Ethiopia Electric Utility Oromia Region Nekemt District

Ethiopia Electric Utility Oromia Region Nekemt District EEU is a public Enterprise with the main responsibility of distributing electricity.
'light for all'

23/11/2024
04/10/2024

ውድ #የድህረ ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኛችን በመስከረም ወር የተጠቀሙበትን ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ እንዴት ማስላት እንዳለብዎ ያውቃሉ? ካለወቁ በምሳሌ እናስረዳዎ!!

አንድ ደንበኛ በመኖሪያ ቤቱ 4 ባለ 60 ዋት አምፖሎች በቀን ለ6 ሰዓት በወር ለ30 ቀናት ቢያበራ፣ 3000 ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የሚጠቀም የእንጀራ ምጣድ በቀን ለ2 ሰዓት በወር ለ10 ቀናት ቢጠቀም እና 1000 ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የሚጠቀም ምድጃ በቀን ለ5 ሰዓት በወር ለ30 ቀናት ቢጠቀም ፤

በዚህም መሰረት፡-
1ኛ. 4 አምፑል X 60 ዋት x 6 ሰዓት x 30 ቀናት = 43,200 ዋት.ሰ፣
2ኛ. 3000 ዋት ኤሌክትሪክ የኃይል የሚጠቀም የእንጀራ ምጣድ x 2 ሰዓት x 10 ቀናት=60,000 ዋት.ሰ፣
3ኛ.1000 ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የሚጠቀም ምድጃ x 5 ሰዓት x ለ30 ቀናት = 150,000 ዋት.ሰ፣
ሶስቱም ሲጠቃለሉ 43,200 ዋት.ሰ + 60,000 ዋት.ሰ + 150,000 ዋት.ሰ = 253,200 ዋት.ሰ ይሆናል፡፡

ይህም ወደ ኪሎ ዋት ሰዓት ሲቀየር 1 ኪሎ ዋት ሰዓት = 1000 ዋት ሰዓት በመሆኑ፤ 253,200 ዋት ሰዓት = 253.2 ኪሎ ዋት ሰዓት ይሆናል፡፡

በዚህ ስሌት መሰረት ከላይ በምሳሌው የጠቀስነው ደንበኛ በወር 253.2 ኪ.ዋ.ሰ የኤሌክትሪክ ኃይል ቢጠቀም በተቀመጠው እርከን መሰረት በ2.46 ብር ይባዛል፡፡
በዚህ መሰረት 253.2 ኪ.ዋ.ሰ x 2.46 ብር= 622.872 ብር ይመጣል፡፡ የአገልግሎት ክፍያ ብር 42.95 እና የቴሌቪዥን አገልግሎት ክፍያ 10 ብር ሲደመርበት በአጠቃላይ የደንበኛው ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ 675 ብር ከ 80 ሳንቲም ይሆናል ማለት ነው፡፡

ይህ የፍጆታ ሂሳብ ስሌት የሚያገለግለው ለድህረ-ክፍያና ለመስከረም ወር ብቻ ነው፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

28/09/2024
24/09/2024

በቤት ውስጥ የሚኖረን የኤሌክትሪክ አጠቃቀም እና ልናደርጋቸው የሚገቡ ቅድመ ጥንቃቄዎች 👇

👉የኤሌክትሪክ አገልግሎት ለአንድ ሃገር ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት የሚያበረክተው አስተዋጾ እጅግ ከፍተኛ ቢሆንም በአጠቃቀምና ጥንቃቄ ጉድለት ምክንያት በአካል እና በንብረት ላይ ጉዳት ብሎም ሞት ሲያስከትል ይስተዋላል፡፡

👉ተቋሙ አዲስ ደንበኞቹን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ የመስመር ዝርጋታ የሚያከናውነው እስከ ቆጣሪ ድረስ ያለውን በመሆኑ ከቆጣሪ በኋላ በቤት ውስጥ የሚከናወኑ የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታዎች በቂ ልምድ ባለው ባለሞያና ደረጃቸውን በጠበቁ የኤሌክትሪክ ቁሳቁሶች መሆን ይኖርበታል፡፡

👉ደንበኞች በቤት ውስጥ ሆነ ከቤት ውጪ የሚጠቀሙባቸው ማንኛውም የኤሌክትሪክ ቁሳቁሶች ከህፃናት ዕይታ ማራቅ እንደሚያስፈልግና ለጊዜው የማይጠቀሙባቸውን የኤሌክትሪክ መገልገያ ቁሳቁሶችን ከሶኬት ላይ ነቅሎ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል ፡፡

👉ከዚህ በተጨማሪም ለኤሌክትሪክ አደጋ ስጋት የሚሆኑ ቁሳቁሶችን ማስወገድ፤ እርጥበት እና እርጥበት አዘል ሁኔታዎችን ከኤሌክትሪክ አካባቢ ማስወገድ፣ ትክክለኛ እና ደረጃቸውን የጠበቁ የኤሌክትሪክ ቁሳቁሶችን መጠቀም አስፈላጊ ነው፡፡

👉የቤት ውስጥ የመስመር ዝርጋታ የሚያከናውን አካል ቅድሚያ ከቆጣሪ ኤሌክትሪክ በማቋረጥ ሁሌም በጥንቃቄ እና ሀሳቡን ሰብስቦ ስራውን በትኩረት ሊያከናውን ይገባል፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

24/09/2024

አገልግሎት ጠያቂ ድርጅቶችና ግለሰቦች በራሳቸው አቅም ግብዓት በማቅረብ ሊገነቡ የሚችሉበት አሰራር ተተግብሯል

18/09/2024

በከፍተኛ ኃይል አስተላላፊ መስመር ላይ ባጋጠመ ብልሽት ምክንያት የተቋረጠ የኃይል አቅርቦት

ከመንዲ እስከ አሶሳ የተዘረጋ 132 ኪ.ቮ ከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ ባጋጠመ ብልሽት ምክንያት

👉 በአሶሳ ከተማ፣ ባምባሲ፣ ኡራ፣ አብራሃሞ፣ ሸርቆሌ፣ መንጌ፣ ኩርሙክ፣ ሆሞሻ፣ ቶንጎ፣ ኡንዱሉ፣ ነብልድግሉ ወረዳዎችና አካባቢዎቻቸው

👉 እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል ግዳሚ፣ በጊ፣ ቆንዳላ ፣ ቃቄ ከተሞች እና በዙሪያቸው ያሉ አካባቢዎች የኃይል አቅርቦቱ ተቋርጧል፡፡

ስለሆነም የደረሰው ብልሽት በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የጥገና ቡድን በኩል ተጠግኖ አገልግሎቱ እስኪመለስ ክቡራን ደንበኞቻችን በትዕግስት እንድትጠብቁን እናሳውቃለን።

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

🚨 Clarification on Electricity Tariff 🚨Recent reports falsely claim a significant hike in Ethiopia's electricity tariffs...
17/09/2024

🚨 Clarification on Electricity Tariff 🚨

Recent reports falsely claim a significant hike in Ethiopia's electricity tariffs. The truth? The new tariff, effective from Meskerem 1, 2017, reflects moderate adjustments aimed at fairness and sustainability, especially for households (nearly 90% of the customer base).

💡 How to Calculate Your Energy Bill:

1️⃣ Check your consumption (in kWh)
2️⃣ Find your stage in the tariff chart below.
3️⃣ Multiply your total kWh by the rate for your stage.

⚙️ Example: Let’s say you consume 150 kWh in a month.

Step 1: Your monthly consumption is 150 kWh.
Step 2: You fall into the third stage (101-200 kWh).
Step 3: The third stage rate is 1.89 birr per kWh.

🖍 Calculation

150 kWh × 1.89 birr = 283.50 birr

Your total energy consumption bill for the month would be 283.50 birr.

______
Below is a comparison between the old and the new (Meskerem 2017 tariffs) for household customers

10/09/2024

Address

NEKEMTE, OROMIA
Nekemte

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopia Electric Utility Oromia Region Nekemt District posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Ethiopia Electric Utility Oromia Region Nekemt District:

Share

Category