Ethio-Abay Dam Media

Ethio-Abay Dam Media Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ethio-Abay Dam Media, Construction Company, Los Angeles, CA.

በአንከሻ ጓጉሳ ወረዳና በአገው ግምጃ ቤት ከተማ አስተዳደሮች በጋራ የተዘጋጀ የብልፅግና ፓርቲ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ስር በሚገኙት በእነዚህ ሁለት አስተዳደ...
05/24/2026

በአንከሻ ጓጉሳ ወረዳና በአገው ግምጃ ቤት ከተማ አስተዳደሮች በጋራ የተዘጋጀ የብልፅግና ፓርቲ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።

በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ስር በሚገኙት በእነዚህ ሁለት አስተዳደሮች አዘጋጅነት በአገው ግምጃ ቤት ከተማ እየተካሄደ የሚገኘው ይህ ህዝባዊ ሰልፍ፤ "በላቀ ሕዝባዊ ተሳትፎ፣ ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር" በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ ነው። ሰልፉ ብልፅግና ፓርቲ ባለፉት የለውጥ ዓመታት ያስመዘገባቸውን ስኬቶችና ለመጪዎቹ አምስት ዓመታት የነደፈውን ልማታዊ ጉዞ የሚደግፍ ሲሆን፣ ጎን ለጎንም የብልፅግና ፓርቲ የ"ይምረጡኝ" ቅስቀሳ እየተካሄደበት ይገኛል።

የሰከነ አመራር ልክ እንደ እንስቷ መሪ!! ​አመራር የሚመዘነው በሰላም ጊዜ ሳይሆን በፈተናና በችግር ወቅት ነው። ፈተናን ወደ ዕድል፣ ስጋትን  ወደ ተስፋ የሚቀይር መሪ ደግሞ የትኛውንም ማዕ...
05/20/2026

የሰከነ አመራር ልክ እንደ እንስቷ መሪ!!

​አመራር የሚመዘነው በሰላም ጊዜ ሳይሆን በፈተናና በችግር ወቅት ነው።
ፈተናን ወደ ዕድል፣ ስጋትን ወደ ተስፋ የሚቀይር መሪ ደግሞ የትኛውንም ማዕበል የመሻገር ጥበብ አለው።

​የዶ/ር ሙሉነሽ ደሴ ልዩ መገለጫ በትክክልም ይህ "የሰከነ አመራር" ነው።
ጩኸትና ዛቻ ባለበት ቦታ በእርጋታ፣ መቃቃር ባለበት ቦታ በውይይት፣ ግጭት ባለበት ቦታ በጥበብ መፍትሄ በመስጠት የሚታወቁ ድንቅ እንስት ናቸው።

​ይህ የአመራር ብቃት የሀገራችንን የብልፅግና ዕሳቤ መሬት ካስረገጡት ዋና ዋና ምሰሶዎች ጋር ቀጥታ ይገናኛል።

ብልፅግና የሚረጋገጠው በሁከት ሳይሆን በሰከነ አስተዋይነት፣ በብተና ሳይሆን በሕዝቦች ትስስርና አንድነት ነው።

ዶ/ር ሙሉነሽ ደሴ ዘላቂ ሰላምና ልማትን ለማረጋገጥ ሌት ተቀን እየተጉ ያሉት በትክክልም ይህንን የጋራ ብልፅግና ጉዞ ስኬታማ ለማድረግ ነው።

​ይህ ለብዙ ሴት እህቶቻችን ትልቅ የሞራል ስንቅና "እኛም እንችላለን!" የሚል ታላቅ ተስፋን የጫረ በተግባር የተረጋገጠ የአመራር ጥበብ ነው።

​ክብር ለሚገባው ክብር እንሰጣለን።
ለሀገር ሰላምና ልማት ሌት ተቀን ለምትተጋው ለዚች ባለውለታ እንስት መሪያችን ያለንን አክብሮት እንገልጻለን።

እውነተኛው አሳፋሪ ድራማ የቱ ነው?****************************በአንከሻ ወረዳ "ተፈፀመ" ተብሎ እየተሰራጨ ያለው የፈጠራ ፅሁፍ የተወሰኑ የፖለቲካ ሀይሎችን የሞራል ውድቀትና ...
05/19/2026

እውነተኛው አሳፋሪ ድራማ የቱ ነው?
****************************
በአንከሻ ወረዳ "ተፈፀመ" ተብሎ እየተሰራጨ ያለው የፈጠራ ፅሁፍ የተወሰኑ የፖለቲካ ሀይሎችን የሞራል ውድቀትና የሐሳብ ድህነት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው። ተፎካካሪ ነን የሚሉ አካላት በሀሳብና በፖሊሲ መወዳደር ሲያቅታቸው በ AI /ሰው ሰራሽ አስተውሎት የተቀነባበሩ የሀሰት የምርጫ ካርድ ምስሎችን በመፍጠር ህዝብን ለማደናገር ደፋ ቀና እያሉ ይገኛሉ።

የተሰራጨውን ምስል በጥሞና ብትመለከቱት እውነታውን በቀላሉ ትረዳላችሁ። ካርዱ እውነተኛ ቢሆን ኖሮ የመራጩ ሙሉ ስም፣ የምርጫ ክልል እና የምርጫ ካርዱ በግልፅ ይነበብ ነበር። ነገር ግን በቴክኖሎጂ የተፈጠረ የውሸት /AI-generated ምስል በመሆኑ ምንም አይነት ትክክለኛ መረጃ አይታይበትም። "በሞተ ሰውና በእንስሳት ስም ካርድ ወጣ" እየተባለ የሚነዛው አሉባልታም ለዚሁ የሀሰት ምስል ማጀቢያነት ሆን ተብሎ የተቀነባበረ ርካሽ የፖለቲካ ትርክት ነው።

ለስልጣን ሲባል እስከዚህ ድረስ ዝቅ ማለት የሀሰት ምስል እያቀነባበሩ ማሰራጨት እና ህዝብን መዋሸት ትልቁ የፖለቲካ ኪሳራ ነው። ትክክለኛው ህሊና-ቢስነትና የማፈሪያዎች ስራም ይሄው የዲጂታል ውንብድና ነው!!!

እውነትን በ AI ምስል መቅበር አይቻልም!!!

05/18/2026

የእነ አዲሱ መኮነን ጭንብላቸው ሲገፈፈ!!

ከአብራካቸው የወጣው ምስክርነት

​አዲሱ መኮነን (የአገው ለፍትሕ ዲሞክራሲ ሊቀመንበር) ወይም አሁን ላይ የሰላም ጥምረት ኢትዮጵያ ም/ፕሬዘዳንት እና የእነ መዝገቡ ቦጋለ ግብረ አበሮቹ የአዊ ህዝብ ጋሻና መከታ የሆኑ መስለው የሚነግዱበት የጥቅም ጭንብል የገዛ ቀኝ እጃቸው፣ የውስጥ ሚስጥራቸው አዋቂው ቀሲስ ስንታየሁ የኔባት የሰራሩትን ደባ እና ሴራ በይፋ ዘርግፎታል።
እኛ "እነዚህ ሰዎች ለአዊ ህዝብ ፀር ናቸው" ስንል በባዶ ጥላቻ አልነበረም፤ በተጨባጭ ምክንያት ነው።
ለራሳቸው ጊዜያዊ ጥቅም ሲሉ፣ ዘመናትን የተሻገረውን የአዊን ህዝብ የመቻቻልና የመከባበር ታሪክ ለማፍረስና ህዝብን ከህዝብ ለማባላት እየሰሩ ነው።
የአዊ ህዝብ በስማችን የሚነግዱትን፣አንድነታችንን የሚንዱትንና እርስ በእርስ ሊያባሉን የሚጥሩትን እነዚህን ለግል ጥቅማቸው የቆሙ ቡድኖች በቃችሁ ልንላቸው ይገባል።
እውነቱ አደባባይ ወጥቷል፤ ምርጫው የኛ ነው።

05/18/2026

የአዊ ህዝብ ስም የንግድ ካርድ አይደለም!!

የአገው ለፍትህና ዲሞክራሲ ሊቀመንበር አዲሱ መኮነን የግል ጥቅሙ እስከተጠበቀ ድረስ ብቻ ነው አብሮ የሚቆመው። የራሱ ጥቅም ከጎደለ አንዲትም ቀን ቢሆን በአንድ ፓርቲ ውስጥ መቆየት የማይችል፣ ጥቅሙን ፍለጋ ከቦታ ቦታ የሚዘዋወር "የፖለቲካ ተጓዥ" ነው።
እስከዛሬ ከ7 በላይ ፓርቲዎችን ያቀያየረው ለዚህ ነው።

​እኛ በአዊ ህዝብ ስም የሚነግድ ከፋፋይና ዘረኛ ነው የምንለው በምክንያት ነው።
ታሪኩና ጥቅመኝነቱ በግልጽ የሚያሳየው ይሄንኑ ነው።
የአዊ ህዝብ፣በስምህ የሚነግዱትንና የግል ጥቅማቸውን ለማሳደድ አንተን መሰላል የሚያደርጉትን ነቅተህ ጠብቅ!

​ #ሀቅ #ፖለቲካ

05/17/2026

የአዊ ህዝብ በስምህ የሚነግደውን ወዳጅና ጠላትህን ለይተህ እወቅ!!!

ለዘመናትበአብሮነት፣በመቻቻልናበመከባበር የኖረው ኩሩው የአዊ ህዝብ ዛሬም ለራሳቸው የግል ጥቅም ሲሉ በስሙ ሊነግዱና ሊያባሉት ለሚፈልጉ ሃይሎችን ተንቅቆ ማወቅ አለበት።
​የፍትሕ ለአገው ዲሞክራሲ ፓርቲ ሊቀመንበር አዲሱ መኮነን፣ የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ሻምበል አለምረው እና የእነ መዝገቡ ቦጋለ ቡድን በተቀናጀ ከውስጥና ከውጭ ካለው ሃይል ጋር እየሰሩ ያሉት አፍራሽ ስራ ለአዊ ህዝብ ሳይሆን ለራሳቸው ለግል እኩይ ዓላማና ለስልጣን ጥቅም እንደሆነ ከራሳቸው አንደበት መረጃ እየወጣ ይገኛል።
አዲሱ መኮነን አዲስ አበባ (አዲስ አምባ ሆቴል ) ላይ ባደረገው የአባላት ስብሰባ ላይ በአዮ ጓጉሳ ወረዳ አንበላ ቀበሌ ➡ 760 ታጣቂ ኃይል ማሰልጠኑን፣በተመሳሳይ ለማ ቀበሌ ላይ ➡ 520 ታጣቂ ኃይል ማሰልጠኑን በኩራት ተናግሯል።
ጥያቄው እዚህ ላይ ነው፦ "ሰላማዊና ህጋዊ ፓርቲ ነኝ" የሚል አካል በምስጢር ታጣቂ ያሰለጥናልን? ይህ ህዝብን ከጎረቤቱ ጋር ለማባላትና ህዝባችንን ለጥፋት ለመዳረግ የሚደረግ ሴራ ካልሆነ ሌላ ምን ሊሆን ይችላል?
​የእነዚሁ ሰዎች የቀኝ እጅ በመሆን አብሯቸው ሲሰራ የነበረው ቀሲስ ስንታየሁ የኔባት በገሃድ ወጥቶ ጉዳቸውን በዚህ መልኩ እየዘረገፈው ይገኛል።
ይህ የሚያሳየው እኛ እነዚህ ግለሰቦች ለአዊ ህዝብ ፀር ናቸው፤ ስንል በምክንያት እና በማስረጃ እንደነበር ምስክር ነው።
የአንበላ አከባቢው ህዝብ ሲፈናቀል ሲሰደድ ያልደረሱት እኒህ ቡድኖች በህዝብ ስም እየነገዱ ነው።

ዋናው አላማቸው ለራሳቸው ስልጣንና ጥቅም ሲሉ የአዊን ህዝብ ለዘመናት ጠብቆት ከኖረው የመቻቻልና የመከባበር እሴት ማውጣት፤ እርስ በእርስ ማባላትና ማናቆር

​የራሳቸው የቅርብ ሰው የመሰከረባቸውን እነዚህን የአስመሳይ ቡድኖች ሴራ ነቅተን ልንጠብቀው ይገባል።
ህዝባችን ሰላሙንና አንድነቱን የሚያስከብረው እንዲህ ያሉትን ከፋፋዮችን ማንነታቸውን ሲረዳ ብቻ ነው።

ሰማ ጥሩነህ ሽፈራው (ዶ/ር)በአማራ ክልል አዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ኮሶበር ምርጫ ክልልለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የብልፅግና ፓርቲን ወክለው የቀረቡ ዕጩ ተወዳዳሪ ኢትዮጵያ ወደ ተምሳሌት ሀ...
05/16/2026

ሰማ ጥሩነህ ሽፈራው (ዶ/ር)

በአማራ ክልል አዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ኮሶበር ምርጫ ክልል
ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የብልፅግና ፓርቲን ወክለው የቀረቡ ዕጩ ተወዳዳሪ

ኢትዮጵያ ወደ ተምሳሌት ሀገር!

ብልፅግናን ይምረጡ !!
ምልክታችን የስንዴ ነዶ ነው!!

🕊ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም??

ከነፈሰው ጋር የማይነፍስ፣ የፅናት ተምሳሌት!!​አቶ በላይነህ የኔሰው በየአቅጣጫው የሚነፍሰው የፖለቲካ ንፋስ ሳይበግራቸው፣ መርህንና ህዝባዊ አደራን አንግበው የቆሙ ፅኑ መሪ ናቸው።​አቶ በላ...
05/15/2026

ከነፈሰው ጋር የማይነፍስ፣ የፅናት ተምሳሌት!!

​አቶ በላይነህ የኔሰው በየአቅጣጫው የሚነፍሰው የፖለቲካ ንፋስ ሳይበግራቸው፣ መርህንና ህዝባዊ አደራን አንግበው የቆሙ ፅኑ መሪ ናቸው።

​አቶ በላይነህ የኔሰው ለአዊ ህዝብ ሰላምና አንድነት ሌሊት ከቀን የሚተጉ፣ ትልቅ ትንሹን እኩል የሚያዩ አስተዋይና በሳል መሪ ናቸው። የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደርን ከውስጥ ከፋፋዮች፣ ከጎጥና ከመንደር ጠባብ አስተሳሰብ ተሸካሚዎች በብልሃትና በጽናት የታደጉ እውነተኛ የህዝብ ልጅ ናቸው።
​ለሴረኞችና ለአብሮነት ፀር ለሆኑ ኃይሎች ሁሉ የራስ ምታትና የእግር እሳት የሆኑት አቶ በላይነህ፣ ለአዊ ህዝብ የምንጊዜም ኩራትና ጀግና መሪ ናቸው።

​ #ጽናት #መሪነት #አዊ #አንድነት

Address

Los Angeles, CA

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio-Abay Dam Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share