Yibeltal

Yibeltal Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Yibeltal, Chemical company, Bahir dar, Bahir Dar.

24/08/2022

☞ከህይወትህ ውስጥ የወደቀብህን ሁሉ ለማንሳት አታጎንብስ። አንዳንዴ ለወደቀብህ ነገር ስታጎነብስ በብዛት ይወድቅብሃል። ስለወደቁት ነገሮች ዘላቂ መፍትሄ አስብ። ጉዞህንም በጥንቃቄ ቀጥል•••

❀ #ፈጣሪን ፡ ሁሌ ፡ አመስግን•••

♦ታመህም ፡ ቢሆን ፡ አመስግን•••

♦አተህም ፡ ቢሆን ፡ አመስግን•••

♦ብቻህን ፡ ብትሆንም ፡ አመስግን•••

♠ #ሁሌ ፡ አፍህ ፡ በምስጋና ፡ ብቻ ፡ ይሞላ:: ስታመሰግኑ ይጨመራችኃል ይላልና ቃሉ•••

ብሩህ ቀን ይሁንላችሁ

______________✍🏽
♥️ፍቅር ይሻለናል♥️

24/08/2022

ይህንን ፅሁፍ ካላነበብክ ፌስቡክ መጠቀምህን አቁም

✅✅‼ ባልና ሚስት በትዳርና በፍቅር አብረው ይኖሩ ነበር ። እኚህ ባልና ሚስት ሁለት ልጆች ነበራቸውና ለልጆቹ ማሳደጊያ ባልየው ተጨማሪ ስራ ሊሰራ ተሰማምተው ራቅ ወዳለ አገር ሄዶ መስራት ጀመረ ። ለብዙ ዓመታት ከቆየ በኋላ ወደናፈቁት ቤተሰቦቹ ለመሄድ ሲነሳ ያልገመተው ነገር ከቀጣሪዎቹ ሰማ ። ደሞዙ በተለያየ ምክንያት ተቆራርጦ ከሚጠብቀው ከግማሽ በታች የሆነው 30 ብር ተሰጠው ።

✅✅‼ የተሰጠውን ተቀብሎ እግረ መንገዱ ስራ ካገኘ እየሰራ ጠርቀም ያለ ብር ይዞ ቤተሰቦቹ ጋር ለመሄድ ተነሳ ። በመንገዱ አንድ ሸምገል ያሉ አባት አገኘ "ወዴት ትሄዳለህ ልጄ ከየት ነውስ ምትመጣው ?" አሉት ። እሱም ከመጀመርያው እስከ መጨረሻው ነገራቸው ። እሳቸውም እንዲህ አሉት "እንግዲያውስ የምትፈልገውን ነገር ማግኘት ቀላል ነው ፤ እሱም እንዴት አባቴ ?" ሲል ጠየቃቸው እሳቸውም "በል አንድ አስር ብሩን አምጣና እነግርሃለሁ" አሉት የቸገረው ነውና አንስቶ ይሰጣቸዋል ።

✅✅‼ እኒህ አባትም "አቋራጭ ነው ብለህ በማታውቀው መንገድ አትሂድ" ይህ ምክር አንድ ነው ይሉታል ። ሁለተኛውን አምጣና ሁለተኛውን መንገድ ልንገርህ ይሉታል ። እሱም በየዋህነት ይሰጣል "በማያገባህ አትግባ ፤ ይሄ ደግሞ ሁለተኛው ምክሬ ነው" ይሉታል ። "በቃ ይሄ ነው ?" ቢላቸው "አዎን ልጄ ሶስተኛውን አምጣና በጣም አሰፈላጊውና የመጨረሻውን ስጦታዬን ልስጥህ" አሉት ሰጠ ። እሳቸውም "ክፉ ለማድረግ አትቸኩል" ብለውት በባዶ ኪሱ ከሶስቱ ምክሮች ጋር አሰናበቱት ። እሱም ጉዞውን ወደ ቤቱ አደረገ ።

✅✅‼ በመንገድ ነጋዴዎች አግኝቶ እያወጋ ሲጓዝ መሸ ። ነጋዴዎቹም ለምን ባቋራጭ አንሄድም በማለት ጉዞ ጀመሩ ። እሱም አብሯቸው ጉዞ እንደጀመረ የሽማግሌው አባት ምክር አንድ ትዝ አለው ። "አቋራጭ ነው ብለህ በማታውቀው መንገድ አትሂድ" የሚለው ። ስለዚህ ተመልሶ በሚያውቀው መንገድ ተጉዞ ብቻውን ከጨለመ በኋላ ከተማ ገባ ። "የመሸበት እንግዳ ነኝ አሳድሩኝ" በማለት ሰው ጠየቀ ። አንድ የዛ ከተማ ሰውም "ይኸውልህ ወንድሜ እዛ ቤት ሂድ ያሳድርሃል ፤ ነግር ግን እዛ ሰው ቤት የገባ አይወጣም ለማንኛውም እድልህን ሞክር ።" እሱም የተባለበት ቤት አንኳኩቶ ቤት የእንግዳ ነው ተብሎ ገባ ።

✅✅‼ ታድያ ከቤቱ ባለቤት ጋር ሲያወጉ ከየት እንደመጣ ቢነግረው ባለቤቱ ተገርሞ "እንዴት ሆነክ ተረፍክ ባልከው መስመር ይመጡ የነበሩ ነጋዴች ተዘርፈው ነጋዴዎቹም ተገለው ከተማው ለቅሶ ብቻ እኮ ነው የሆነው" አለው ። ያቺ አስር ብር የገዛት ምክር በብር የማትገዛ ህይወቱን አተረፈችለት ማለት ነው ። ስለመሸ የቤቱ እመቤት ምግብ ለእንግዳው ልታቀርብ ከጓዳ ብቅ አለች" እንግዳው አይኑን ማመን አልቻለም ። የተወሰነ አካሏ ብቻ ነው ሰው የሚመስለው በዛ ላይ ማስፈራቷ ወደ ጓዳ እስክትገባ ናፈቀ ።

✅✅‼ "ከዚህች ጋር እንዴት ትኖራለህ?" ብሎ ሊጠይቅ ሲል አንድ ነገር ትዝ አለው "በማያገባህ አትግባ" የሚለው ። ሆዱ መጠየቅ እየፈለገ ፍላጎቱን ተቋቁሞ አደረ ። ደግሞ ሌላ ፈተና የቤቱ ባለቤት ከመሄድህ በፊት የማሳይህ ነገር አለኝ ብሎ ወደ ጓሮ ወሰደውና የሰው አጽም የሞላበት ሜዳ አሳየው እንግዳውም "ይሄ ምንድ ነው ?" ማለት ፈልጎ ነበር ግን በማያገባህ አትግባ ብሎ ራሱን እየነቀነቀ ዝም አለ ። የቤቱ ባለቤትም ተገርሞ "በእውነት አንተ የምትገርም ሰው ነህ ፤ ይህ የምታየው ሰው ሁሉ ስለሚስቴ የማያገባቸውን አስተያየት ስለሰጡ የተገደሉ ናቸው ፤ እንዳንተ እዚህ ቤት በእንግድንት የመጡ ነበሩ ።

✅✅‼ አንተ ግን ታላቅ ሰው ስለሆንክ የሀብቴን 1/4 ኛ ሰጥቼሃለሁና ይዘህ ትሄዳለህ" ተብሎ ባለ ብዙ ሀብት ሆኖ ወደ ቤቱ ሄደ ። እዛች ደሳሳ ጎጆ የደረሰው ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት ነበር ። ሁሉም ነገር ቢለወጥም ቤቱን ግን አላጣውም ። በትልቅ እንጨት የምትዘጋ በሩን ገፋ ሲያደርጋት ተከፈተች ። አይኑ ግን ከማያምነው ነገር ላይ አረፈ ። ሚስቱ ሁለት ጎረምሶች መሀል ተኝታለች ። በንዴት ጦፎ ትልቅ ድንጋይ አንስቶ ወደ ውስጥ ሊገባ ሲል 3ተኛው ምክር ትዝ አለው ። "ክፉ ለማድረግ አትቸኩል" የሚለው ። ከቤቱ ውጭ በተጋደመው ዛፍ ላይ ቁጭ ብሎ አደረ ። ሚስት በጠዋት ተነስታ ደፋ ቀና ስትል ድንገት ባሏን ስታየው እልልታዋን አቀለጠችው ዘላ ተጠመጠመችበት ።

✅✅‼ ከእንቅልፉ የነቃው ባል በመደናገጥ ሳለ እጆቹን ይዛ ወደ ቤት ገብታ ሁለቱን ጎሮምሶች አሰተዋወቀችው "ይህ የመጀመርያ ልጅህ ይህ ደግሞ ሁለተኛው" ብላ እንግዲህ የመጨረሻው ምክር የልጆቹን ነፍስ ከማጥፋት እረዳው ማለት ነው ። ሰውዬው ሶስቱ የሽማግሌው አባት ምክሮች በደስታ ከቤተሰቡ ጋር እንዲቀላቀል አደረጉት ።

ስለዚህ ወዳጄ ሆይ አንተም በህይወት ስትኖር ፦
1. አቋራጭ ነው ብለህ በማታውቀው መንገድ አትሂድ
2. በማያገባህ አትግባ
3. ክፉ ለማድረግ አትቸኩል

✅✅‼ ፌስቡክን ለመታወቅ ሳይሆን ያወቅነውን ለማሳወቅ እንጠቀም ፡፡ ማወቅ መልካም ነው ያወቁትን ማሳወቅ ደግሞ ፍፁም በጎነት ነው ፡፡ በምድር ላይ የምናደርጋቸው ነገሮች ሁሉ በሰማይ ላይ የዘላለም ደመወዝ ሆነው ይከፈሉናል ፡፡ ሁሌም ቢሆን ከክፋት ይልቅ በጎ በጎውን ነገር እናስብ መልካምነት ለራስ ነውና ፡፡

✅✅‼ ስለዚህ አንተም ይህ አሁን ያነበብከው መጣጥፍ ትምህርት ሰጪ ሆኖ ካገኘሀው የእርስዎ ዘመዶችህ እንዲያነቡትና ትምህርት እንዲወስዱ ዘንድ ሼር ያድርጉላቸው ።

✅✅‼ አዳዲስና ትምህርት ሰጪ የሆኑ ፅሁፎች በየቀኑ እንዲደርሳችሁ ሼር፣፣ላይክ

21/08/2022
06/08/2022

Address

Bahir Dar
Bahir Dar

Telephone

+251913001225

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Yibeltal posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share