Amhara Industry Parks Development Corporation

Amhara Industry Parks Development Corporation Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Amhara Industry Parks Development Corporation, Industrial Company, Bahir Dar.

የፈተና ጥሪ ማስታወቂያ
12/06/2026

የፈተና ጥሪ ማስታወቂያ

12/06/2026
እውቅናና ሽልማት ተሰጠ።ግንቦት 30/2018 ዓ.ም በኮምቦልቻ ከተማ በተካሄደው የኢትዮጵያ ታምርት ክልላዊ የማጠቃለያ መድረክ ምርት አምርተው ኤክስፖርት በማድረግ፣ ስትራቴጂክ ተኪ ምርት በማም...
09/06/2026

እውቅናና ሽልማት ተሰጠ።

ግንቦት 30/2018 ዓ.ም በኮምቦልቻ ከተማ በተካሄደው የኢትዮጵያ ታምርት ክልላዊ የማጠቃለያ መድረክ ምርት አምርተው ኤክስፖርት በማድረግ፣ ስትራቴጂክ ተኪ ምርት በማምረት፣ በዘርፈ ብዙ ኢንቨስትመንት በመሰማራት ስኬታማ የሆኑና መሬት ወስደው በፍጥነት ወደ አፈፃፀም የገቡ ባለሀብቶች የዋንጫ፣ የሜዳሊያ እና የሰርተፊኬት ሽልማት ተሰጧቸዋል።

በተመሳሳይ ለአምራች ኢንዱስትሪዎች አገልግሎት በማቅረብ ውጤታማ የሆኑ ተቋማትም እውቅና የተሰጣቸው ሲሆን ኮምቦልቻ ከተማ መድረኩ እንዲሳካ ላደረገው ዘርፈ ብዙ ስራ እንዲሁም የንቅናቄ መድረኩን ስፓንሰር በማድረግ ፀደይ ባንክ እውቅና ተሰጥቷቸዋል።

መረጃው የአማራ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ነው።

ለኢንዱስትሪ ልማት ተግተን እንሰራለን!!

"አምራች ኢንዱስትሪ የኢኮኖሚ የልብ ምት ነው " አሕመዲን ሙሐመድ ( ዶ.ር)የአማራ ክልል "ኢትዮጵያ ታምርት" ክልላዊ የማጠቃለያ መርሐ ግብር "ኢትዮጵያ ታምርት ለሁለንተናዊ ሉዓላዊነት" በሚ...
09/06/2026

"አምራች ኢንዱስትሪ የኢኮኖሚ የልብ ምት ነው " አሕመዲን ሙሐመድ ( ዶ.ር)

የአማራ ክልል "ኢትዮጵያ ታምርት" ክልላዊ የማጠቃለያ መርሐ ግብር "ኢትዮጵያ ታምርት ለሁለንተናዊ ሉዓላዊነት" በሚል መሪ መልዕክት ግንቦት 30/2018 ዓ/ም በኮምቦልቻ ከተማ ተካሂዷል።

በመርሐ ግብሩ ከባለሃብቶች እና ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተደርጓል።

በውይይቱ የተገኙ ባለሃብቶች የግብዓት፣ የኀይል አቅርቦት እና የመሠረተ ልማት ዝርጋታ እንዲሟላ ጠይቀዋል። የክልሉን ኢንቨስትመንት ለማሳደግ ሰላምን ማረጋገጥ እንደሚገባም ተናግረዋል።

ክልሉ ተወዳዳሪ እንዲኾን ከተፈለገ ሰላምን ማረጋገጥ እና ለኢንዱስትሪ ማነቆ የኾኑ ችግሮችን መፍታት ይገባል ነው ያሉት። የማስፋፊያ ቦታዎችን ማመቻቸት እንደሚገባም ገልጸዋል።የፋይናንስ ተቋማት ለባለሃብቶች የብድር አቅርቦት እንዲያመቻቹም ጠይቀዋል።

የአማራ ክልል ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኀላፊ እንድሪስ አብዱ የክልሉ ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ባለሃብቶች የሚያነሷቸውን ችግሮች በዘላቂነት ለመፍታት በትኩረት እየሠራ መኾኑንም ተናግረዋል።

ችግሮች እንዲፈቱ ተደጋጋሚ ውይይቶች እየተደረጉ እና አቅጣጫዎች እየተቀመጡ መኾናቸውንም ገልጸዋል። የፋይናንስ ተቋማት የብድር አቅርቦት እንዲያመቻቹ ውይይት መደረጉንም አንስተዋል። ጥያቄዎችን ደረጃ በደረጃ እንደሚፈቱም ገልጸዋል።

በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የከተማ ዘርፍ አስተባባሪ አሕመዲን ሙሐመድ (ዶ.ር) የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የኢኮኖሚ መዋቅር ለውጥ ማምጣቱን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ችግሮችን እየፈታ፣ የአምራች ኢንዱስትሪዎች ምርት እንዲጨምር ያደረገ ነው ብለዋል።

"አምራች ኢንዱስትሪው የኢኮኖሚው የልብ ምት ነው" ያሉት አስተባባሪው የልብ ምት የኾነውን ዘርፍ በቅንጅት ማሳደግ ይገባል ነው ያሉት። አምራች ኢንዱስትሪው ያለበትን ማነቆ እየፈቱ መሄድ እንደሚገባም አመላክተዋል።

የኀይል አቅርቦትን እና ሌሎች ችግሮችን መፍታት አለብን ነው ያሉት። ከተቋማት ጋር ያለን ቅንጅት ማጠናከር እንደሚያስፈልግም አንስተዋል። ለኢንዱስትሪ የሚመጥን የሰው ኀይል መገንባት እንደሚገባም አመላክተዋል። ባለሃብቶች ጥራቱን የጠበቀ ምርት እንዲያመርቱም አስገንዝበዋል። በተገቢው መንገድ በመሥራት ኢትዮጵያን ከኢኮኖሚ ጥገኝነት እንዲያላቅቁ እና በሁሉም መስክ ራሷን የቻለች እንድትኾን እንዲተጉም አሳስበዋል።

ለኢንዱስትሪ ልማት ተግተን እንሰራለን!!

"የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ለውጥ ለማምጣት በየትኛውም ዘርፍ ማምረት ያስፈልጋል" ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደየአማራ ክልል "ኢትዮጵያ ታምርት" ክልላዊ የማጠቃለያ መርሐ ግብር "ኢትዮጵያ ታምርት ለ...
08/06/2026

"የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ለውጥ ለማምጣት በየትኛውም ዘርፍ ማምረት ያስፈልጋል" ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ

የአማራ ክልል "ኢትዮጵያ ታምርት" ክልላዊ የማጠቃለያ መርሐ ግብር "ኢትዮጵያ ታምርት ለሁለንተናዊ ሉዓላዊነት" በሚል መሪ መልዕክት በኮምቦልቻ ከተማ ግንቦት 30/2018 ዓ/ም ተካሂዷል።

በመርሐ ግብሩ የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የተገኙ ሲሆን ከባለሃብቶች እና ከባለድርሻ አካላት ጋርም ውይይት ተካሂዷል።

የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ኢንዱስትሪዎች የሚያነሱትን የኀይል አቅርቦት ችግርን ለመፍታት ጥረት ሲደረግ መቆየቱን ገልጸዋል። አሁንም ችግሮችን ለመፍታት በትኩረት እንደሚሠራ ገልፀዋል።በበርካታ የክልሉ አካባቢዎች የኀይል አቅርቦት ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችሉ ሥራዎች እየተሠሩ መሆኑን ገልፀዋል። የነዳጅ አቅርቦት ቅድሚያ ለሚሰጠው መስጠት እና ለአልሚ እንዱስትሪዎች መጠቀም እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

የፋይናንስ አቅርቦት እንዲኖር ከባንኮች ጋር ተደጋጋሚ ውይይቶች መደረጉንም የገለጹት ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ለኢንዱስትሪ ማስፋፊያ የሚጠየቁ የመሬት ጥያቄዎችን በፍጥነት ለመመለስ እንሠራለን ነው ያሉት። ነገር ግን መሬት ወስደው አጥረው ያስቀመጡ አሉ፤ እነዚህ ወደ ሥራ መግባት አለባቸው ብለዋል።

ባለሃብቶች የወሰዱትን መሬት በጊዜው ተጠቅመውበት ቢኾን ኖሮ የክልሉ ኢንዱስትሪ ምርት አሁን ካለበት በላቀ ደረጃ ያድግ እንደነበር አንስተዋል።

የገበያ ትስስር እንዲኖር ለሀገር ውስጥ ምርቶች ቅድሚያ የሚሰጥ የንግድ መመሪያ መጽደቁንም ገልጸዋል። ኢንዱስትሪውን የሚመራ ብቁ የሰው ኀይል መፍጠር እንደሚገባም ተናግረዋል። ባለሃብቶች በፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጆች አማካኝነት ብቁ የሰው ኀይል ማሠልጠን እንዳለባቸውም ገልጸዋል።

በብቁ የሰው ኀይል ያልተመራ ኢንዱስትሪ ተወዳዳሪ አይኾንም ነው ያሉት። የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ለውጥ ለማምጣት ማምረት ያስፈልጋል ብለዋል። የእኛ የማደግ ማዕከላዊ ሃሳብ በየትኛውም ዘርፍ ማምረት የሚል ነው ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ ፤ መሪዎች ምርት እና ምርታማነት እንዲያድግ በትኩረት እንዲሠሩም አሳስበዋል። አሁን የተጣለብንን ታሪካዊ ኀላፊነት ካልተወጣን ታሪካዊ ተጠያቂነት ይመጣል ብለዋል። የኢንዱስትሪውን ተወዳዳሪነት ለማሳደግ ቀዳሚ ጉዳይ መኾኑንም ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የመርሐ ግብር ማሟያ አይደለም፤ ችግሮችን እየፈቱ የሚጨበጥ ሥራ መሥራት ነው ዋናው ጉዳይ ነው ያሉት።

ክልሉ ትልቅ የመልማት ጸጋ ያለው ነው ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ ለሀገር ትልቅ አበርክቶ ያለው ክልል መኾኑን ገልጸዋል። ያለውን ጸጋ በአግባቡ ማውጣት እና መጠቀም ያስፈልገናልም ነው ያሉት።

ባለሃብቶች በወሰዱት መሬት ላይ በአግባቡ እንዲያለሙ ወደ ልማት ያልገቡትም ወደ ልማት እንዲገቡ አሳስበዋል። የክልሉ መንግሥት ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ በትኩረት እየሠራ መኾኑንም ተናግረዋል።

(መረጃው የአሚኮ ነው)

ለኢንዱስትሪ ልማት ተግተን እንሰራለን!!

የአማራ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ለእስልምና እምነት ተከታዮች  በሙሉ እንኳን ለ 1 ሺህ 447 ኛው የኢድ አል ዓደሃ (አረፋ) በዓል በሠላም አደረሳችሁ እያለ፤ በዓሉ የሰላም፣ የደ...
27/05/2026

የአማራ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ለእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ 1 ሺህ 447 ኛው የኢድ አል ዓደሃ (አረፋ) በዓል በሠላም አደረሳችሁ እያለ፤ በዓሉ የሰላም፣ የደስታ እና የፍቅር እንዲሆንላችሁ መልካም ምኞቱን ይገልፃል።

ዒድ-ሙባረክ!!

ለኢንዱስትሪ ልማት ተግተን እንሰራለን!!

ግንቦት 18/2018 ዓ/ም የባህር ዳር ከተማ ነዋሪዎች፣ የመንግስት ሠራተኞችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ለብልፅግና ፓርቲ ያላቸውን ድጋፍና አጋርነት በባህር ዳር ከተማ በተካሄደ ህዝባዊ ...
26/05/2026

ግንቦት 18/2018 ዓ/ም የባህር ዳር ከተማ ነዋሪዎች፣ የመንግስት ሠራተኞችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ለብልፅግና ፓርቲ ያላቸውን ድጋፍና አጋርነት በባህር ዳር ከተማ በተካሄደ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፉ ገለጹ።

በድጋፍ ሰልፉ ላይ የአማራ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አመራሮች እና ሠራተኞች የተሳተፉ ሲሆን ምርጫው ሠላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ተዓማኒነት ባለው መልኩ እንዲከናወን የበኩላቸውን ሚና እንደሚወጡ በድጋፍ ሰልፉ ላይ ገልፀዋል።

ለኢንዱስትሪ ልማት ተግተን እንሰራለን!!

የጎንደር የተቀናጀ አግሮ-ኢንዱስትሪ ፓርክ ግንባታ አስመልክቶ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ አረጋ ከበደ ያስተላለፉት መልዕክትዛሬ የጎንደር አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ ግንባታን አስጀ...
24/05/2026

የጎንደር የተቀናጀ አግሮ-ኢንዱስትሪ ፓርክ ግንባታ አስመልክቶ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ አረጋ ከበደ ያስተላለፉት መልዕክት

ዛሬ የጎንደር አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ ግንባታን አስጀምረናል።

የኢኮኖሚ ዕድገት የሚረጋገጠው ጸጋችን በመለየት አቅደን ጠንክረን መስራት ስንችል ብቻ ነው።

የሕዝባችን ጥያቄም በዘላቂነት የሚመለሰው ጸጋችን ለይተን በምንሰራው የጋራ ስራ ነው። የሕዝባችን ተጠቃሚነት እና ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ አቅደን እየሰራን ነው።

ዛሬ ግንባታውን ያስጀመርነው አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ በክልላችን በ25 ዓመት የአሻጋሪ እድገት እና የዘላቂ ልማት ፋኖተ ካርታችን እና በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት እንፈፅማቸዋለን ብለን በዕቅድ ከያዝናቸው ኢንዱስትሪዎች መካከል አንደኛው ነው።

አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርኩ ለበርካታ ዜጎች የስራ እድል በመፍጠር አውንታዊ ሚና ይጫወታል። ለአካባቢው አርሶ አደሮች ሰፊ የገበያ ትስስር ይፈጥራል፤ ወጪ እና ተኪ ምርቶችን ለማምረት ያስችላል።

ቀጣናው በሀገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የግብርና ምርት ዕምቅ አቅም ያለው፤ በተለይ የቅባት እህሎች በስፋት የሚመረቱበት በመሆኑ ያለንን ጸጋ በአግባቡ አልምተን ለመጠቀም እና ዕሴት ለመጨመር ያስችለናል።

የጎንደር አግሮ እንዱስትሪ ፓርክ የግብርና ምርቶችን በማቀነባበር ለአካባቢው የግብርና ልማት ሽግግር እንዲኖር ድልድይ ሆኖ ያገለግላል።

በመሆኑም የኢንዱስትሪ ፓርኩ በተያዘለት ጊዜ ሰሌዳ ውስጥ እንዲጠናቀቅ ልዩ ትኩረት ሰጥተን የምንሰራ ይሆናል።

ግንቦት 16/2018 ዓ/ም

የጎንደር የተቀናጀ አግሮ-ኢንዱስትሪ ፓርክ ለጎንደርና አካባቢው የኢኮኖሚ የስበት ማዕከል ሆኖ ያገለግላል - አቶ አረጋ ከበደየአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ የጎንደር የተቀናጀ አግ...
24/05/2026

የጎንደር የተቀናጀ አግሮ-ኢንዱስትሪ ፓርክ ለጎንደርና አካባቢው የኢኮኖሚ የስበት ማዕከል ሆኖ ያገለግላል - አቶ አረጋ ከበደ

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ የጎንደር የተቀናጀ አግሮ-ኢንዱስትሪ ፓርክ ለአካባቢው የኢኮኖሚ የስበት ማዕከል ሆኖ ያገለግላል አሉ፡፡

ርዕስ መስተዳድሩ ከኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል እና ሌሎች የስራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን የጎንደር የተቀናጀ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክን ግንባታ አስጀምረዋል፡፡ ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ በክልሉ የግብርናና ኢንዱስትሪ ሽግግርን ለማምጣት በትኩረት እየተሰራ ይገኛል።

በአማራ ክልል በቀጣይ አምስት ዓመታት ስምንት የኢኮኖሚ ዞኖች ለማልማት መታቀዱን ጠቁመው፥ የሚያለማውን ባለሀብት መለየትና የልማት መሰረተ ልማቶችን ማሟላት ትኩረት የተሰጣቸው ተግባራት ናቸው ብለዋል፡፡

የአርሶ አደሩን ግብርና ምርትን ጥራት በማሳደግ ለኢንዱስትሪ ፓርኮች መመገብ ከቻለ ሁለንተናዊ የኢኮኖሚ ዋስትና ማረጋገጥ ይችላል ነው ያሉት።

ግንባታው በፍጥነትና በጥራት መጠናቀቅ አለበት ያሉት ርዕስ መስተዳድሩ፥ ለዚህም የአካባቢው መስተዳድርና የሚመለከታቸው አካላት የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ አሳስበዋል።

በክልሉ የአምራች ኢንዱስትሪውን አቅም ለማሳደግ ፓርኮች በስፋት እየተገነቡ ሲሆን፥ ፓርኩ ለአካባቢው የኢኮኖሚ መነቃቃት ተጨማሪ አቅም እንደሚፈጥር ነው የተገለጸው፡፡

የኢንዱስትሪ ሚንስትሩ መላኩ አለበል በበኩላቸው፥ በሀገር አቀፍ ደረጃ 17 የኢንዱስትሪ ዞኖች መለያታቸውን ገልጸው፥ ከእነዚህም ውስጥ ሦስቱ ግንባታቸው ተጠናቋል ነው ያሉት።

የግብርና ምርቶችን እሴት በመጨመር ፓርኮች ወሳኝ ሚና እንዳላቸው የገለጹት ሚኒስትሩ፥ ባለሀብቶችን ወደ ስራ በማስገባት ውጤታማ ስራ ማከናወን እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

የተቀናጀ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርኩ በ8 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ወጪ የሚገነባ ሲሆን፥ ለፓርኩ ስራ ከአካባቢው ለተነሱ አርሶ አደሮች 718 ሚሊየን ብር በላይ ካሳ ተከፍሏል፡፡

ፓርኩ ተጠናቆ ወደ ስራ ሲገባ ለ221 ሺህ ወጣቶች የስራ ዕድል እንደሚፈጥርና በዓመት ከ1 ሚሊየን ቶን በላይ የግብርና ምርቶችን የማቀነባበር አቅም እንደሚኖረው ተገልጿል፡፡

ለኢንዱስትሪ ልማት ተግተን እንሰራለን!!

የአምራች ኢንዱስትሪው ለሀገር ኢኮኖሚ የሚኖረው ሚና ታላቅ መኾኑ ተገለፀ። ይህ የተገለፀው ዛሬ ግንቦት 16/2018 ዓ/ም የጎንደር የተቀናጀ አግሮ-ኢንዱስትሪ ፓርክ ግንባታ ማስጀመሪያ ስነ-ስ...
24/05/2026

የአምራች ኢንዱስትሪው ለሀገር ኢኮኖሚ የሚኖረው ሚና ታላቅ መኾኑ ተገለፀ።

ይህ የተገለፀው ዛሬ ግንቦት 16/2018 ዓ/ም የጎንደር የተቀናጀ አግሮ-ኢንዱስትሪ ፓርክ ግንባታ ማስጀመሪያ ስነ-ስርዓት ላይ ሲሆን በስነ-ስርዓቱ የአምራች ኢንዱስትሪው ለሀገር ኢኮኖሚ የሚኖረው ሚና ታላቅ መኾኑን የአማራ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ብርሃኑ ጣምአለው ገልጸዋል።

የጎንደር የተቀናጀ አግሮ-ኢንዱስትሪ ፓርክ ለሀገር ኢኮኖሚ ትልቅ አቅም እንደሚኾን የገለፁት አቶ ብርሃኑ ጣምአለው ፓርኩ የሚገነባበት ስፋራ ከሦስተኛ ወገን ነጻ ማድረግ መቻሉን ጠቅሰው ፓርኩ ወደ ግንባታ እንዲገባ ድጋፍ ላደረጉ ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል።

አቶ ብርሃኑ አክለውም ግንባታው ተጠናቆ ወደ ስራ ሲገባ ለማክሮ ኢኮኖሚ እድገት ትልቅ አስተዋጽኦ የሚያደርግ እና ግብርናውን እንደሚያዘምን ገልፀው፤ የፓርኩ ግንባታ በተያዘለት ጊዜ እና ጥራት እንዲጠናቀቅ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል።

የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አወቀ አስፈሬ በበኩላቸው የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ብዙ ጸጋዎች ያሉት አካባቢ መኾኑን ገልፀው፤ ባለው ጸጋ ልክ ሳይለማ መቆየቱን ተናግረዋል።

የጎንደር የተቀናጀ አግሮ-ኢንዱስትሪ ፓርክ መገንባት የአካባቢውን ጸጋ ለመጠቀም እንደሚያስችልና የኢንዱስትሪ ፓርኩ የእድገት ተስፋ መኾኑንና የኢኮኖሚ መነቃቃትን እንደሚፈጥርም ገልጸዋል።

ለኢንዱስትሪ ልማት ተግተን እንሰራለን!!

Address

Bahir Dar
74

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amhara Industry Parks Development Corporation posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Amhara Industry Parks Development Corporation:

Shortcuts

Share