01/09/2026
የኢልኒኖ ተጽዕኖ ተቋቁሞ በአጭር ጊዜ ምርት በሚሰጡ ሰብል ዝርያዎች አ/አደሮችንና በማህበር የተደራጁ ስራ-አጥ ወጣቶችን የመደገፍ ስራ እየተሰራ ይገኛል።
ነሐሴ 25 ቀን 2018 ዓ.ም
#አረካ፤
ማዕከሉ የኢልኒኖ ተጽዕኖ ተቋቁሞ በአጭር ጊዜ ምርት በሚሰጡ ሰብል ዝርያዎች አ/አደሮችንና በማህበር የተደራጁ ስራ-አጥ ወጣቶችን የመደገፍ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ የማዕከሉ ዳይሬክተር ገነነ ገዛኸኝ(ዶ/ር) ገልጸዋል።
አየር ንብረት ለውጥ የሚያመጣውን ተፅዕኖ በአርሶ አደር ያስከተለውን ጉዳት ለመካካስ ማዕከሉ የራሱን ድርሻ እየተወጣ እንደሚገኝ ተገልጿል። በዚሁ መሠረት ድርቅን የሚቋቋሙና የመድረሻ ጊዜያቸው አጭር የሆኑ ሰብል ዝርያዎችን በቦሎሶ ሶሬ፣በአረካ ከተማ፣በዳሞት ጋሌ፣በዳሞት ሶሬ እና በድጉና ፋንጎ ወረዳዎች ከ86 ሄ/ር በላይ መሳ መሸፈኑን የማዕከሉ ቴክኖሎጂ ሽግግርና ኮሙኒኬሽን ምርምር ስ/ሂደት አስተባባሪ የሆኑት አቶ ታደለ ህርጎ ገልጿል።ቦሎቄ SER-125 ፣አረካ-1 ጤፍ ፣ CR-37ጤፍ፣በላም አተር፣በስንዴ ዝሪያዎች ለአ/አደርና በስራ እድል ፈጠራ ላይ የተደራጁ ወጣቶች ድጋፍ ተደርጓል።