GAHFamily Media

GAHFamily Media WE ARE 'REALY CARE' "FOR YOUR SECURITY!!!

30/05/2026
 #እኔ  #እመርጣለሁ
30/05/2026

#እኔ #እመርጣለሁ

   ዋንግ የተባለው ግለሰብ ለብዙ አመታት በሆድ ህመም ለ2 አሰርት አመታት ስሰቃይ በምርመራው ባዕድ ነገር እንደተገኘ ተነገረለት።ሆስፒታልም 🏥 ደርሰው የደም ናሙናውም ተወስዶ ምንም ህመም ባ...
20/04/2026





ዋንግ የተባለው ግለሰብ ለብዙ አመታት በሆድ ህመም ለ2 አሰርት አመታት ስሰቃይ በምርመራው ባዕድ ነገር እንደተገኘ ተነገረለት።

ሆስፒታልም 🏥 ደርሰው የደም ናሙናውም ተወስዶ ምንም ህመም ባለመገኘቱ የተለያዩ የህክምና አማራጮችን በመጠቀም ምርመራ ስደረግ በውስጡ የሙቀት መለኪያ ተገኘለት።

ግለሰቡም ቻይናዊ ስሆን በ8 አመቱ የሙቀት መለኪያ 🌡️ ውጦት በቤተሰብ ፍራቻ ሳይነግረው በመቆየቱ የጨጓራ ግድግዳ ወግተው ለአመታት ስለቆየ የሆድ ህመም በመምሰል ደም የቀላቀለ ሰገራና ህመም ተሰቃይቶ በመቆየቱ ወደ ሆስፒታል 🏥 ባመራው ወቅት ነው ይህንን የሰማው።

በህክምናው ለሁለት ሰዓታት በቆየው ቀዶ ጥገና ህክምና ተሰግስገው የቆየው 🌡️thermometer ወጣለት ።

እንደዚህ አይነት አድስና ድንቃ ድንቅ መረጃ ለማግኘት
በፌስቡክ GAHFamily Media
በቴሌግራም https://t.me/GAHFamilyMedia
ይቀላቀላሉ !!

✨ የቆለጥ ደም ስር መጥበብ (Varicocele) በወንዶች ጤና ላይ ያለው ተፅዕኖ🚨👉የቆለጥ ደም ስር መጥበብ ወይም መለጠጥ (Varicocele) ማለት በቆለጥ ከረጢት ውስጥ የሚገኙ የደም ስሮ...
25/03/2026

✨ የቆለጥ ደም ስር መጥበብ (Varicocele) በወንዶች ጤና ላይ ያለው ተፅዕኖ🚨

👉የቆለጥ ደም ስር መጥበብ ወይም መለጠጥ (Varicocele) ማለት በቆለጥ ከረጢት ውስጥ የሚገኙ የደም ስሮች ልክ እንደ እግር ላይ እንደሚወጡ የደም ስሮች (Varicose veins) ሲያብጡና ሲለጠጡ የሚከሰት ሁኔታ ነው። ምንም እንኳን ብዙ ወንዶች ምልክት ባያሳዩም፤ ሁኔታው ግን የቆለጥን ጤናማ የስራ አካባቢ በማናጋት ለተለያዩ ችግሮች ሊዳርግ ይችላል።
🔍 በቆለጥ ጤና ላይ የሚያመጣቸው ዋና ዋና ጉዳቶች
🩸 የመውለድ ብቃት መቀነስ
ይህ ችግር በቀላሉ ሊታከሙ ከሚችሉ የወንዶች መካንነት መንስኤዎች ቀዳሚው ነው። የዘር (S***m) ቁጥርን መቀነስ፣ የመንቀሳቀስ አቅምን ማዳከም እና ቅርጹ የተስተካከለ ዘር እንዳይመረት ያደርጋል።
📉 የቆለጥ መኮማተር (Atrophy)
በደም ስሩ መለጠጥ ምክንያት የዘር ማምረቻ ቱቦዎች ስለሚጎዱ፤ የተጠቃው ቆለጥ (አብዛኛውን ጊዜ የግራው) መጠኑ ሊያንስና ሊለሰልስ ይችላል።
⚖️ የሆርሞን መዛባት
የወንድነት ሆርሞን (Testosterone) አመራረት ላይ እንቅፋት ሊሆን ይችላል። ይህም የፍላጎት መቀነስ፣ ድካም እና የጡንቻ ጥንካሬ ማጣትን ሊያስከትል ይችላል።
😫 የማያቋርጥ ህመም
አንዳንድ ወንዶች በቆለጥ አካባቢ የመክበድ ስሜት ወይም የሚመላለስ ህመም ይሰማቸዋል። ይህ ህመም በተለይ ለረጅም ሰዓት ሲቆሙ ወይም አካላዊ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ሊባባስ ይችላል።
🌡️ ችግሩ ለምን ይከሰታል?
🔥 የሙቀት መጨመር
ጤናማ ዘር ለመመረት ቆለጥ ከሰውነታችን የሙቀት መጠን በትንሹ ቀዝቀዝ ያለ ቦታ ያስፈልገዋል። በደም ስሮቹ ውስጥ ደም ተከማችቶ ሲቆይ ሙቀቱ ስለሚጨምር የዘር ፍሬዎቹ "እንደመቀቀል" ይሆኑና ይጎዳሉ።
🧪 ኦክሳይዳይቲቭ ስትረስ እና መርዛማ ነገሮች
የቆመ ደም በቆለጥ አካባቢ ጎጂ የሆኑ የሜታቦሊዝም ውጤቶች እንዲከማቹ በማድረግ የቆለጥ ህብረ ህዋሳትን ይጎዳል።
🌬️ የኦክስጅን እጥረት
በደም ስሮቹ ውስጥ ያለው ከፍተኛ ጫና ጤናማ የደም ዝውውርና የኦክስጅን አቅርቦት ወደ ቆለጥ እንዳይደርስ እንቅፋት ይሆናል።
🩺 የህክምና ባለሙያ ማማከር የሚገባው መቼ ነው?
🐛 በቆለጥ ከረጢት ላይ ልክ እንደ "የትል ስብስብ" የሚሰማ እብጠት ካለ።
📏 በሁለቱ ቆለጦች መካከል ከፍተኛ የሆነ የመጠን ልዩነት ሲኖር።
🛌 ሲተኙ የሚጠፋ ነገር ግን ሲቆሙ የሚመለስ የማያቋርጥ ህመም ካለ።
👶 ለአንድ አመት ያህል መደበኛ የሆነ ጥንቃቄ የጎደለው ግንኙነት ተደርጎ ልጅ መውለድ ካልተቻለ።

#ዶክተርአፍሪካንይጠይቁ
GAHFamily Media

🗳️ የ2018 ምርጫ፡ ከፍተኛ የዕጩዎች ቁጥር ያስመዘገቡ ሦስት ፓርቲዎች!​በመጪው የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ መረጃ መሠረት፣ ለሕዝብ ተወካዮች እና ለክልል ምክር ቤቶች በከፍተኛ ቁጥር ዕጩዎቻቸው...
24/03/2026

🗳️ የ2018 ምርጫ፡ ከፍተኛ የዕጩዎች ቁጥር ያስመዘገቡ ሦስት ፓርቲዎች!

​በመጪው የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ መረጃ መሠረት፣ ለሕዝብ ተወካዮች እና ለክልል ምክር ቤቶች በከፍተኛ ቁጥር ዕጩዎቻቸውን ያስመዘገቡ ሦስት የፖለቲካ ፓርቲዎች ታውቀዋል።

​የዕጩዎች ቁጥር ደረጃ፦

​🥇 1ኛ. ብልፅግና ፓርቲ
​የዕጩዎች ብዛት፡ 2,950

​🥈 2ኛ. የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ)
​የዕጩዎች ብዛት፡ 1,256

​🥉 3ኛ. ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት (ትብብር ለኢትዮጵያ)
​የዕጩዎች ብዛት፡ 1,032

​📌 ልብ ሊባሉ የሚገቡ ነጥቦች፦

​በአጠቃላይ በሀገሪቱ 3,466 የምክር ቤት መቀመጫዎች (547 ለፌዴራል፣ 2,919 ለክልል) ይገኛሉ።

​አንድም ፓርቲ ሁሉንም መቀመጫዎች የሚሸፍን ዕጩ አላቀረበም።

​ከፍተኛ ቁጥር ያስመዘገበው ብልፅግና ፓርቲ እንኳን ከጠቅላላው መቀመጫ በ 516 ዕጩዎች ያነሰ ቁጥር ነው ያስመዘገበው።

​ዝርዝር መረጃዎችን እንደደረሱን ማቅረባችንን እንቀጥላለን። ይከታተሉን!

​ #ምርጫ2018 #ኢትዮጵያ #ብልፅግና #ኢዜማ

☕ የቡና አፍቃሪ ነዎት? የጤናዎ ወዳጅ ወይስ ጠላት?◾ቡና የብዙዎቻችን የጠዋት መጀመሪያ ቢሆንም፣ አንዳንዴ ግን የልብ ምት መጨመርና መረበሽ ሊፈጥርብን ይችላል። ታዲያ ሳይንሱ ስለ ቡና ጥቅም...
22/03/2026

☕ የቡና አፍቃሪ ነዎት? የጤናዎ ወዳጅ ወይስ ጠላት?
◾ቡና የብዙዎቻችን የጠዋት መጀመሪያ ቢሆንም፣ አንዳንዴ ግን የልብ ምት መጨመርና መረበሽ ሊፈጥርብን ይችላል። ታዲያ ሳይንሱ ስለ ቡና ጥቅምና ጉዳት ምን ይላል? ዛሬ በዝርዝር እንመለከታለን።
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
🕹️በየቀኑ የሚለጠፉ ተመሳሳይ ጠቃሚ ምክሮችን እንድያገኙ በመጀመርያ ፔጃችን ልጥፉን በማድረግ ይጀምሩ!!
🕹️ጥያቄዎን ደሞ መስጫ ቦታ ወይም በዚህ #ቴለግራም ግሩፕ ገብተው ይላኩልን‼️መልስ እንሰጣለን።
: https://t.me/GAHFamilyMedia
እናመሰግናለን🙏🙏🙏
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
💡 በሳይንስ የተረጋገጡ የቡና የጤና ጥቅሞች፥
◾ቡና በተመጣጣኝ መጠን ሲወሰድ (በቀን ከ3-4 ስኒ) በርካታ የጤና በረከቶች አሉት፦

◾ ለልብ ጤና (Cardiovascular Health)፦ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት በመጠኑ ቡና መጠጣት የልብ ስራን በማቀላጠፍ ለልብ ድካም የመጋለጥ እድልን ይቀንሳል።

◾ የስኳር በሽታን መከላከል፦ በየቀኑ ቡና መጠጣት በዓይነት 2 ስኳር በሽታ (Type 2 Diabetes) የመያዝ እድልን ዝቅ እንደሚያደርግ በ "Journal of Internal Medicine" ላይ የወጡ ጥናቶች ያሳያሉ።

◾ የአእምሮ ጤና ጥበቃ፦ ቡና እንደ አልዛይመር (Alzheimer's) እና ፓርኪንሰን (Parkinson's) ያሉ የአእምሮ በሽታዎችን የመከላከል አቅም አለው።

◾ የጉበት ጤና፦ በተለይ የጉበት ካንሰርን፣ የጉበት ጠባሳን (Cirrhosis) እና የጉበት ስብን ለመከላከል ይረዳል።

◾ ለስሜት መነቃቃት (Mood Enhancement)፦ ካፌይን የነርቭ ስርዓትን በማነቃቃት ድብርትንና የጭንቀት ስሜትን ለመቀነስ ይረዳል።

◾ ከፍተኛ የፀረ-ኦክሲደንት (Antioxidants) ምንጭ፦ ሴሎቻችን እንዳያረጁና ለካንሰር እንዳይጋለጡ የሚከላከሉ ንጥረ ነገሮች በቡና ውስጥ በከፍተኛ መጠን ይገኛሉ።
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
⛔ ከመጠን በላይ መጠጣት የሚያስከትላቸው የጤና እክሎች፥
◾ማንኛውም ነገር ከመጠን ካለፈ ጉዳቱ ያመዝናል። በቀን ከ 4 ስኒ በላይ መጠጣት የሚከተሉትን ችግሮች ሊያስከትል ይችላል፦

📢 የጭንቀትና የእንቅልፍ መዛባት፦ ካፌይን ማዕከላዊ የነርቭ ሥርዓትን ስለሚያነቃቃ ከፍተኛ መረበሽና የእንቅልፍ እጦት (Insomnia) ሊያስከትል ይችላል።

📢 የልብ ምትና የደም ግፊት መጨመር፦ ቡና ለጊዜው የደም ግፊትን ከፍ ሊያደርግ ይችላል። የልብ ህመም ተጋላጭነት ካለብዎ የልብ ምት መዛባት ሊፈጥር ስለሚችል ጥንቃቄ ያስፈልጋል።

📢 የሱስ ተገዢነት (Caffeine Dependence)፦ ካፌይን ሱስ የማስያዝ ባህሪ አለው። በድንገት ሲያቆሙት ከባድ ራስ ምታትና ብስጭት ሊያጋጥምዎት ይችላል።

📢 የምግብ መፈጨት ችግር፦ በተለይ ባዶ ሆድ ላይ መጠጣት የጨጓራ አሲድ እንዲጨምር በማድረግ ቃር (Heartburn) እና የምግብ አለመፈጨት ችግር ይፈጥራል።
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
💊 ጠቃሚ ምክሮች፥
🕹️ መጠኑን ይወስኑ፦ የጤና ጥቅሙን ለማግኘት በቀን ከ3-4 ስኒ ባይበልጥ ይመከራል።
🕹️ ሰዓት ይምረጡ፦ ለተስተካከለ እንቅልፍ ሲባል ከቀኑ 9 ሰዓት በኋላ ቡና ባይጠጡ ይመረጣል።
🕹️ ባዶ ሆድዎን አይጠጡ፦ ጨጓራዎ እንዳይቆጣ ሁልጊዜ ከምግብ በኋላ ወይም ከምግብ ጋር ይጠጡ።
🕹️ ልዩ ጥንቃቄ፦ ነፍሰ ጡር እናቶች፣ የደም ግፊትና የጨጓራ ህመም ያለባችሁ ሰዎች አጠቃቀማችሁን ከሀኪም ጋር ማማከር አለባችሁ።

📩ጤናዎ በእጅዎ ነው! በመጠኑ በመጠጣት ራስዎን ይጠብቁ።
ዶ/ር ብሩክ (Dr. Birhk)

19/03/2026

Check out getinetchem’s post.

16/03/2026

Watch, follow, and discover more trending content.

14/03/2026

Check out getinettafese’s video.

S
12/03/2026

S

Watch, follow, and discover more trending content.

Address

Hospital
Leeds

Opening Hours

Monday 6am - 6pm
Tuesday 12am - 11am
Wednesday 1am - 1pm
Thursday 2am - 2pm
Friday 7am - 7pm

Telephone

+251931186003

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when GAHFamily Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to GAHFamily Media:

Share