11/12/2024
የከፍተኛ ኃይል ተጠቃሚ ደንበኞች ቆጣሪዎች ሙሉ በሙሉ በኤ.ኤም.አይ ስማርት ቆጣሪዎች ተቀየሩ
**********************
በመላው ሃገራችን ያሉ የከፍተኛ ኃይል ተጠቃሚ ደንበኞች ነባር ቆጣሪዎች ሙሉ በሙሉ በኤ.ኤም.አይ ስማርት ዘመናዊ ቆጣሪዎች መቀየራቸውን የኤ.ኤም.አይ ፕሮጀክት ኃላፊ አቶ ዘሪሁን አበበ ገለጹ፡፡
ከ24 ኪሎ ዋት በላይ ተጠቃሚ የሆኑ 39,463 ከፍተኛ ኃይል ተጠቃሚ ደንበኞች ኤሌክትሮ ሜካኒካል ቆጣሪዎች ሙሉ በሙሉ በኤ.ኤም.አይ (Advanced Metering Infrastructure – AMI) ስማርት ቆጣሪዎች መቀየራቸውን ተናግረዋል፡፡
የ50 ሺህ ከፍተኛ ኃይል ተጠቃሚ ደንበኞችን ቆጣሪዎች በኤ.ኤም.አይ ስማርት ቆጣሪዎች ለመቀየር የታቀደ ቢሆንም ያሉት ደንበኞች 39,463 ብቻ በመሆናቸው ለነዚህ ደንበኞች ሙሉ በሙሉ መቀየሩን ኃላፊው ጠቅሰዋል፡፡
ቀሪዎቹ 10,537 ኤ.ኤም.አይ ስማርት ቆጣሪዎች ደግሞ ለአዲስ ደንበኞች እንዲውሉ ተደርጓል ብለዋል፡፡
ኤ.ኤም. አይ. ስማርት ቆጣሪ የቆጣሪ ስርዓቱ ከሰው ንክኪ ነፃ በመሆኑ ትክክለኛ የክፍያ ትዕዛዝ እንዲዘጋጅ እያገዘ እንደሚገኝም ገልጸዋል፡፡
ደንበኞችም የዚህ ስማርት ቆጣሪ ተጠቃሚ በመሆናቸው ካሉበት ቦታ ሆነው የኤሌክትሪክ ፍጆታቸውን መከታተል ችለዋል ብለዋል፡፡
ነባሮቹ ኤሌክትሮ ሜካኒካል ቆጣሪዎች ከፍተኛ እድሜ ያስቆጠሩ በመሆናቸው በትክክል የኤሌክትሪክ ኃይል ፍጆታን ለመለካት አያስችሉም ነበር ሲሉ አቶ ዘርይሁን ገልጸዋል፡፡
በአሁኑ ሰዓት በኤ.ኤም.አይ ስማርት ቆጣሪ አማካኝነት ደንበኞች ትክክለኛ የፍጆታ ክፍያ እንዲከፍሉ ተቋሙም ትክክለኛ የኃይል ፍጆታ ሂሳብ እንዲሰበስብ ማድረግ ተችሏል፡፡
ከኤ.ኤም.አይ ስማርት ቆጣሪዎች የኃይል መቆራረጥን ድግግሞሽና ኤሌክትሪክ ተቋርጦ የሚቆይበትን መረጃ ማግኘት የተቻለ ሲሆን ይህም በቀጣይ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመሮች ላይ የማስተካከያ ስራ ለመስራት እንደሚያግዝ ይታመናል፡፡

Ethiopian Electric Utility -የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት