Esseynew Mihiretu Melesse

Esseynew Mihiretu Melesse Senior Design Engineer! Senior Design and Supervisor Engineer

የአድዋ ጦርነት (130ኛ ዓመት)፡የአድዋ ጦርነት በየካቲት ፳፫ ቀን ፲፰፻፹፰ ዓ.ም. በኢትዮጵያና ኢጣሊያ መካከል የተካሄደ ውጊያ ሲሆን የአንደኛው የኢትዮጵያና ጣሊያን ጦርነት ክፍል ነው።በጊ...
28/02/2026

የአድዋ ጦርነት (130ኛ ዓመት)፡
የአድዋ ጦርነት በየካቲት ፳፫ ቀን ፲፰፻፹፰ ዓ.ም. በኢትዮጵያና ኢጣሊያ መካከል የተካሄደ ውጊያ ሲሆን የአንደኛው የኢትዮጵያና ጣሊያን ጦርነት ክፍል ነው።በጊዜውም የኢትዮጵያ ንጉስ በአፄ ሚኒሊክ እና በ ጣልያኑ የሰራዊቱ አዛዥ በነበሩት ሞሶሎኒ ጊዜም ነበር ።በ ኢትዮጵያ አሸናፊነት የጣልያን የቀኝ ግዛት ማስፋፋት ተኮላሸ።

ምኒሊክ ተወልዶ ባያነሣ ጋሻ ' ግብሩ እንቁላል ነበር ይሄን ጊዜ አበሻ፤

***

ገበየሁ ቢሞት ተተካ ባልቻ

መድፍ አገላባጭ ብቻለብቻ፤

***

የአድዋ ሥላሴን ጠላት አረከሰው

ገበየሁ በሞቴ ግባና ቀድሰው፤

የአድዋ ድል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ክብር ማኅተም፤ የጥቁር ህዝቦች የነፃነት ተጋድሎ ቀንዲል ነው፡፡ የመላው ዓለም ተፈጥሮአዊ ግብር እና ሰብአዊ ክብር የታደሠው፤ በእውነትና በፍትህ ህልውናና ምልዓት ላይ የተሰካ ትልቅ ጥርስ የተነቀለው … በአድዋ የታላቅ ህዝቦች ታላቅ ድል ነው፡፡

ከአዲስ አበባ ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ ስንሄድ 1066 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ታላቁ ጦርነት የተደረገበትና ታላቁ ድል የተገኘበት ሥፍራ አድዋ ከተማና የከተማው ግድም ገመገሞች ይገኛሉ፡፡ በኢትዮጵያውያን አቡሻኽር (Julian calendar) የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም፤ ወይም በአውሮጳውያን የዘመን አቆጣጠር (Gregorian Calendar) February (የካቲት) መጨረሻ እና March (መጋቢት) መጀመሪያ ላይ 1896. ለጦርነቱ መነሻ የሆነው ውል የተፈፀመው በዚሁ ዘመን ከአዲስ አበባ በስተሰሜን 468 ኪሎ ሜትር ርቀት ግድም ከውጫሌ ከተማ ግርጌ ከአምባሰል ተራራ ሥር ወሎ ውስጥ ንጉሥ ይስማ እየተባለ በሚጠራ ሥፍራ ነው፡፡

ሸልዶ ተራራ ወይም (ሶሎዳ ተራራ)፤ ማርያም ሸዊቶ፤ አዲ ተቡን፤ ረቢ አርእየኒ (እግዚሃር አሳየኝ)… በመሠኘት የሚታወቁት እነዚህ ገመገሞችና ተራራማ ሥፍራዎች ዋነኞቹ የጦር ግንባሮች ናቸው፡፡ በመቶ ሺህ የሚሠላ የኢትዮጵያ ገበሬ ሠራዊት ከአንድ ቀን ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ የአውሮጳ ቅኝ ገዢ ወራሪዎችን ድባቅ ከመታና ረግጦ ካስወጣ በኋላ ከምሽቱ አራት ሰዓት ግድም (የካቲት 23 ቀን) እንዳማርያም ላይ ተሰባስቦ በአንድ እግሩ ቆሞ ቀኙን (ድሉን) ለሰጠው አምላክ ምሥጋና አቅርቧል፡፡ አባት ሆይ፤ ንቀውን የመጡ የአገራችንን ድንበርና ልዕልና የደፈሩ የአውሮጳ ኮሎኒያሊስት ወራሪዎችን እንድናሸንፍ (ድል እንድናደርግ) ስለረዳኸን እናመሰግንሃለን ...

ሃያ ዘጠኝ ሺህ ፈረሰኞችን ጨምሮ ከመቶ ሺህ እስከ መቶ ሃያ ሺህ የሚገመት አንድ ሺህ ኪሎ ሜትር በባዶ እግሩ የተጓዘ የኢትዮጵያ የገበሬ ሠራዊት በወታደራዊ አካዳሚ የሠለጠነውን የአውሮጳ ወራሪ ጦር የካቲት 23 ማለዳ አሥራ አንድ ሰዓት ግድም ገጥሞ ከረፋዱ አራት ሰዓት ላይ ማሸነፉን አረጋግጧል ይለናል የታሪክ ተመራማሪው ጆርጅ በርክሌይ የአድዋ ጦርነትና ዳግማዊ አፄ ምኒሊክ በተሰኘና ዳኘው ኃይለሥላሴ ወደ አማርኛ በተረጐሙት መጽሐፉ ላይ፡፡ የኢትዮጵያ ገበሬ ሠራዊት ፈረሱ ላይ ሆኖ የጋሻውን እምብርት መሬት ላይ እያጠቀሰ ጐራዴውን አየር ውስጥ እየቀዘፈ ባበደ መንፈስ (በተቆጣና በቆረጠ መንፈሥ) በጀግንነት ተዋግቷል፡፡

ጦርነቱ በተጀመረ ከአምስት ሰዓት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ሃምሣ ስድስቱም የኢጣሊያ መድፎች ሙሉ ለሙሉ ተማርከዋል፤ የቅኝ ገዢውን ወራሪ ሠራዊት ከመሩት ጀኔራሎች ጄኔራል አልቤርቶኒ ሲማረክ የሠራዊቱ ዋና አዛዥ ጄኔራል ባራቴሪ ከጥቂት አጃቢዎቹና በሽንፈት ከተበታተኑ የኢጣሊያ ወታደሮች ጋር ሸሽቷል፡፡

በዚህ ድብልቅልቅ ያለ ውጊያ ከሃምሣ ስድስቱ የኢጣሊያ መድፎች በተጨማሪ ብዙ ሺህ ቀላልና ከባድ መትረየሶች እንዲሁም የነፍስ ወከፍ ጠመንጃዎች በአሥር ሺሆችና በመቶ ሺዎች ከሚቆጠሩ መሰል ጥይቶቻቸው ጋር ተማርከዋል፡፡ በአጠቃላይ ምርኮው ወደ አዲስ አበባ የተጓጓዘው በአምስት መቶ አጋሰሶች ተጭኖ ነው፡፡

በማግስቱ የካቲት 24 ቀን 1888 ዓ.ም ከጠዋቱ አራት ሰዓት ላይ የኢጣሊያ ምርኮኞች በምኒሊክ ድንኳን ፊት ሲያልፉ የኢትዮጵያ ጀግና የገበሬ ሠራዊት እየፎከረ እየሸለለ አሳልፉዋቸዋል፡፡ ጄኔራል አልቤርቶኒ በምርኮኛነት ኢትዮጵያ ውስጥ ቆይቶ አገሩ ከተመለሰ በኋላ በፃፈው መጽሐፍ ላይ ከሚፎክሩት ጥቁር የነፃነት ተዋጊዎች መሃከል አንዱ እንደ እኛው ነጭ አውሮጳዊ ነው ብሎአል፡፡ ይህ ሰው ከፈረንሣይ አገር ወደ ኢትዮጵያ ለጦር መሣሪያ ጥገና የመጣ ካፒቴን ኦርዲናንስ ሲሆን፤ አሁን ጊዜው የጦርነት ስለሆነ ወደ አገርህ ተመለስ ቢባል ቢሠራ አሻፈረኝ ብሎ ከእኛ ጋር አድዋ ድረስ የዘመተ ነው፡፡

ኢትዮጵያ በአድዋ ጦርነት ላይ ከተዋጋችባቸው የጦር መሣሪያዎች ሠማንያ ሺህ የሚሆኑት አሮጌ ጠመንጃዎች የተገዙት ከፈረንሳይ አገር በምሥጢር ነው፡፡ ጠመንጃዎቹን ገዝተው ወደ ኢትዮጵያ ያስገቡት ለመጀመሪያ ጊዜ መኪና ወደ ኢትዮጵያ ያስገቡት በሥጋ በደምና በትውልድ አርመናዊ በነፍስና በመንፈስ በዜግነትና በልብ ፍቅር ኢትዮጵያዊ የሆኑት የኢትዮጵያ የልብ ወዳጅ ሰርኪስ ቴሪዝያን ናቸው፡፡

አሁን በመዲናችን የሚገኘው የአርሾ ላቦራቶሪ ባለቤትና በዓለም ላይ ኢትዮጵያን የመሰለ ውብ አገር የለም ያሉኝ ዶክተር አርሻቪር ቴሪዝያን ኢትዮጵያ ውስጥ አርመናዊ ትውልድ ኖሮት ኢትዮጵያዊ ዜግነት የሌለው (ኢትዮጵያዊ ያልሆነ) አርመን ያለመኖሩን ያጫወቱኝ ከአሥራ አምስት ዓመታት በፊት ነው፡፡ የሠማንያ ሺህ ጠመንጃዎቹን አገዛዝ ሁናቴ የሚያውቁት ደግሞ ከአርሾ ቀደም የሚሉትና ከአሥራ ስድስት ዓመታት በፊት ለሪፖርተር ጋዜጣ ይሄንኑ በአንደበታቸው የገለፁት አቬዲስ ቴሪዝያን ናቸው፡፡ ሠርኪስ ቴሪዝያን ጠመንጃዎቹን ከገዙ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ያስገቡት በጅቡቲ በኩል ነፋስ ባህሩን ሲያነሳና እንደ ግድግዳ ሲያቆም በዚያ ተፈጥሮአዊ ክንውን በመጠቀም ደብቀውና ሸሽገው ነው፡፡

የአድዋ ድል ለመጀመሪያ ጊዜ የተከበረው በሠባተኛ ዓመቱ በ1895 ዓ.ም (እ.ኤ.አ በ1903) ከአንድ መቶ ዘጠኝ ዓመታት በፊት አሁን ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ያለበት ሥፍራ ምኒሊክ አደባባይ ነው፡፡ በክብረ በዓሉ (በድል በዓሉ) ላይ ዲፕሎማቶችና የውጪ አገር መንግሥታት ተወካዮች አርበኞች የመንግስት ባለሥልጣኖች ብዙ ሺህ ፈረሰኞችና ሥፍር ቁጥር (ወፈ ሠማይ የሆኑ) ኢትዮጵያውያን ከሊቅ እስከ ደቂቅ መገኘታቸውን፤ ከፈረሰኞቹ ብዛት የተነሳ ፀሐይ በአቧራ እስከመጋረድ መድረሷን ጳውሎስ ኞኞ የኢጣሊያና የኢትዮጵያ ጦርነት በተሰኘ መጽሐፉ ላይ ጽፎአል፡፡ እንዲሁም ተክለፃዲቅ መኩሪያን የመሳሰሉ ኢትዮጵያውያን የታሪክ ተመራማሪዎችና የውጪ አገር ዜግነት ያላቸው ፀሐፍትና ተመራማሪዎች በተለያዩ መፃሕፍቶቻቸው ይሄንን አሣምረው ጽፈውታል፡፡

ታላቁ የጥቁር ህዝቦች ድል (የአድዋ ድል) በመላው ዓለም ፖለቲካ ላይ ከፍተኛና ዋነኛ ለውጦች አምጥቶአል፡፡ የእንግሊዝ ጋዜጦች በአድዋ ድል ማግስት የዓለም ታሪክ ተገለበጠ ታላቅ የትውልድ ኃይል በአፍሪቃ ተቀሰቀሰ … ብለው ፃፉ፡፡ በኢንሳይክሎፒዲያ ብሪታኒካ፡- ዘመናዊት ኢትዮጵያን የፈጠረ የተባሉት ዳግማዊ ዓፄ ምኒሊክ በሌሉበት (እርሳቸው በአካል ባልተገኙበት የነፃነት ተጋድሎ መሪዎች ጉባኤ) የአፍሪቃና የመላው ዓለም ጥቁር ህዝቦች የነፃነት ተጋድሎ መሪ ተደርገው ተመረጡ፡፡

ጦርነቱ ከመደረጉ በፊት እ.ኤ.አ በ1880ዎቹ መጀመሪያ ጀርመን አገር በርሊን ከተማ ላይ በተደረገው የአውሮጳ ቅኝ ገዢ (ኮሎኒያሊስት) መንግስታት ሥልጣናትና ልሂቃን የጦር ጄኔራሎችና ሊቃውንት ስብሰባ ላይ ጥቁር ትልቅ ትል ነው ቅንቡርስ ነው እንጂ ነፍስ ያለው ሰው አይደለም ብለው የነበሩ አፈሩ፤ እውነትና ፍትህ ኢትዮጵያና አፍሪቃ ከበሩ፡፡ ከሲግመንድ ፍሮይድ የሳይኮ አናላይሲስ ጥናትና ምርምር በፊት፡- ጥቁር ህዝብ ትልቅ ትል ላይሆን ነፍስ ያለው ሰው ከሰውም ሰው ጀግና መሆኑን በተጨባጭ ያስመሰከረ የኢትዮጵያ ገበሬ ሠራዊት ነው፡፡

ከፈረንጅ የአውሮጳ መንግሥታት ሩሲያና ፈረንሳይ የአድዋን ድል ከልብ ደገፉ፡፡ ጀኔራል ባራቴሪ በአገሩ በኢጣሊያ ጦር ፍርድ ቤት ቀርቦ ማዕረጉ ተገፈፈ፡፡ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሲኞር ክሪስፒ በፈቃዳቸው ሥልጣናቸውን ለቀቁ፡፡

የኢጣሊያዊው ንጉሥ አማኑኤል ኡምቤርቶ የልደት ቀን የሀዘን ቀን እንዲሆን ተወሰነ፡፡ ሮማ (ሮም)ን ፍሎሬንስን ሚላኖ (ሚላን)ን ቬነስን…የመሳሰሉ የኢጣሊያ ከተሞች ምኒሊክ ለዘላለም ይኑር በሚሉ የተቆጡ አውሮጳውያን ትዕይንተ ህዝብ አድራጊዎች ተጥለቀለቁ፡፡ ኢትዮጵያ በአድዋ ጦርነት ወቅት በዋናው የጦር ግንባር ገጥማ በፍልሚያ ድል ማድረግ ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ በአራት መስክ ሠለጠነች በምትባለው አውሮጳዊት አገር ኢጣሊያ ላይ ድል ተቀዳጅታለች፡፡ ይኸውም፡- በጦርነት እና በወታደራዊ መረጃ (Military Security intellegence)፤ በዲፕሎማሲና በፖለቲካ ጥበብ ነው፡፡

በፖለቲካ ጥበብ በኢጣሊያ ቅኝ ገዢ ብልጣብልጥ የመንግሥት ሥልጣን ላይ ድል የተቀዳጀችው ገና ጦርነቱ ሳይጀመር ለጦርነቱ መጀመር መነሻ የሆነው የውጫሌ ውል በተደረገበት ሥፍራ ነው፡፡

የውጫሌ ውል አንቀጽ አሥራ ሰባት የጣሊያንኛው፡- ኢትዮጵያ ከአውሮጳ መንግሥታት ጋር ማድረግ የምትፈልገውን ግንኙነት በኢጣሊያ መንግስት በኩል ማድረግ አለባት ሲል፤ አማርኛው ደግሞ ኢትዮጵያ ከአውሮጳ መንግሥታት ጋር ማድረግ የምትፈልገውን ግንኙነት በኢጣሊያ መንግሥት በኩል ማድረግ ትችላለች ይላል፡፡

የአማርኛው የኢትዮጵያን ሉአላዊነትና ልዕልና ያከብራል፤ የጣሊያንኛው የኢትዮጵያን ሉአላዊነትና ልዕልና መድፈር ብቻ ሳይሆን ብሔራዊ ክብሯንና ጥቅሟን ይነካል፡፡ ይሄን የተገነዘቡት የኢትዮጵያ መሪዎች የውሉ አንቀጽ አሥራ ሰባት የጣሊያንኛ ትርጓሜ የኢትዮጵያን ክብርና ጥቅም በማይነካና ሉአላዊነቷን በሚያከብር መልኩ እንዲስተካከል በተደጋጋሚ ወተወቱ፡፡ መወትወቱ ውጤት ሳያመጣ ቢቀር፤ ምኒሊክ፡- መዘግየት አደገኛ ነው ጣይቱ አሉ፤ ስለዚህ ጉዞ ወደ ወሳኙ ጦርነት (ማድረግ) የግድ ነበር፡፡

የኢትዮጵያን አገራዊ ክብርና ጥቅም ህልውናና ልዕልና ሲሆን ሲሆን በውድ ካልሆነ ደግሞ ሳይወድ በግድ ማስከበርና ማስጠበቅ የአንድ አገር መንግሥት ዋነኛ ግዴታና ኃላፊነት ነው፡፡

ስለዚህ አባቶቻችን (የጥንት ወላጆቻችን) ውትወታቸው አልሰማ ቢል ጦር እንግጠም አሉ፡፡

ይሄ የፖለቲካ ጥበብ ብልጫ ወይም ድል ነው፡፡

በወታደራዊ መረጃ (Military Security intellegence) ብልጫ የኢንቲጮ ተወላጅ በሆኑት ባሻዬ አውአሎም ሀረጐት አማካይነት ኢትዮጵያ ሠለጠነ የተባለውን የአውሮጳ ኃይል አሸንፋ ጣሊያኖች ባልፈለጉት ቦታና ባልመረጡት ጊዜ ወደ ጦርነት እንዲገቡ አድርጋለች፡፡

በወታደራዊ ሣይንስ (Military Science) አገባብ ለጦርነት የተንቀሳቀሰ አንድ ሠራዊት ወዲያውኑ ወደ ጦር ግንባር መግባት አለበት፡- ይሄ አንድ ነጥብ ነው፡፡ ሌላው ነጥብ አንድ ለግዳጅ የተንቀሣቀሠ ሠራዊት ለመሰናዶም ሆነ ለመከላከል ውጊያ በአንድ የመከላከያ ወረዳ ከሠፈረ በዚያ መከላከያ ወረዳ ከስድስት ወራት በላይ መቆየት የለበትም፡፡ በአንድ ቦታ ላይ ከስድስት ወራት በላይ ከቆየ ሊደርስ የሚችል የወታደራዊ ሥነልቦና (Military Psychology) ጉዳት አለ፡፡ የመሸገበትን የመከላከያ ወረዳ እየተለመማመደ ሲሄድ ስለሚዘናጋና የውጊያ ስሜቱ እየቀነሰ (እየቀዘቀዘ) ስለሚመጣ ጉዳት አለው፡፡ ከሎጂስቲክ አኳያ የውጊያ ዝግጁነቱም አደጋ ላይ ስለሚወድቅ (በሌላ አነጋገር ስንቅ እየጨረሰ ስለሚሄድ) በነዚህ ምክንያቶች በአፋጣኝ ወደ ጦርነት መግባት ለሠራዊቱ ድል አድራጊነት ትልቅ ጥቅም አለው፡፡

የኢትዮጵያ በሠላም ጊዜ ገበሬ በጦርነት ጊዜ ጀግና ተዋጊ እንጂ ዘመናዊ ወታደራዊ መሠረት ያለው Professional Army ባልነበራት በዚያ ዘመን ለአንድ መቶ ሃያ ሺህ ሠራዊት የሎጂስቲክ አገልግሎት እየሰጡ ለረጅም ጊዜ መቆየት አስቸጋሪ ነው፡፡ ስለዚህ የጀግንነት ግለት ሳይበርድ የሎጂስቲክ (ስንቅ ትጥቅ መድሃኒት) አቅም ሳይዳከም በፍጥነት ጦር መግጠም እጅግ አስፈላጊ ነበር፡፡ የኢትዮጵያ ሠራዊት ጦርነቱን ፈጥኖ ለመግጠም ጣሊያኖች ወደ አድዋ መምጣት አለባቸው፤ ወይም ደግሞ የእኛ ሠራዊት ጣሊያኖች ወደመሸጉበት የኤርትራ ከፍተኛ ቦታዎች መሄድ አለበት፡፡ ከነዚህ ሁለት ሁኔታዎች የአንደኛው መሆን የግድ ነበር፡፡ ወደ ጣሊያኖች መሄድ ከፖለቲካ ሁኔታዎች ባሻገር ከወታደራዊ ሳይንስ አንፃር የሚመረጥ አይደለም፡፡ በምሽግ ውስጥ ሆኖ የሚከላከል ሠራዊትና ከምሽግ ወጥቶ የሚያጠቃ ሠራዊት መስዋዕትነት የመክፈል ዕድሉ እኩል አይደለም፤ ለሚከላከል አንድ ወታደር ሶስት የሚያጠቃ ወታደር ነው የሚያስፈልገው፡፡

ስለዚህ ጣሊያኖች ወደ አድዋ እንዲመጡ ማድረግ የግድ ሆነና የአድዋ ድል ቁልፍ የምላቸው የአርባ ዓመቱ ጐልማሣ ባሻዬ አውአሎም ሀረጐት ተጠሩና ለአንድ ታላቅ አገራዊ ኃላፊነት እንዲሠናዱ ተደረገ፡፡ ይሄ ሁሉ በምሥጢር ነው የተከወነው፡፡ በሚቀጥሉት ቀናት አውአሎም ለኢጣሊያ ኮሎኒያሊስት ወራሪዎች ከሚሠልሉ የአገር ተወላጆች (ፌርማቶሪዎች) ጋር ወደ ባራቴሪ ተላኩ፡፡ ከመሄዳቸው በፊት ስንቅ ማለቁና ተስቦ በሽታ በሠራዊቱ ውስጥ መግባቱ ፌርማቶሪዎች ባሉበት ተለፈፈ፡፡ አውአሎምና ፌርማቶሪዎቹ ወደ ኤርትራ ዘልቀው ለጄነራል ባራቴሪ ይሄንኑ ነገሩት፡፡

ባራቴሪ ጊዜው አሁን ነው አለና የካቲት 22 አመሻሽ ላይ በአውአሎም መሪነት ሠራዊቱን ይዞ ወደ አድዋ ተመመ፡፡ የካቲት 21 እንዳይነሣ ዝናብ ስለያዘው እንጂ ታላቁ ጦርነት የካቲት 22 ሊደረግ ይችል ነበር፡፡ ስለዚህ ጄነራል ባራቴሪ በዝናብ በመያዙ ምክንያት ዘመቻውን በማግሥቱ አደረገና የካቲት 22 ቀን 1888 ዓ.ም ሌሊቱን ሙሉ ሲጓዝ አድሮ ሊነጋ ሲል የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም አድዋ ጦር ግንባር ደረሠ፡፡ አውአሎም ከፊት ለፊታቸው የጀግናው የቱርክ ፓሻ የአፍሪቃ ጀኔራል አሉላ አባነጋ የገበሬ ሠራዊት ምሽግ እንደታያቸው መሮጥ ጀመሩ፡፡ ባራቴሪ፡- አውአሎም አውአሎም ብሎ ተጣራ፡፡ እስሀ ዝዋአልካዮ አያውለና ብለውት ዘለው አሉላ ምሽግ ውስጥ ገቡ፡፡ ዛሬ አንተን አያድርገኝ ማለታቸው ነው በአማርኛ፡- እስሀ ዝዋአልካዮ አያውለና፡፡

ከጥቂት ደቂቆች በኋላ ምድር ቁና የሆነችበት ድብልቅልቅ ያለው ጦርነት ተጀመረ፡፡ የኢትዮጵያ ጀግና የገበሬ ሠራዊት ከጠዋቱ አራት ሠዓት ግድም ታላቁን የአድዋ ድል መቀዳጀቱን አረጋገጠ ፡፡ ብዙ ሺህ የኢጣሊያ ወታደሮች በጦር ሜዳ ተገደሉ፡፡ ብዙ ሺዎች ደግሞ ቁስለኛና ምርኮ ሆኑ፡፡ የተቀረውንና ድል ተመትቶ የተበታተነውን የኢጣሊያ ወታደር እያሣደደና እያባረረ አፍሪቃዊው ኃይል ፈጀው ብሎ ፅፎአል ጆርጅ በርክሌይ፡፡ ከሚሸሹት መሃከል አንዱ የአውሮጳዊው ወራሪ ሠራዊት ዋና አዛዥ ጄኔራል ባራቴሪ ነው፡፡

ይሄ (በአውአሎም ብስለትና ሥልጡንነት መስዋዕትነትና ኢትዮጵያዊ ፍቅር የተገኘው) ሰለጠነ በሚባለው የአውሮጳ ኃይል ላይ አልሰለጠነም በሚባለው አፍሪቃዊ ኃይል የተጨበጠ ትልቅ የወታደራዊ መረጃ (Military Security intelligence) ብልጫ ወይም ድል ነው፡፡

በወታደራዊ ሣይንስ ደግሞ ወታደራዊ መረጃ ለወታደራዊ ግጃጅ አፈፃፀም ዋነኛና ወሣኝ ጠቀሜታ አለው፡፡ በዚህች ዓለም ላይ ከተደረጉ አብዛኞቹ ጦርነቶች ድል ያደረጉት የወታደራዊ መረጃ ብልጫ የነበራቸውና ፍትህና እውነትን ፖለቲካዊ መሠረት ያደረጉት ናቸው፡፡ እኛ ሁለቱንም ነበረን፤ ዓላማችን የአገራችንን ጥቅምና ክብር ህልውናና ልዕልና ማስከበር ነፃነታችንን ማስጠበቅ ሲሆን፡- ይህም የፍትህና የእውነት ነፍሥ ነው፡፡ በአገር ወዳዱ ባሻዬ አውአሎም ሀረጐት አማካይነት ደግሞ በአውሮጳ ላይ የወታደራዊ መረጃ ብልጫን ተቀዳጀን፡፡ ኢትዮጵያ በረጅም ዘመን ታሪኳ ከውጪ ወራሪዎች ጋር ባደረገቻቸው ጦርነቶች ሁሉ፡- እውነትና ፍትህን መሠረት አድርጋለች፡፡

የዲፕሎማሲያዊ ድሉን የተቀዳጀችው ኢትዮጵያ፡- አውሮጳ ውስጥ ባስቀመጠቻቸው የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ወላጅ አባት ራስ መኮንንና ግራዝማች ዮሴፍ በተሰኙ ዲፕሎማቶቿ አማካይነት ነው፡፡ ጣሊያኖች ኢትዮጵያውያን ያልሰለጠኑ በመሆናቸው በምርኮኞች ላይ ሠብአዊነት የጐደለው ድርጊት ይፈፅማሉ ብለው ያስወራሉ፡፡ ግራዝማች ዮሴፍ በተለያዩ ቋንቋዎች እየፃፈ ለአውሮጳ ጋዜጦች ይሄን ያስተባብላሉ፡፡ ከጥቂት ጊዜያት በኋላ ደግሞ ኢትዮጵያ ልክ ዲፕሎማቶቿ እንዳሉት ምርኮኞችን ግብር አብልታ አካላቸዉም ምቾታቸውም ሳይጓደል ወደ አገራቸው ሰደደች፡፡

በዚህም ዲፕሎማሲያዊ ሥልጣኔዋን ለመላው አውሮጳ እና ለመላው ዓለም በተጨባጭ አሳየች፡፡ ከመቶ ዓመታት በላይ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያላት ብቸኛ አፍሪቃዊት አገር፡- ኢትዮጵያ ነች፡፡ የአብዛኞቹ የአፍሪቃ አገሮች ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ረጅም ዕድሜ ከስድሣ ዓመት አይዘልም፡፡ ኢትዮጵያ፡- ከኢጣሊያና ከፈረንሣይ ከአሜሪካ (USA) እና ከእንግሊዝ ከሩሢያና ከጀርመን (ከስድስት አገራት) ጋር ከመቶ ዓመታት ለሚበልጥ ጊዜ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትን አዳብራ እና አፅንታ ቆይታለች፡፡

በአድዋ ድል፡-

ዋነኛው ድል በጦር ግንባር ፍልሚያ የተገኘው ድል ነው፤ ታላቁ የአድዋ ድል፡፡

የአድዋ ጦርነት(የጥቁሮች የነፃነት ተምሳሌት) የተደረገው በሁዳዴ ፆም ውስጥ ነው፡፡ ከዚያ በፊት በአፄ ቴዎድሮስ ዘመነ መንግሥት የተደረገው የመቅደላ ጦርነትም በሁዳዴ ፆም ውስጥ ነው የተካሄደው፡፡ በአድዋ ጦርነት ፆምና ውጊያ አብሮ ስለማይሄድ ግብፃዊውን ጳጳስ ሠራዊቱን ይፍቱትና እንደ ልቡ ይዋጋ ቢባሉም ባለመፍታታቸው ከኢትዮጵያ የገበሬ ሠራዊት ጿሚ የሆነው እየፆመ ለመዋጋት ተገዶአል፡፡ በመቅደላ ውጊያ ዓፄ ቴዎድሮስ [ካሣ ኃይሉ ወልደጊዮርጊስ (አባ ታጠቅ ካሣ) (መዩሣው ካሣ) (ወሬሣው ካሣ)] ሊወጋቸው ለመጣው እንግሊዛዊው ጄኔራል ናፒዬርና ሠራዊቱ ፆምህን ፈትተህ ከእኔ ጋር ውጊያ ግጠም ብለው አንድ ሺህ በጐች ልከውለታል፡፡

ከአድዋ ጦርነት በፊት ባሉት ጥቂት ወራትና ሣምንታት መቀሌና አምባላጌ ላይ የተደረጉ ጦርነቶች አሉ፡፡ የመቀሌን ከተማ በኢጣሊያዊው ኮሎኔል ጋሊያኖ ከሚመራው አውሮጳዊ ሠራዊት ለማስለቀቅ መስዋዕትነቱ የበዛ በመሆኑ፡- መቀሌ የተለቀቀችው በፈረንጆች ሚሊኒየም BBC (British Broadcasting Corporation) የሚሊኒየሙ ምርጥ ሠብዕና ብሎ ከአህጉር አፍሪቃ ባጫቸው ከጐንደር ቤተሠብ በሚወለዱት እቴጌ ጣይቱ ብጡል ሥልጡን ወታደራዊ መላ ነው፡፡

ዝርዝሩን እዚህ አላወሣውም እንጂ መቀሌ በጣይቱ ልዩ ወታደራዊ ብቃት መያዝዋን መግለፅ ይጠቅማል፡፡ በኋላ ላይ ኮሎኔል ጋሊያኖ በአድዋ ጦርነት ተማርኮ፡- የምንሊክን ፊት ከማይ ግደሉኝ ብሎአል፡፡ በአምባላጌው ጦርነት ሊቀ መኳስ አባተ መድፍ ተኩሠው በጣሊያን መድፍ አፍ ውስጥ እስከ መክተት የዘለቀ አነጣጣሪነታቸውን አሣይተዋል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት ሥልጣናት፡- ማዕከል ወሎ ውጫሌ በነበረበት ሁናቴ፤ ዳግማዊ ዓፄ ምኒሊክ (አባ ዳኘው) ለህዝባቸው የክተት ጥሪ ካደረጉ በኋላ ከዳር እስከ ዳር የተንቀሣቀሠው የተቆጣ ኢትዮጵያዊ ሠራዊት ሢተም፤ ሲገባኝ ከሠሜን ኢትዮጵያ ከጐንደር ከጐጃም ከወሎና ከትግራይ … የተንቀሳቀሰው አትንኩኝ ያለ ኢትዮጵያዊ ጀግና ከሚተምመው ሠራዊት የተገናኘው በትውልድ አቅራቢያው ሆኖ ነው፡፡

መጓጓዣ በሌለበት ዘመን የሠሜኑን የኢትዮጵያ ጀግና የገበሬ ሠራዊት ወደ ሰሜን ለማዝመት ሲባል በመሀል አገር ማሰባሰብ የሚያስፈልግበት ሁኔታ አልነበረም፡፡

የውጫሌ ውል /ይስማ ንጉስ/ለዓድዋ ጦርነት ምክንያት የሆነው የውጫሌ ውል የተፈራረሙበት ቦታ "ይስማ ንጉስ" በደቡብ ወሎ ዞን በአምባሰል ወረዳ የሚገኝ ሲሆን ቦታው ከዞኑ ዋና ከተማ ደሴ በ50...
20/02/2026

የውጫሌ ውል /ይስማ ንጉስ/
ለዓድዋ ጦርነት ምክንያት የሆነው የውጫሌ ውል የተፈራረሙበት ቦታ "ይስማ ንጉስ" በደቡብ ወሎ ዞን በአምባሰል ወረዳ የሚገኝ ሲሆን ቦታው ከዞኑ ዋና ከተማ ደሴ በ50 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል።
ለታሪካዊው የአድዋ ጦርነት መነሻ በመሆን ከሚጠቀሱ ምክንያቶች መካከል የውጫሌ ውል በቀዳሚነት ይጠቀሳል። የውጫሌ ውል በዳግማዊ አፄ ሚኒሊክና በጣሊያን ንጉስ ኡምቤርቶ ወኪል ኮውንት አንቶሎኒ መካከል ሚያዚያ 25 ቀን 1881ዓ.ም መፈረሙ ይታወቃል።
የውሉ የአማርኛና የጣሊያንኛ ትርጉም የሚቃረኑ ናቸው። በተለይ የውሉ 17ኛ አንቀፅ የአድዋ ጦርነት መንስኤ መሆኑ ይታወቃል። በዚህ ውል ውስጥ 17ኛው አንቀጽ አማርኛው፣ "የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ከአውሮፓ ነገሥታት ለሚፈልጉት ጉዳይ ሁሉ በኢጣሊያ መንግሥት አጋዥነት መላላክ ይቻላቸዋል" ሲል፣ የኢጣሊያንኛው ደግሞ "የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ከአውሮፓ ነገሥታት ለሚፈልጉት ግንኙነት በኢጣሊያ መንግሥት አማካይነት ማድረግ ይገባቸዋል" ይላል። የውጫሌ ውል የአድዋ ጦርነት መንስኤ ለአድዋ ድል በዓል መከበር ደግሞ መነሻ መሆኑ መረጃዎች ያሳያሉ።
ጣሊያን የውጫሌ ውል የንግድና የፍቅር ነው በማለት ብትቀርብም ከመነሻው ጀምሮ ብዙ ጥርጣሬ፣ ክርክር እና ተቃውሞ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ሲሰማ እንደነበር ታሪክ ያስታውሳል፡፡ በተለይ በአንቀጽ 3 እና 17 ምክንያት የተነሳው ተቃውሞ በቀጥታ በሁለቱ አገራት መካከል ለተካሄደው ጦርነት መነሻ እንደሆነ ይታመናል፡፡
በአንቀጽ 17 አማካኝነት ጣሊያን አምታች የሆነ ቃል በመጠቀም የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት በመገርሰስ የጣልያን ሞግዚት እንድትሆን ቀዳዳ እያበጀች መሆኑ ሲታወቅ ለነፃነቱ ቀናኢ በሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ ዘንድ ከፍተኛ ቁጣን ቀስቅሷል፡፡ በዚህ ጊዜ እቴጌ ጣይቱ “እኔ ሴት ነኝ፣ ጦርነት አልወድም፡፡ ግን እንዲህ መሳዩን ውል ከምቀበል ጦርነት እመርጣለሁ፡፡" ይስሙ ንጉሥ” የሚል ታሪካዊ ንግግር አድርገዋል፡፡ ይሄን ንግግራቸውን ተከትሎም የውጫሌ ውል የተፈረመበት ቦታ “ይስማ ንጉሥ" በሚል ተሰይሞ እዚህ ዘመን ደርሷል፡፡

ታላቁ ባለቅኔ ሙሉጌታ ተስፋዬ (አያሙሌ) “የባለቅኔው ኑዛዜ” ሰሞኑን የታተመ መጽሐፍ ነው፡፡ የአንድ ‹‹ተራ›› ገጣሚ ግርድፍ ግለታሪክ የሰፈረበት መጽሐፍ፡፡ ብዙ የጅዝብና (hippie) ሕይ...
04/02/2026

ታላቁ ባለቅኔ ሙሉጌታ ተስፋዬ (አያሙሌ)

“የባለቅኔው ኑዛዜ” ሰሞኑን የታተመ መጽሐፍ ነው፡፡ የአንድ ‹‹ተራ›› ገጣሚ ግርድፍ ግለታሪክ የሰፈረበት መጽሐፍ፡፡ ብዙ የጅዝብና (hippie) ሕይወት የኖረ፣ ትንሽ ኮስታራ ሕይወትን በስሱ ያጣጣመ የአንድ ኢትዮጵያዊ ባለቅኔ ቅንጭብ ታሪክ፡፡ ሰውየው በ1946 ወልዲያ ተወልዶ በ1996 ዓለም ገና ሕይወቱ አለፈች፡፡ ትንሽ ትንሽ የጋሽ ስብሐትን የሚመስል ሕይወት፣ ትንሽ ትንሽ የብአዴን ታጋዮችን የሚመስል ሕይወት፣ ብዙ ብዙ የጎዳና ሕይወት ኖሯል፡፡ ይህ ባለቅኔ ሙሉጌታ ተስፋዬ ወይም አያ ሙሌ ይባላል፡፡
የአያ ሙሌ ነገር ግራ ነው! ሕይወቱም ሲበዛ ዥንጉርጉር ናት፡፡
ለምሳሌ ተራ ገጣሚ ነው እንዳንል እጅግ ተወዳጆቹ ሙዚቃዎች የርሱ አሻራ ያረፈባቸው ኾነው እናገኛለን፡፡ ብኩን ሰው ነው እንዳንል በኢህአፓ እሳት ፖለቲካ ዉስጥ ተወልዶ፣ በማርክሲዝም ሌኒኒዝም ነዶ፣ በብአዴን በስሎ፣ በNGO ደመወዝ ከብሮ፣ በኢህአዴግ ላዕላይ ቤት ገብቶ፣ በጋዜጠኝነት ሠርቶ፣ ከመንግሥት አፓርታማ ተበርክቶለት የሴኮ ቱሬ ጎረቤት ኾኖ የኖረ ሰው ነው፡፡
ደግሞ ያን ሰምተን ለአንቱታ ስናዘጋጀው ድንገት ሥራውን ጥሎ ይጠፋል፡፡ ዘበኛ፣ ኩሊ፣ ወዛደር፣ ጎዳና ተዳዳሪ ይሆናል፡፡ ብቻ ያያ ሙሌ ነገር ለወሬም አይመች፡፡
ያኔ ኢህአዴጎች እንደገቡ ሰሞን (ለነገሩ እጃቸውን ይዞ አዲሳባ ካስገቧቸው ሰዎች ዉስጥ አንዱ እሱ ራሱ ነው) አንድ የከበረ ወዳጁ ወደ አንድ የመንግሥት መሥሪያ ቤት ክበብ ይዞት ይገባል፡፡ የአያ ሙሌን ቆሸሽ ማለት የተመለከተ ታጋይ ዋርዲያ ‹‹አታ…ተመለስ!›› ሲል ሙሌን በቁጣ ያስቆመዋል፡፡ “አይ…ከኔ ጋር ነው ነው፣ ችግር የለም” ብሎ ወዳጁ ከለላ ሰጥቶ ያስገባዋል፡፡ ሙሌ ወደ ወስጥ ከመግባቱ በፊት ግን አንድ ነገር ከነከነው፤ ተመልሶ ወደ ታጋዩ ዋርዲያ ጆሮ ጠጋ ብሎ ‹‹ትናንት በበረባሶ አርገህ ገብተህ ዛሬ በረባሶ ያረገ መናቅ ጀመርክ?›› ብሎት ገባ፣ በትግርኛ፡፡
ሙሌ ትግርኛ ብቻ ነው እንዴ ታዲያ አቀላጥፎ የሚናገር? ግዕዙስ፣ አፋርኛስ፣ ኦሮሚኛውስ፣ አረብኛና እንግሊዝኛወስ፣ ፈረንሳይኛውስ…በሁሉም ይቀኝባቸዋል፡፡ ትንሽ ልጅ እያለ እንደውም ‹‹ጋይድ›› ነበር፡፡ ሊስትሮም ነበር፡፡ ሊስትሮ እያለ የአንድ ደንበኛውን ካልሲ በቀለም ቡሩሽ አበላሽቶ እጅግ ጥብቅ ኩርኩም ቀምሷል፡፡ ያቺ ኩርኩም እስከዛሬም ታመኛለች ይል ነበር፣ በሕይወት ሳለ፡፡ ታዲያ ለመጀመርያ ጊዜ ኤን ጂ ኦ ተቀጥሮ ረብጣ ብር ያገኘ ለት በሲሶው ጠርሙስ ዉስኪ ገዝቶ ጫማ ይጠርግባት የነበረችው ቦታ ላይ ሄደና ዉስኪውን ሙሉ እዚያው አርከፈከፈው፡፡ ሙሌ በቀለኛ ሳይሆን አይቀርም፡፡
በቀለኛ ቢኾን ግን ሐብታም ኾኖ መኖር ነበረበት እኮ!
ደግሞ ማርክሲስት ብለነው ልናልፍ ስንል መጽሐፍ ቅዱስን ከፍ ባለ ደረጃ አጥንቷል፣ ከቤተክርሲያ ደጅ አይጠፋም፡፡ ዉሎ አዳሩም እዛው ነበር ይሉናል፣ የሚያውቁት፡፡ ታዲያ ቆራጥ ክርስቲያን ነበራ! ስንል ቁርዓንን 30 ጁዝ “ሀፍዟል* ይሉናል፡፡ እንዲያው ወሎ ዉስጥ ከቄሶችና ከሼካዎች እኩል ማውራት ይቻለዋል ብለው ይመሰክሩለታል፡፡ ብቻ የአያ ሙሌ ነገር ግራ ነው፡፡
በ1992 ለወጣው ፈርጥ መጽሔት ትንሽ ስለአስተዳደጉ ፍንጭ ሰጥቶ ነበር፣ ያን ዕለት ለጋዜጠኛ እንዲህ አለው…፡፡
“…ምን መሰለህ፣ እኔ ዲቃላ ነኝ፤ አባቴ ትግሬ ናቸው፤ እናቴ የዋድላ ደላንታ ሴት ናት፡፡ ወልዲያ ዉስጥ ሙጋድ የሚባል ቦታ እናቴ ከፊት ለፊት ጠላ ትሸጥ ነበር፡፡ አባቴ ደግሞ በጓሮ በኩል ጨው ይሸጣል፡፡ እናቴ ጠላውን እየሸጠች ታንጎራጉራለች፡፡ እንጉርጉሮዋ የኒህን ቄስ ቀልብ ጠለፈ፡፡ ቄሱ ሽማግሌ ቢልኩ አይሆንም ይባላሉ፡፡ እናቴና አባቴን የምታገናኝ አንዲት በር ነበረች፡፡ ቄሱ አይሆንም ሲባሉ በሯን ገንጥለው ገቡ፡፡ እኔ ተወለድኩ፡፡…”
ብጽአት ስዩም ‹‹አደራ ልጄን አደራ›› እያለች በእንባ የምታዜመውን ግጥም የጻፈላት ሙሌ ነው፡፡ ለአበበ ተካ ‹‹ወፊቱ››ን የጻፈለት ሙሌ ነው፡፡ ለሀና ሸንቁጤ፣ ለኩኩ ሰብስቤ እያልን ብንቀጥል ማቆምያ የለንም፡፡ ቆንጥሮ እየሰጠ አንበሽብሿቸዋል፤ ፍዝ ኾኖ አድምቋቸዋል፡፡ እነሱን የዝና ማማ ላይ ሰቅሎ እሱ እታች ወርዶ ይተኛል፡፡ ጎዳና፡፡
ሙሌ ድሮ ድሮ እንደ ኢህአፓም እንደ ብአዴን አድርጎት ነበር፡፡ ምን አድርጎት ነበር ብቻ! ቆራጥ ታጋይ ነበር እንጂ፡፡ በኢህአዴግ አምናለሁ ይል ነበር፣ አፍ አውጥቶ፡፡ ከተበላሹም አለቃቸውም እያለ ይዝት ነበር፡፡ እነ በረከት፣ እነ ታምራት ላይኔ፣ እነ ሕላዌ ዮሴፍ የሙሌ ግጥም ነፍሳቸው ነበር፡፡ ሙሌ የወልዲያ ልጅ ይሆን እነጂ አባቱ የትግራይ ሰው ናቸው፡፡ ለትግልና ለታጋዮች የቀረበውም ለዚሁ ሳይሆን አይቀርም፡፡ የኢህዲን (ብአዴን) 20ኛ ዓመት ላይ ግጥም እንዲያቀርብ ተጋበዘ፡፡
ሙሌ ትልልቆቹ ብአዴኖች ባሉበት መድረክ ላይ ወጥቶ እንዲህ ተቀኘ…፣
ምንም ነኝ ግን አማራ
ለዚያውም ደሜ አረንጓዴ
የፈጠረኝን አምኜ፣ በጎቼን ከተኩላ ጋር የማሰማራ
ምንም ነኝ ግን አማራ
ኩራት እንጂ ሞት ያልፈራሁ
አማራ ነኝ መቃ አንገት፤ ራሴ ከብዶኝ የማልንገታገት
የሰው ጣባ ሥር የማልለገት፤
ማንም እንዳስመለከተው ያሻውን ስም ቢያወጣልኝ
እድሜ ላባይ ጣና ልጅ ያን ቀን የማስቆርሰው፣ ድፎ ዳቦ አያጣልኝ
ያው ወንድሞቼ ይመስክሩ
በናት ጡት ወተት ባይሰክሩ
የዛሬ ሃያ ዓመት ተክራርዋ ወርደውም ባልመከሩ
ምንም ነኝ ግን አማራ!
በዚህን ጊዜ ብአዴኖች አንገታቸውን ደፉ፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮም ይፈሩት ጀመር፡፡
አያ ሙሌ የከተማ ባህታዊ
በዚህ መጽሐፍ የተወሱ በርካታ ገጠመኞች ሙሉጌታ ተስፋዬን የሱፊ ፈላስፋ፣ የከተማ ባህታዊ አንዳንዴም ንግርት አዋቂ ያስመስሉታል፤ ሊኾንም ይችላል፡፡
አንድ ቀን ሙሌ አዲስ ጫማ ገዝቶ መንገድ ሲያቀና አንድ በባዶ እግራቸው የሚሄዱ የኔ ቢጤ አይቶ ይጠራቸውና፣ “እስቲ ይሄን ይለኩት” ይላቸዋል፡፡ “የኔ ቢጤውም ልኬ ነው ይሆነኛል” ይሉታል፡፡ “በሉ ይሂዱ” ብሏቸው እርሱ በባዶ እግሩ መንገዱን ቀጠለ፡፡
አያ ሙሌ በየአድባሩ በየአገሩ በአብያተ ክርስቲያኑ ሁሉ እየዞረ እንደ ለማኞች ሆኖ ለምኖ የተሰጠውን መልሶ ለለማኞቹ ማደል ጀምሮ ነበር፡፡ እንዲያውም አንድ ጊዜ የአለቃ ተስፋዬ ልጅ ሚካኤል ሲለምን ታዬ ተብሎ ተወራበት፡፡ እሱ ግን ግድ አልነበረውም፡፡ “እብዶች” አያ ሙሌን ካዩ አይለቁትም፡፡ ይከተሉታል፤ ይወዱታል፡፡ በተሻለ ያወሩታል፡፡ ለምሳሌ ወልዲያ አባ ግርሻ የሚባሉ አንድም ሰው የማይቀርባቸው በአእመሮ መታወክ የሚሰቃዩ ሰው ነበሩ፡፡ ሙሌ ግን ጠጅ ቤት ወስዶ አብሯቸው ዉሎ ያድር ነበር፡፡ በሰላም፡፡
አንድ ቀን ደግሞ አንድ እንጨት የተሸከሙ ሰውዬን በመንገድ ያገኝና ‹‹እስካሁን አልሸጡትም?›› ይላቸዋል፡፡ ሰውየውን ለካ ሌላ መንገድ ላይ ሲዳክሩ ቀደም ብሎ አይቷቸው ነበር፡፡ “ገዥ አጣሁ ልጄ” አሉት፡፡ “ስንት ነው?” ይላቸዋል፡፡ ሁለት ብር መኾኑን ሲነግሩት አምስት ብር ሰጥቶ “በሉ ይጣሉትና ሄደው ይረፉ” ብሎ አሰናበታቸው፡፡
አያ ሙሌ በደህናው ጊዜ በቤተመንግሥት በከፍተኛ የመንግሥት ስብሰባዎች መዝጊያ ላይ ሁሉ ግጥሞችን ያቀርብ ነበር፡፡ ቦረና ድረስ ሄዶ የዋለልኝ መኮንን ታዋቂ ዘጋቢ ፊልም ለመጀመርያ ጊዜ የሠራውም እሱ ነበር፡፡ መንግሥታዊ መጽሔትና ጋዜጣ ላይ ሂሳዊ ጽሑፎችን እያቀረበ የተደላደለ ኑሮ ሲኖር ቆየ፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን ድንገት ከኢህአዴግ ሰዎች ራቀ፡፡ ሽጉጡን አስረክቦ፣ መንግሥት የሰጠውን ቤት ጥሎ ጎዳና ወጣ፡፡ ላይመለስ፡፡
የኾነ ቀን ግን ወዳጆቹ ፈልገው አፈላልገው ደመወዙን ይዘውለት መጡ፡፡ ያልሠራሁበትን አልበላም ብሎ ሳይቀበል ቀረ፡፡ ሕይወቱንም በኬሻ በጠረባ አደረገ፡፡ አንድ ጊዜ ደግሞ የኾነ መልዕክተኛ ታምራት ላይኔ በጥብቅ እንደሚፈልገውና እርሱም ሊያደርሰው እንደመጣ ይነግረዋል፡፡ አያ ሙሌ አጭር መልስ ሰጠ ‹‹ አመሰግናለሁ፤ መንገዴን ለይቻለሁ!››
በሌላ ጊዜ ደግሞ የማስታወቂያ ሚኒስቴር የነበረው በረከት ስምኦን አያ ሙሌ ያለበት ድረስ ደፍሮ በመምጣት በግል አናግሮት ነበር፡፡ ‹‹እንዲህ ለመሆን ነው ሥራህን የተውከው? በል ወደ ሥራህ ተመለስ፣ ቢያንስ ጥለኻት የመጣሃትን የ11 ዓመት ሕጻን ልጅህ አታሳዝንህም?›› ይለዋል፡፡ አያ ሙሌ ቱግ ብሎ ምላሽ ሰጠ፡፡ “የኔ ልጅ ሕጻን አይደለችም፣ አንተን በአንድ ዓመት ትበልጠሀለች፡፡”
የአያ ሙሌ ወዳጆችና የነፍስ ልጆች
በርከት ያሉ አድናቂዎችና የነፍስ ልጆች ነበሩት፡፡ ብዙዎቹ የጎዳና ልጆች ናቸው፡፡ ቀሪዎቹ የጥበብ ወዳጆች፡፡
ከአያ ሙሌ የጥበብ ወዳጆች አንዱ ጋሽ ስብሐት ነው፤ ሌላኛዋ ስንዱ አበበ ናት፡፡ ስንዱ የሙሌን ሁለት ልጆች እሱ ጎዳና ከወጣ በኋላ በማሳደግ፣ በተባይ እየተበላ የሚሰቃየውን አያ ሙሌንም ቢኾን እንደነገሩ በመያዝ፣ አልፎ አልፎ ጎዳና ድረስ ሄዶ ምግብ በማቀበል ረድታዋለች፡፡ አራት ኪሎ ማለዳ ካፌ አካባቢ በሚገኘው አፓርታማዋ መጥቶ በር ላይ ቁጢጥ ይላል፣ ሲርበው፣ ሲጠማ፡፡ (በርግጥም ስንድን እጅግ ይወዳት ነበር ይባላል፣ ሙሌ፤ ስሟንም ጉኖ ዘበናይ ነበር የሚላት፡፡ ስንዱም አዋዋሏ ተጽእኖ አድርጎበት ይሆን እንጃ ብቻ አንዳንዴ እሷም እንደሙሌ ከመስመር ትወጣ ነበር ልበል?፣ እርሷም እኮ የምትታወቀው ከመስመር የወጡቱ ወዳጅ በመኾን ነው፡፡
ለምሳሌ አብዮታዊ ዲሞክራሲ ስትሰራ ድርጅቱ ከሰጣት የጥያቄ ዝርዝር አፈንግጣ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስን እንዲህ ጠየቀቻቸው፤
“ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ከርዕሰ ጉዳያችን ወጣ እንበልና ኢትዮጵያ በድርሰት እንድታብብ ያደረጉ እነ ሐዲስ አለማየሁ፣ ከበደ ሚካኤል፣ ስብሀት ገብረእግዚያብሔር እና ሌሎችም ዛሬ አስታዋሽ አጥተዋልና ችላ ተብለው ክብራቸው በማይመጥን ሁኔታ እየኖሩ ነው፤ ለመሆኑ መንግሥት እነዚህን ሰዎች ከወደቁበት ለማንሳት ምን አቅዷል?”
መልስ የማያጡት የነበሩት ሰው መልስ መስጠት ጀመሩ፤
“እርግጥ ነው ያልሻቸውን ሰዎች እናውቃቸዋለን፣ በመጽሐፎቻቸው ተምረናል፡፡ እናደንቃቸዋለን፡፡ ከአንድ ኢትዮጵያዊ አርሶ አደር ለይተን ግን የምናደርግላቸው ምንም ነገር አይኖርም፤ አራት ነጥብ፡፡”
በማግስቱ መሥሪያ ቤቷ ስንዱ አበበን በሥነ ምግባር ጉድለት…ምናምን ብሎ አሰናበታት፡፡ የአያ ሙሌን የባለቅኔው ምህላን የግጥም ስብስብ ከየትም ከየትም ሰብስባ ያሳተመችው እሷ ናት፡፡ ሙሌ ጻፈው፣ ጥሎት ይሄዳል፤ ዞሮም አያየው፡፡ ዘፋኞች ግን ከሥር ከሥሩ የሚጥለውን እያነሱ ይከብራሉ፡፡
የከተማ ባሕታዊው አያ ሙሌ
አያ ሙሌ ድምጻዊ አበበ ተካ በገነነበት ወቅት የዘፋኙ ሥራ አስኪያጅ በመሆን በየክፍለ ሀገሩ ይዞር ነበር፡፡ ያን ሰሞን በርከት ያለ ገንዘብ ያገኘበት ጊዜ ነበር፡፡ እንዲያዉም አዲሱ ገበያ አንድ ግቢ ቤት የዓመት ኪራይ ከፍሎ ልጆቹን በሥርዓት ማሳደግ ጀምሮ ነበር፡፡ ያን ሰሞን ከአበበ ተካ ጋር ጎንደር በሄደበት አጋጣሚ በርከት ያሉ የተቸገሩ ሰዎች ሰብሰብ ብለው ያያል፡፡ “ኑ ወዲህ” ብሎ አሰልፎ ብዙ ሺ ብር ሲያድል ፖሊስ ሁኔታው ጥርጣሬ ፈጥሮበት አያ ሙሌን ቁጥጥር ሥር ያውለዋል፡፡ አበበ ተካ ነው ሄዶ ያስፈታው፡፡ ብቻ ያያ ሙሌ ነገር ግራ ነው፡፡
ገጣሚ ሙሌጌታ ተስፋዬ እጅግ በከፋ ድህነት እንዳደገ ይነገራል፡፡ ቡና ቤት እየሠራች ስላሳደገችው እህቱ የጻፈውን ሐና ሸንቁጤ ዘፍነዋለች፡፡ ‹‹አደራ ልጄን አደራን›› ብጽአት ተጫውተዋለች፡፡ ለካንስ ከሕይወቱ እየጨለፈ ነው የሚያስለቅሳቸው፡፡
“እኔ በልጅነቴ በባዶ ሆዴ ነበር የተማርኩት፡፡ እናቴ ምሳ የምታቀርብለኝ ምግብ ከሌላት እኔን ላለማየት በሩን ቆልፋ ትጠፋ ነበር፡፡” ብሏል በአንድ ወቅት፡፡
የወላጅ እናቱ እናት የኾኑት አያቱ እናንዬ ቀን የለበሱትን ቀሚስ ማታ እንደ ብርድልብስ እያለበሱ ነበር ያሳደጉት፡፡ እናንዬን በጣም ይወዳቸዋል፡፡ እርሳቸው የሞቱ ቀን እንዳዘነው ያዘነበት ወቅት የለም፡፡ እናንዬ በገሀድ የማይታይ ነገር ይታያቸው ነበር ይባላል፤ የጅብ ቋንቋም ይረዱ ነበር፡፡ ጅብ ሲጮኸ አይ እከሌ ሊሞት ነው ብለው ይናገራሉ፤ ያሉት ሲኾን በገሀድ ይታይ ነበር፡፡ ታዲያ እንደ አናንዬ ሁሉ አያ ሙሌም አልፎ አልፎ ነገሮች ይገለጡለት ነበር ይላል ግለታሪኩን የጻፈው ፋሲካ ከበደ፡፡ የሚገርመው አያ ሙሌና የአሁኑ ቢሊየነር ሼክ አላሙዲ ወልዲያ ዉስጥ ጎረቤታሞች ነበሩ፡፡
ለምሳሌ አንድ ቀን አለም ገና አካባቢ የመነኮሳትን ቀሚስ የለበሱ አንዲት ሴትዮ አተኩሮ ካያቸው በኋላ “ወይ እማማ! በገመድ ታንቀው ሊሞቱ ነው ማለት ነው?” ብሏቸው ሲያልፍ አብሮት የነበረው ወዳጁ ‹‹ምነካህ ሙሌ፣ ጎረቤት ናቸው እኮ…›› ይለዋል፡፡ ከጊዜ በኋላ ሴትየዋ ሞቱ፤ በገመድ ታንቀው፡፡
በአንድ ወቅት ደግሞ ሃያ ሁለት አካባቢ በሚያዘወትርበት ቤት አንድ ሳቅና ጨዋታ የሚያበዛን ልጅ ‹‹ልትሰበር ነው›› አለው፡፡ ሌላ ቀንም እንዲሁ ፌዝ ሲያበዛ ‹‹ወንዝ ሊወስድህ ነው›› አለው፡፡ ልጁ ከጊዜ በኋላ ክፍለ ሀገር በሄደበት መሞቱ ተሰማ፡፡ ሲጣራ ደራሽ ወንዝ ወሰደው ተባለ፡፡፡
በሌላ ቀን ደግሞ አያ ሙሌ ጓደኛውን በሌሊት ቀስቅሶ ተነስና ፍቅረኛህን ከቤቷ ጠርተህ ይዘሀት ና ይለዋል፡፡ አሻፈረኝ ይላል፡፡ ሙሌ ጎተጎተው፡፡ በዚህ ዉድቅት ሌሊት ፍቅረኛውን ማስጠራት የከበደው የሙሌ ወዳጁ እስኪነጋ ዎክ ማድረግ ይጀምራል፡፡ ለአንድ ሰዓት ያህል ዎክ አድርጎ ሲመለስ ልጅቱ ከአንድ ወንድ ጋር ከሆቴል ስትወጣ አገኛት፡፡
አንድ ጊዜ ደግሞ አሜሪካን ግቢ ከመንፈስ ልጁ ጋር በችግር ጎዳና ላይ ሳለ ሙሌ ድንገት ከጎዳናው እምር ብሎ ተነስቶ አንድ ሙስሊም ሰውዬን በአረብኛ ያናግራቸውና ተመልሶ ጎዳናው ላይ ቁጭ ይላል፡፡ ሰውየው ቆየት ብለው የታሰረ ረብጣ ብር በሾፌራቸው ይልኩለታል፡፡ ሙሌም ‹‹መልስላቸው፣ እኔ ለማኝ አይደለሁም ›› ሲል ብሩን ሳይቀበል ቀርቷል፡፡
በሌላ ወቅት ደግሞ አንዲት ተከታዩ የነበረች ልጅ ቤት ድንገት ይሄድና ‹‹ነፍስሽ ጠርታኝ ነው የመጣሁት፤ እንዴት እንደዚህ አይነት ቆሻሻ ሀሳብ ታስቢያለሽ? አትውሸክሸኪ፡፡” በማለት ከገሰጻት በኋላ ‹‹ማር ይስሀቅ›› የሚባል መጽሐፍ እንድታነብ አዟት ነበር፡፡ የሚገርመው ታዲያ ልጅቷ የምትኖርበትን አድራሻም ኾነ ራሷን የማጥፋት ሐሳብ እንደነበራት ትንፍሽ ብላለት አታውቅም ነበር፡፡
አያ ሙሌና ድርቅ
እጅግ በአስቸጋሪ ድህነት ዉስጥ ያደገው ሙሌ እጅግ አሳዛኝ የረሀብ ክስተቶችን ተመልክቷል፡፡ በድርቁ ጊዜ በአንድ መንግሥታዊ ባልሆነ የጃፓን ተራድኦ ድርጅት ዉስጥ ይሠራ ነበር፡፡ ለያውም ዳጎስ ያለ ገንዘብ እየተከፈለው፡፡ በአንድ ዕለት ከመቅጽበት ሥራውን ጥሎ ጠፋ፡፡ ለምን እንደጠፋ ለረዥም ዓመታት ለማንም ትንፍሽ ብሎ አያውቅም ነበር፡፡ አንድ ቀን ግን ለወዳጁ ዳዊት ከበደ ወይሳ ነገረው፡፡ ለጽሑፍ ስለማይመች እዚህ ጋር አላካተትኩትም፡፡ ሙሌ ያን የሕጻናት ረሀብ ከተመለከተ በኋላ ጠፋ ጠፋ፡፡ ከዚያ በኋላ ዘለግ ላለ ጊዜ አየሁት የሚል ሰው አልነበረም፡፡ በየ10 ዓመቱ ከጎበኙን ድርቆች ዉስጥ የ67፣ የ77፣ የ87 በይበልጥ ይጠቀሳሉ፡፡ በድርቅ ላይ ከተጻፉ ጽሑፎች ደግሞ በብዙዎች ሕሊና የቀረችው የሙሌ ቅኔ ናት፡፡ እውነት ከመንበርህ የለህማ! የምትለው፡፡
ምነዋ መንግሥተ ሰማይ የምህረትሽ ቀን ራቀ
ምነው ትንግርትሽ ረቀቀ
ምነው ኪዳንሽ ታጠፈ መዝሽ ወዘናሽ ነጠፈ
እንደ ደጎሳ ድፍድፍ ላቦትሽ ተንጠፈጠፈ
አሳርሽ ጠሎ አሰፈፈ
እያለ የሚቀጥለው ይህች ድንቅ ሥራው አስራ ምናምን ገጽ አንዲት ሳይደናቀፉ በቃል የሚወጧት ቅኔ ናት፡፡ ምናልባት የሙሉጌታ ተስፋዬ Masterpiece ልንላት እንችል ይሆናል፡፡
አያ ሙሌና ዘፋኞች!
ሙሌ የተመጠነ ጨዋታና ቀልድም ያውቃል፡፡
አንድ ቀን ተፈራ ነጋሽ አያ ሙሌን ይዞት ሆቴል ከበድ ያለ ምሳ ካበላው በኋላ ‹‹ባክህ እስቲ ስለ ድህነት ቆንጆ ግጥም ሥራልኝ ይለዋል፡፡ ‹‹ተፌ ስለድህነት ከሆነ ያን ሁሉ ምግብ ከመጋበዝህ በፊት አትነግረኝም ነበር?›› ብሎት ነበር፡፡
አያ ሙሌ ድምጻዊ አበበ ተካን ‹‹በምሰራልህ ሥራ የቃል ኪዳን ሚስትህን ከአሜሪካ ካላመጣኋትማ ምኑን ባለቅኔ ሆንኩት ብሎት ነበር፡፡ ካሴቱ ከወጣ በኋላ ደግሞ አበበ ተካ ‹‹እሙ ነይ እሞ እሞ ነይ›› ስዘፍን ስሜት ዉስጥ ስለምገባ አለቅሳለሁ ቢለው ሙሌ ቀበል አርጎ ‹‹አይ አቤ! ደሞ አንተ ምን ታለቅሳለህ፡፡ እኔ ነኝ እንጂ የማስለቅስህ” ብሎት ነበር፡፡ እሞ ነይን ለቅድስት ድንግል ማርያም ያለውን ጥልቅ ፍቅር የገለጸበት ሥራው እንደሆነ ይነገራል፡፡
አያ ሙሌ ያቺን ሰዓት
አያ ሙሌ የፈጠራቸው በይበልጥ በኢህአፓ ዘመን ይጽፋቸው ከነበሩ ጽሑፎቹ የተወሰዱና አሁን ጥቅስ መኾን የቻሉ አባባሎች አሉት፡፡ በወቅቱ እሱ ካገነናቸው አባባሎቸ ዉስጥ ሰው ማለት ሰው የሆነ ነው ሰው የጠፋ ዕለት የምትለዋ ትታወሳለች፡፡ አያ ሙሌ ግን ሰው የሚኾንለት ሰው አልነበረውም፡፡
ለበርካታ ጊዜያት በየገዳማቱ ይጠፋ ነበር፡፡ በእንጦጦ ሐመረ ኖህ ኪዳነ ምህረት ጾም ጸሎት ያዘውትር ነበር፡፡ ለተወነሱ ቀኖች በተመስጦ ያለምግብ ያሳልፍ ነበር፡፡ አንድ ወቅት ቤት ሲገባ የሚላስ የሚቀመስ አጥቶ እጅግ ከመራቡ የተነሳ ያገኘውን በርበሬ በዉሀ በጥብጦ በመጠጣቱ ለሰዓታት ራሱን ስቶ ነበር፡፡ ከነቃ በኋላም…ከሰው ፊት ይህ በርበሬ ይሻላል ብሎ ተናገረ፡፡
አንድ ቀን ደግሞ የዘፈን ግጥም ክፍያ 20ሺ ብር ተቀብሎ በሚያዘግምበት ሰአት “አንተ፣፣አንተን እኮ ነው ና ተሸከም…!” በማለት አንድ ሰው ቢጠራው “ወንደሜ ሆይ! በፍቅር አጠራር ብትረጠራኝ ኖሩ በነጻ እሸከምልክ አልነበር” ብሎት መንገዱን ይቀጥላል፡፡ ሰውየው ተበሳጨ፣ “ከምትለምን ሰርተህ አትበላም? ለማኝ” ሲልም ሰደበው፡፡
አያ ሙሌ ከአፍቅሮተ ነዋይ የራቀ የከተማ መናኝ ነበር፡፡ መታወቂያ፣ ስልክ፣ እድር፣ የመኖርያ ቤትም ሆነ ቋሚ አድራሻ አልነበረውም፡፡ ወገን ዘመድ የሚለው ሰውም እንዲሁ፡፡ የሚኖረውም በእምነት ነው ‹‹እንደ ወፊቱ ልዋል›› ይል ነበር፣ አዘውትሮ፡፡ ከሥራዎቹ ሁሉ የአበበ ተካን ወፊቱን አብልጦ የሚወደው ለዚሁ ይሆን?
አያ ሙሌ ድንገት አምርሮ የሚያለቅስባቸው ጊዜያትም ነበሩ፡፡ በግንቦት ወር 1996 አሁን ማረፍ ነው የምፈልግው ብሎ ቤት ተከራየ፡፡ ወይዘሮ ከበቡሽን ሲሰናበትም…”ነገርኩሽ አልሰማሽም፣ ልሄድ ነው አልረሳሽም” ብሏቸው ነበር፡፡ የፒያሳን አቀበት እየወጣ ቴድሮስ አደባባይ ሲደርስ ድንገት ሐሳቡን ቀይሮ ወደ ጎላ ሚካኤል ዞሮ አማትቦ ዘለግ ላለ ሰዓት ፀለየ፡፡ ሦስት ቁጥር አውቶብስ ይዞ ዓለምገና ሄደ፡፡ አንድ ሆቴል ዉስጥ 13 ቁጥር መኝታ ይዞ አደረ፡፡ ጓደኞቹ ግማሽ በድን ኾኖ ከሆቴሌ ሲያወጡት የሆቴሉ ዘበኛ እንዲህ ተናገሩ፡፡
“ኸረ ይሄ ሰው ነብይ ሳይሆን አይቀርም፡፡እንዲችው ሌሊቱን ሙሉ ለጆሮ የሚከብዱ ነገሮችን ሲናገር ነው ያነጋው”
በነገታው ነሐሴ 28፣ ቀን 1996 ዓ.ም አረፈ፡፡

ኢትዮጵያ፡የስራ ስንበት ክፍያ እና የካሳ ምንነት፡የአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ በተለምዶ የአገልግሎት ክፍያ እየተባለ ለሚታወቀው የስራ ስንብት ክፍያ ትርጉም ያልሰጠ ቢሆንም በተለያዩ ፅሁፎች ...
02/02/2026

ኢትዮጵያ፡
የስራ ስንበት ክፍያ እና የካሳ ምንነት፡
የአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ በተለምዶ የአገልግሎት ክፍያ እየተባለ ለሚታወቀው የስራ ስንብት ክፍያ ትርጉም ያልሰጠ ቢሆንም በተለያዩ ፅሁፎች ከተሰጠው ትርጉም መረዳት እንደሚቻለው የሥራ ስንብት ክፍያ ማለት አሠሪው ከቅጥሩ በኋላ ወይም ቅጥሩ ሲጠናቀቅ ለሠራተኛው የሚሰጠው ማካካሻ እና/ወይም ጥቅማጥቅሞች ነው። በአዋጁ ስለስራ ስንበት ክፍያ ከተቀመጡ አጠቃላይ ድንጋጌዎች የሚወሰደው ግንዛቤ ከዚህ ትርጉም ጋር የሚጣጣም ሆኖ ይገኛል። በተመሳሳይ አዋጁ ስለካሳ ምንነት ትርጉም ያልሰጠ ሲሆን ከድንጋጌዎቹ አጠቃላይ መንፈስ መረዳት እንደሚቻለው በአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ ካሳ ማለት በአሰሪው ጥፋት የስራ ውል ተቋርጦ ወደ ስራ እንዲመለስ ለሠራተኛ ፍርድ ቤት ወስኖለት ሠራተኛው ወደ ስራ ለመመለስ ፍቃደኛ ካልሆነ በስራ መቋረጥ ምክንያት አሰሪ ለሠራተኛው ገንዘብ በካሳ መልክ የሚከፍልበት የክፍያ አይነት ነው። አዋጁ ለስራ ስንብት ክፍያ እና ካሳ ትርጉም ያልሰጠ ቢሆንም ክፍያዎቹ የሚከፈሉበትን ሁኔታ እና የክፍያ ስሌቱን በዝርዝር አስቀመቀጧል።
የስራ ስንበት ክፍያ የሚከፈልባቸው ሁኔታዎች"
በአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 39 ስር የስራ ስንብት ክፍያ የሚከፈልባቸው ሁኔታዎች ተዘርዝረው ይገኛሉ። ይኸውም የሙከራ ጊዜውን የጨረሰ እና አግባብነት ባለው የጡረታ ሕግ መሠረት የጡረታ አበል ለመቀበል ብቁ ያልሆነ ሠራተኛ በሚከተሉት ሁኔታዎች የስራ ስንብት ክፍያ ይከፈለዋል።
ድርጅቱ በመክሰሩ ወይም በሌላ ምክንያት ለዘለቄታው በመዘጋቱ የሥራ ውሉ ሲቋረጥ ( በአዋጁ አንቀጽ 24/4 ተመልክቷል )፣
በሕግ ከተደነገገው ምክንያት ውጪ በአሰሪው አነሳሽነት የሥራ ውሉ ሲቋረጥ ( የስራ ውል በአሠሪ አነሳሽነት ሊቋረጥ የሚችልባቸው ህጋዊ አግባቦች በአዋጁ አንቀጽ 26 ተመልክተዋል)፣
በአዋጁ በተመለከቱት ሁኔታዎች መሠረት ሠራተኛው ከስራ ሲቀነስ (የሠራተኛ የስራ ቅነሳ በአንቀጽ 29 ተመልክቷል)
በአሰሪው ወይም በሥራ መሪ ወሲባዊ ጥቃት ወይም ትንኮሳ የተፈጸመበት እንደሆነ ወይም ድርጊቱ በሌላ ሠራተኛ እንደተፈጸመ ሪፖርት ተደርጎለት አሰሪው ተገቢውን እርምጃ ባለመውሰዱ ሠራተኛው የሥራ ውሉን ያቋረጠ እንደሆነ (ያለማስጠንቀቂያ የስራ ውል በሠራተኛው አነሳሽነት ሊቋረጥ የሚችልባቸው ሁኔታዎች በአዋጁ አንቀጽ 32(1)ለ ተመልክቷል)፣
አሠሪው በሠራተኛው ላይ ሰብዓዊ ክብሩንና ሞራሉን የሚነካ ወይም በወንጀል ሕጉ መሠረት የሚያስቀጣ አድራጎት በመፈጸሙ የተነሣ ሠራተኛው የሥራ ውሉን ያቋረጠ እንደሆነ ( በአንቀጽ 32(1)ሀ ስር ተመልክቷል)፣
አሠሪው ለሠራተኛው ደኅንነት ወይም ጤንነት የሚያሰጋ አደጋ እንዳይደርስ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶት እርምጃ ባለመውሰዱ የተነሳ ሠራተኛው የስራ ውሉን ሲያቋርጥ (ያለመስጠንቀቂያ የስራ ውል በሠራተኛው አንሳሽነት ሊቋረጥ የሚችልበት ምክንያት እንደሆነ በአዋጁ አንቀጽ 32(1)ሐ ተመልክቷል)፣
ሙሉ ወይም ዘላቂ የአካል ጉዳት በመድረሱ ሠራተኛው ሥራ ለመሥራት አለመቻሉ በሕክምና ተረጋግጦ የሥራ ውሉ ሲቋረጥ(በአዋጁ አንቀጽ 24(5) ተመልክቷል)፤
ቢያንስ አምስት ዓመት በአሠሪው ዘንድ የሥራ አገልግሎት ኖሮት በህመም ወይም በሞት የሥራ ውሉ ሲቋረጥ ወይም በሥራው ላይ የሚያስቆይ ከሥልጠና ጋር የተያያዘ ለአሠሪው የውል ግዴታ ሳይኖርበት ሥራውን በገዛ ፈቃዱ ሲለቅ፤
በኤችአይቪ/በኤድስ ህመም ምክንያት በራሱ አነሳሽነት የሥራ ውሉን ያቋረጠ እንደሆነ፤ ከአሰሪው የስራ ስንብት ክፍያ የማግኘት መብት አለው።
አንድ ሠራተኛ የስራ ስንብት ክፍያ ከማግኘቱ በፊት ቢሞት የሥራ ስንብት ክፍያው በአንቀጽ 110/2 ለተመለከቱት ጥገኞቹ ማለትም የሟች የትዳር ጓደኛ፤ ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ የሟች ልጆች እና በሟች ድጋፍ ይረዱ የነበሩ የሟች ወላጆች ይከፈላል። ለሟቹ ጥገኞች የሚከፈለው የስራ ስንብት ክፍያ በአዋጁ አንቀጽ 110 በሚከፈለው የካሳ አከፋፈል መሠረት የሚፈፀም ይሆናል።
የስራ ውል ሲቋረጥ ካሳ የሚከፈልባቸው ሁኔታዎች፡
አንድ አሰሪ ወይም ሠራተኛ የስራ ውልን ሲያቋርጥ በአዋጁ ወይም አግባብ ባለው ሌላ ሕግ የተወሰኑትን አስፈላጊ ሁኔታዎች ያላሟላ እንደሆነ የሥራ ውሉ መቋረጥ ህገ-ወጥ እንደሆነ የአዋጁ አንቀጽ 42 ይደነግጋል። ህገ-ወጥ የስራ ውል መቋረጥ ከሚያስከትላቸው ውጤቶች መካከል ወደ ስራ ከመመለስ ባሻገር የካሳ ክፍያ አንዱ ነው። በአዋጁ አንቀጽ 43/1 ስር እንደተደነገገው በአዋጁ አንቀጽ 26(2) በተመለከቱት ምክንያቶች አሰሪው የስራ ውሉን ቢያቋርጥ ሠራተኛውን ወደ ስራ የመመለስ ግዴታ ያለበት ሲሆን ሠራተኛው ወደ ስራ ለመመለስ ካልፈለገ ግን ካሳ እንዲከፈለው የመጠየቅ መብት አለው። በአዋጁ አንቀጽ 26(2) ስር እንደተደነገገው የሚከተሉት የሥራ ውልን ለማቋረጥ ተገቢ ምክንያቶች ሆነው ሊቆጠሩ የማይችሉ በመሆኑ የስራ ውል ሲቋረጥ ሠራተኛው ከስራ ስንብት ክፍያ በተጨማሪ የካሳ ክፍያ የማግኘት መብት አለው። እነሱም፡-
ሀ) ሠራተኛው በሠራተኞች ማኅበር አባል መሆኑ ወይም በማኅበሩ ሕጋዊ ተግባሮች ተካፋይ መሆኑ፤
ለ) ሠራተኛው የሠራተኞች ተጠሪ ሆኖ ለመሥራት መፈለጉ ወይም መሥራቱ፤
ሐ) ሠራተኛው በአሠሪው ላይ ቅሬታ ማቅረቡ ወይም በፍርድ ቤት በቀረበ ክስ ወይም በሌላ ሰው ክስ ተካፋይ መሆኑ፤
መ) የሠራተኛው ብሔር፣ ጾታ፣ ሐይማኖት፣ የፖለቲካ አመለካከት፣ የጋብቻ ሁኔታ፣ ዘር፣ ቀለም፣ የቤተሰብ ኃላፊነት፣ የዘር ሐረግ፣ እርግዝና፣ አካል ጉዳተኝነት፣ ወይም ማኅበራዊ አቋም፡፡ በመሆኑም በእነዚህ ምክንያቶች የስራ ውልን ያቋረጠ አሰሪ ሠራተኛውን ወደ ስራ የመመለስ ወይም የካስ ክፍያ የመፈፀም ግዴታ አለበት።
በተጨማሪ በአንቀጽ 32(1) (ያለማስጠንቀቂያ የስራ ውልን ማቋረጥ) መሠረት የስራ ውልን የሚያቋርጥ ሠራተኛ በአንቀጽ 40 (የስራ ስንብት ክፍያ መጠን) ከተመለከተው የስራ ስንብት ክፍያ በተጨማሪ የመጨረሻ ሣምንት አማካይ የቀን ደሞዙ በ30 ተባዝቶ ካሳ ይከፈለዋል። ይህ ክፍያ አግባብ ባለው የጡረታ ሕግ በተሸፈነ ሠራተኛ ላይም ተፈፃሚ እንደሚሆን አዋጁ ይደነግጋል። ሆኖም ሠራተኛው የስራ ውሉን ያቋረጠው በአንቀጽ 32(1)ለ ላይ በተመለከተው ምክንያት የሆነ እንደሆነ ከሥራ ስንብት ክፍያው በተጨማሪ የቀን ደመወዙ በ90 ተባዝቶ የሚከፈለው ሲሆን ይህ ክፍያ አግባብ ባለው የጡረታ ሕግ በተሸፈነ ሠራተኛ ላይም ተፈጻሚ እንደሚሆን በአዋጁ አንቀጽ 41(2) ስር ተደንግጎ ይገኛል።
በሌላ በኩል ሠራተኛው ለአሰሪው ካሳ የመክፈል ኃላፊነት የሚኖርበት ሁኔታ በአዋጁ የተመለከተ ሲሆን ይህም በአንቀጽ 31(በማስጠንቀቂያ የስራ ውል ስለማቋረጥ) ወይም በአንቀጽ 35(2) (የማስጠንቀቂያ ጊዜ) ስለማስጠንቀቂያ የተጠቀሱትን አስፈላጊ ሁኔታዎች ያላሟላ ሠራተኛ ለአሠሪው ካሣ ይከፍላል። በዚህ መሠረት የሚከፈለው ካሣ አሰሪው ለሠራተኛው ከሚከፍለው ቀሪ ክፍያ ውስጥ ከ30 ቀናት የበለጠ መሆን እንደሌለበት በአዋጁ አንቀጽ 45 ላይ ተደንግጎ ይገኛል።
በአጠቃላይ የስራ ስንብት እና የካሳ ክፍያ የሚከፈልባቸው ሁኔታዎች በአዋጁ የተመለከቱ በመሆኑ ሠራተኛው በሕግ አግባብ ክፍያዎቹን የመጠየቅ እና የማግኘት መብት አለው። አሠሪም እንደዚሁ።

Today marks 10 years of የኢትዬጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በጎንደር፡! Thank you all for helping keep this community strong.ግብዝና ደካ...
28/01/2026

Today marks 10 years of የኢትዬጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በጎንደር፡! Thank you all for helping keep this community strong.
ግብዝና ደካማ የሆነው የሰውን ሥጋ አሸንፎ፣ መከራን ተቀብሎ፣ ችግርን ተቋቁሞ፣ ፈተናን አልፎ መንፈሳዊ ሕይወትን ለመኖርና ክርስቲያን ለመሆን የሚደረገው ትግል እራሱን የቻለ ተጋድሎ እንደሚያስፈልገው የታወቀ ነው፡፡ እውነተኛ ለሆነው የክርስትና እምነተና ኦርቶዶክሳዊ ሃይማኖት የሚከፈለው መሥዋዕትም የተለየ ስፍራ አለው፡፡
ጾመ ሰብአ ነነዌ:
ጾመ ነነዌ ከሰባቱ የአዋጅ አጽዋማት አንዷ ስትኾን የምትጾመውም ለሦስት ቀናት ነው፡፡ ይህቺ ጾም የምትጀመርበት ዕለትም ልክ እንደ ዐቢይ ጾም ሰኞን አይለቅም፡፡ ጾሟ የምትጀመርበት ቀን ሲወርድ ወይም ወደ ኋላ ሲመጣ እስከ ጥር ፲፯ ቀን ድረስ ነው፡፡ ቀኑ ሲወጣ ወይም ወደ ፊት ሲገፋ ደግሞ እስከ የካቲት ፳፩ ቀን ይረዝማል፡፡ ጾመ ነነዌ በእነዚህ ፴፭ ቀናት ውስጥ ስትመላለስ (ከፍ እና ዝቅ ስትል) ትኖራለች፤ ከተጠቀሱት ዕለታት አትወርድም፤ አትወጣም፡፡ በዚህ ዓመትም (፳፻፱ ዓ.ም) ጥር ፳፱ ቀን ትጀመራለች፡፡
‹‹ጾመ ሰብአ ነነዌ፤ የነነዌ ሰዎች ጾም›› የሚለው የጽሑፋችን ርእስ እንደሚያስረዳው ይህቺን የሦስት ቀን ጾም የጾሟት በነነዌ ይኖሩ የነበሩ ሰዎች ናቸው፡፡ ከተማዋም (ነነዌ) በጤግሮስ ወንዝ ዳርቻ የምትገኝ ስትኾን መሥራቿም ናምሩድ ነው /ዘፍ.፲፥፲፩-፲፪/፡፡ ጥንታዊቷ የነነዌ ከተማ ለአሦር መነሻ የኾነች፤ እጅግ ሰፊና ያማረች፤ የቅጥሯ ርዝመትም ፲፪ ኪሎ ሜትር የሚሸፈን ነበር፡፡ በከተማዋ ንጉሡ ሰናክሬም ብዙ ሕንጻዎችን ገንብቶባት ነበር /ዮናስ ፬፥፲፩/፡፡ በዚያ ዘመን የነበሩ የነነዌ ሰዎች ኀጢአታቸው በዝቶ እግዚአብሔር ሊያጠፋቸው ሲል ቸርነትና ምሕረቱ የማያልቅበት እግዚአብሔር መክሮ፣ ዘክሮ እንዲመልሳቸውና ንስሐ እንዲገቡ ነቢዩ ዮናስን ወደ ነነዌ ሕዝብ ላከው /ሉቃ.፲፩፥፴/፡፡
ዮናስ የስሙ ትርጕም ‹ርግብ› ማለት ነው፡፡ በዳግማዊ ኢዮርብዓም ዘመነ መንግሥት የነበረ ነቢይ ነው፡፡ ይህ ነቢይ መኖሪያው በገሊላ በጋትሔፌር ድንበር ከተማ ነበረ፡፡ አባቱም አማቴ ይባላል፡፡ ኢዮርብዓም ሶርያውያንን አባሮ የእስራኤልን ድንበር እንዲመልስ ነቢዩ ዮናስ ትንቢትን ተናግሯል /፪ኛነገ.፲፬፥፳፭፤ ዮናስ ፩፥፩/፡፡ ነቢዩ ኤልያስ ያስነሣው የሰራጵታዋ መበለት ሕፃን ነቢዩ ዮናስ እንደ ኾነ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ያስረዳል /፩ኛነገ.፲፯፥፲፱/፡፡ መድኀኒታችን ክርስቶስም የዮናስን ከዓሣ ኾድ መውጣት የራሱ ትንሣኤ ምሳሌ አድርጎ ነግሮናል /ማቴ.፲፪፥፲፱-፵፪፤ ሉቃ.፲፩፥፴-፴፪/፡፡
እግዚአብሔር ‹‹ሔደህ በነነዌ ላይ ስበክ›› ባለው ጊዜ ነቢዩ ዮናስ ‹‹አንተ መሐሪ ነህ፤ ልትጠፉ ነው ብዬ ተናግሬ ብትምራቸው ሐሰተኛ ነቢይ እባላለሁ›› ብሎ ላለመታዘዝ እስራኤልን ለቆ በመርከብ ወደ ተርሴስ ሸሸ፡፡ እግዚአብሔርም ታላቅ ነፋስን አስነሥቶ መርከቧ በማዕበል እንድትመታ አደረገ፡፡ ከዮናስ ጋር በመርከቧ ተሳፍረው የነበሩ ነጋድያንም ያላቸውን ሀብት ወደ ባሕሩ መጣል ሲጀምሩ ነቢዩ ዮናስ ጥፋቱን ተገንዝቦ ‹‹ማዕበሉ በእኔ ምክንያት የመጣ ስለ ኾነ ንብረታችሁን ሳይኾን እኔን ወደ ባሕር ጣሉኝ›› ብሎ ተማጸናቸው፡፡ እነርሱም ‹‹ስለዚህ ሰው ነፍስ እንዳንጠፋ፣ ንጹሕም ደም በእኛ ላይ እንዳይደረግብን አይኾንም›› አሉ፡፡
ወደ ባሕሩ ለመጣል ዕጣ በተጣጣሉ ጊዜም ዕጣው በዮናስ ላይ ስለ ወጣ ነጋድያኑ ዮናስን ወደ ባሕሩ ጣሉት፡፡ ወዲያውኑ ከእግዚአብሔር ዘንድ የታዘዘ ታላቅ ዓሣ አንበሪ ዮናስን በአፉ ተቀብሎ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት አሳድሮ ወደ ነነዌ አደረሰው፡፡ እግዚአብሔር የቅል ተክልን ምሳሌ በማድረግ ቅጠሉ በመድረቁ ዮናስ ባዘነ ጊዜ ‹‹አንተ ላልደከምክበት እና በአንድ ቀን በቅሎ ላደገ ቅል ስታዝን እነሆ በታላቂቱ ነነዌ ከተማ ያሉ ከአንድ መቶ ሃያ ሺሕ በላይ ሕዝብና እንስሳቱ የእጄ ፍጥረቶች ስለ ኾኑ ያሳዝኑኛል›› በማለት ነቢዩ ዮናስም ውሸታም ላለመባል መኮብለሉ ስሕተት መኾኑን አስረድቶታል፡፡
ዮናስም ነነዌ መሬት ላይ መድረሱን ባወቀ ጊዜ ከእግዚአብሔር መሸሽ አለመቻሉን ተረዳ፤ የነነዌ ሰዎችንም ‹‹ንስሐ ግቡ›› እያለ መስበክ ጀመረ፡፡ የነነዌ ሰዎችም ንስሐ በገቡ ጊዜ እግዚአብሔር ይቅር ብሎ ከጥፋት አድኗቸዋል፡፡ ሐሰት እንዳይባልም እሳቱ እንደ ደመና ኾኖ ከላይ ታይቶአል፡፡ የታላላቁ ዛፍ ቅጠል እስኪጠወልግ ድረስ አድርቆ ለሕዝቡ አሳይቷቸዋል፡፡ ንስሐቸው በከንቱ እንዳልቀረ አስረድቷቸዋል /ትንቢተ ዮናስን በሙሉ ይመልከቱ/፡፡ ታኅሣሥ ፭ ቀን የሚነበበው የመጽሐፈ ስንክሳር ክፍል ‹‹ወበልዐ አሐደ ኀምለ›› በማለት ንስሐ ያልገቡ አንድ አገር ያህል ሰዎች በእሳቱ እንደ ጠፉ ይነግረናል፡፡
ጾመ ነነዌ የሦስት ቀን ሱባኤ ናት፤ በሦስት ቀናት ጾምና ጸሎት ንስሐ የገቡ የነነዌ ሰዎች ከጥፋት እንደ ዳኑ ዅሉ፣ በብሉይ ኪዳን አስቴር ሦስት ቀን ጾማ፣ ጸልያ በእስራኤል ላይ የመጣውን መቅሠፍት እንዲመለስ አድርጋለች /አስ.፬፥፲፭-፲፮/፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ከበዓል ስትመለስ ሕፃኑ ልጇ ኢየሱስ ክርስቶስ መንገድ ላይ ጠፍቶአት ከሦስት ቀን ፍለጋ በኋላ በቤተ መቅደስ አግኝታዋለች /ሉቃ.፪፥፵፮/፡፡ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ለሄሮድስ በሰጠው ምላሽ መልስ ሦስት ቀን የሱባኤ ፍጻሜ መኾኑን ገልጿል /ሉቃ.፲፫፥፴፪/፡፡
ጾመ ነነዌ የእግዚአብሔርን ቸርነትና መሐሪነት የምናስታውስበት ጾም ነው፡፡ ይኸውም እኛ ፍጡራኑ በበደልን ጊዜ ፈጽሞ ከማጥፋት ይልቅ ምክንያት ፈልጎ እንድንድን ያደርገናል፡፡ ዮናስ ለስብከት ፈቃደኛ ባይኾን እንኳን እግዚአብሔር በተለየ ጥበቡ እንዲሔድ አድርጎታል፡፡ በእርግጥ እግዚአብሔር ሌላ የሚልከው ነቢይ አጥቶም አይደለም፤ እርሱንም ጭምር ሊያስተምረው ስለ ፈለገ እንጂ፡፡ የነነዌ ሰዎች የተነሳሕያን ምሳሌ ናቸው፡፡ ይህም ማለት ሰው ጥፋቱን አምኖ ንስሐ ከገባ እግዚአብሔር ይቅር ማለቱን አይተውም፡፡ ለዚህም ነው ዮናስን ‹‹አንተ ላልደከምክበት እና በአንድ ቀን በቅሎ ላደገ ቅል ስታዝን እነሆ በታላቂቱ ነነዌ ከተማ ያሉ ከአንድ መቶ ሃያ ሺሕ በላይ ሕዝብና እንስሳቱ የእጄ ፍጥረቶች ስለ ኾኑ ያሳዝኑኛል›› ያለው፡፡
ቀደምት የቤተ ክርስቲያን አባቶቻችን ይህን እና ሌሎች አጽዋማትን እንድንጾም የወሰኑልን ያለ ምክንያት አይደለም፡፡ ሕጉ የተዘጋጀልን እንደ ነነዌ ሰዎች እኛም ጾመን፣ ጸልየን ከኀጢአታችን እንነጻ ዘንድ ነው፡፡ ዛሬ ዓለማችን በኀጢአት ማዕበል እየተናወጠች ባለችበት ወቅት እኛም እንደ ነነዌ ሰዎች ከበደላችን ብንመለስ እና ንስሐ ብንገባ ቸሩ ፈጣሪያችን እግዚአብሔር ይቅርታና ምሕረት የባሕርይ ገንዘቡ ስለ ኾነ ‹‹ወደ እኔ ተመለሱ፤ እኔም ይቅር እላችኋለሁ፤›› ይለናል፡፡
ስለኾነም በነቢዩ ዮናስ ላይ የተደረጉ ተአምራትንና ካለመታዘዝ የሚመጣ ቅጣት ቀላል አለመኾኑን በማስተዋል፣ ለነነዌ ሰዎች የወረደውን ምሕረት በመገንዘብ ለእግዚአብሔርም ኾነ ለሃይማኖት አባቶች እና ለወላጆቻችን መታዘዝ ይገባናል፡፡ ስንጾምም እግዚአብሔር አምላካችን መዓቱን በምሕረት፣ ቍጣውን በትዕግሥት መልሶ በኀጢአት ለጠፋው ዓለም ይቅርታውን ይልካል፡፡ በመጾማችን ራሳችን ከመዓትና ከመቅሠፍት ከመዳናችን ባሻገር በእኛ በደል ምክንያት አገራችን፣ ዕፀዋቱና እንስሳቱም ሳይቀር ከድርቅና ከቸነፈር ይተርፋሉና፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡

With Teddy Afro – I just got recognized as one of their top fans! 🎉
25/01/2026

With Teddy Afro – I just got recognized as one of their top fans! 🎉

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያ ለኢትዮጵያ ሀገረ ምስረታ ያላት ሚና(ቤተ ክህነት እና ቤተ መንግሥት)እንደ መግቢያ የሰው ልጅ አብሮ ለመኖር እንዲችል አካሄዱን የሚቆጣጠሩትና የሚመሩ...
21/01/2026

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያ ለኢትዮጵያ ሀገረ ምስረታ ያላት ሚና(ቤተ ክህነት እና ቤተ መንግሥት)

እንደ መግቢያ የሰው ልጅ አብሮ ለመኖር እንዲችል አካሄዱን የሚቆጣጠሩትና የሚመሩት ወደ ተፈለገውም ዕድገትና ብልጽግና እንዲደርስ የሚያስችሉት ሁለት የሥልጣን ተቋማት (ቤተ-መንግሥት እና ቤተ-ክህነት) አሉ። እነዚህ ተቋማት አንዱ ለመንፈሳዊ፣ ዘላለማዊና ሰማያዊ ጉዞውና ፍላጎቱ ሌላው ለሥጋዊ ጊዜያዊና ምድራዊ ጥቅሙና ዕድገቱ ላይ ተመሥርተዋል። በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ቤተ መንግሥትና ቤተ ክህነት በጥብቅ ግንኙነት ለረጅም ዓመታት አብረው ዘልቀዋል፤ ትስስሩም በሁለቱም መፈላለግ ላይ የተመሠረተ ነበር። መንግሥትና ሃይማኖት የተለያዩ ናቸው የሚለው መርሕ ተግባራዊ አፈጻጸሙ አጠያያቂ ነው፤ ሁለቱም በተመሳሳይ ሕዝብ ላይ ስለሚያተኩሩ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ‹‹መነካካታቸው›› አይቀሬ ነውና። በሀገራዊ ጉዳዮች ከመንግሥት ጋር መተባበር በየትኛውም አኳኋን ‹‹ፖለቲከኛ›› ሊያሰኝ አይገባም፤ ለሃይማኖቱም ምድራዊ ህልውና የሀገር ሰላምና ልማት ያስፈልጋልና። የሁለቱም ህልውና የተመሠረተው በሕዝቡ ላይ መሆኑ ያገናኛቸዋል ብቻ ሳይሆን ወደ የራሳቸው ፍልስፍና በመሳብ ሂደት ውስጥ ያነታርካቸዋል። ቤተ ክርስቲያን ‹‹በምድር ያለች የእግዚአብሔር መንግሥት›› ናት፤ ምድራዊው መንግሥትም በሕዝብ ተመሥርቶ፣ ለሕዝብ የሚሠራ፣ ሕዝባዊ ነው። እናም ሁለቱም ያለ ሕዝብ (ሰዎች) ሀልዎታቸው ሊነገር አይችልም።


ግንኙነቱ አዎንታዊም ይሁን አሉታዊ የቤተ መንግሥትና የቤተ ክህነት ትስስር በዓለምም ሆነ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ የነበረ፣ ዛሬም ድረስ የሚስተዋል ነው። የኢትዮጵያ ነገሥታትና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ግንኙነት እንዲህ በቀላሉ የሚገለጽ አይደለም፤ የረጅም ጊዜ ቁርኝት ነበራቸውና። በብሉይ ኪዳን በንግሥት ሳባ የተጀመረው ግንኙነት (፩ነገ.፲፥፩)፤ በኋላ በሐዲስ ኪዳን ደግሞ በ፴፬ ዓ.ም. በዘመኑ የአገሪቱ ገንዘብ ሚኒስቴር በነበረው (ጃንደረባው ባኮስ) አማካይነት ክርስትናን ስትቀበል (የሐዋ.፰፥፳፮-፵፪) የበለጠ ተጠናከረ። ይህ ክስተት ከተለመደው የግሪኮ-ሮማን ዘመን የክርስትና ታሪክ (ክርስትና በተራ ሕዝቦች ተጀምራ ወደ ነገሥታቱ ከምትጎተትበት ሁኔታ) ጋር ተቃራኒ ነበር፤ በተገላቢጦሹ በኢትዮጵያ ክርስትናን ለሕዝቡ የሰበከው የቤተ መንግሥቱ ጃንደረባ ነውና።

ቤተ ክህነት ነገሥታቱን ቀብታ በማንገሥ ሕዝቡም ለእነርሱ እንዲገዛ ባላት ተሰሚነት በማሳመን፣ ለሕዝብ ጠንካራ ማኅበራዊና ሥነ ልቡናዊ ግንባታ ግንባር ቀደም ሚናን ተጫውታለች። ነገሥታቱም አንድም ሃይማኖተኞች ስለ ነበሩ፣ በሌላም መልኩ ደግሞ ለፖለቲካዊ አስተዳደራቸው እጅግ ስለምታስፈልጋቸው ማለትም የመንግሥታቸው ህልውና የሚለካው ከቤተ ክርስቲያን ጋር በሚኖራቸው ግንኙነት መጠን ስለ ነበር፡ ቤተ ክርስቲያንን የሙጥኝ ብለዋት አልፈዋል፤ በአንድ መልኩ ሲደግፏትና በሌላ ጊዜም ሲገፏት፡ ማለትም ሲጠቀሙባት ኖረዋል።

ቤተ ክርስቲያን በዚህ ሁሉ ጉዞዋ ለሀገር ያበረከተቻቸው አስተዋጽኦዎች አሉ። እነሱም በሀገር ግንባታ፣ ከመንግሥት ጋርግንኙነት በመፍጠር፣ በመልካም ዜጋ ግንባታ፣ በፖለቲካ፣ በሀገር ጥበቃ እና አርበኝነት የነበራት አበርክቶ ቀላል አይደለም። ድርሻዋም ምን እንደ ነበር የሚከተሉትን ጥቂት ማብራርያዎችን እንመልከት።

በሀገር ግንባታ

ሀገራችን ኢትዮጵያ በዓለም ሕዝቦች ዘንድ ተፈርታ እና ተከብራ እንድትኖር ካደረጓት ነገሮች አብዛኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሠራቻቸው ሥራዎች ናቸው። አንድን ሀገር ሀገር የሚያሰኘው ሕዝቡ እና የአኗኗር ዘይቤው፡ ያለው መልክዐ ምድሩና ሕዝባዊ ሥርዓተ ማኅበር ነው። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለሀገራችን ኢትዮጵያ መሠረት እና ጉልላት፣ድር እና ማግ ናት። ለሀገሪቱ ብቻ ሳይሆን ለመላው አፍሪካ የኩራት ምንጭ መሆንዋን የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ታቦም ቤኪ የተናገሩትን ጠቅሶ በፍቅር ለይኩን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ድርሻ እንዲህ አስፍሮታል። ዘመናዊው የአፍሪካ የነፃነት ንቅናቄ የመነጨው ወደ ፲፱ኛው ክፍለ ዘመን ማብቂያ አካባቢ በደቡብ አፍሪካ ነበር፣ የዚህ ንቅናቄ የቀድሞ መሥራቾች የሀገራችን የመጀመሪያዎቹ ዘመናዊ አፍሪካውያን ልሂቃን ናቸው። የተነሡትም ከአብያተ ክርስቲያናት ትምህርት ቤቶች ሲሆን፣ የመጀመሪያዎቹ አፍሪካውያን የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችም ነበሩ።

እነዚህ ዘመናዊ የአፍሪካ ልሂቃን ከአውሮፓውያን ሚስዮኖች ራሳቸውን አላቀው በቤተ ክርስቲያናን ላይ ባለቤትነታቸውን ሲያውጁ፣ እንደመነሻ የተጠቀሙት የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል በመዝሙረ ዳዊት ፷፰ ላይ ይገኛል፤ ይህም፡- ‹‹መኳንንት ከግብጽ ይመጣሉ፣ ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች።›› የሚለው ነው። አፍሪካ የአውሮፓውያን የቅኝ ግዛት እሽቅድድም ሰለባ ሆና በኖረችበት ወቅት ኢትዮጵያ ነፃነቷን እንደያዘች መቀጠሏ መነሳሳትን ይሰጣቸው ነበር፤ እናም በመጽሐፍ ቅዱስ እንደተተነበየው ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ስትዘረጋ ቤተ ክርስቲያናችን በአፍሪካዊ ሥነ ምግባር ትሞላለች ብለው ያምኑ ነበር። ይህች እውነተኛ የአፍሪካ ቤተ ክርስቲያን ደግሞ አፍሪካውያን በሙሉ ለነፃነት፣ ለባህላቸው፣ ለልዑላዊነታቸው፣ ለማንነታቸውና ለሰብአዊነታቸው እንዲከበር ላላቸው ህልም እንደማከማቻ ቦታ ሆና ታገለግላለች ብለው ያምኑ ነበር። ታዲያ በዚህ እውነታ እና ታሪካዊ ሀቅ ላይ ተመሥርተው ነበር። እነዚህ የጠቀስናቸው አብያተ ክርስቲያናት ራሳቸውን የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ብለው የሰየሙት፣ በአህጉራችን ላይ የመጀመሪያው ዘመናዊ የብሔራዊ ንቅናቄ የሆነው የደቡብ አፍሪካው አፍሪካን ናሽናል ኮንግረስ ፓርቲ (ANC) የተወለደውም ከእነዚሁ ከሀገራችን የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ነው...የፓርቲያችን የመጀመሪያ ፕሬዝዳንት የነበሩት ቄስ ጆን ዱቤም የዚሁ የደቡብ አፍሪካ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን መሪ ነበሩ…።›› በማለት ገልጿል።

ሀገራችን ኢትዮጵያ ለቅኝ ገዥዎች እንዳትንበረከክ የሰበኩን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አባቶች እነ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ሰማዕትን እና እነ አቡነ ሚካኤልን ማን ይረሳቸዋል። የሀገር ፍቅርን ከነኩራቱ፣ ጀግንነትን ከነጥብዓቱ፣ ፊደልን ከነቁጥሩ፣ ዘመንን ከነቀመሩ ለሀገራችን ኢትዮጵያ ያበረከተችው ቤተ ክርስቲያናችን ናት። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሀገራችን በኢትዮጵያ የሀገረ መንግሥት ግንባታ የነበራትን ሚና ለመረዳት የመንግሥት አወቃቀር በኢትዮጵያ ምን እንደ ነበር በሚገባ ማጤን ይገባል።

ለምሳሌ ከንግሥት ማክዳ ከቀዳማዊ ምኒልክ ዘመን ጀምሮ ሰሎሞናዊ ሥርወ መንግሥት ከመጽሐፍ ቅዱሱ ከንጉሥ ሰሎሞን የዘር ሐረግ የተገኙ ነገሥታት ሥዩመ እግዚአብሔር (በእግዚአብሔር የተቀቡ እየተባሉ) የቤተ ክርስቲያናችን ብፁዓንና ቅዱሳን ፓትርያርኮች እየቀቡ ያነግሡአቸው እንደ ነበር የኢትዮጵያን ታሪክ የተማረ ሁሉ የሚያውቀው እውነት ነው። እስከ ደርግ ዘመነ መንግሥት ድረስ የነበሩ የኢትዮጵያ ነገሥታት ንግሥናቸውንም ሆነ አስተዳደራቸውን የሚያገኙት ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ነበር። ከዚህም የተነሣ ንጉሡ እና ፓትርያርኩ የጠበቀ ቁርኝት እንደነበራቸው በሁሉ የታወቀ ነው።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዛሬ ላለችው ኢትዮጵያ መሠረታዊ መገለጫዋ ናት ብሎ የጻፈው (ያዕቆብ ቡልቲ ፳፻፲፪፡፲) ነው። አክሎም በገጽ ፲ ላይ ‹‹የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እጅግ ጠቃሚ ድርሻ በኢትዮጵያ እድገት ላይ ተጫውታለች›› በማለት ይገልጻል። ሲያብራራም ‹‹በትምህርት መስክ የትምህርት ሚኒስቴር በመሆን እንደዚሁም በልማት መስክ ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽንን በማቋቋም በዚህ ኮሚሽን የገጠር የንጹሕ ውኃ ሥራ፣ ኤች.አይ.ቪ ኤድስ መከላከል ላይ እንዲሁም ንጽሕና እና ጤና አጠባበቅ ላይ እያበረከተች ያለውን አስተዋጽኦን አስፍሯል።››

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሀገረ መንግሥት ግንባታ ለኢትዮጵያ ያበረከተችውን አስተዋጽኦ ምን እንደ ነበር ማሳየት ተገቢ ነው። ለሀገር ግንባታ ካበረከተቻቸው አስተዋጽኦዎች መካከልም የሚከተሉት ተጠቃሾች ናቸው። የተስተካከለ ሥነ ምግባራዊ ሰብእና ያለው፣ አርበኛ ጀግናና ሀገር ወዳድ ትውልድ መፍጠር፣ ማኅበራዊ ጥንካሬ በመፍጠር፣ በአፈርና ብዝኃ ሕይወት ጥበቃ፣ ሀገር በቀልና ዓለማቀፋዊ ትምህርቶችን በማስፋፋት፣ የባህልና የቱሪዝም፣ የሥነ ጽሑፍ፣ የሥነ ቅርጻ ቅርጽ፣ የኪነ ሕንፃ፣ የሥነ ዜማ ጥበባዊ ሀብቶችን በማስፋፋት በማስጠበቅ ብሎም ለዓለም በማስተዋወቅ፣ በሕዝቦች መካከል ጠንካራ ማኅበራዊ ትስስርንና ሀገራዊ አንድነትን በመፍጠር፣ በድህነት ቅነሳ፣ አካል ጉዳተኞችን በማብቃት፣ የሀገርን ምጣኔ ሀብታዊ ዕድገት በማፋጠን፣ ሰላምም በማስፈን፣ ለምሁራን በጥናትና ምርምር ማዕከልነት እንዲሁም ዘመናዊ ሕክምና ባልነበረበት ወቅት የሕክምና ማዕከል ሆና ስታገለግል መኖሯ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ካበረከተቻቸው አስተዋጽኦዎች መካከል ተጠቃሾች ናቸው።

ከመንግሥት ጋር ያላት ግንኙነት

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለዘመናት የሀገሪቱ መሪ እና አስተዳዳሪዎችን በማስተማር በማብቃት በመሾም ሲያጠፉ በመገሠጽ የመሪነት ሚናዋን እስከ ፲፱፻፷፮ ዓ.ም ድረስ ስትጫወት የነበረች ሲሆን እስከዚሁ ዘመንም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሃይማኖት የነበረ ሲሆን እስከዚሁ ዘመን ድረስ ምንም ዓይነት ልዩነት በቤተ መንግሥቱ እና በቤተክህነቱ መሀል አልነበረም ከደርግ ዘመነ መንግሥት ጀምሮ ከላይ እንደገለጽነው መንግሥት እና ሃይማኖት ተለያይተዋል። ‹‹የመንግሥት እና የቤተ ክርስቲያን አንድነት እንደ ቀኝ እና ግራ እጅ ነበር›› ብሎ የጻፈው ዓለማየሁ ብርሃኑ የተባለው አጥኚ የሀገሪቱ ንጉሥ እስከ ፲፱፻፷፮ ዓ.ም ድረስ የቤተ ክርስቲያኒቱ አባል መሆን እንደ ነበረበትም እንዲሁ አእምሮ የተባለ ምንጭን (፲፱፻፸) ጠቅሶ ገልጧል። የሀገሪቱን ሕግ የሚያወጡት እንደዚሁም ሀገሪቱን ሲመሩ እና ሲያስተዳድሩ የነበሩትም የቅድስት ቤተ ክርስቲያን አባላት በመሆናቸው የሃይማኖቱ ጠበቆች ነበሩ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሀገሪቱ ሁነኛ የመንግሥት የልማት አጋር ስትሆን በሁሉም የሀገራችን ስፍራዎች ሁሉ ከኅብረተሰቡ ጋር በጥብቅ በሥነ ምግባር እና በምጣኔ ሀብት አብራ የምትሠራ መሆንዋን ይገልጻል። አክሎም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሀገሪቱ ሁነኛ የልማት አጋር በመሆን የምትጫወተው ሚና ቀላል እንደማይባል ነው። (ዓለማየሁ ብርሃኑ፣ ፳፻፲፱)

ዓለማየሁ ብርሃኑ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተቋማዊ አስፈላጊነት በከተማ ልማት (Relevance of Ethiopian Orthodox Tewahido Church Institutional Setup for Rural Development:) በሚል ርእስ ባዘጋጀው የ፪ኛ ዲግሪ ማሟያ ጽሑፉ ላይ ገጽ ፲ ‹‹የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጥንታዊ፣ ታሪካዊ፣ ብሔራዊ እና ሃይማኖታዊ እንደ መሆንዋ በሀገሪቱ ላይ በርካታ አሻራዎችን አኑራለች። በሀገር አንድነት እና በሰላም ግንባታ፣ በሀገር ነፃነት እና ሉዓላዊነት እንዲጠበቅ ቤተ ክርስቲያኒቱ የአርበኝነት ሚናን ስትጫወት ነበር›› ሲል ገልጧል። አክሎም ኢትዮጵያ በአፍሪካ አህጉር የራስዋ የሆነ ፊደል ያላት በዛም የምትጽፍ እና የምታነብ እንድትሆን፣ የራስዋ የሥነ ጽሑፍ ታሪክ ያላት የራስዋ የቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ ትምህርት ቤት ያላት አሁንም የምትጠቀምበት ፊደል፣ ቁጥር እና የዘመን መቁጠሪያ የቤተ ክርስቲያን ሀብት እንደ ሆነ፤ በ፮ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ቤተ ክርስቲያን ባፈራችው በቅዱስ ያሬድ የተገኘው የዜማ ስልት ከመንፈሳዊው አገልግሎት ባሻገር ለዓለማዊው ዜማም መሠረት ሆኖ ሀገር እንደምትገለገልበት ይገልጻል።

በመልካም ዜጋ ግንባታ

የመልካም ዜጋ ግንባታ የሀገራችን መንግሥት መርሕ ነው። በሥነ ትምህርት (በትምህርት ፖሊሲው) ላይ በዓላማ ከተቀመጡ ቁልፍ ቃላት አንዱ መልካም ዜጋ መፍጠር ነው። እርግጥ የዘርፉ ምሁራን እንደሚስማሙበት የሥነ ምግባር እና ሥነ ዜጋ ትምህርት መልካም ዜጋ ፈጥሯል ወይ የሚለው ጥያቄ ውስጥ የሚገባ ነው።

በዚህም ምክንያት የሀገሪቱ የትምህርት ሥርዓት በቅርቡ እንደገና ተሻሽሏል። መልካም ዜጋ ሀገሩን የሚወድ ሙስና (ጥፋትን) የሚንቅ በበጎ ሥነ ምግባር የታነፀ፣ ክፉውን የሚጠላ ነው። እርግጥ እንደዚህ ያለ ዜጋ ለመፍጠር የሥነ ዜጋ ትምህርት እና የሥነ ዜጋ እና ሥነ ምግባር መምህራን አልቻሉም። መልካም ዜጋ የሚፈጠረው ስለ መልካም ዜግነት በመጽሐፍ በማስተማር ብቻ ሳይሆን መልካም ዜጋ ሆኖ በማሳየትም ጭምር ነው። የመልካም ዜጋ ግንባታ የሚጀመረው እንደ ሕንፃ ከታች ነው። ብዙ ጊዜ በሀገራችን ስለ መልካም ዜጋ ግንባታ የሚሰበከው ግን ልጆች ካደጉ በኋላ ነው።



ሕጻናት ከሕፃንነታቸው ጀምረው መልካም ዜጋ ሆነው እንዲያድጉ በፈሪሀ እግዚአብሔር ሰውን በማክበር በትሕትና እንዲያድጉ የቤተ ክርስቲያንን ሚና ማንም ሊተካው አይችልም። ሀገር የምትፈልገው መልካም ዜጋ ከሀገራችን የትምህርት ሥርዓት ብቻ ሳይሆን ከሃይማኖት ተቋማትም ጭምር ነው። መንግሥት ይህን ዐውቆ ለመልካም ዜጋ ግንባታ የሃይማኖት ተቋማት የሚያበረክቱትን አስተዋጽዖ ትልቅ ቦታ በመስጠት በሚያስፈልገው ነገር ሁሉ ከጎናቸው ሊቆም እና አብሯቸው ሊሠራ ይገባዋል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ደግሞ በሥነ ምግባር የታነፀ መልካም ዜጋ ማፍራት ትችልበታለች። ታዲያ ለዚህ ተግባሯ መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ ሊያደርግላት ይገባል። ይህ ሲሆን ሙስናን የሚጠየፍ በመልካም አስተዳደር የተመሰከረለት ተስፋ የሚጣልበት ከክፉ ሥራ ሁሉ የራቀ የሀገሩን ጥቅም ለሌላው አሳልፎ የማይሰጥ ሀገሩን የሚወድ ለሀገሩ የሚሞት ዜጋን ማፍራት ይቻላል።

በፖለቲካ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከትላንት እስከ ዛሬ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ ማንም ሊተካው የማይችለውን ሚና እየተጫወተች ያለች ሀገር ናት። ኦርቶዶክስ ሀገር ናት ሀገራችን እንደ ሀገር ሉዓላዊነትዋ ተጠብቆ እንዲቆይ ያደረገችው ዛሬ ድረስ በየትኛውም ዓለም እንድንኮራ መመኪያ እና መኩሪያ የሆነች ቤተ ክርስቲያን ናት። ምዕራባዊ ባህል እና ፍልስፍና ያልተቀላቀለባት ቅድስት፣ አሐቲ፣ ኩላዊትና ሐዋርያዊት ናት። ለሀገራችን በፖለቲካው መስክ ደግሞ እስከ ደርግ ዘመነ መንግሥት ድረስ ነገሥታቱን ቀብታ በማንገሥ በንግሥናቸው ዘመንም ስታማክር በማጠናከር፣ መልካም ሲሠሩ በማመስገን ክፉም ሲሠሩም ያለ ፍርሀት በመገሠጽ ተቋማዊ ኃላፊነቷን በትጋትና በቁርጠኝነት ስትወጣ ኖራለች። የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሀገር ወዳድ ልጆችን ወልዳ ያሳደገች፣ ጀግንነትንና የሀገር ፍቅርን ያስተማረች ለሀገር መሞት ክብር መሆኑን የእምነት አባቶቿን እነ አቡነ ጴጥሮስ እና አቡነ ሚካኤልን ፊት አውራሪ በማድረግ ፋሺስት ኢጣሊያን የተፋለመች፣ ታቦት አውጥታ ዐውደ ውጊያ ድረስ የዘመተች የሀገር ባለ ውለታ ቤተ ክርስቲያን ናት። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዛሬ የሀገራችን ልዕልና ቋንቋችን እና ማንነታችን ተጠብቆ በራሳችን ቋንቋ የምንናገረው በራሳችን ፊደልም የምንጽፈው ቤተ ክርስቲያን በፖለቲካው መስክ በነበራት ንቁ ተሳትፎ ማንነታችንና ክብራችን ተጠብቆልን ስለ ኖረ ነው።

ዛሬ ላይ ግን ጥንት የነበራት ፖለቲካዊ ሚና በዓለማዊነት አገዛዝ ስም ተዳፍኖ ሀገርን የሚያበጣብጥ፣ የሕዝብን ሰላም የሚያናጋ የዘረኝነት መንፈስ በሰሜን እና በደቡብ በምስራቅ እና በምዕራብ ተንሰራፍቶባታል። ይህም ቤተ ክርስቲያን በሀገር ፖለቲካ ላይ የነበራት ሚና መቀማት ውጤት እና የውጭ ኃይሎች ሥውር የማፈራረስ ተልእኮ እንዲሁም የሴራ ፖለቲካቸው (የሴራቸው) ውጤት ነው። አሁንም ቢሆን ሀገራችን ዕሴቷንና ባህሏን ጠብቃ እንደ ሀገር መቆም የምትችለው የእምነት ተቋማት ጠንካራ ዘመኑን የዋጀ አመራር ሲኖራቸው ነው።

ኢትዮጵያዊነት ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴ ከሰሀራ በታች ባሉ በቅኝ ግዛት ጊዜ የተጀመረ ፖለቲካዊ ሃይማታዊ እንቅስቃሴ ሲሆን የተጀመረውም ከላይ ለመግለጽ እንደ ተሞከረው በደቡብ አፍሪካ ነው።

እንቅስቃሴው በ፲፰፻፹ እ.አ.አ. በአፍሪካ ያሉ ክርስቲያኖችን ሁሉ በአንድ ለመሰብሰብ የተመሠረተ ነው እንደ ትመቡ ተሪቢያል ቤተ ክርስቲያን እና የአፍሪካ ቤተክርስቲያን (Tembu tribal church and the Church of Africa. ቃሉን መጀመሪያ የተጠቀመው Mangena Mokone የተባለ ሰው የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያንን ባገኘ ጊዜ እንደ ሆነ እና ዘረኝነትን ለመዋጋት እና ቅኝ ገዥዎችን ለመቃወም የተጀመረ እንቅስቃሴ እንደነበረ የሚገልጸው ብሪታኒካ ኮነሰስ ኢንሳይክሎፒዲያ ገጽ ፮፻፴፱ ላይ ነው። በዚሁ መጽሐፍ ላይ በናይጄሪያ፣በካሜሮን፣በጋና እና በሌሎች ቦታዎች ላይ ይህ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ መጀመሩን ይገልጻል።

ወደ ቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ለመሳለም የሚሄዱ የኢትዮጵያ መነኮሳት እና ምእመናን እስከ ፲፮ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ድረስ መልካም የሆነ የውጭ ግንኙነት ይፈጥሩ እንደነበር እና በሀገራችን ስላለው ጥሩጥሩ ነገር እንደ አምባሳደር በመሆን በደረሱበት ሁሉ ለሚያገኙት በመንገር ሀገራቸውን ማስተዋወቃቸውን የሚነግሩን በአ.አ.ዩ.የታሪክ እና የቅርስ ጥናት የት/ት ክፍል መምህር የሆኑት ዲ/ን ጌታቸው መረሳ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሚና በመካከለኛው ዘመን የውጭ ግንኙነት በሚል ርእስ ባቀረቡት ጥናታዊ ጽሑፋቸው ገጽ ፫ላይ ነው።

በሀገር ጥበቃ እና አርበኝነት

የሀገር ሉዓላዊነት የሚጠበቀው በሀገር የቁርጥ ቀን ልጆች የሥጋ የደም እና የአጥንት ዋጋ የነፍስ ዋጋ በመክፈል ነው። ለዚህ ደግሞ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንግንባር ቀደም በመሆን ሀገርን ከጠላት በመከላከል እና ወራሪ ኃይልን በጸሎትም እንደዚሁም ልጆችዋን ወደ ዐውደ ጦር ግንባር በመላክ ለሀገር ያላትን ታማኝነት ከየትኛውም በኢትዮጵያ ከሚገኙ ቤተ እምነቶች በላይ ለዘመናት ስታሳይ ኖራለች። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሰውን ግደሉ ብላ አታስተምርም በሀገር ሉዓላዊነት ላይ ሲመጡ በመጀመሪያ በጸሎት፣ በትሕትና እና በዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ነገሮች እንዲያልቁ ትጥራለች እንደዛ ሆኖ ማለቅ ካልቻለ ግን ወደ ዐውደ ጦር የሚያስወጣ ግዳጅ ሲመጣ ታቦት አውጥታ እግዚኦታ አድርሳ ልጆችዋን ለጦርነት ትልካለች። አሸንፈውም ሲመጡ ጀግንነታቸውን በመጽሐፍ በሐውልት ትዘክራለች፣ የሞቱትን ፍትሐት ፈታ ወደ ላይኛው መንግሥት በክብር ትሸኛቸዋለች።

Address

Angle Street
London
49

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Esseynew Mihiretu Melesse posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Esseynew Mihiretu Melesse:

Featured

Share