03/05/2026
የሲዳማ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ከተቋቋመ ሁለት አመታትን ያስቆጠረ የግንባታ ተቋም ሲሆን ባለፉት ሁለት አመታት የክልሉ መንግስት የክልሉን ህብረተሰብ የንፁህ መጠጥ ዉሃ ሽፋን ለማሳደግ የሚያደርገውን ጥረት በማገዝ በንፁህ የመጠጥ ዉሃ አቅርቦት ዘርፍ ሰፊ ስራ ሲሰራ ቆይቷል፡፡
ኮርፖሬሽኑ ባለፉት ሁለት ዓመታት ከ2.3 ቢሊየን ብር በላይ የዉለታ ዋጋ ያላቸውን 24 ከከፍተኛ እስከ አነስተኛ የመጠጥ ዉሃ ግንባታ ፕሮጀክቶችን በተቋራጭነት ዉል በመግባት ሲገነባ ቆይቷል፡፡ በዚህም የከተሞች፣ የጤና ተቋማት፣ የማረሚያ ተቋማት እንዲሁም ሌሎች ለህብረተሰቡ አገልግሎት የሚዉሉ የመጠጥ ዉሃ ግንባታ ፕሮጀክቶችን ገንብቷል፡፡ በተለይም ከፍተኛ የዉሃ እጥረት ባለባቸው የከተሞች የንፁህ መጠጥ ዉሃ አቅርቦት ላይ በተቋራጭነት በመሳተፍ እስከ 2ሚሊየን ሊትር መያዝ የሚችሉ ትላልቅ የኮንክሪት ዉሃ ማጠራቀሚያ ገንዳዎች ግንባታ እና ትላልቅ የመስመር ዝርጋታ ሥራዎችን በመስራት የህብረተሰቡን የመጠጥ ዉሃ ችግር ለመቅረፍ የበኩሉን አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል፡፡
በንፁህ መጠጥ ዉሃ አቅርቦት የተሻለ ነገን ለመገንባት እየሠራ የሚገኘው ኮርፖሬሽናችን በያዝነው በ2018 በጀት ዓመት እየገነባቸው ከሚገኙ ፕሮጀክቶች ዉስጥ በፌደራልና በክልሉ መንግስት ድጋፍ እየተገነቡ የሚገኙት የሀዋሳ ከተማ የፋራ ሂጣታ፣ የአለታ ጩኮ ከተማ እና የአለታ ወንዶ ከተማ ከፍተኛ የመጠጥ ዉሃ ግንባታ ፕሮጀክቶች የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
#ሲኮሥኮ
ሚያዝያ 25/2018 ዓ.ም.
ጥራት ላለው ግንባታ-ሲኮሥኮ