Getahun.S

Getahun.S Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Getahun.S, Structural Engineer, Sodo.

24/02/2026

By streamer ' ishowspeed ' .... infrastructure of Ethiopua

16/02/2026

How china made construction so difficult for other !!!!😔😔😔😔

13/02/2026

THE House which is easy to construct !

13/02/2026

12/02/2026
12/02/2026

የconstruction ስራ ይማሩ ከኛ ጋር ።

12/02/2026

Follow for more #እባካችሁ follow አድርጉ

📌ኢትዮጵያ ልታስገነባው ላቀደችው ግዙፍ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት የሚመረጡ ኮንትራክተሮች፣ ከግንባታ ብቃታቸው በተጨማሪ የራሳቸውን የፋይናንስ ምንጭ (Funding) ይዘው እንዲመጡ ቅድመ ሁኔታ መ...
11/02/2026

📌ኢትዮጵያ ልታስገነባው ላቀደችው ግዙፍ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት የሚመረጡ ኮንትራክተሮች፣ ከግንባታ ብቃታቸው በተጨማሪ የራሳቸውን የፋይናንስ ምንጭ (Funding) ይዘው እንዲመጡ ቅድመ ሁኔታ መቀመጡን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቀ።

📌በአየር መንገዱ አዲስ አቅጣጫ መሰረት፣ የግንባታ ጨረታውን የሚያሸንፉ ኮንትራክተሮች ፕሮጀክቱን የገንዘብ ድጋፍ የሚያደርግላቸውን አበዳሪ ባንክ አብረው ይዘው እንዲመጡ ተጠይቀዋል።

📌ይህ መንግስት፣ አበዳሪዎች እና ኮንትራክተሮች በጋራ የሚሳተፉበት የሦስትዮሽ የፋይናንሲንግ ሞዴል፣ የብድር ሂደቱን ይበልጥ ፈጣንና ውጤታማ ለማድረግ ያለመ መሆኑን ካፒታል ጋዜጣ ሰምቷል።

📌እንደ ሌሎቹ የመንግስት ብድሮች ቀጥተኛ ያልሆነው ይህ የኤርፖርት ግንባታ ብድር፣ "ውስብስብና ብዙ ጠመዝማዛ መንገዶች ያሉት" ተብሎ ተገልጿል።

📌የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰዉ ለተቋሙን ግማሽ ዓመት አፈፃፀም ባቀረቡት ወቅት እንደተናገሩት፤ ብድሩን የሚወስደው በቀጥታ የኢትዮጵያ መንግስት ወይም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሳይሆን፣ ለዚሁ ፕሮጀክት ተብሎ ራሱን ችሎ የሚቋቋም ልዩ ድርጅት ነዉ።

📌ለብድሩ ዋስትና ተደርጎ የሚቀርበውም ራሱ የሚገነባው ኤርፖርት መሆኑን ዋና ስራ አስፈፃሚዉ አስረድተዋል።

📌ለአዲሱ ኤርፖርት ግንባታ በአጠቃላይ 9 ቢሊየን ዶላር ገደማ ከብድር ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል። እስካሁን ባለው ሂደት በሞሮኮ በተካሄደ ዓለም አቀፍ ወርክሾፕ ላይ የተለያዩ አበዳሪ ድርጅቶች እስከ 6 ቢሊየን ዶላር የሚደርስ የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ ፍላጎታቸውን መግለጻቸውን ካፒታል ጋዜጣ ለመረዳት ችሏል።

📌"አበዳሪዎች በፕሮጀክቱ አዋጭነት ላይ ሙሉ እምነት እንዲኖራቸው በፓሪስ፣ ለንደን፣ ቻይና እና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ሰፊ የምክክር መድረኮች ተካሂደዋል" ሲሉ አቶ መስፍን ጣሰዉ ገልጸዋል።

📌ፕሮጀክቱን በፋይናንስ ረገድ ውጤታማ ለማድረግ የአፍሪካ ልማት ባንክ በዋና አስተባባሪነት የተሰየመ ሲሆን፣ ኬፒኤምጂ እንደ ፋይናንስ አማካሪ በመሆን እየሰሩ እንደሚገኙ ተገልጿል።

📌የአዋጭነት ጥናቱ ካለፈው ህዳር ወር ጀምሮ ለአበዳሪዎች የተሰጠ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ድርጅቶቹ ተጨማሪ መረጃዎችን እየገመገሙ እንደሚገኙ ተጠቁሟል።

📌በቢሾፍቱ አቅራቢያ 'አቡሴራ' በተባለ አካባቢ የሚገነባው ይህ አዲስ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ቅዳሜ ጥር 2 ቀን 2018 ዓ.ም. መሰረተ ድንጋይ መቀመጡ የሚታወስ ሲሆን አጠቃላይ የብድር ስምምነቱና ውሳኔው እስከ መጪው ታህሳስ 2026 (እ.ኤ.አ) መጨረሻ ድረስ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።

(Capital)

Eng. Gech

የግዙፉ የአውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ተጀመረ 📌የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በቢሾፍቱ ከተማ አቅራቢያ የሚገነባውን አዲሱንና ግዙፉን ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ዲዛይን እና የግንባታ ክት...
10/02/2026

የግዙፉ የአውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ተጀመረ

📌የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በቢሾፍቱ ከተማ አቅራቢያ የሚገነባውን አዲሱንና ግዙፉን ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ዲዛይን እና የግንባታ ክትትል ሥራ ለታዋቂው የሕንፃ ጥበብ ድርጅት ዛሃ ሃዲድ አርኪቴክቸር (Zaha Hadid Architects) መስጠቱን ተከትሎ የግንባታው ሂደት በይፋ መጀመሩን ወርልድ አርክቴክቸር ዘግቧል።

📌ይህ 6 ቢሊዮን ዶላር የሚፈጅ ሜጋ ፕሮጀክት በዋናነት በብድር በሚገኝ ፋይናንስ የሚከናወን ሲሆን፣ ሲጠናቀቅም በዓመት 100 ሚሊዮን መንገደኞችን የማስተናገድ አቅም ይኖረዋል ተብሏል።

📌አየር መንገዱ አሁን ካለበት የቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የማስተናገድ አቅም በላይ እያደገ በመምጣቱ፣ ይህ አዲስ ፕሮጀክት ለአፍሪካ አቪዬሽን ኢንዱስትሪ ትልቅ ስትራቴጂካዊ መፍትሔ ሆኖ ቀርቧል።

📌አዲሱ አውሮፕላን ማረፊያ ከአዲስ አበባ በስተደቡብ ምስራቅ 40 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው በቢሾፍቱ አካባቢ 35 ካሬ ኪሎ ሜትር ስፋት ባለው ቦታ ላይ የሚያርፍ ሲሆን፣ የመጀመሪያው የግንባታ ምዕራፍ በፈረንጆቹ 2029 ተጠናቆ 60 ሚሊዮን መንገደኞችን ማስተናገድ ይጀምራል።

📌የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው እንደገለጹት፣ አዲሱ አውሮፕላን ማረፊያ በሥራ ላይ ሲውል የአሁኑ የቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አገልግሎት አይቆምም፤ ይልቁንም ለሀገር ውስጥ በረራዎች፣ ለቪአይፒ አገልግሎቶችና ለቀጣናዊ በረራዎች ትኩረት ሰጥቶ አገልግሎቱን ይቀጥላል።

📌የፕሮጀክቱ ዲዛይን የኢትዮጵያን ባህላዊ ቅርሶችና የተፈጥሮ ውበት ከዘመናዊ የሕንፃ ጥበብ ጋር ያቀላቀለ እንደሚሆንም ተገልጿል።
ለፕሮጀክቱ ግንባታ ሲባል ከአካባቢው ለሚነሱ ነዋሪዎች የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ተገቢውን ካሳ የመክፈልና የመልሶ ማቋቋም ሥራ እንደሚያከናውን የታወቀ ሲሆን፣ ግንባታውም የአካባቢውን ሥነ-ምህዳር በማይጎዳ መልኩ እንዲከናወን ልዩ የዲዛይን ጥንቃቄ ተደርጓል።

📌አዲሱ አውሮፕላን ማረፊያ 4 ማኮብኮቢያዎችን፣ ዘመናዊ የንግድ ማዕከላትንና የሆቴል አገልግሎቶችን በማካተት በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ዕድገት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እንደሚኖረውና በሺዎች ለሚቆጠሩ ዜጎች የሥራ ዕድል እንደሚፈጥር የታመነበት ቢሆንም፣ ባለሙያዎች ግንባታው በሥነ ምህዳር ላይ ሊያደርስ የሚችለውን ጫና አስመልክቶ የጥንቃቄ እርምጃዎች እንዲወሰዱ ማሳሰባቸውን የዜና ምንጩ አክሎ ገልጿል።

አሐዱ ረድዮ

በኢትዮጵያ ረጅሙ ህንፃ   ዋና መሥሪያ ቤት ሲሆን፣ ዝርዝር መረጃውም የሚከተለው ነው፦ዋና ዋና መረጃዎችቁመት፦ 209.3 ሜትር።የወለል ብዛት፦ 53 ወለሎች (ከምድር በላይ)።ጠቅላላ ስፋት፦ 1...
10/02/2026

በኢትዮጵያ ረጅሙ ህንፃ ዋና መሥሪያ ቤት ሲሆን፣ ዝርዝር መረጃውም የሚከተለው ነው፦
ዋና ዋና መረጃዎች
ቁመት፦ 209.3 ሜትር።
የወለል ብዛት፦ 53 ወለሎች (ከምድር በላይ)።
ጠቅላላ ስፋት፦ 150,000 ካሬ ሜትር።
አድራሻ፦ አዲስ አበባ፣ ራስ ደስታ ዳምጠው መንገድ (ቸርችል ጎዳና ማብቂያ)።
የግንባታ ወጪ፦ 303.5 ሚሊዮን ዶላር ገደማ።
የምረቃ ቀን፦ የካቲት 6 ቀን 2014 ዓ.ም (የካቲት 13, 2022)።
ተቋራጭ፦ የቻይና ስቴት ኮንስትራክሽን ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (CSCEC)።
አገልግሎቶች እና ገፅታዎች
መገልገያዎች፦ ሲኒማ ቤቶች፣ የገበያ ማዕከላት፣ ጂምናዚየም፣ የውበት ሳሎን እና የህፃናት መጫወቻ ቦታዎችን ይዟል።
ምግብ እና እይታ፦ በህንፃው አናት ላይ ሁለት ምግብ ቤቶች እና የከተማዋን እይታ ለመመልከቻ የሚያገለግል ቦታ (sightseeing tower) አለው።
ቴክኖሎጂ፦ የውሃ እና የኤሌክትሪክ አጠቃቀምን በዘመናዊ መንገድ ለመቆጣጠር የIBM ቴክኖሎጂን ይጠቀማል።
የመኪና ማቆሚያ፦ እስከ 1,500 መኪናዎችን ማቆም የሚችል ዘመናዊ ሜካኒካል የመኪና ማቆሚያ አለው።
ዲዛይን፦ በጀርመኑ Henn Architekten የተነደፈ ሲሆን፣ የህንፃው ውጫዊ ክፍል እንደ አልማዝ እንዲያብረቀርቅ ተደርጎ ከ5,000 በላይ በሚሆኑ መስታወቶች ተሸፍኗል።

አሁን ላይ የንግድ ባንክ ህንፃ ረጅሙ ቢሆንም፣ ግንባታው እየተከናወነ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (EEP) ዋና መሥሪያ ቤት ሲጠናቀቅ 327.5 ሜትር ቁመት እና 62 ወለሎች በመያዝ ቀዳሚነቱን እንደሚረከብ ይጠበቃል።
ቀጣይ ቀን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (EEP) ዋና መሥሪያ ቤት ሕንፃ ሁኔታ አደርሳለሁ ።

ወጭውን በግማሽ ቀንሰው እንደዚህ አይነት የሚያማምሩ የመኖሪያ ቤቶቹን ማሰራት የተሻለ ነው ። በCONCRETE AND  BLOCKET ከሚሰሩ ቤቶች ይልቅ በኮንቴነር ማሰራት 50% ብር ይቀንሳል ...
07/02/2026

ወጭውን በግማሽ ቀንሰው እንደዚህ አይነት የሚያማምሩ የመኖሪያ ቤቶቹን ማሰራት የተሻለ ነው ። በCONCRETE AND BLOCKET ከሚሰሩ ቤቶች ይልቅ በኮንቴነር ማሰራት 50% ብር ይቀንሳል ።

eg :- 1 ኮንቲነር ሁለት (2) ክፍል ልሆን ይችላል ታድያ ወጭውን በዛ ገምቱ ።

እሄ ቤት AA ውስጥ የተሰራ ቤት የው ። 🫙 House made of container 🫙

🫙 ከ ኮንቴነር የተሰራ ቤት 🫙

📍 Addis Ababa Ethiopia 🇪🇹 | አዲስ አበባ

Address

Sodo

Telephone

+251923119805

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Getahun.S posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Getahun.S:

Share