Hibir Construction Corporation/ ኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን

  • Home
  • Ethiopia
  • Bahir Dar
  • Hibir Construction Corporation/ ኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን

Hibir Construction Corporation/ ኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ነገን እንገነባለን!! አድራሻ፡- ባሕር ዳር ከተማ ከአማራ ፓይፕ ፋብሪካ ኃ/የተ/ የግል ኩባንያ ፊት ለፊት
+251 58 220 4493
+251 58 220 45 01 (ፋክስ)
1678 (የመልክት ሣጥን ቁጥር)

እንኳን ደስ አላችሁ!! Congratulations!!ኮርፖሬሽናችን በ2024/2025 በጀት ዓመት  ባስመዘገበው  የላቀ የሥራ አፈፃፀም ከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር የዕውቅና ሽልማት  አበርክ...
19/04/2026

እንኳን ደስ አላችሁ!!
Congratulations!!

ኮርፖሬሽናችን በ2024/2025 በጀት ዓመት ባስመዘገበው የላቀ የሥራ አፈፃፀም ከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር የዕውቅና ሽልማት አበርክቶለታል።

የከተማና መሰረተ ልማት ሚንስትር 1000 ኮንትራክተሮችን ያሳተፈ የመሰረተ ልማት ፌስቲቫል ባካሄደው መድረክ በኮንስትራክሽን ኢንደስትሪው ዘርፍ የላቀ አፈፃፀም ያስመዘገቡ 20 ተቋራጮችን ለይቶ 10 ተቋራጮችን በደረጃ አንድ እና 10 ተቋራጮችን በደረጃ ሁለት ለይቶ የዕውቅና ሽልማት አበርክቷል።

በዚህ የዕውቅና መርሃ ግብር ላይ ኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን የላቀ አፈፃፀም ካስመዘገቡት ምርጥ አስር ተቋራጮች ውስጥ ሆኖ በመገኘቱ በዓይነቱ ከፍያለ ሃገር ዓቀፍ የዕውቅና ሽልማት ተበርክቶለታል።

ስለሆነም ለመላው የኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን አመራርና ሰራተኞች እንዲሁም ከኮርፖሬሽኑ ጋር አብራችሁ የምትሰሩ አጋርና ባለ ድርሻ አካላት ለዚህ ዕውቅና መገኘት የነበራችሁ ሚና ከፍተኛ በመሆኑ በድጋሜ እንኳን ደስ አላችሁ!!

በድካማችሁ፣ በጥረታችሁ እና በአብሮነታችሁ ለተገኘው የዕውቅና ሽልማት በእጅጉ ልትኮሩ ይገባል።

በመጨረሻም በየደረጃው የምትገኙ የተከበራችሁ የኮርፖሬሽኑ አመራርና ሰራተኞች ይህንን የዕውቅና ሽልማት እንደ አንድ ትልቅ መስፈንጠሪያ ተጠቅመን አሁን ያለውን ዓለማቀፋዊ እና ሃገራዊ የኮንስትራክሽን ፈተናዎችን የሚያሻገሩ መፍትሄዎችን መጠቀም ይጠይቃል።

ይህ ሲሆን በሁሉም ፕሮጀክቶቻችን ለመፈፀም የታቀደውን አሳክተን 2025/2026 በጀት ዓመት ከዳግም የዕውቅና ሽልማት ባሻገር በዕራያችን ያመላከትነውን በምስራቅ አፍሪካ የኮንስትራክሽን ኢንደስትሪ ገብያ ውስጥ ለመቀላቀል የሚያስችለውን ሁሉ ሆነን መዘጋጀት ይጠበቅብናል።

ኢንጅነር መብት አድማስ
CEO

ኅብር ኮንስትራክሽን
ነገን እንገነባለ!!!

ክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያ
16/04/2026

ክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያ

12/04/2026
09/04/2026

ኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት እና የትንሳኤ በዓል በሰላምና በጤና አደረሳችሁ እያለ መልካም ምኞቱን ይገልጻል !!

03/04/2026

ለመላው የሰቆጣ ከተማ ነዋሪዎች በሙሉ ኀብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን በሰቆጣ ከተማ አሰፓልት የማንጠፍ ሥራ እንደጀመረ ይታወቃል።

ሆኖም የአስፖልት የማንጠፍ ሥራውን ሆን ብሎ ለማስተጓጎል በህቡ እና በግልፅ የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች እንዳሉ ተገንዝበናል።

የክልሉ መንግስት የአካባቢውን የልማት ጥያቄ ለመፈታት በትኩረት ከሚከታተለው ፕሮጀክት ውስጥ አንዱ ይህ ፕሮጀክት ነው።

ከዚህ በተጨማሪ የመንገድ ግንባታው በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር እና በአማካሪ ድርጅቱ ከፍተኛ ክትትል እና ቁጥጥር የሚሰራ መሆኑን በውል መገንዘብ አስፈላጊ ነው።

የከተማውን አስፖልት በጥራት ለማንጠፍ የአስፋልት ድብልቁን ፈትሾ እና የተገኘውን ውጤት አይቶ ወደ ተሟላ ሥራ ለመግባት አስፓልት ድብልቅ ምጥጥንን ደረጃውን ለይቶ ወደ ሙሉ ሥራ መግባትን ይጠይቃል።

በሙከራ ትግበራው ዕለትም የአስፋልት ድብልቅ የምጥጥን ክፍተት እንዳለበት ተለይቷል።

ይህ የሙከራ ስራ በአማካሪ መሃንዲሶች በኩል አስተያየት ተሰጥቶበት አሰፓልቱ በማግስቱ ተቆርጦ እንዲነሳ የተወሰነ ነው።

ኮንትራክተሩም በማግስቱ እንደቆረጠው ግልፅ ነው። በዛሬው ዕለትም የተቆረጠው አስፋልት ተነስቷል።

ይህንን ምስል ይዘው የሚያራግቡ ግለሰቦች ዋና አላማቸው ምን እንደሆነ ግልፅ ነው።

ኅብር የክልሉ የልማት ድርጅት ከመሆኑም በላይ በጥራት የማይታማ መሆኑን ማወቅ ያስፈልጋል።

የምንገነባው ሃገራችንን ነው። መሰረታችን ትርፍ አለመሆኑንን ይልቁንም የክልላችንን የልማት ክፍተት መሙላት መሆኑንም መረዳት ጠቃሚ ነው።

የደሴ ከተማ አስተዳደርን፣ ከጎንደር ከተማ አስተዳደር፣ ከቡሬ የተቀናጀ አግሮ ኢንደስትሪ ፖርክ የአስፍልት መንገዶችን ጥራትና መመልከት ጥሩ ነው።

ነገር ግን የሥራውን ባህሪ ከመረዳትም ይሁን ካለመረዳት ሻከረ፣ ለሰለሰ፣ ወፈረ፣ ቀጠነ በማለት ከሙያ ውጭ የሆነ በመሰለኝ የሚሰነዘር ሃሳብና ተግባርን በየጊዜው እየተከታተሉ መለየትና ማረም ያስፈልጋል።

በአሁኑ ወቅት ነዳጅና ሌሎች የኮንስትራክሽን ግብዓቶችን በቀላሉ ማቅረብ ፈተና በሆነበት በዚህ ወቅት ለሥራዎች ተጨማሪ አቅም መሆን ሲገባው አደናቃፊ እና አደናጋሪ ሃሳብ ይዞ በማህበራዊ ሚዲያ መራገቡ በእጅጉ አሳዝኖናል።

ስለሆነም የአካባቢው ማህበረሰብ የመንገድ ግንባታ ጥራትን አስመልክቶ የሚለቀቁ የተዛቡ መረጃዎችን በማረም፣ የክትትልና ቁጥጥር ሥራውን ለአማካሪዎች እና ለባለሞያዎች በመተው ለመንገድ ግንባታው ተጨማሪ ሃይል በመሆን የማይተካ ሚናውን እንዲወጣ እንጠይቃለን።

ኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን በጥራት የማይደራደር መሆኑንን እየገለፅን ድንገት ለሚፈጠር ማንኛውም የጥራት ክፍተት ኃላፊነቱን ይወስዳል።

ኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን
ነገን እንገነባለን

29/03/2026

የሎት-1 ከጋሸና ላሊበላ ብልባላ እና 15 ኪ.ሜ የላሊበላ ማቋረጫ መንገድ ሥራ ፕሮጀክት በላሊበላ ከተማ ውስጥ በ2.9 ኪ.ሜ ርዝመት፤ 22 እና 12 ሜትር ስፋት የአስፓልት እና ኮንክሪት መንገድ ለማንጠፍ ስራ ዝግጁ ነው ።

ኢንጅነር ደሳለኝ መልክነው ፕሮጀክት ኃላፊ

በ22 እና 12 ሜትር ስፋት 2.9 ኪ.ሜ የላሊበላ ከተማ ውስጥ በአስፓልት እና ኮንክሪት ለማልበስ የአፈር ቆረጣ ፣የስትራክቸር፣ የሰብቤዝ እና የመሬት ድልዳሎ ሥራው 90% ተጠናቋል።

ለአስፖልትና ኮንክሬት ግንባታ የሚውል በቂ የሆነ የተለያዩ የጠጠር ዓይነቶች፣የሲሚንቶ እና የብረት ግብአቶች ክምችት ተይዟል።

ለፕሮጀክቱ ሥራ እጅግ አስፈላጊ ከሆኑ ማሽኖች ውስጥ ወለህ ላይ የአስፓልት ፕላንት እና ላሊበላ ከተማ ዘመናዊ የሆነው ኮንክሪት ባችንግ ፕላንቶች ዝግጁ መሆናቸው ለፕሮጀክቱ ትልቅ አስተዋፅኦ አለው።

እነዚህ ማሽኖችን ተከትሎ መቅረብ ያለባቸውን ሌሎች እንደ ኮንክሬት ፔቨር እና አስፓልት ለማንጠፍ አስፈላጊ የሆኑ ማሽኖችን በቅርቡ ወደ ፕሮጀክቱ ለማስገባት በልዩ ሁኔታ እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው።

ከዚህም በተጨማሪ በጋሸና ከተማ ውስጥ 900ሜትር ርዝመት እና የ30ሜትር ስፋት የማፋሰሻ ዲች፣ የአፈር ቀረጣ ፣ የሰቤዝ እና ሌሎች የስትራክቸር ስራዎች በጣምራ ኮንትራክተሩ በዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን በኩል በጥሩ ሁኔታ እየተሰራ ይገኛል።

ኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን
ነገን እንገነባለን!!!

28/03/2026

ከሰቆጣ አበርገሌ የሚደርሰው የ60 ኪ.ሜ የጠጠር መንገድ ጥገና በጥሩ አፈፃፀም ላይ እንደሚገኝ ተገለፀ።

የፕሮጀክት ኃላፊው ኢንጅነር ሰፊው ባየ ለትራፊክ አስቸጋሪ የነበረውን ይህንን የ60 ኪ.ሜ መንገድ ጥገና ኘሮጀክት ኮርፓሬሽኑ ከኢትዮጵያ መንገድ አስተዳደር ውል ተይዞ ከገባበት ዕለት ጀምሮ የጥገና ሥራው እንደቀጠለ ነው ብለዋል።

የመንገድ ጥገና ሥራውን ከክረምት ወራት በፊት አጠናቆ ለማስረከብ ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ነው። እስከ አሁን ባለው 15 ኪ.ሜ ጥገና ማከናወን የተቻለ ቢሆንም በሃገር አቀፍ ደረጃ ከገጠመን የነዳጅ እጥረት ጋር ተያይዞ በዕቅዳችን ልክ እንዳንሰራ ተገደናል ነው ያሉት።

ኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን
ነገን እንገነባለን!!!

የወራቤ - ቦዠባር የአስፓልት መንገድ ግንባታ 75.1% ደረሰበህብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን እየተከናወነ የሚገኘው የ41.34 ኪ.ሜ የወራቤ - ቦዠባር የአስፓልት መንገድ ግንባታ አፈጻጸም 7...
27/03/2026

የወራቤ - ቦዠባር የአስፓልት መንገድ ግንባታ 75.1% ደረሰ
በህብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን እየተከናወነ የሚገኘው የ41.34 ኪ.ሜ የወራቤ - ቦዠባር የአስፓልት መንገድ ግንባታ አፈጻጸም 75.1% ላይ ደርሷል።
🏗️ ዋና ዋና የግንባታ ኩነቶች፡
* የተከናወኑ ስራዎች፡ የአፈር ቆረጣና ሙሌት 96%፣ የውሃ ማፋሰሻ (ድሬኔጅ) 67%፣ እንዲሁም 14 ኪ.ሜ የአስፓልት ንጣፍ ስራ ተጠናቋል።
* መዋቅሮች፡ 40 የፓይፕ ከልቨርቶች፣ 6 የስላብ ከልቨርቶች እና የአንድ ድልድይ ግንባታን ያካትታል።
* የማጠናቀቂያ ጊዜ፡ ፕሮጀክቱ እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2026 እ.ኤ.አ ድረስ ተጠናቆ ለአገልግሎት እንዲበቃ በትኩረት እየተሰራ ነው።
🌟 የፕሮጀክቱ ፋይዳ፡
መንገዱ ሲጠናቀቅ ቀደም ሲል የነበረውን የ2 ሰዓት ከ30 ደቂቃ ጉዞ ወደ 1 ሰዓት ዝቅ ያደርገዋል። ይህም የአካባቢው ማህበረሰብ የግብርና ምርቶችን (ገብስ፣ ድንችና ቅመማ ቅመሞችን) በፍጥነት ወደ ገበያ ለማቅረብና ለማህበራዊ አገልግሎቶች ተደራሽነት ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል።
ህብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን
ነገን እንገነባለን!!

26/03/2026

በብልባላ ሰቆጣ ሎት 02 አስፋልት መንገድ ሥራ ፕሮጀክት ሰቆጣ ከተማ ላይ በ 16/07/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:30 እስከ ምሽቱ 2:20 የነበረውን አስፓልት የማንጠፍ ሥራን የሚያሳይ አጭር ቅኝት።

ኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን
ነገን እንገነባለን!!

መላው የብልባላ ሰቆጣ ሎት 02 አስፋልት መንገድ ሥራ ፕሮጀክት አመራርና ሰራተኞች እንኳን ደስ አላችሁ።እናንተ ከቅድመ አስፓልት ፕላት ተከላ እስከዛሬው ዕለት ባሳያችሁት ከፍተኛ የሥራ ሞራል ...
25/03/2026

መላው የብልባላ ሰቆጣ ሎት 02 አስፋልት መንገድ ሥራ ፕሮጀክት አመራርና ሰራተኞች እንኳን ደስ አላችሁ።

እናንተ ከቅድመ አስፓልት ፕላት ተከላ እስከዛሬው ዕለት ባሳያችሁት ከፍተኛ የሥራ ሞራል ፣ ትጋት እና መናበብ እነሆ ለዚህ በቅተናል።

ወደፊትም እንደ ፕሮጀክት የማንወጣው ተራራ የማንሻገረው ወንዝ እንደማይኖር አረጋግጫለሁ።

ኢንጅነር ሰፊው ባየ
ፕሮጀክት ኃላፊ

ኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን
ነገን እንገነባለን!!

Address

Bahir Dar
1678

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Hibir Construction Corporation/ ኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Hibir Construction Corporation/ ኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን:

Share