Ethiopian Air Force Global Network - የኢትዮጵያ አየር ሃይል ዓለም አቀፍ ሕብረት

  • Home
  • Ethiopia
  • Debre Zeyit
  • Ethiopian Air Force Global Network - የኢትዮጵያ አየር ሃይል ዓለም አቀፍ ሕብረት

Ethiopian Air Force Global Network - የኢትዮጵያ አየር ሃይል ዓለም አቀፍ ሕብረት የኢትዮጵያን አንድነት ለመናድ ሲባል ብቻ ኃላፊነት በጎደለው

©  ቀን: ግንቦት 18 ቀን 2018 ዓ.ም (May 26, 2026)ለክቡር የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትርአድራሻ: አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያጉዳዩ: የብ/ጄኔራል አሸናፊ ገ/ፃዲቅን ብሄራዊ የጀግንነት ታ...
29/05/2026

©

ቀን: ግንቦት 18 ቀን 2018 ዓ.ም (May 26, 2026)

ለክቡር የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር
አድራሻ: አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

ጉዳዩ: የብ/ጄኔራል አሸናፊ ገ/ፃዲቅን ብሄራዊ የጀግንነት ታሪክ ለማስታወስ እና ጥሪ ለማቅረብ የተዘጋጀ ልዩ የድጋፍ ደብዳቤ

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር፤

ለሀገራችን እድገት እና ደህንነት ለምታደርጉት ከፍተኛ አመራር ያለኝን ታላቅ አክብሮት እየገለጽኩ ፣ የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር ኃይል እውቅና ያተረፉ ድንቅ ተዋጊ አብራሪ የሆኑትን የብ/ጄኔራል አሸናፊ ገ/ፃዲቅን ተአምራዊና ታሪካዊ የጀግንነት ውለታ በመጥቀስ፣ በመንግሥት ደረጃ ተገቢው ብሄራዊ እውቅና፣ መታሰቢያ እና የክብር ጥሪ እንዲደረግላቸው ይህንን የድጋፍ ደብዳቤ በታላቅ ኩራት አቀርባለሁ።

ብ/ጄነራል አሸናፊ ገ/ፃዲቅ የውጊያ ጄት (F-5 ተዋጊ አውሮፕላን) እየበረሩ ሳለ በአውሮፕላኑ የፊት ለፊት መደገፊያ እግር (Nose Gear) ሳይወርድ በመቅረቱ ምክንያት ያጋጠማቸውን ከፍተኛ የቴክኒክ ብልሽት እና የተደቀነውን እጅግ አደገኛ ሁኔታ በከፍተኛ ጥበብና ጀግንነት በመወጣት በኢትዮጵያ አቪዬሽን ታሪክ ውስጥ የማይረሳ ደማቅ ታሪክ አስመዝግበዋል።
በወቅቱ ከነበረው የአቪዬሽን መመሪያ አንጻር ራሳቸውን በፓራሹት አስወንጭፈው (Eject አድርገው) ሕይወታቸውን ማዳን የሚችሉበት የተፈቀደ አሰራር ቢኖርም ፣ እሳቸው ግን የሀገር ሀብት የሆነውን ውድ ተዋጊ አውሮፕላን ላለማጣት እና አውሮፕላኑን ያለምንም ቁጥጥር ቢለቁት በድሬዳዋ ከተማ ሰላማዊ ሰዎች ላይ ሊያደርስ የሚችለውን የህይወትና የንብረት እልቂት ለማስቀረት ሲሉ የገዛ ሕይወታቸውን ለአደጋ አጋልጠው አውሮፕላኑን ለማሳረፍ ወስነዋል።

በወቅቱ የድሬዳዋ አየር ማረፊያ የደህንነት ሰራተኞች በማኮብኮቢያው ላይ አረፋ (Foam) ቢረጩም፣ ማረፉ ግን አሁንም እጅግ አስፈሪና አደገኛ ነበር ፤ ሆኖም ብ/ጄነራል አሸናፊ አውሮፕላኑን በጣም በተረጋጋ ሁኔታ በማብረር የኋላ መጋለቢያ እግሮቹ (Main Gears) ብቻ መሬት እንዲነኩ ካደረጉ በኋላ፣ ፍጥነቱ እየቀነሰ በሄደ ቁጥር የፊቱ ክፍል መሬት ደርሶ እንዳይጋይና እሳት እንዳይነሳ የቁጥጥር ዘንጉን (Stick) ወደ ኋላ በመሳብ አፍንጫውን በአየር ላይ አንሳፈው አቆይተውታል። በመጨረሻም አውሮፕላኑ ፍጥነቱን ጨርሶ ሊቆም ጥቂት ሜትሮች ሲቀሩት ብቻ አፍንጫው መሬት እንዲነካ በማድረግ፣ ያለምንም እሳት አደጋ እና ያለ ምንም የሰው ህይወት ጉዳት አውሮፕላኑን በሰላም ማሳረፍ የቻሉ ሲሆን፣ ይህ አስደናቂ የመብረር ብቃት፣ የጸና ዲሲፕሊን እና ለሀገር ንብረት የነበራቸው ተቆርቋሪነት አውሮፕላኑ በወቅቱ ቀላል ጥገና ተደርጎለት ድጋሚ ለበረራ እንዲበቃ አስችሏል።

በመሆኑም ይህንን የመሰለ ለሀገርና ለወገን በራስ ህይወት የመጨከን ታላቅ የጀግንነት ምሳሌነትን ለትውልድ ማስተማሪያ እንዲሆን በታሪክ መዝገብ ጎልቶ እንዲቀመጥ፣ ለጄኔራሉ ብሄራዊ የክብር ጥሪና ተገቢው እውቅና እንዲሰጣቸው ክቡርነትዎ አስፈላጊውን መመሪያ ይሰጡ ዘንድ በአክብሮት እጠይቃለሁ።

ከታላቅ አክብሮት ጋር

ETAF_GlobalNetwork
www.formerethiopianairforce.com

 #የሩሲያ የጦር አውሮፕላኖች በአደገኛ ሁኔታ የብሪታንያ የስለላ አውሮፕላንን Intercept አደረጉ!በጥቁር ባህር ላይ በረራ እያደረገ የነበረ የብሪታንያ የስለላ አውሮፕላንን ሁለት የሩሲያ ...
21/05/2026

#የሩሲያ የጦር አውሮፕላኖች በአደገኛ ሁኔታ የብሪታንያ የስለላ አውሮፕላንን Intercept አደረጉ!

በጥቁር ባህር ላይ በረራ እያደረገ የነበረ የብሪታንያ የስለላ አውሮፕላንን ሁለት የሩሲያ የጦር አውሮፕላኖች "በተደጋጋሚ እና በአደገኛ ሁኔታ" ማቋረጣቸውን (Intercept እንዳደረጉት) የዩናይትድ ኪንግደም መከላከያ ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታወቀ።

የብሪታንያ መከላከያ ሚኒስትር ጆን ሂሊ በሰጡት መግለጫ፣ "ይህ ክስተት የሩሲያ አብራሪዎች በዓለም አቀፍ የአየር ክልል ውስጥ በሚንቀሳቀስ ያልታጠቀ አውሮፕላን ላይ የሚያሳዩት አደገኛ እና ተቀባይነት የሌለው ባህሪ ማሳያ ነው። እነዚህ ድርጊቶች ከባድ የአደጋ ስጋት እና አላስፈላጊ ውጥረትን ይፈጥራሉ" ብለዋል። ሚኒስቴሩ አክሎም፣ የሩሲያው Su-27 የጦር አውሮፕላን ከብሪታንያው አውሮፕላን አፍንጫ እስከ ስድስት ሜትር (19 ጫማ) ርቀት ድረስ ተጠግቶ እንደነበር ገልጾ፣ የክስተቱን የሚያሳይ የ12 ሰከንድ ቪዲዮ ይፋ አድርጓል።

ባለስልጣናቱ እንደገለጹት፣ ይህ ክስተት ከ2022 ወዲህ በብሪታንያ የስለላ አውሮፕላን ላይ የደረሰ እጅግ አሳሳቢው ትንኮሳ ነው። በአዲሱ ክስተት፣ አንደኛው የሩሲያ Su-35 የጦር አውሮፕላን እጅግ ከመጠጋቱ የተነሳ የብሪታንያውን አውሮፕላን የአደጋ ጊዜ መከላከያ ስርዓቶች እንዲነቁ እና ራስ-ሰር የበረራ መቆጣጠሪያው (አውቶፓይለት) እንዲቋረጥ አድርጎታል። በተጨማሪም ሌላኛው 'Su-27' የተሰኘ አውሮፕላን በብሪታንያው አውሮፕላን ፊት ለፊት ስድስት ጊዜ በማለፍ አደገኛ ትንኮሳ ፈጽሟል። ይህ አውሮፕላን በዓለም አቀፍ የአየር ክልል ውስጥ መደበኛ በረራ እያደረገ የነበረው፣ ብሪታንያ ከኔቶ አጋሮቿ ጋር የምታደርገውን የምስራቃዊ ቀጠናን የማስጠበቅ ስራ አካል በመሆን ነበር።

ሚኒስትር ጆን ሂሊ ይህ ክስተት ብሪታንያ ኔቶን፣ አጋሮቿን እና ፍላጎቶቿን ከሩሲያ ጥቃት ለመከላከል ያላትን ቁርጠኝነት ወደኋላ እንደማይመልሰው አስጠንቅቀዋል። ይህ የአየር ላይ ፍጥጫ የተሰማው፣ የብሪታንያ ባህር ኃይል ሦስት የሩሲያ ሰርጓጅ መርከቦችን ከአትላንቲክ ውቅያኖስ አካባቢ ማባረሩን ሚኒስትሩ ካስታወቁ ከጥቂት ቀናት በኋላ ነው። እነዚህ ሰርጓጅ መርከቦች ለአንድ ወር የዘለቀ "ሚስጥራዊ ዘመቻ" በማድረግ ከብሪታንያ በስተሰሜን በሚገኙ ወሳኝ የባህር ውስጥ ኬብሎች እና የነዳጅ ቧንቧዎች አቅራቢያ ሲንቀሳቀሱ እንደነበር ተገልጿል። ሚኒስትሩ በሚያዝያ ወር መጀመሪያ ላይ ለሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ባስተላለፉት መልዕክት፣ በብሪታንያ የባህር ውስጥ ኬብሎች እና የነዳጅ መስመሮች ላይ የሚቃጣ ማንኛውም ሙከራ "ከባድ መዘዝ" እንደሚያስከትል ማስጠንቀቃቸው ይታወሳል።

የዩክሬኑን ጦርነት ተከትሎ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ግንኙነት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ እያሽቆለቆለ ይገኛል። የብሪታንያ መከላከያ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለስልጣናት በዚህ የቅርብ ጊዜ የአየር ላይ ትንኮሳ ዙሪያ በሩሲያ ኤምባሲ በኩል ይፋዊ የቅሬታ ደብዳቤ አቅርበዋል። ይህ የአየር ላይ ማቋረጥ በሁለቱ ሀገራት መካከል እየተባባሰ የመጣው ወታደራዊ ፍጥጫ የቅርብ ጊዜ ማሳያ ሲሆን፣ ከዚህ ቀደም በታህሳስ 2025 እና በህዳር 2025 በተመሳሳይ የሩሲያ ሰርጓጅ መርከቦች እና የስለላ መርከቦች በብሪታንያ የውሃ ክልል አቅራቢያ ትንኮሳዎችን ሲፈጽሙ መቆየታቸውን ዘገባው አስታውሷል።

www.formerethiopianairforce.com

  !The New strategic Change !------------------------------አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የነበረውን የጦር መሳሪያ ገደብ አነሳች ።ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ በኢትዮ...
12/05/2026

!
The New strategic Change !
------------------------------
አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የነበረውን የጦር መሳሪያ ገደብ አነሳች ።

ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ ተጥሎ የነበረውን የጦር መሳሪያ ገደብ እና ከደህንነት ዘርፍ ጋር የተያያዙ እገዳዎችን ማንሳቷ ተሰምቷል። ይህ እርምጃ በሁለቱ ሀገራት መካከል የነበረውን የዲፕሎማሲ ግንኙነት ወደ ተሻለ ደረጃ ለማምጣት የተወሰደ መሆኑ ተገልጿል።

አሜሪካ እገዳውን የጣለችው በ2021 በሰሜን ኢትዮጵያ በተካሄደው የትግራይ ጦርነት ወቅት ነበር። በወቅቱ ዋሽንግተን በጦርነቱ ዙሪያ በተነሱ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እና የሰብዓዊ ቀውስ ምክንያት የጦር መሳሪያ ሽያጭን እና የደህንነት ትብብርን ገድባ ነበር።

አሁን ግን የአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ያለው የፀጥታ ሁኔታ፣ የቀይ ባሕር የንግድ መስመር ጠቀሜታ እና የኢትዮጵያ በቀጠናው ያላት ስትራቴጂካዊ ሚና አሜሪካን አዲስ ውሳኔ እንድትወስድ እንዳደረጋት ተንታኞች ይናገራሉ።

የአሜሪካ መንግሥት በተለይ “በአፍሪካ ቀንድ የሚፈጠሩ የፀጥታ ችግሮችን ለመቆጣጠር ከኢትዮጵያ ጋር ያለው ትብብር አስፈላጊ ነው” የሚል አቋም መያዙ ተጠቁሟል።


www.formerethiopianairforce.com

07/05/2026

የቅጥር ምልመላ ማስታወቂያ

የኢፌዴሪ አየር ኃይል የምልመላ ማስታወቂያ©FDRE Defence Force  በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የኢፌዴሪ አየር ኃይል፤ በተዋጊ አውሮፕላን አብራሪነት እና በቴክኒሽያንነት የሙያ ዘርፎች ...
05/05/2026

የኢፌዴሪ አየር ኃይል የምልመላ ማስታወቂያ
©FDRE Defence Force

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የኢፌዴሪ አየር ኃይል፤ በተዋጊ አውሮፕላን አብራሪነት እና በቴክኒሽያንነት የሙያ ዘርፎች ፍላጎት ያላቸውንና የምልመላ መስፈርቱን የሚያሟሉ ወጣቶችን መልምሎ ለማሰልጠን ይፈልጋል።

✅ አጠቃላይ መመዘኛዎች
• ዜግነት ኢትዮጵያዊ የሆኑ፤
• ለኢፌዴሪ ሕገ-መንግሥት ተገዥ የሆኑ፤
• መልካም ሥነ-ምግባር ያላቸው፣
• በውትድርና ለማገልገልና ሙያው የሚጠይቀውን ሥልጠና ለመውሰድ ፍቃደኛ የሆኑ፤
• የወንጀል ጥፋት ሪከርድ የሌለባቸው ለመሆኑ ከትውልድ ቦታቸው ወይም ከሚኖሩበት አካባቢ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
• ሙሉ ጤንነት ያላቸውና የሕክምና ምርመራ ለመውሰድ ፍቃደኛ የሆኑ፤
• ከዚህ በፊት በውትድርና ወይም በፖሊስነት ያልሰሩና የማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት አባል ያልሆኑ እንዲሁም ትዳር ያልመሰረቱ።

✅ ለትምህርትና ሌሎች መመዘኛዎች
ለተዋጊ አውሮፕላን አብራሪነት የምልመላ መስፈርቶች
• የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ ሆነው ከ2015-2017 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ፈተና ወስደው አጠቃላይ ውጤት 350 እና ከዚያ በላይ ያላቸው፤
• በእንግሊዝኛ፣ በሂሳብ እና በፊዚክስ ትምህርቶች አማካይ ውጤት 50% እና ከዚያ በላይ ያላቸው፤
• እድሜ ከ18-22 ዓመት፣ ቁመት አንድ ሜትር ከ65 እና ከዚያ በላይ እንዲሁም ክብደት ከ50-65 ኪሎግራም የሆኑ።

✅ ለቴክኒሽያንነት የምልመላ መስፈርቶች
• የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ ሆነው በ2015-2017 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስደው አጠቃላይ ውጤት 200 እና ከዚያ በላይ ያላቸው፤
• እድሜያቸው ከ25 ዓመት ያልበለጠ፣ ቁመታቸው 1.65 ሜትር እና ክብደታቸው ከ50-65 ኪሎ ግራም የሆኑ።

✅ ለአጫጭር ኮርስ ሰልጣኞች የመመልመያ መስፈርቶች
• በመጀመሪያ ዲግሪ በሜካኒካል፣ በኤሌክትሪካልና በኮምፒውተር የሙያ ዘርፎች የተመረቁ፤ እንዲሁም በተለያዩ የቴክኒክ ሙያዎች በደረጃ 4 እና በደረጃ 5 ተረምቀው የሲኦሲ ምዘና ውጤት ያላቸው፤
• እድሜ ከ27 ዓመት ያልበለጡና ቁመት 1 ሜትር ከ65 የሆኑ።

✅ የሙያ አይነቶቹን ሙሉ ዝርዝር በየምዝገባ ጣቢያዎቹ የማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ መመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

✅ መስፈርቱን የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች የ8ኛ እና 12ኛ ክፍል ማስረጃዎቻችሁን ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ በመያዝ ቀርባችሁ መመዝገብ የምትችሉ ሲሆን፤ በአየር ኃይል አካዳሚ የሚሰጠውን የመግቢያ ፈተና ማለፍ ይጠበቅባችኋል።

✅ ምዝገባ የሚካሄድባቸው የክልል ከተሞች
• ትግራይ ክልል - መቀሌ
• አፋር ክልል - ሠመራ
• አማራ ክልል - ባህርዳር ፣ጎንደር ፣ ደሴ፣ ደብረብርሃን
• ኦሮሚያ ክልል - አዳማ፣ ቢሾፍቱ ፣ባሌጎባ፣ አሰላ ሻሸመኔ ፣ነቀምት፣ አምቦ፣ ጅማ ፣መቱ፣ ወሊሶ ፣ፊቼ፣ ሸገርሲቲ፤
• ሶማሌ ክልል - ጅግጅጋ
• ቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል - አሶሳ
• ጋምቤላ ክልል - ጋምቤላ
• ሲዳማ ክልል - ሃዋሳ
• ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል - ቦንጋ
• ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል - ሆስአና
• ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል - ወላይታ ሶዶ
• የድሬዳዋ ከተማ መስተዳደር - ድሬዳዋ
• ሀረሪ ክልል - ሀረር
• የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር - አዲስ አበባ

✅ ምዝገባ የሚካሄድባቸው ቦታዎች - በሁሉም የክልል የዞንና የወረዳ ፀጥታ ቢሮዎች ይሆናል።

በኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር የአየር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official

27/04/2026

ብ/ጄ አሸናፊ ገ/ጻድቅ አገር ቤት ከተመለሱ በኋላ ምን ገጠማቸው ?

26/04/2026

ብ/ጄ አሸናፊ ገ/ጻድቅ ከ22 ዓመታት የአሜሪካን ኑሮ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ተመለሱ

©Jemal Abdulaziz ከግፉዓን ኢትዮጵያዊያን ጎን የቆሙት "ቡናማው ጭልፊት” በሚል የጀብዱ ስም የሚታወቁት ኮሎኔል ሮቢንሰን ማን ናቸው?ኮሎኔል ሮቢንሰን ኢትዮጵያ በፋሽት ኢጣሊያ በተወረ...
17/04/2026

©Jemal Abdulaziz
ከግፉዓን ኢትዮጵያዊያን ጎን የቆሙት "ቡናማው ጭልፊት” በሚል የጀብዱ ስም የሚታወቁት ኮሎኔል ሮቢንሰን ማን ናቸው?

ኮሎኔል ሮቢንሰን ኢትዮጵያ በፋሽት ኢጣሊያ በተወረረች ወቅት ዓፄ ሀይለስላሴ ወዳጆቻቸውን ድጋፍ እንዲያደርጉላቸው በጠየቋቸው መሠረት ጥያቄያቸውን ከተቀበሉ የሌሎች ሀገራት ዜጎች መካከል አንዱ ነበሩ፡፡

"ቡናማው ጭልፊት” The brown condor በሚል የጀብዱ ስም የሚጠሩት ኮሎኔል ጆን ቻርለስ ሮቢንሰን ትውልዳቸው አሜሪካ ሲሆን በ1903 በፍሎሪዳ ነበር የተወለዱት። በአሜሪካ ሰራዊት ውስጥ የኮሎኔልነት ማዕረግ ያገኙት ኮሎኔል ጆን ቻርለስ ሮቢንሰን ጥቁር አፍሪካዊ አሜሪካዊ ናቸው። በወጣትነት ዘመናቸው የአውሮፕላን አብራሪነት ሙያን የተቀላቀሉት ኮሎኔል ጆን ቻርለስ ሮቢንሰን ለኢትዮጵያ ባለውለታ ከሆኑ የውጭ ሀገር ዜጎች መካከል ተጠቃሽ ናቸው።

ጀት አብራሪው ሮቢንሰን ከኢትዮጵያውያን ጎን በመቆም ከ700 በላይ ሰዓታት በረራ በማድረግ ፋሽስት ኢጣሊያንን በጀት ተዋግተዋል፡፡ ሮቢንሰን ከኢትዮጵያ ነጻነት መልስ በኋላም ቢሆን ወደ ሀገራቸው ከመመለስ ይልቅ የኢትዮጵያ አየር ሀይል ባልደረባ ሆነው በርካታ ኢትዮጵያውያንን የአየር በረራና የቴክኒክ ትምህርት ያስተማሩ ባለውለታችን ናቸው፡፡

25 ዓመትትን ያበረሩት ኮሎኔል ሮቢንሰን በሌላ የአውሮፕላን አደጋ ለተጎዳ ሰው ደም በማስፈለጉ ምትክ ደም ይዘው ህይወት ለማትረፍ ከአዲስ አበባ ወደ ናዝሬት ሲጓዙ በችኮላ ምክንያት በተፈጠረ የበረራ ስህተት በልዕልት ፀሐይ ሆስፒታል ግቢ ውስጥ አውሮፕላኗ በመከስከሷ የመቁሰል አደጋ ደረሰባቸው፡፡ በዚህ ሳቢያም ከአስር ቀናት የህክምና ቆይታ በኋላ ህይወታቸው ውለታ በዋሉላት ምድር አለፈ፡፡ ቀብራቸውም በአዲስ አበባ ቅዱስ ጴጥሮስ ወጳውሎስ ተፈጽሞ ሀውልት ቆሞላቸዋል።


www.formerethiopianairforce.com

የኢትዮ-ሶማልያ ጦርነት ዕውቅ ጀግና ብ/ጄ አሸናፊ ገ/ፃድቅ ከ22 ዓመታት የስደት ኑሮ በኋላ  መጋቢት 22 ቀን 2018 ዓም  ማለዳ አዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ደርሰዋል...
12/04/2026

የኢትዮ-ሶማልያ ጦርነት ዕውቅ ጀግና ብ/ጄ አሸናፊ ገ/ፃድቅ ከ22 ዓመታት የስደት ኑሮ በኋላ መጋቢት 22 ቀን 2018 ዓም ማለዳ አዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ደርሰዋል ።

ጄ/ል አሸናፊ በ1969 ዓም የሶማልያ መንግስት የሀገራችንን ምስራቃዊ እና ደቡብ ምስራቅ ግዛት በዕብሪት በወረረበት ወቅት በግምባር በመሰለፍ እና የጠላትን አውሮፕላን አየር ላይ በማጋየት ድንቅ ጀብዱ ከፈፀሙት የሀገራችን ጀግኖች መካከል አንዱ መሆናቸው የሚታወስ ነው ።

ጄ/ል አሸናፊ በ1983 ዓም የመንግስት ለውጥን ተከትሎ ከአስር አመታት በላይ የአለ አንዳች ፍርድ በእስር እንዲማቅቁ ከተደረጉ በኋላ ወደ አሜሪካ የመምጣቱ ዕድል ገጥሟቸው ለ22 ዓመታት ከቤተሰቦቻቸው ተለይተው በስደት ለመኖር ተገደዋል ። ከሁሉም በላይ የሕይወት አጋራቸው ባለቤታቸው ከዚህ አለም ድካም ሲያርፉ አፈር ለማልበስ እንኳ ሳይችሉ ቀርተዋል ።

ጄ/ል አሸናፊ ገ/ፃድቅ የስደት ዘመናቸው አብቅቶ በሕይወት መስዋዕትነት በመክፈል ነፃነቷን አስከብራ እንድትኖር ወደ አደረጓት ውድ ሀገራቸው ለመመለስ በመታደላቸው የኢትዮጵያ አየር ኃይል ግሎባል ኔትዎር እንኳን ደስ አልዎት በማለት ደስታውን ይገልፃል ።

www.formerethiopianairforce.com

From G/L Ashenafi album

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዛሬ 80 ዓመት ሞላውየኢትዮጵያ አየር መንገድ የዛሬ 80 ዓመት (መጋቢት 30 ቀን 1938 ዓ.ም) በአነስተኛ አውሮኘላን ከአዲስአበባ በአስመራ በኩል ወደካይሮ የመጀመ...
09/04/2026

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዛሬ 80 ዓመት ሞላው

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የዛሬ 80 ዓመት (መጋቢት 30 ቀን 1938 ዓ.ም) በአነስተኛ አውሮኘላን ከአዲስአበባ በአስመራ በኩል ወደካይሮ የመጀመሪያውን በረራ አደረገ። ዛሬ ከ80 ዓመት በኋላ 150 እጅግ ዘመናዊ አውሮፕላኖችን በመያዝ ወደ 145 መዳረሻዎች በረራዎችን በማድረግ በዓለም አቀፍ ደረጃ ስመጥር ከሆኑ አየር መንገዶች አንዱ ለመሆን በቅቷል።

አቶ መስፍን ጣሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩኘ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ለተቋሙ ሠራተኞች (የቀድሞዎቹን ጨምሮ) እንዲሁም አጋሮች እንኳን ደስ አላችሁ ካሉ በኋላ አየር መንገዱ ባለፉት 80 ዓመታት ከአንድ አውሮኘላን በረራ ተነስቶ በአሁን ጊዜ በበረራ ብቻ ሳይሆን በአውሮፕላን ጥገና፣ በስልጠና፣ በተቋም ግንባታ፣ በአውሮኘላን ማረፊያዎች ጥገናና ግንባታ እንዲሁም በሆቴል... ተደጋጋፊ በሆኑ ዘርፎች መሰማራት ችሏል። ይኸም አየር መንገዱ የአቪየሽን ግሩኘ ወደመሆን ማሳደግ ችሏል ብለዋል።

አየር መንገዱ በአሁን ሰዓት 150 ዘመናዊ አውሮፕላኖች በመያዝ፣ ከ28 ሺ በላይ ሰራተኞቹ እየታገዘ በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ መሆን መቻሉን በአሁን ሰዓት ተጨማሪ 117 አውሮኘላኖች ማዘዙን ጠቅሰዋል።

አየር መንገዱ ከገጠሙት ተግዳሮቶች አንዱ የኮቪድ ሕመምን ተከትሎ የተከሰተው ችግር መሆኑን በማስታወስ በወቅቱ በርካታ አለምአቀፍ አየር መንገዶች ለኪሳራ ሲዳረጉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ችግሩን በጥበብ ማለፉን አቶ መስፍን ተናግረዋል።

በአሁን ሰዓት የኢራንን ጦርነት ተከትሎ የነዳጅ ዋጋ ወደእጥፍ የሚጠጋ ጭማሪ ማስከተሉ ፈተና መሆኑን በመጥቀስ ይህንን ወጪዎችን በመቀነስና በቲኬት ላይ መጠነኛ ጭማሪ በማድረግ ለማለፍ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ጠቅሰዋል።

የአየር መንገዱ 80ኛ ዓመት በተለያዩ መርሐግብሮች ለቀጣይ 6 ሳምንታት እንደሚከበር ተገልጿል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ 10 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር ወጪ በቢሾፍቱ ከተማ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ከ3 ወራት በፊት ማስጀመሩ የሚታወስ ነው።


www.formerethiopianairforce.com

Address

Debre Zeyit

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Air Force Global Network - የኢትዮጵያ አየር ሃይል ዓለም አቀፍ ሕብረት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Ethiopian Air Force Global Network - የኢትዮጵያ አየር ሃይል ዓለም አቀፍ ሕብረት:

Share