15/09/2022
ትምህርት ሚኒስቴር ምንም በማያውቁ ህሊና ቢሶች እየተመራ እንደሆነ በሚሰራው ስራና በሚያወጣቸው ህግና ደንቦች ማወቅ ይቻላል።ትምህርት ሚኒስቴር ማለት ከዛሬ 10 ዓመት በፊት ለፒኤችዲ ተማሪዎች የፀደቀን የምርምርና የጥቅማ ጥቅም ክፍያ የአንድ ብር እንኳን ጭማሪ ሳያደርጉ እንደገና አፀደቅን ብለው ደብዳቤ የሚፅፉ የካድሬዎች ስብስብ ነው።የ12ኛ ክፍልን የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና መፈተን የዩኒቨርሲቲ መምህራን ድርሻ አይደለም የሃይስኩል መምህራን ናቸው መፈተን ያለባቸው ምክንያቱም የምትወረወረው ሽርፍራፊ ሳንቲምም ብትሆን መጠቀም ያለባቸው እነሱ ነበሩ።
ነገር ግን የዩኒቨርሲቲ መምህር ይፈትን ሲባል ቀድመው የነቁትና ትምህርት ሚኒስቴር ለመምህራን ያለውን ንቀት የተረዱት ባለመፈተን እንተባበር አንድ እንሁን መብታችን በተደራጀ መልኩ እናስከብር ሲሏችሁ መፈተን የሚፈልግ ተብሎ ማስታወቂያ ሲለጠፍ በሰልፍ የተመዘገባችሁ ለትግል የማትመቹ መምህራኖች እርማችሁን አውጡ።
የኑሮው ሁኔታ የት ላይ እንደደረሰ የማያውቁ ትምህርትን ወደ ኋላ እየጎተቱት ያሉ ካድሬዎች ለምትፈትኑበት አበል እንኳን ሒሳብ መሥራት አቅቷቸው በድሮው መመሪያ አበላችሁ ይከፈላችኋል ተብላችኋል።አያችሁ የንቀታቸውን ንቀትና አዲስ የአበል አከፋፈል መመሪያ ማዘጋጀት አለመቻላቸውን????
መያዣው ደግሞ
ለመፈተን ተመዝግቦ የማይፈትን መምህር ከስራ ይባረራል በሌላ መስሪያ ቤትም ሆነ በNGOዎች እንዳይቀጠር ሰርኩላር ደብዳቤ ይጻፋል ብለዋል።እያንዳንድሽ ምንም እንደማታመጡ ስለሚያውቁ በማይፈትን መምህር ላይ ይህንን ተግባራዊ እንደሚያደርጉት እርግጠኛ ነኝ።
እንደ መፍትሔ
1. ባሪያ ምንጊዜም ባሪያ ነውና የቤታችሁን ጎደሎ ፈተና በመፈተን አበል አግኝታችሁ ልትሞሉ በሰልፍ የተመዘገባችሁ ፈታኞች ፈተናውን ፈትኑ ግን ለማይቀረው ትግል ራሳችሁን ብታዘጋጁ
2. የሚሰጣችሁ አበል የአልጋ ወጭ የማይችል በመሆኑ ከሄዳችሁ በኋላ ለእንግልትና ለስቃይ እንዳትዳረጉ ደህና ብር ተበድራችሁም ቢሆን ብትይዙ።
3. ትራንስፖርት በግላችሁ ስለሆነ የምትሄዱት አንድ ቦታ የተመደባችሁ ተነጋግራችሁ ኩንትራት መኪና ብትይዙ።በነገራችን ላይ የትራንስፖርት ክፍያ መንግስት እከፍላለሁ ብሏል ግን የሚገርመው መንግስት የሚከፍለው መንገድ ትራንስፖርት ባወጣው ተመን ብቻ ነው።እናንተ ደግሞ የምትከፍሉት መንገድ ትራንስፖርት ካወጣው ታሪፍ ከ3 እጥፍ በላይ ነው።
4. ለትግል የማትመቹ መምህራን መንግስት ለመምህራን ያለውን ንቀት በውል ተረድታችሁ ወደ ትግሉ ብትቀላቀሉ እያልኩ የሚከተለውን ላስታውሳችሁ።
የፈተና አስፈጻሚዎች ክፍያ አይነት፣ ተመን እና አፈጻጸም
በክፍል ሁለት በቀረበው የፈተና አስተዳደር አስፈፃሚዎች የኃላፊነት ዓይነት መሰረት የተለያዩ
ክፍያዎች በተለያየ ተመን እና ብዛት ተፈፃሚ የሚሆን ይሆናል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ የክፍያ
ዓይነቶች፣ ተመን እና ብዛት እንደሚከተለው ቀርቧል።
12. የውሎ አበል ክፍያ
አንድ ፈተና አስፈፃሚ ከፈተና አስተዳደር ስራው ጋር በተያያዘ ከሚኖርበት አካባቢ ርቆ በመሄድ
ስራውን የሚያከናውን ሆኖ ሲገኝ በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የቀን ውሎ አበል አከፋፈል መመሪያ
መሰረት የቆይታ ጊዜ፣ የቆይታ ቦታ፣ የደመወዝ መጠን እንዲሁም የበረሃ አበል ተመንን መነሻ
በማድረግ የሙሉ ቀን ወይም / እና የቁርስ እና ምሳ አበል ተሰልቶ የጉዞ ቀናትን ጨምሮ ክፍያ
ይከፈላል፣
13. የአገልግሎት ክፍያ /session payment/
13.1. አንድ የፈተና አስፈፃሚ ከፈተና አስተዳደር ስራው ጋር በተያያዘ በሚሰጠው ኃላፊነት እና
ስራው ላይ ባለው የተሳትፎ ጊዜ መሰረት በተለያየ ተመን ሴሽን ሂሳብ ተሰልቶ ክፍያ
ይከፈላል፣
13.2. የፈተና ስራው በአንድ ማዕከል ሁሉም ተፈታኞች ተሰባስበው የሚሰጡ በመሆኑ በፈተና
አስፈጻሚዎችና በፈተና አሰጣጥ ሂደቱ ላይ ከፍተኛ ጫና የሚያሳደር በመሆኑ በቅድመ
ፈተና እና በድህረ ፈተና የሚከናወኑ ተግባራት ከግምት ውስጥ በማስገባት ከዚህ በፊት
በአንድ ፈተና አይነት አንድ የነበረው ሴሽን ወደ ሁለት እንዲያድግ ተደርጓል፡፡
13.3. በቅደመ ፈተና በማዕከል ያለው የፈተና የክዘና ማዕከል አንድ በመሆና ከፍተኛ ቁጥር
ያለው ተፈታኝና ፈተና አስፈጻሚ ስለሚሰማራ አስቀድሞ ገብቶ የቅደመ ዝግጅት ስራዎችን
መፈጸም ያስፈልጋል፣ በዚህም አንድ የቅደመ ፈተና ሴሽን እንዲያዝለት ይደረጋል፡፡
13.4. የከሰአቱ ፈተና 9፡00 ተጀምሮ የሚጠናቀቀው 12፡00 ላይ በመሆኑ የድህረ ፈተና የመልስ
ወረቀት ቆጠራና ርክክብ ሥራዎችም እስከምሽቱ የሚዘልቁ በመሆናቸው ይህንን ታሳቢ
ያደረገ የሴሽን ክፍያ ስርአት መከተል የግድ አስፈላጊ ሆኗል፡፡ በመሆኑም በቅደመ ፈተና፣
ጠዋት፣ ከሰአትና በድህረ ፈተና አራት ሴሽኖች ፈተና በሚሰጥባቸው ቀናት ይኖሩታል፣
13.5. የሴሽን ብዛቱም ለዓይነ ስውር ተፈታኞች በአንባቢነት የሚመደብ ፈተና አስፈፃሚ
በአራቱም ቀናት በስራው ላይ ተሳታፊ ከሆነ አስር ሴሽን ተሳቢ የሚደረግለት ሲሆን
ለተፈጥሮ ሳይንስ አስራ አራት እና ለማህበራዊ ሳይንስ ፈተና አስፈጻሚዎች አስራ ሁለት
ሴሽን በሁለቱም ለተሳተፈ ሀያ ስድስት ሴሽን ታሳቢ ተደርጎ ክፍያ የሚፈፀም ይሆናል።
- 36 -
13.6. የክፍያ ተመኑም ባለፉት አመታት ለኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ፈተናው ጥቅም
ላይ ሲውል የነበረውን የ250 ብር (ፖሊስ፣ ሹፌር፣ የመልስ ወረቀት ቆጣሪ)፣ 300ብር (ለፈታኝ፣ለሱፐርቫይዘርና የፋይናንስ ባለሙያ)፣ 360 ብር(ጣቢያ ኃላፊ፣ የፋይናንስ ኃላፊ)፣450ብር (የጉድኝት ማዕከል አስተባባሪ፣ የማዕከል ኃላፊና የዩኒቨርሲቲ ግብረ ኃይል) እና 460 (የአይነ ሥውር አንባቢ) ብር ክፍያ እንደ ኃላፊነታቸው በተዋረድ የሚከፈል ይሆናል።