Abebe Alemu

Abebe Alemu Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Abebe Alemu, Mining Company, 12, Jijiga.

09/06/2024

24.6K likes, 338 comments. “አቡነ የማታ ገዳም”

25/11/2021

ችግር ያሳድጋል!
ችግርዎን ይጋፈጡ እንጅ ከችግርዎ አይሽሹ።

☞ ኑሮ በየቀኑ የምንወጣው ተራራ ነው፡፡አንዱን ጨርሰን ስንደሰት ሌላኛው ይደቀናል፡፡ሌላኛውን ስንወጣ የባሰው ደግሞ ይጠብቅናል፡፡

☞ የማያቋርጥ ስቃይ አለብን፡፡ስቃዩ ግን ጥሩ ነው፡፡ትክክለኛ አቅማችን የሚወጣው ከትክክለኛ ፈተና ጋር ስንታገል ነው፡፡

☞ ብዙ ሰው ከፊቱ ያለውን ተራራ ግዝፈት እንጂ በውስጡ ያለውን የፈጣሪን ጉልበት አያውቅም፡፡ ተራራው ከፊትለፊቱ ሲደቀን የሚወጣበትን መንገድ ከመፈለግ ይልቅ ማማረርን ይመርጣል፡፡ምክንያቱም ማማረር ቀላል ነዋ፡፡

☞ ማለቃቀሱን ማንም ያውቅበታል፡፡ወደ ተራራው ጫፍ የሚወስደውን መንገድ ማግኘት ግን ከባድ ነው፡፡ይህ የጥቂት ጀግና ሰዎች ስራ ነው፡፡ላብ፣ ደምና እንባ ማፍሰስን ይጠይቃል፡፡ብዙ ሰዎች ደግሞ ይህን ማድረግ አይፈልጉም፡፡ ፊሪ እና ሰነፎች ናቸው፡፡በራሳቸው ጉልበት ፤ በፈጣሪያቸውም ሐይል እምነት የላቸውም፡፡ ምኞታቸው ሁሉም ነገር አልጋ በአልጋ አንዲሆን ነው፡፡ህይወት ደግሞ ተራራ በተራራ እንጂ አልጋ በአልጋ አይደለም፡፡

☞ ዓለም አሁን ካለችበት ከፍታ የደረሰችው በችግር ነው፡፡ችግር ባይኖር? ሰዎች ዛሬም ድረስ በዋሻ ውስጥ ነበርን፡፡መብራት፣ መኪና፣ እርሻ፣ ፕሌን፣ ኢንተርኔት፣ ስልክ፣ ኮምፒውተር፣ ቤትና ሁሉም ለሰው ልጆች ጠቃሚ የሆኑ ነገሮች የተወለዱት በችግር ምክንያት ነው፡፡ሰዎች ችግራቸውን ለማሸነፍ ሲታገሉ ዛሬ ፍጹም ልዩ የሆነ አለም ፈጥረዋል፡፡ ታዲያ ምስጋና ለአቶ ችግር አይገባም ትላላችሁ?

☞ ከፊትለፊታችሁ ያለው ተራራ ምንድን ነው? ችግራችሁ ምንድን ነው? ገንዘብ ማጣት? ስራ አጥነት? የተበላሸ ትዳር? ስደት? በሽታ? በራስ መተማመን ማጣት? ሱስ? ምንድን ነው?

☞ ችግራችሁን የምትመለከቱትስ እንዴት ነው? ተራራችሁን የምታዩት እንዴት ነው? ሊያሳድጋችሁ እንደመጣ ስጦታ? ወይስ ሊያስቆማችሁ እንደመጣ ፈተና?

ይህ የምርጫ ጉዳይ ነው፡፡ብዙ ሰው ችግሩን እንደ ጠላት ይመለከታል፡፡ችግራችሁን እንደ ወዳጅ አድርጋችሁ ካያችሁ ግን እናንተ ትክክለኛ ጀግና ናችሁ፡፡ እሱን ለማሸነፍት ስታነቡ፣ ሰው ስታማክሩ፣ ሞያ ስትለማመዱ፣ ስትነግዱ፣ ገንዘብ ስትቆጥቡ፣ ጸሎት ስታደርጉ ፍጹም ሌላ ሰው ትሆናላችሁ፡፡ ሌሎች ከታች ሆነው ሲያማርር እናንተ ከተራራው ጫፍ ትደርሳላችሁ፡፡ከአናቱ ሆናችሁ ንፁህ አየር ትምጋላችሁ፡፡በከፍታው ያለውን ቪውም enjoy ታደርጋላችሁ፡፡ሌላ ችግር ሲጋረጥባችሁም አትደናገሩም፡፡ሌላ መፍትሄ ፈልጋችሁ ታሸንፉታላችሁ፡፡
©ማንያዘዋል እሸቱ - Psych ጤና

04/03/2021
18/06/2020

በ2012 በጀት ዓመት 11 ወራት ውስጥ ወደ ውጪ ከተላከ ሥጋ እና ወተት ምርት ከ68 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ተገኘ
*******************
በ2012 በጀት ዓመት 11 ወራት ውስጥ ወደ ውጪ ከተላከ የሥጋ እና ወተት ምርት 68 ነጥብ 13 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገቢ መገኘቱን የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገለጸ።

ይህ የተገለጸው የሥጋ እና ወተት ኢንስቲትዩት የ2012 በጀት ዓመት የ11 ወራት የኤክስፖርት አፈጻጸምን በዘርፉ ከተሰማሩ ባለድርሻ አካላት በተገመገመበት ወቅት ነው።

በበጀት ዓመቱ 11 ወራት ከሥጋ እና ወተት 113 ነጥብ 81 ሚሊየን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ 68 ነጭብ 13 ሚሊዮን ዶላር ገቢ የተገኘ ሲሆን፣ ከበግ እና ፍየል ሥጋ 61 ነጥብ 31 ሚሊዮን ዶላር፣ ከዳልጋ ከብት 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ዶላር፣ ከእንስሳት ተረፈ ምርት 2 ነጥብ 93 ሚሊዮን ዶላር እንዲሁም ከማር፣ ከሰም፣ ከዓሣ ምርት እና ከወተት 2 ነጥብ 60 ሚሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱ ተገልጿል።

የእርድ እንስሳት አቅርቦት ጥራት ችግር፣ የእንስሳት ማቆያ እጥረት፣ የብድር አቅርቦት እጥረት፣ ሕገ ወጥ የቁም እንስሳት ንግድ እና የመብራት መቆራረጥ የተነሣ የተያዘውን እቅድ ሙሉ በሙሉ መፈጸም አለመቻሉን የሥጋ እና ወተት ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲቱት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ መኮንን ጋሹ ተናግረዋል።

በንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የንግድ ማስፋፊያ ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ በበኩላቸው፣ ከሚፈለገው አካል ያለመድረስ እንጂ የአቅርቦት ችግር የለም፤ በአቅራቢዎች እና በቄራዎች መካከል ቀጥተኛ ግንኙነት እንዲኖር እና የአቅርቦት ሠንሰለቱን ለማሳጠር እንሠራለን ብለዋል።

ዘርፉ አትራፊ ሆኖ አርብቶ አደሩ ተጠቃሚ የሚሆንበት አሠራር በመዘርጋት እና የወጪ ንግድ መነሻ የሚሆን ዋጋ በማዘጋጀት ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ እንደሚሠራ መናገራቸውን ከንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ አመልክቷል።

የምንሰራቸውን ዜናዎች በትክክለኛው ቴሌግራም ቻናላችን ለማግኘት ቀጣዩን ሊንክ ይጠቀሙ
https://t.me/EBCNEWSNOW

07/05/2020
04/04/2020

Share! Share! Share!

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
ርእሰ ባሕታውያን ሊቀ አእላፍ ቆሞስ አባ ዮሐንስ ተስፋ ማርያም ከኢትዮጵያ ውጭ በተለያዩ ሀገራት ከሚኖሩ፣ በጸሎታቸው ከተለያዩ በሽታዎች ከተፈወሱ፣ ከሰይጣን ማሰሪያ ከተፈቱ፣ በረከት ካገኙና ‹‹ትጋት የአባ ዮሐንስ የመንፈስ ቅዱስ ፍሬዎች›› በሚል በአንድነት በማኅበር ከተሰባሰቡ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻቸው ጋር በመሆን በተለያዩ ጊዜያት የበጎ አድራጎት ሥራዎችን እየሠሩ እንደሚገኙ ይታወቃል፡፡ አሁንም በእንባ፣ በጸሎት እግዚአብሔርን ከመለመንና ሕዝቡ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ከማስተማር ጋር በመላው ዓለም ላይ የተከሰተውንና ምድራችን እያስጨነቀ ያለውን የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል ድጋፍ እንዲያደርጉ በተጠየቁት መሰረት ለአማራ ክልል በሽታውን ለመከላከል የሚውልና ለጎዳና ተዳዳሪዎች ድጋፍ የሚሆን 1,685,000 (አንድ ሚሊየን ስድስት መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ) ብር ድጋፍ አድርገዋል፡፡ ይህም ለአማራ ክልል ጤና ቢሮ ለሕክምና እቃዎች መግዣና ለጎዳና ተዳዳሪዎች ድጋፍ የሚሆን 1,000,000 (አንድ ሚሊየን) ብር፣ እንዲሁም የደቡብ ጎንደር ዞን ጤና ጥበቃ መምሪያ በአጠቃላይ በዞኑ ውስጥ ለሚገኙ ለሁሉም ወረዳዎች ለሕክምና ቁሳቁስ መግዣና ለጎዳና ተዳዳሪዎች ድጋፍ የሚሆን 585,000 (አምስት መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ) ብር ድጋፍ ያድርጉልን ብሎ በጠየቀው መሰረት 585,000 (አምስት መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ) ብር ድጋፍ አድርገዋል፡፡ በዞኑ ውስጥ ላሉ ሁሉም ወረዳዎች በዞኑ ጤና መምሪያ በኩል ከተደረገው ድጋፍ ሌላ ደራ ወረዳ ተጨማሪ የ100,000 ብር እርዳታ ያሥፈልገናል ብለው በመጠየቃቸው የ100,000 (አንድ መቶ ሺህ) ብር ድጋፍ ተደርገላቸዋል፡፡ እንዲሁም በዚሁ በደራ ወረዳ ከአራት መቶ በላይ የሚሆኑ አመራሮች ለአምስት ቀናት ላደረጉት ስብሰባ ድጋፍ በጠየቁት መሰረት አባታችን አባ ዮሐንስ ተስፋ ማርያም በስብሰባው መክፈቻና መዝጊያ ቀናት በመገኘት ስለ ልማት፣ ስለ ጸጥታና ስለጤና አስደሳች የሆነ ትምህርት ሰጥተው የጠየቁትን 123,800 (አንድ መቶ ሃያ ሦስት ሺህ ስምንት መቶ) ብር ድጋፍ ያደረጉላቸው ሲሆን በአጠቃላይ ከ1,808,000 (አንድ ሚሊየን ስምንት መቶ ስምንት ሺህ) ብር በላይ ድጋፍ አድርገዋል፡፡ አባታችን አባ ዮሐንስ ተስፋ ማርያም ከዚህም በፊት ከትጋት የአባ ዮሐንስ የመንፈስ ቅዱስ ፍሬዎች ማኅበር ጋር በመሆን በ2011 ዓ.ም በሰሜን ጎንደር ለተፈናቀሉ ወገኖች የ1,000,000 (አንድ ሚሊየን) ብርና የ300 ኩንታል እህል ድጋፍ ማድረጋቸውና በአንበሳሜ ከተማ ዘመናዊ ትምህርት ቤት ሠርተው ማስረከባቸው አይዘነጋም፡፡ እንግዲህ፡- ብርሃንን ሠራሁ፥ ጨለማውንም ፈጠርሁ ደኅንነትን እሠራለሁ፥ ክፋትንም እፈጥራለሁ፤ እነዚህን ሁሉ ያደረግሁ እግዚአብሔር እኔ ነኝ። ኢሳ. 45÷7 ተብሎ እንደተጻፈ በቸርነቱ ሰላምንና ጤናችንን የሚሰጠንም ደግሞም ስናጠፋ የሚገስጸንም እሱ አምላካችን እግዚአብሔር ስለሆነ በሰው ልጆች ላይ እየደረሰ ያለውን ክፉ መቅሰፍት በመሐሪነቱ ያስወግድልን፤ በይቅርታው ይጎብኘን፡፡

03/02/2020

#ከገባሽ ስሚኝ ልንገርሽ…
****\\\\\\\\\\\\\\\\\\\\\*****
#ውበትሽን አይቶ የተመኘሽ እና ውስጥሽን(ስብእናሽን)
አይቶ ያፈቀረሽ ሰው #የተለያዩ ናቸው።
#ለምን ነገርከኝ እንዳትይኝ??? ምክንያቱም አስብልሻለዋ!!!

#እኛ ወንዶች ስንባል የፈለግነውን ነገር እስክናገኝ ድረስ ሴትን ልጅ ንግስት ማድረግ እናውቅበታለን። #ከልቡ ያፈቀረ ሰው ግን ተብታባ ነው። ውሸትን ለመግለፅ እንኳን አንደበት የለውም። ነገር ግን በውስጣዊ ማንነትሽ ተማርኮና እጅ ሰጥቶ የቀድሞ ማንነቱን ወዲያ አሽቀንጥሮ ጥሎ ሌት ተቀን አንችን በምናቡ ሲያወጣ እና ሲያወርድ ፣ ያንቺን ህይወት ለማድመቅ የራሱን ሲያፈዝ ፣ ከሰው በላይ የነበረው ላንቺ ፍቅር ሲል መቀመቅ ሲወርድ ፡ ያኔ ላንቺ ያንስብሻል። ያኔ ላንቺ ተራ ሰው ይመስልሻል።
#እናም ፍቅርሽን ሳይሆን ገላሽን ለተመኘው ትሰጪና ዳግም ብትፈጠሪ እንኳን ዳግመኛ የማታገኝውን ንፁህ አፍቃሪሽን ልብ አንኮታኩተሽ እንዳይሽር እንዳይድን አርገሽ ትሰብሪዋለሽ።
#እሱም ለዘላለም ልቡ ታሞበት እንደማቀቀ ፍቅሩን ተቀምቶ አዝኖ ቁርጡን አውቆ ይቀመጣል።
#አንቺ ግን ሳታውቂው ከፍቅር ፊልሞች ላይ ባየው አማላይ ቃላቶች ወይም ከፊክሽን መፅሀፎች ላይ በሸመደደው የሽንገላ ቃላቶች ያታለለሽ ሰው ግን ከአንድ ለሊት መኝታ በኋላ ለአይኑ እንኳን ይጠየፍሻል።
#በቃላት ድርደራ በስጦታ ጋጋታ ንግስት ያስመሰለሽ ሰው ያሻውን ፈፅሞ ሲያበቃ የሰናፍጭ ቅንጣት ያህል እንኳን ዋጋ አይሰጥሽም ፡ ከጥፍሩ ቆሻሻ እኩል እንኳን አይቆጥርሽም።

#እናም ሄዋኔ ለዚህ ነው የተመኘሽ እና ያፈቀረሽ የተለያዩ ናቸው ያልኩሽ።99 ነጥብ።
************* ጨ ፡ ረ ፡ ስ ፡ ኩ ፡ ***********
>ውጫዊ ውበት ቀልብን ይስባል >>>ውስጣዊ ማንነት ግን ልብን ያስገዛል

Address

12
Jijiga

Telephone

+251920669312

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Abebe Alemu posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Abebe Alemu:

Share

Category