25/08/2025
ለወጣት ፈጠራ ባለሞያዎች የቀረበ የስልጠና ጥሪ
=============================
በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ስር የሚገኘው የኢትዮጵያ ባለ ተሰጥኦና ተውህቦ ማበልጸግ ትምህርት ቤት የአጭር ጊዜ የሥልጠና መርሃ ግብሮች በተለያዩ ዘርፎች አዘጋጅቶ በመመዝገብ ላይ ይገኛል።
👉 የስልጠና ዘርፎቹ
🌐 ዲጂታል እና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ
🤖 ሮቦቲክስ እና ኤሌክትሮኒክስ
🛰 አስትሮኖሚ እና የጠፈር ቴክኖሎጂ
🧬 ባዮቴክኖሎጂ
🔬 ስቴም
👉 ስልጠናውን ለመውሰድ ማን ማመልከት ይችላል?
✔️ እድሜ 15-21
✔️ በሳይንስ ወይም በፈጠራ ሀሳቦች የተሻለ አፈጻጸም ያለው
✔️ ሃሳባቸውን ለመግለጽ የ3 ደቂቃ ቪዲዮ ማስገባት የሚችል
👉ምዝገባው የሚጠናቀቀው፡ ጷግሜ 2/2017/ ሴፕቴምበር 7፣ 2025
👉የምዝገባው ሊንክ 👉 https://egate.et ነው።
👉በስልጠናው ዙርያ ለጥያቄዎች ካሏችው፡-
📞 +251 925 518 888
📧 [email protected]
ተሰጥኦና ተውህቦን ማበልጸግ የነገውን ትውልድ በመቅረጽ ውስጥ የማይተካ ድርሻ አለው!
EGATE provides high-quality training, mentorship and opportunities in Digital and Emerging technologies, Robotics and Electronics, Astronomy and Space Technology, Biotechnology and STEAM.