እንቅፋት የሆነብኝ ባህሪዬ ምንድን ነው? ለመሆንና ለማድረግ ላሰብኩት ነገር ተገቢ የሆነ ማዳበር ያለብኝ ባህሪይ ምንድን ነው? ማስወገድም ሆነ ማዳበር ለሚገባኝ ባህሪ መውሰድ ያለብኝ እርምጃ ምንድን ነው? ሊያግዘኝ የሚችል ሰው ማን ነው?
አትርሳ . . .
• ካለህበት የሕይወት ወይም የኑሮ ደረጃ ጋር አብሮ የሚሄድና የሚመጥን የባህሪይ ልህቀት ሲኖርህ ይህ ጨዋነትህ በዚያ ደረጃ እንድትቆይ ያደርግሃል፡፡
• ለወደፊት ለመድረስ ለምትፈልገው ዓላማና ደረጃ የሚመጥንን ማንነትና ማህሪይ አስቀድመህ በመለየት ያንን መለማመድና ማዳበር ስትጀመር ባለህበት ቦታ በፍጹም አትቆይም፣ በዚያ ደረጃ ላይ ያሉ ሰዎች ስለሚፈልጉህ ወደሚቀጥለው ደረጃ ትሸጋገራለህ፡፡
• ይህቺ አለም ያጠራት በባህሪይ ጥራት የላቀ ሰው እንጂ ያወቀና የተራቀቀ ሰው አይደለም፡፡
LIKE & SHARE !!!

06/01/2020

የማስገባትና የማቆየት ሕግ(Dr. Eyob Mamo)
የማይለወጠው እውነታ፡- አንድን ነገር በእጅህ ባስገባህበት መንገድ ብቻ በእጅህ ታቆየዋለህ!
ቀድሞ የአንተ ያልነበረና አሁን ግን በእጅህ ላይ ያለ ማንኛውንም ነገር ንገረኝ፡፡ ከዚያም በእንዴት አይነት ሁኔታ በእጅህ እንዳስገባኸውና የአንተ እንዳደረከው ግለጽልኝ፡፡ እኔ ደግሞ ጊዜ ሳላባክን ወደፊት ያንን ነገር በእጅህ ለማቆየት ያለህን ብቸኛ መንገድ እነግርሃለሁ፡፡
በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ ነገሮችን በእጃችን ለማስገባት እንጣጣራን፡፡ ያፈቀርነውን ሰው የእኛ ለማድረግ፣ ስራን ለማግኘት፣ ንግድን ለመጀመር፣ የተለያዩ ንብረቶችና ቁሳቁሶች ባለቤት ለመሆን፣ ስልጣንን ለመጨበጥ . . . ፍላጎታችን ዘርፈ-ብዙ ነው፡፡ ይህ ፍላጎት ሲጋጋል ደግሞ ምንም አይነት መንገድ ተጠቅመንም ቢሆን ያንን ነገር በእጃችን የማስገባታችንን ሩጫ ጥጉ ድረስ ይወስደዋል፡፡
አንድን ነገር የእኛ ለማድረግ የመፈለጋችንን ያህን፣ ያንን ለማድረግ የምንጠቀምበትን መንገድ ጉዳይ አብረን ማሰቡ አስፈላጊ ነው፡፡ ምክንያቱም ማንኛውንም ነገር በእጃችን ለማስገባት በተጠቀምንበት መንገድ ብቻ ነው ነገሩ እጃችን ከገባ በኋላ ማቆየት የምንችለው፡፡ ከጊዜያዊው ያላለፈ አይነት ሕይወት የመኖር ፍላጎት ካላደረብን በስተቀር፡፡
ሲተነተን፡- በኃይል እጃችን የገባን ነገር በእጃችን ለማቆየት ካለማቋረጥ ኃይልን መጠቀም አለብን፡፡ በማታለል እጃችን የገባን ነገር ለማቆየት ካለማቋረጥ ማታለል አለብን፡፡ በውሸት እጃችን የገባን ነገር ለማቆየት ካለማቋረጥ መዋሸት አለብን . . . እያለ እውነታው ይቀጥላል፡፡ ከተርታው ሰው እስከ አገር አመራሩ ድረስ እውነታው ፈጽሞ አይለወጥም፡፡
አንዲትን ሴት ለማግባት ካለው ፍላጎት የተነሳ የሌለውን ነገር እንዳለው የዋሸን አንድ ሰው ብናስብ፣ ተሳክቶለት ያችን ሴት ቢያገባት፣ ነኝና አለኝ ብሎ ያስተዋወቀው እንደሌለ እንዳይታወቅበት ምን አይነት ጡዘት ውስጥ እንደሚገባ ማስላት አያዳግትም፡፡ ቀድሞ ለማስታወቂያነት የተጠቀመበትን ድራማ እውን ማድረግ ሲያቅተው ግንኙነት መዛባት ይጀምራል፡፡
በስራውም መስክ ቢሆን እውነታው ይኸው ነው፡፡ የሌለንን እንዳለን፣ ያልሆንነውን ደግሞ እንደሆንን አሳይተን በውሸት በገባንበት የስራ መስክ ውስጥ ለመቆየት ምን ማድረግ እንዳለብን መገመት አያስቸግርም፡፡ ካለማቋረጥ ስንሸፋፍንና ስንዋሽ ልንኖር ነው፡፡
መፍትሄው፣ አታላይነትን፣ ምላስን፣ ዛቻን፣ ኃይልንና ስልጣንን ተጠቅመን በወጣንበት የውሸት ከፍታ ላይ ለመቆየት እድሜ ልካችንን ክንፋችንን ስናርገበግብ ከመኖር፣ ያለንንና የሆንነውን ትክክለኛውን ነገር አቅርበን በተረጋጋ ሁኔታ ውሎ ማደርና በልክ መኖር እጅግ የተመረጠ ነው፡፡
LIKE & SHARE !!!

19/12/2019

Address

Addis Ababa

Telephone

+251913267328

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Yohamaf Construction Engineering-YCE posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Yohamaf Construction Engineering-YCE:

Share